Back to Front Page

ግማደ ትግራይ የሄደበት እና ቀሪው ግማድ የሚሄድበት መባቻ ላይ የሚከበር የ125 አመት የአድዋ ድል በአል

ግማደ ትግራይ የሄደበት እና ቀሪው ግማድ የሚሄድበት መባቻ ላይ የሚከበር የ125 አመት የአድዋ ድል በአል

 

ሲበቃም ያበቃል !

 

            ናርዶስ የማነ  አዲስ አበባ 02-22-21

 

የዛሬ 125 ዓመት የጣልያን ጦር ኢትዮጵያን ለመቆጣጠር እና በቅኝ ግዛቱ ስር ለማድረግ በማሰብ ወረራ ፈጸመ። ያኔ የነበሩት አባቶቻችን በተለየም የሰሜኑ ትግራይ ሰዎች ከጣሊያን ጋር ግብግብ ሲገጥሙ ሲጥሉና ሲወድቁ እንደነበር ሸዋ አይነግረንም። ይልቁንም በጊዜው የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት የነበሩት አጤ ሚንሊክ ከሸዋ ጦራቸውን ክተት ብለው ወደ ትግራይ እያስፎከሩ እያስገበሩ በመምጣት ጣልያንን ገጠሙ ከዛም እሳቸው ድል አደረጉ ይላል ግለ ታሪካቸው። ። ይህም 125 አመት ሞላው። እዚህ ላይ የሚነሳው ጥያቄ ምኒሊክ ከሸዋ ተነስተው አድዋ እስኪደርሱ ጣልያን ቁጭብሎ ሲጠብቃቸው ነበርን? የሚለው ነው። ከሆነ ከዚህ የሰለጠነ ውጊያ የምንማረው ብዙ ስነስርአት ሊኖር ነው። የዚህ ጽሁፍ አላማ ማን ቀድሞ ተዋጋ ስላልሆነ ወደፊት የምመለስበት ይሆናል። የዚህ ፅሁፍ ዋና አላማ ግን የዛሬ 125 አመት ግማደ ትግራይን በምኒሊክ ጣው የትግራይ ህዝብ ዛሬም በዘመናዊ ሚኒሊኮችን ቀሪውን ግማድ ለማጣት ዳር ላይ የደረሰ መሆኑን ለማሳየት ነው። በዚህም መሰረት አመክንዮዎችነንና ምሳልዎችን ብመጠቀም ለማብራራት ይሞከራል።

በታሪክ ድርሳናትና የአጼዎች መዘክር መሰረት የኢትዮጵያ ሰራዊተ በምንሊክ መሪነት ተዋግተው አሸነፉ እንበል። ይህ ከሆነ መታየት ያለባቸው ሁለት አበይት ጉዳዮች ይኖራሉ። እነደኛው በወቅቲ የንጉሱ ጭንቅት ጣልንን ማስወጧት ብቻ ነበር ወይ የሚለወ ነው። እንደጸሃፊው እምነት ከሆነ ምኒሊክ ውግያውንደርጉ ሌላ ታሳቢ ያደረጉት ነገር ቢኖር የለንግስናቸው ስጋት የነበረው የሰሜኑ ክፍል መበተን እና አቅም ማዳከም ጭምር ነው። ይህም የሆነበት ምክን የሸዋ ፖለቲካ መነሻና መድረሻ የትግራይን አቅም በማዳከም አማሃራዊ ስርወ-መንግስትን በዘላቂነት ማስፈን ነው። እዚሀ ላይ ተጨማሪ የሚሆኑ ማስረጃዎችን ማየት ካስፈለገም የሚኒሊክ ስርወ መንግስትና መስፋፋት እንዴት እንደነበር የታሪክ ድርሳናትን ማገላበጥ ይጠቅማል። ለዚህም ነው ምኒሊክ ከአድዋ ጦርነት ማግስት ትግርኛ ተናጋሪውን ማህበሰረብ ለሁለት በመክፈል ማዳከም የሚለውን ስልታቸው ተግባራዊ አድርገው የተመለሱት። ከአድዋ መልስ የተፈረሙ ስምምነቶች ለዚህ ዋቢ ናቸው። የውጫሌ ስምምነት እና ልሎች ስምምነቶችን ለመገንዘብ ሌሎች መጣጥፎችን ዋቢ ማድረግ ይቻላል።

