Back to Front Page

ታሪክ ፊት ለፊት ሲገጥምህ ያለህ አማራጭ፤…

 

ታሪክ ፊት ለፊት ሲገጥምህ ያለህ አማራጭ፤

ከባላገሩ

ወርሃ ጥቅምት

 

በዚህ ጽሁፍ የአህዳዊ የአብይ የግለሰብ አምባገነን  መንግስት ተቃርኖዎችን ለማመለከት ይሞከራል ። በአብይ መንግስት ዘመን እያንዳንድዋ ቀን  የጦርነት ዋዜማ ሆናለች።የአብይ ውስጠ ተቃርኖ አምባገነናዊ ጨፍላቂ ህልሙ መደመር በሚል ጭምብል ሸፋፍኖ ሊግተን መሞከሩ ነው።የአገራችን ህዝቦች ከአደጋ ጋር ተፋጠዋል። ህገ መንግስታዊ  ስርአት እየተናጠ ነው ።  አሃዳዊ ዲሞክራሲያዊ  አይደለም ያለው ማነው እየተባለን ነው ። ህገ መንግስት ይከበር ብሎ ዘብ ለቆመው የትግራይ ህዝብ ለመቅጣት በጀት ተከለክለዋል። ክልሎች ፈራርሰዋል ዲሞክራሲያዊ ብሄርተኝ ነት  ተውንጅለዋል ።የፖሎቲካ ፓርቲዎች  የማክሰም ወንጀል እየተሰራ ነው። እስከወዲያኛው ነጻ ምርጫ ብሎ የለም ተብለናል። የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላት አምባገነን ኢሳያስ የአገራችን የጸጥታ መዋቅር ተቆጣጥርዋል። ህዝባዊ ትግል ቀጥለዋል ። ዲሞክራሲያዊ ህገመንግስት የሚጋፍ ሃይሎች በርትተዋል ።የዲምክራሲ ሃይሎች የመጨረሻ  ምሽጋቸው አጠናክረው ወደ ማጥቃት  ተሸጋገረዋል ።ታሪክ ፊት ለፊት ሲገጥም  ያለው አማርጭ  በቡጥኝ መምታት ነው ።እዚህ ላይ ደርሰናል

  አገራችን የሁላችንም ስለሆነች የገጠመንን ፈተና እንዴት መወጣት እንዳለብን መምከር አለብን ።  እውነትን ፊት ለፊት መጋፈጥ አለብን። አብይ በድንገት መጣ በድንገት ወደ አንድ አረብ አገር ይሄዳል ይሰደዳል። እኛ ግን መኖሪያችንም መቀበሪያችንም አገራችን ኢትዮጵያ ናት ። አብይ አንድ ኢትዮጵያዊ ማግኘት ያለበት ከፍተኛ ሃላፊነት ቢሰጠውም በህልም እና  በትንቢት ለመኖር መርጦ የአገር ክህደት ፈጽመዋል ።  ለነጻነት መስዋዕት መክፈል ለኢትዮጵያውያን አዲስ ባለመሆኑ አሁንም የክህደት መንግስት የሚወገደበት ሰአት ደርሰዋል 

Videos From Around The World

አገራችን የገጠማት ፈተና እየተንደረደረ ከሚመጣ ናዳ ማመሳሰል ይቻላል። ናዳው ሲመጣ እያየን ከናዳው ፍጥነት በላይ መሮጥ አልቻልንም። በዚህ ምክንያት ከጭፍለቃ ስለመትረፋችን  አጠራጣሪ ሆኗል። እንዳንሮጥ የአብይ ቡድን እግር ተወርች አስሮ ይዞናል።ታሪክ ፊት ለፊት ሲገጥምህ በቦክስም ጭምር መምታትና ማለፍ ያሰፈልጋል።  ቡድኑ ብልጽግና ብሎ በመሰየም አገር የተሰራችበትን ድርና ማግ እየበጠሰ ዋልታና ማገሩዋን  እያፈረሰ ይገኛል።  ሰው በሃይማኖቱ፣ በማንነቱ እና በፖለቲካ እምነቱ በየዕለቱ እየተገደለ ነው ። የጋራ የአንድነት ቃል ኪዳን ህገ መንግስቱን እንደተመኙት አፍረሰውታል።  የብሄር ብሄረሰቦች  ህዝባዊ ስልጣን በጠራራ ጸሃይ ተቀምቷል። የቡድን እና የግለሰብ ህገ መንግስታዊ መብት አጥር ወይም ከለላ ተጥሷል። የትግራይ ክልል እንነጋገር ባለች ከፌደራል  ማህበራችን እንድትወጣ  እየተገፋች ነው ።ዲሞክራሲያችን ከአደጋ ይጠብቁታል የተባሉት ተቋማት በተምች ተመትተዋል። ሀገር ወዳዶችም በፍርሃት ተውጠዋል።ትንሽ የጮሁትም  ወህኒ ላይ ተገኝተዋል።  ዋስትና የለንም።ዋስትናችን  እና ተስፋችን በዲሞክራሲያዊ ምርጫ የተመሰረተው የትግራይ መንግስት ብቻ መሆኑ ደግሞ በጣም ይገርማል  ።

