|
ስሜን አልቀይርም
ኢዮብ ከጮማ እምኒ 11-06-20
ስሜን አልቀይርም ... ስሜ የራሴ ነው የትሰጠኝ ከአባቴ ... የተመረቀ በእናቴ ሐጎስ ነኝ ... የ ገ/መስቀል የልጅ ልጅ የዛች የቆፍጣና ... የለታይ የልጅ ልጅ ስብሀት አጎቴ ነው ... አባይ የእህቴ ልጅ አንበበው ፓስፓርቴን ... ስሜ ነው ግደይ ... ... የዛ የጀግናው ልጅ ከስምህ ነው ችግሬ ... ብለህ ብትበድለኝ ፓስፓርቴን አይተህ ... መብቴን ብትነፍገኝ ስሜን አልቀይርም ... የትግራይ ውላጅ ነኝ
የ ኬርያ ልጅ ... የቀሼ ገብሩ ወንድም የአሞራ አጎት ... የአምባዬ አባት ... ... ስሜን አልቀይርም ... ስሜን አልቀይርም
መች እኔ በደልኩህ ... ስምህን አይቼ ሽዋንግዛው ሆነህ ... በአባትህ እርግጤ ደመላሽ አጎትህ ... መሆኑን አውቄ ... መች አዳላሁ እኔ .. ስምህን አይቼ
ስሜን አልቀይርም ... ስሜን አንበህ ... ደምህም ከፈላ አልቀይርም ስሜን .. ዛሬም ሆነ ኋላ የሀጂ አብዱ ልጅ ነኝ ... የዛ የስመ ጥሩ የመለስ የአክስት ልጅ ... የዛ ጀግና ኩሩ ኃየሎም ታላቄ ... ስዮም አብሮ አደጌ ስሜን አልቀይርም ... አልሻም አንዳርጌ ስሜን አልቀየርም .... .... እርገጣቸው ብዬ .. ራሴን እኔ አልጠራም
Back to Front Page |