|
አይጥ ሞቷን ስትሻ
የሩሳሌም ባርናባስ Nov 3rd 2020
አይጥ ሞቷን ስትሻ ስታበዛ ሩጫ ሄዳ ታሸታለች የድመት አፍንጫ ድሮ በልጅነት አማርኛ ስማር ይህች ትንሽ ግጥም ታስደስተኝ ነበር ታዲያ ዛሬም ይኸው ኣብይቱ አይጥ ከበፊት አይጦች መስሏት የምትበልጥ የተንኮል መአቶች ሰብስባ ለቃቅማ ኢሱ የሚሉት ግንድ ጀርባው ላይ ተጋድማ የተንኮል መረቧን በሰሯ ጠምጥማ ተሽሎክሉኳ ገባች ትግራይ ልታደማ:: ትርክት ወሬ ሰርታ ለሁሉም ለፈፈች ትርክቱንም ስሙ "ድመቷ ህወሓት አላኖር አለችኝ
አማራ አገር መጥታ በጩቤ ወጋችኝ ኦሮሞ አገር ስሸሽ ሸኔን ተገን አርጋ በጥይት ፈጀችኝ ቤንሻጉል ላይ ብሄድ በቦምብ አረሰችኝ ጩኸቴን ስሙልኝ ከዚች ክፉ ድመት ባካችሁ ገላግሉኝ ለክፉ ቀን ብየ ወታደር ባሰፍር የሰሜን ጦር ሃይሌን ዘረፈች በስውር አለቃ አሳፍሬ መቀለ ብልከው ከድፍረቷ ብዛት አሳፍራ ላከችው ትእግስቴም አለቀ ከጫፉ ደረሰ ተኝቼም አላድር ህወሓት የሚሉት ካልተደመሰሰ ጒዳየም አደለ አገር ቢደረመስ እኔን ያልፈለገ ቢሞት ሆነ ቢያለቅስ ጦሬን አንስቻለሁ ብልጽግናን ላነግስ ከጓደኛየ ጋር ከጀግናው አሳያስ። ህወሓት ድመቷም እንዲህ ነገረቻት፣ 'አንቺ መርዛም አይጥ አብይ ነኝ ባይዋ እኔ አገር ስትመጪ ስምሽ ነው ኣንጭዋ' 'አልሰማሽም እንዴ ወይስ ረስተሽው ነው ካንቺ የከፉ አይጦች መቃብር እዚህ ነው' ነይ ግቢ ላስጐብኝሽ ወልቃይት ነው ራያ የቱነው ምኞትሽ? ወደመጣሽበት ጒድጓድ ነው ምከትሽ ነይ እስኪ ጠጋ በይ አፍንጫየ ድረሽ ከነግሳንግስሽ እዚህ ነው እምቀብርሽ የሁሉን ገበታ መርዘሽ መራርዘሽ ስትቅበጠበጪ ከኔ አፍንጫ ደረስሽ? አብይ ሞቷን ስትሻ ስታበዛ ሩጫ ሄዳ ታሸታለች የወያኔ አፍንጫ ሲባል የነበረው እስከነ ተረቱ ባንቺ ላይ እንዳይደርስ በክልፍልፊቱ አይጥ ሞቷን ስትሻ ሰታበዛ ሩጫ ሄዳ ታሸታለች የድመት አፍንጫ።
|