ጭፍለቃን በመደመር ሽፋን፤

የለውጥ ሰው ነኝ ያልከው እንዴት ነህ ።  በጊዜ የጮኸ ጅብ አመሻሹን ላይበላን  ዋስትና የለንም።በድንገት የሞት ጥላ ስር ተገኘን። የአህዛብ አረመኔ ድርጊት ተመኝቶ የአቶ ኢሳያስ ምክር አስፈለገው ። ከዚያማ ስውር ግድያዎች ፣ድብቅ እስርቤቶች ለመድነው። ። የአሁኑ ቡድንም ብቸኛው አማራጭ  መደመር  መሆኑ እየነገረን ነው።በመደመር  ሽፋን ያለ ተፎካካሪ በብቸኝ ነት   ዘላለሙን ሊገዛን ያስባል። የፓርቲ ብዙህነት ፣በፖለቲካ ምርጫ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር የሚባል ነገር የለም። ልዩነት በአንድነትም ውበት መሆኑ ቀርቶ  አፍራሽ ተብለዋል ። ተፈጥሯዊ የሆነውን የብዙህነት ጸጋ ተነፍገናል ። መደመር ማለት ማፍረስ ሆነ ።  የመደመር  አገዛዝ  በመፈንቅለ መንግስት፣ በመፈንቅለ ስርአት፣ በመፈንቅለ ፈዴራል፣ በመፈንቅለ ክልላዊ መንግስታት መፈንቅለ ፓርቲዎች፣ መፈንቅለ ሃይማኖት  በመጨረሻም በመፈንቅለ  አገርና ህገ መንግስት ይገለጻል። ክልሎች ፈራርሰዋል። የፓርቲ መሪዎች ታስረዋል። ስብስባም ማካሄድ የሚቻልበት ዕድልም የለም።ወታደራዊ አስተዳደር ሰፍኗል ። በአጠቃላይ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ  በተንጣለለ ባህር በመስመጥ ላይ በምትገኝ መርከብ የምትመሰል ሆና ተሳፋሪዎቿ ደግሞ  በስጋትና በጭንቅ ተውጠው ኤሎሄ ኤሎሄ  እያሉ ይገኛሉ። በአደጋ ግዜ የደርሰልናል የተባለው መከላከያ  የገዥው ጠባቂ

ብዙህነት ያንድነት ጸጋ፣

  በብሄር ማንነት እና በአገራዊ አንድነት መካከል ያለውን አንድነት የማይረዳ አመራር ከኢህአዲግ ማህጸን መፈልፈሉ ገራሚ ነገር ነው። የፈረንሳይ አብዮት ሂዶ ሂዶ ናፖሊዮን ቦናፓርት መውለድ የወቅቱ ጸሃፍት በአግራሞት ጠይቀዋል። የፈረንሳይ አብዮት አይጥ ወለደ ብለው ጻፍዋል ።አብይ ወደ ስልጣን  ሲመጣ ቦናፓርት መምጣቱ ብዙ ሰው ማስተዋሉ እርግጠኛ መሆን አይቻልም ። የኢትዮጵያ የዲሞክራሲ  ስርአት መቀልበሱ እስካሁን ያለው ሁኔታ አመላክቷል ።የአብይ የመጀመርያ  የፓርላማ  ንግግሩ  በብዙዎቹ  ዘንድ  ጥያቄ ጭሮባቸዋል ።  አጠያያቂው ጉዳይ  ጠ/ሚኒስትር የመንግስት ስልጣን  የብሄር ብሄረሰቦች  ስለመሆኑ ሳይነገር ማለፉ  ነበር። እየቆየ ሲሄድ ብሄር ብሄረሰብ የሚለው ነገር ከነጭራሹ እየተጸየፈው ሄደ። ይባስ ብሎ የብሄር ብሄረሰቦች  አመታዊ በአል በተከበረበት ወቅት የአገሪቱ ፕሬዝዳንት በመሰቀል አደባባይ  ባደረጉት ንግግር ብሄር የሚለውን ቃል ሳይናገሩ አልፉት ።  ፕሬዝደንቷ የተቀመጡበት ስልጣነ ወንበር የብሄር ብሄረሰቦች መሆኑን በጣሙኑ ዘነጉት ።