ይህ የሸፍጥ ፖለቲካ በንጉሱ ግዜም በመቀጠል ኤርትራ በኮንፈደረሽን መመለስ ያለበቃቸው እና ንጉሱ ከምንሊክ የተሻሉ ሁኖ ለመታየት ከነበራቸው ህልመ ፉደረሸኑ መፈረሱ አወጁ፡፡ የኤርትራ ነግሱ ፌደረሽኑ ማፈረስ ሳይውል ሳያድር የኤርትራ ነጻነት የሚል ሃሳብን ወለደ። ከረጅም ጊዜ በኃላም ኤርትራ የምትባል አገር በድጋሚ እውን እንድትሆን ምክንያት ሆነ። ብዙ ሰው ኤርትራ ነጻ መውጧቷን ወደ ኢትዮጰያ ከተመለሰችበት የአጼ ኃይለ ስላሴ ዘመነ መንግስት ጋር በማነፃፀር በቁንጽሉ ለመረዳትና ለሚኒሊክ ጥፋቶች ይቅርታ ማድረግን ይመርጣሉ። ይህንንም በማድረግ የኤርትራን ነጻ አገር መሆን ከኢህአዴግ ጋር የማስተሳሰርና ትልቁን ስእል ችላ ማለት ይፈልጋሉ። ለዚህ ሃሳባቸው ዋናው ምክንያት ለምኒሊክ ይቅርታን በማድረግ ለጥፋቱ ተጠያቂ የሚሆን የአብርሃም በግ ፍለጋ ላይ ስያማትሩ ይስተዋላል። ይህ ትውልድ ከሽዋውያን አባቶቹ ሲሰማ የኖረውን ታረክ እና የሸዋ የበላይነትን ስካር ለማስጠበቅ ኩራት እራት ብሎ የተነሳ ጭፍን ሆኖ እናገኘዋለን። ይህ የተንኮል ድር ላለፉት 125 አመታት በስራ ላይ ቆይቷል። በሸዋ ስርወ መንግስት ያኔ የተቀበረው የተንኮል መርዝ አሁንም እያመረቀዘ ነው።

Videos From Around The World

እዚህ ላይ ልብ ሊባል የሚገባው ነገር ቢኖር የተንኮሎቹ ሁሉ ዋና መሰረቱ የሸዋ ፖለቲካ የትግራይን የፖለቲካ ተገዳዳሪነት ለማስቀረትና ተገዢ የሆነ ህዝብን በትግራይና ኤርትራ ለመፍጠር ያለመ ነው። ይህንን አላማ ለማሳካት ሃይል የታከለበትና ያልታከለበት የተለያየ እርምጃ ይወስዳሉ። ሃየል ያልታከለባቸው እርምጃዎች ተንኮል በሚባል የሚገለጹ ናቸው። ከነዚህም ውስጥ በኃይማኖታዊ ስርአትና ባህል ውስጥ ያሉ ዶግማዎችን በመጠቀም የቅዱስነትን ትያትር በመጫወት የስነ ልቦና ጫና በማሳደር የዶንኪሆቴ መጽሃፍ ላይ እንዳለው ከበረሃ ንፋስ ጋር በጎራዴ የሚታገል የቀቢጸ ተስፋ ምስልን በመፍጠር አይነኬ መሆን አንዱ ነው። ሌላው ድንቁርናን እና ኋላ ቀርነትን እንደመሳርያ በመጠቀም ህዝቡን ማዳከም ሲሆን ለዚህም ይረዳ ዘንድ የትግራይ ህዝብ በቅስና ትምህርት በመገደብ ከዘመናዊ ትምህርትና ኑሮ ጋር እንዳይገናኝ በማድረግ በአንጻሩ ደግሞ በኤርትራ ምድር ያሉ ወንድሞቻቸው የዘመናዊ ትምህርትና ኑሮ ከጣልያን ጀምሮ የተላመዱ በመሆናቸው የተፈጠረውን ክፍተት በማስፋትና በሌላ በኩል ደግሞ የትግራይን ህዝብ በባእድ ቀኚ ገዢዎች እንዳልተገዛና ነፃነቱን ኣስጠብቆ የኖረ በኣንፃሩ ደግሞ ኤርትራውያን በጣልያን የተገዙ ኣሽከሮች እንደሆኑ ኣስመስሎ በማራገብ  በአንድ ህዝብ ውስጥ መከፋፈልን በመፍጠር ጥላቻና መናናቅን ማራገብ ነው።