 ያስደመመው ነገር  አመራሩ ባለፉት ሁለት አሰርት አመታት የአንድነት ጉዳይ ተረስቶ ነበር የሚለው ትርክቱ በስፋት ማስተጋባት የጀመረው ወደ ስልጣን ከመውጣቱ በፊት ጀምሮ ነው። አንድነት ከምዕተ አመት በላይ ተሰብኮ ሲያበቃ ተረስቶ ነበር ሲባል ግራ የሚያጋባ ነው ። ኢህአዲግ፟ም ለብሄር መብት  ቅድሚያ ይሰጥ ነበር ተብሎ በአጥፊነት ተከሰሰ ።  ይህ አዲስ ትርክት  ጸረ ህገ መንግስት መሆኑ ያስተዋሉ ወገኖች አልነበሩም ማለት አይቻልም ።በዚህም  አገዛዙ ገና ከማለዳ  ያልገመተው ህዝባዊ ተቃውሞ ገጠመው።ሆታና ጭብጨባ ሲጠብቅ የነበረው ቡድን የብሄር መብት መርገጥ በጀመረበት ቅጽበት ተቃውሞ በሀይለኛው ገጠመው። በሲዳማ በወላይታ በኦሮምያ ወጣቶች ኮራን። የደቡብ ክልል የብሄር ብሄረሰቦች መብት ዋልታና መከታ ሆነው ብቅ አሉ ። አዲሱን ቡድን አስጨነቁት። በመጨረሻም ሲዳማ በአሸናፊነት ክልሉን አወጀ ። ገዢው እጁን ለመስጠት ቢገደድም አሁንም ሲዳማ ከብልጽግና ቡድን ነጻ መውጣት ይቀረዋል። ቡድኑ ህዝቦች ለመብታቸው ባሳዩት  ቀናኢነት እየተደናገጠ ሄደ። ክልሎችን በወረራ ለማፍረስ የወሰነውም ይህን ድርጊት ተከትሎ ነው። የወላይታ ወጣቶችም በቀጣይ መስዋዕት በመክፈል ላይ ናቸው ።በዚሁ መካከል የብሄር ጥያቄ ለማክሰም ኢህአዲግን በአስቸካይ ማፍረስ አስፈላጊ ተደርጎ ተመከረበት ።ከኢህአዲግ መፍረስ በሃላ ህገመንግስታዊ ስርአቱ የመናድ አጀንዳ የተያዘ ቢሆንም ከእሳት ጋር መጫወት መሆኑ ስለታመነበት ለግዜው ተወት ያደረጉት ቢመስሉም ዋና አላማቸው ማፍረስ በመሆኑ ፈጸመው የሚተውት አይሆንም። ይህን ያህል ተቃውሞ ይገጥመዋል ብለው የገመቱት አልነበረም ።ያለ ጭሆት ቢፈረስ ይሻላል ተብሎ ተመከረበጥ

ከደቡብ ህዝቦች ጋር የነበረው ግብግብ የተጀመረው አብይ ራሱ ለስብከት አዋሳ በገባበት ዕለት ነበር ። ሰውየው የዲሞክራሲ ጥያቄ በስብከት የሚመለስ ይመስል ወጣቶችን ለማማለል ቢሞክርም ሳይሳከላት ቀረ። የኤጄቶ ጥያቄ በህገ መንግስት መሰረት መመለስ ያለበት መሆኑ እየታወቀ በቃላት ቅላጼ የማደንቆር ሙከራ ተደረገ። የደቡብ ህዝቦች የተለያዩ ብሄሮች  መብታቸው ለማስከበር ያሳዩት ቆራጠነት በአለት ይጻፋል።ጨፋላቂዎች  ያስደነገጠቸው ጉዳይ የደቡብ  ብሄሮች  ለማንነታቸው  ያሳዩት ቀናኢነት ነበር ። የደነገጡ ገዢው ብቻ ሳይሆን ተቀጥላ እና  ደጋፊ ማህበር አርገው  የሚቆጥርዋቸው የአሃዳዊ ፖሎቲካ ተከታዮችም ነበሩ። የደቡብ ህዝቦች የአገሪቱ ዋልታና ማገር መሆናቸው ተዘንግቶ ነበር ።ከዚህ የተነሳ ህገ ወጥ ቡድኑ  ያልተመጣጠነ የሃይል እርምጃ  በወሰደበት ግዜ ደስታቸውን ገለጽ። አሁንም የወላይታ  እና ሌሎች ብሄሮች  በራሳቸው መንገድ እና ፍላጎት  መደራጀት አለባቸው ።ሙሰኛ አደራጅ አያሰፈለጋቸውም። (አባ ዱላ ደቡብን ሲያደራጅ)