ይህ ስልት አንድን ህዝብ የሰለጠነና ያልሰለጠነ እንድሁም በቀኚ ገዢዎች የተገዛና ያልተገዛ በሚል ከፋፍሎና ቅጽል ስም አውጥቶ እርስ በእርሱ በጠላትነት እንዲተያይ ማድረግ ሲሆን ፈረንጆቹ (Counter balance) የሚሉት ኣይነት ነው። ለማራገቢያነትም አጋሜ የሚለውን የቦታ መጠሪያ በትምክህት ለትግራይ ተጋሩ መስጠት፣ በአንጻሩ ደግሞ ዓንሰባ የሚለውን የኤርትራ አካባቢ መጠርያ ለኤርትራውያን  የሞኝነት መገለጫ ማድረግ የመሳሰሉት ማሳያዎች ናቸው። ምኒሊክና የሱ ታረክ አራማጀች ይህንን ጉዳይ እንደ መልካም ተግባር መጠቀማቸው ሳያንስ ህዝቡ መካከል ጦርነትን በመጫር እንዲተላለቅና በቁጠር አናሳ እንዲሆን ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተወራረሱ በከፍተኛ ሁኔታ ሲሰሩበት ይስተዋላል።

ልላው የሃይል እርምጃን መጠቀም ማንበርክክ ሲሆን ቀዳማይ ወያኔ እና ሌሎች የሃይል እርምጃዎችን መመልከቱ በቂ ነው። በነዚህ ሂደቶች ከምኒሊክ በላይ ለኢትዮጵያ ዋጋ የከፈለው የትግራይ ህዝብ ለአገሪቱ መቀጠል የራሱን ድርሻ  ለመወጣትና ከቂም በዘለለ መልኩ የተሻለች አገርን ለመገንባት ያደረገው ጥረት ልብ በማለትና ከግምት ውስጥ በማስገባት በጋራ አገር ከመገንባት ይልቅ መከፋፈልን በመዝራት አብሮነትን የሚጎድል ሆኖ እናየዋለን። ይህንን ለመገንዘብ የሚፈልግ ቢኖር ማድረግ የሚገባው በንጹህ አይምሮ ማሰብና መመራመር ብቻ ነው።

በዚህ ሁሉ የመጠላለፍ ሂደትና ውጣ ውረድ የሸዋ ፖለቲካ ድር ውስጥ የትግራየ ተወላጆች ኢትዮጵያ ወይም ሞት የሚል መፈክር ይዘው ሲዋደቁ እናያለን። ስለሆነም ከቂም የነጻ ቀናኢነትን ለማሳየት እንዲቻል ምሳሌ በመጠቀስ ማብራራቱ የተሻለ ይሆናል የኤርትራ ነጻነትን በተመለከተ ኢህአዴግ የወሰደው እርምጃ ኢትዮጵን ለማዳን የተወሰደ ነው። ለዚህ ማስረጃው ደግሞ የኤርትራ መንግስት ጋር ለን ግንኙነት እንደ ሁለት አገር መሆን ስለሚገባው ኤርትራ ከኢትዮጵ ጋር የሃገሪቱ የውጭ ፖሊሲ በሚፈቅደው እንዲሆን ሆኖ ቆይቷል። በዚህም መሰረት ኢትዮጵያ ከጎረቤቶቿም ጋር ሆነ ሌሎች ሃገራት ጋር የንበራት ግንኙነት በሰጥቶ መቀበል መርህ ላይ በመሞርኮስ ለልማትዋ የሚጠቅም ግንኙኖቶችን ስታደርግ ቆይታለች። ከውጤቱ ኣንጻርም ኣመርቂ የሚባል ኣለም የመሰከረለት የእድገትና ልማት ስኬት ማስመዝገብ ተችሏል። ለዚህም ባለፉት 27 አመታት የተሻሉ የትግራይ ጭንቅላቶችን ወደ ሸዋ በማምጣት አገሪቱ አይታው የማታውቀውን ክብርና እድገት ማሳየቱን ልብ ይሏል።

ይህንን የሸፍጥ ፖለቲካ የተረዱ የተወሰኑ የትግራይ ኤሊቶች ቢኖሩም አብዛኛው የትግራይ ህዝብ ግን የይቅርታና በደሎችን የመርሳት ባህሉን መሰረት ኣድርጎ የሩቁን ምኒሊክን ሳይሆን የቅርቡ የነ ለገሰ አስፋውን በደሎችም በመርሳት አገር አለችን ብሎ ሲሰራና የራሱን ኤሊቶች በጠባብነትና ጸረ ኢትዮጰዊነት ሲፈርጃቸው ኖሯል። ይህ ባይሆን ኖሮ ከሃውዜኑ ጭፍጨፋ በኋላ በምንሊካዊ አስተምህሮትና የተንኮል ክህሎት የተካኑ ነብሰ በላዎች ባላታለሉትና አሁን ላለበት ችግር ባልዳረጉት ነበር። ይህችን ምኒሊካዊት አገር ለማዳን የደም ግብር መገበሩ ባቆመ ነበር። አንዳንዶች ይሄ ኣስተሳሰብ የሁሉም ህዝብ አመለካከት ኣይደለም ይላሉ፡ ይህ ታሪክ ላለፉት 125 አመታት የነበረና ትክክል ላለመሆኑ ማስረጃ የማይቀርብለት ቅጠፈት ነው። በዚህ ሂደት ያልተሞከረው ነገር ቢኖር ከምኒሊክ ልክፍተኞች ጋር ተለያይቶ መኖር ነው።