ኢሃአዲግ ማፍረስ፤

ድርጅቱን የማፍረስ ፍላጎት የአገራችን ዲሞክራሲ ከማስፋት ጋር የተያያዘ አይደለም ።ዲሞክራሲ በአንጻራዊ ምስክርነት  በኢህ አ ዲግ ዘመን ይመስለኛል። ጥያቄው የዲሞክራሲና የልማት ጉዳይ አልነበርም ። የተፈለገው ለቡድንና  ለግለሰብ መብት የሚታገልው  ኢህአዲግ  የብሄሮች ሄርሰቦች  ድርጅት ነው በማለት ማፍረስ ነው  ። ድርጅቱ ታሪክ የለወጠ    የነፍጠኞቸ  ስራአት  ያሸነፈ የታጋዮች ስብስብ መሆኑ ሌላው ችግር ነው  ። ደርግ ን የመጣል ታሪክ የአንድ  መንግስት መለወጥ ሳይሆን የስር አት ለውጥ አስከትሎ ፌደራል ስር አት በመተከሉ ትሪካዊ ጠላቶች ፈጥረዋል ።በዚሁ ደርኝ የመጣል ታሪክ  ህወሃት የአንበሳ ድርሻ የነበርው ኢሆንም ፌደራል ስር አቱን የመገንባት ኝ የሁልም ድርሻ ነበር ። የኢህአዲግ ታሪካዊ ጠላቶች  ጽረ ፈደራል ቡድኖችና የኤርትራ ፕረዝዳንት ናቸው። ድርጅቱን  የማጥፋት ዕቅድም  ከደርግ ዘመን የጀመረ  ነበር ።ይህን ለማስካት በኢህ አዲግ ትል እስኪበቅል  መጠበቅ ነበረብን ።ይህም  በአብይ ዘመን  ተከሰተ ። የሁሉም ስትራተጂ ደግም  ህወሃትን ማፈረስ ነበር ። የኢሳያሰን የአብይ ስርጉድም መነሻውም ይህ ነው ።

 

የትምክህት ሃይሎች  ከዘየዱት ዘዴ አንድ የኢህ አዲግ  አባል  ድርጀቶችን የመቆጣጠርና  ማፈራረስ ነበር ።ቀድሞው በቀላሉ የተቆጣጠሩት ብ አዴን ቢሆንም ቀስበቀስ ኦህዲድን በቁጥጥር አስገቡት ። የደቡብ ህዝቦች ዲሞክራሲዊ ድርጅት አቶ ሃይለማሪያም አፍርሶት ሄደዋል ።ነፍጠኞች ህወሃትን ባይከጅሉትም እሱን የመነጠል ስራ ለአመታት ተሰርተዋል ። የነፍጠኛች ስትራትጂ ኢህ አዲግ ከኢትዮጵያ ህዝቦች፣ ህወሃትን ከኢህ አዴግ ፣ይህ ሲሳክ ደግም  ህወሃትን ከትግራይ ህዝቦች የመነጠል ስልት ተከትለዋል ። ፈደራል ስራአቱ የሚፈርሰው ህወሃት ሲጠፋ ነው በማለትም ተረባረቡበት ። የሁሉም ኒዮነፍጠኛ ሊህቃን ፍላጎት ህወሃትን ማፈረስ ነው ። አብይም ይህን የቤት ስራ  ተሰጠው ።  ዛሬ አዲስ አ በባ ፈንቅል ፤ ትግራይ ብልጽግ ና ፤አርጋዊ በርሄ  ሽማግሌ ጅኔራሎች በመልመል ትግራይ ላይ የሚካሄድው ዘመቻ የዙሁ ያልተሳካ ሴራ አካል ነው። ሲራው ነገ በሌላ መልክ እንድሚቀጠልም መገምት ይቻላል ።ጦርነትም አይኖርም ብሎ ማሰብ አይቻልም።