  እዚህ ላይ ከሚንሊክ ጊዜ ጀምሮ በአጼዎቹ ስርኣታት ወቅት የተፈጸመና ልብ ሊባል የሚገባ ነገር ቢኖር በምኒልክ ግዜ የዛሬ 125 አመት የተቀበረ ፈንጂ አሁንም እየፈነዳ መሆኑ ነው። ትግርኛ ተናጋሪውን ህዝብ ለሁለት ከፍሎ የማናናቅ እና የማተራመስ ስራው አሁንም ከ 125 አመታት በኋላ በሚኒሊክ የልጅ ልጆች ቀጥሏል። የሰሜንና የደቡብ ትግርኛ ተናጋሪዎች ሚኒሊክ በፈጠረው ድንበር ተለያይተው እርስ በእርሳቸው እንዲጫረሱ የማድረጉ ሴራ አሁንም ኣንደቀጠለ ነው። አንዳንዶች ኤርትራ ከእናት ሃገሩዋ ጋር ተቀላቅላ በነበረችበት ጊዜም ችግሩ ነበር ይላሉ። ይሁንና ትግራይና ኤርትራ የሚለው ክፍፍል ግን በአጼውም ግዜ ሆነ ከዛ በኋላ ቀጥሎ እንደ ነበር አይክዱም። ክፍፍሉ የአስተዳደር ነው ይበሉ እንጂ ከዛም የዘለለ ነው። መረሳት የሌለበት ጉዳይ ግን የአገር ውስጠ ክፍፍሉ ገዢዎቻችን እንዲመቻቸው የሚፈጥሩት መሆኑ ነው። ይሕ ማለት መስፈርቱ የህዝቡ ፍላጎት ሳይሆን ለግዛትነት ምቹ መሆን ነው። ይህንን ጥያቄ ለመመለስ ጥረት ደረገው ኢህአዴግ ቢሆንም በሚኒሊካውያን የጭራቅ ምስል ተሰጥቶት የጀመረው እንዳይሳካ ለማድረግ ተሞክሯል። ይሳካ ኣይሳካ የታየ ሆኖ፣ ለአሁኑ የአገሪቱ ቅርጽና አወቃቀር የታገሉ ብሄር ብሄረሰቦችን ማጣቀሻ ማድረጉ በቂ ይመሽለኟል።

የዚህ ፅሁፍ መነሻ ዋና አላማ ምኒሊካው ክ125 አመታት በኋላ ሁለተኛውን የትግራይ ክፍል ከኢትዮጵ ለመነጠል የወሰዱት የዘር ማጽዳት ዘመቻ ነው። የዚህን አመት 125ተኛ የአድዋ ድል በኣል ስናስብ ምን እናስተውላለን የሚለው ጥያቄ መመለስ አለበት።

የዛሬ ሁለት አመት የተጀመረው የምኒሊክ እሳቤ ቀጣይ ዘመቻ በትግራይ ህዝብ ላይ ተጀምሯል። ይህ ዘመቻ ህዝቡን ሳይሆን መሪዎቹን የሚል ይመስላል። እኛ ካልገዛን አገር አስፈልገንም የሚል ቅኝት አለው። መሬቱን እንጂ መሬቱ ላይ ያለውን ህዝብ አለመፈለግ ዋና መገለጫው ነው። ይህ የ125 አመታት በተከታታይ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተሸጋገረ የመጣ ዘመቻ ከልጅ ልጅ ሲወራረድ ቆይቶ ሆድ አደሮችም ተቀብለውት በሰሜንና በደቡብ ተጋሩን ደም በማቃባት የሽብር አረምን በመሃላቸው ለመዝራትና እርስ በራሳቸው እንዲጠባባቁ ለማድረግ ምኒሊክና ሃይለስላሌ የሰሩት ደባ ለተወሰነ ግዜ በድንብርብር አገሪቱን ያስኬደ የፖለቲካ ሸፍጥ አካል ነው። ይህ ሸፍጥ አድጎ አድጎ የነበረችውን የኢትዮጵዊነት እንጥፍጧፊ አድርቆ  የትግራይ ህዝብ ምኒሊካው መኖር እንዲፈልግ ምክንት ሆኗል።

እዚህ ላይ ልብ ሊባል የሚገባው ነገር ሸዋውያን (የእሳቤው ተጋሪ የሆኑና ከየትኛውም የዘር ሃረግ የሚመዘዙትን ያካትታል) የዛሬ 125 አመት ምኒሊክና ሸዋ ተባብረው የትግራይን ግማሽ አሳልፈ ሠጡ። አሁን ደግሞ የተቀረውን ግማሽ አካል በመቀጠቀጥ የውጭና የውስጥ ወራሪ በማሰማራት ወጣቶችን፣ አረጋውንን፣ ሴቶችን፣ አካለ ጎዶሎዎችን በመግደል ሴቶችን መነኮሳትን እና ህጻናትን ሳይቀር በመድፈር፣ ለፍቶ አዳሪውን በረሃብና ቸነፈር በመቅጣት፣  ለዚች አገር የተዘረጋውን የትግራዋይ እጅ ነከሱት። ሕዝቡ ኩራቴ የሚላቸውን ልጆቹን በካቴና በማሰር፣ በሞታቸው እና በግፋቸው ላይ በመዝፈንና በማላገጥ፣ በደስታ ስካር ሰክረው እና የደስታ ችቦ ለኩሰው ያላቸውን የጥላቻ ጥግ አሳዩት። ምግብና መድሃኒት እንዳይደርሳቸው በማድረግ፣ ከ12 አመት በላይ የሆኑትን ሁሉ በጠራራ ጸሃይ በመረሸን፣ በተጋሩ ኃዘን ላይ በአሉን ለማክበር ተዘጋጅተዋል። የዚህ ጉዳይ ልላው አሳዛኝ ገፅታ አሁንም ማንበርከክን እና ዘር ማጥፋትን በመሳርያ በመጠቀም በገደሉትና በበደሉት ህዝብ ላይ በስላቅ መመላለሳቸው ሲሆን ለዚህ ማስዋብ እንዲሆናቸው ከጥትይት የተረፈውን በበሽታና በረሃብ ለማጽዳት መቁረጣቸው ነው። ከቁጥጥር አድማሳቸው ውጭ የሆነውንም በስነልቦና እንዲሸማቀቅ ለማድረግ ምስሎችን በአደባባየ በማዋረድ፣ አዛውንቶችን በካቴና አስሮ በመሳለቅ። አካል ጎዶሎዎችና ማየት የተሳናቸውን በውጊያ ገደልናቸው በማለት በፍጹም ስብራት ራሱን እንዲደፋ እያደረጉ ነው። የትግራይን ህዝብ ሳይሆን መሬቱን አስበልጠው ወደው አንተም የኛ ነህ ብለው ቢዘምሩ ለህዝቡ ምኑ ነው። አንዴ ታላቁ መሪ መለስ እንዲህ ብሎ ነበር አገር ያለ ህዝብ ምንድ ነው? ከንቱ።

የዚህ አመት 125ኛ የኣድዋ ድል በኣል ተጋሩ ለብቻቸው በአሉን የሚያከብሩበት መባቻና የአድዋ ባለድሉ ትግራዋይ ታሪክ መመለስ የሚበሰርባት ዋዜማ ናት። ቀጣዩ አመት ወይም ከዛ የሚቀጠለው አመት ወይም ደግሞ ኣንድ ቀን ኣውን ይሆናል። ክዚች አገር ጋር ያለውን  የመጨረሻ የቁርኝት ገመድ የሚበጠስበት እና የሚኒሊክን ሸር የምናስታውስበት ብቻ ሳይሆን 125 አመት ለፈጀ የሽዋ ፖለቲካ መቋጫ የሚበጅበት አመት ይሆናል ሢበቃም እኮ ያበቃል ትግራይን ብለን የምንምልበት ጊዜ ይመጣል ኢትዮጵያ ያለፈ ታሪካችን ትሆናለች። ለዚህ ላበቁንና አይናችንን ለከፈቱልን የትላንትና የዛሬ የትግራይ ሰማእታት ማስታወሻ ትሁንልኘ።

 

ቸር ያስማን

 

 

ለማነኛው አስተያየታቹ፡ nardoshiyab@outlook.com

 

Back to Front Page