በዚሁ በአፍሪካ ቀንድ ፖሎቲካ በተካሄድት  ትግሎች   ኢህ አደግን  የመሰለ ደርጅት ተከሰቶ አያውቅም ። በኢትዮጵያ  የነበሩ ገዢ መደቦች በማሸነፍ አዲስ የፌደራል ስራ አት መሰረተዋል ።አሁን በስራ ላይ ያለው ህገመንግስትም የኢህ አዲግ የትግል ጻማ ነው ። የኤርትራ ነጻነትም ከአትዮጵያ የዲሞክራሲዊ ትግል  ና ድል የተያያዘ ነው ።  የኢህ አዲግ  ሌላው  መታወቅያ ያሰመዘገበው ፈጣን ልማት ነበር ።ችግሩ በዚሁ ረዥም ሂደት   አባል ድርጅቶቹ   በገዢ መደብ አስተሳሰብ እየተሰረቁ መሄዳቸው ነው   ። በመጀመርያ ሰላባ የሆነው ብአዴን ነበር ።ለመሰለብም ቅርብ ነበር ።  ከቀደሞ ገዢ መደብ ብሄር የበቀሉ ታጋዮች ድርብ ሀላፊነት እንዳላባቸው በመርሳት  ወደ ቀድሞ ትርክት ተመለሱ።  ራሳቸውን የገዢውን መደብ አስተሳሳብ ማራመድ ጀመሩ ። በሄዱበት  ሁሉ የገዢዎች ካባ መከናነብ ብቻ ሳይሆን የቀድሞ ሰንደቅ አላማ ማንዥርገግ  ጀመሩ ።እምዮ ምንሊክ ላይ ሂስ መሰንዘር ጽር አማራ ተባለ ። ገዢ መደቦች የሁሉም ህዝቦች ጠላቶች መሆናቸው እየታወቀ ለአማራ ህዝብ  ሊያለብሱት ጥረት አደረጉ። የገዢው ቡድን የሚገማ አስተሳሰብ ገበያ ያለው መሰላቸው ።ትርክት እንቀየር በማለትም አስደንጋጭ አስተሳሰብ ማራመድ ተያይዙት ። ትርክት መለወጥ ማለት የቀደም ግዢ መደቦች መላዕክት ነበሩ እንድንል እስከማስገደድ የሚሄድ ነው። የቤትመንግስት ዕድሳት የሂደቱ አካል  ሆነ ። የገዢውች ምስልም  እንድንናፈቀው አሸመንምነው አቀረቡት ። በአጭሩ  የታሪክ ክለሳ ተጀመረ።ገና  ብዙ ልበ ወለድ ታሪክ እንሰማለን።

ይህ ሲባል ኢህአዲግ  ከችግር ነጻ ነበር ማለት አይቻልም።ከችግሮቹ  አንዱ  ሁሉም ብሄሮች በድርጅቱ  አለማቀፍ ነበር ። ሶማሊ አፋር ጋምቤላና ቤኒሻንጉል በአባልነት አልታቀፍም  ።በአሁኑ ወቅት ከእነዚህ  ክልሎች በኢህ አዲግ አለመታቀፋቸው   ቅሬታ  ሲያቀርብ ይሰማል ።  ነገር ግ ንቅሬታው   ተገቢ   የሚሆነው ከትግል አንጻር ፌደራል ስር አትን ለማዳን ትልቅ አቅም መሆን ሲችሉ ፍልሚያው ሲከር ዳር ላይ ቆመው የውጤቱ ሰላባ መሆናቸው ነው ።  ከዚህ ውጭ አብይን ለማጀብ ተገለን ነበር የሚልው ትርክት ግ ን እውነታ የለውም ። መገለል ከነበረ ክህገ መንግስቱ አንጻር ብቻ መታየት አለበት ። የክልሎቹ ተወላጆች የመደራጅት መብት በተለየ የከለከለ ህግ አልነበርም ። ፈደራል ስራአት  ሁሉም የተበደሉ ብሄሮች በጋራ የፈጠሩት  መሆኑ መካድ አይቻልም።

 ክልሎችን የማፈረስ ተግባር የተጀመረው በሶማሌ  ክልል  ሆኖ ሲታይ ብዙ ጥያቄ ያሰነሳል ። ለቅሶው ከፍየልዋ በለይ ነው የሚለው የሶማሊ አነጋገር እንድናነሳ እንገደዳለን ።የሶማሌ ክልል ህዝብ በአፍሪካ ረዥሙ የነጻነት ትግል የተካሄደበት አካባቢ ነው ።የነጻነት ትግሉ የተጀመረው አጼ ምኒልክ በህይወት እያሉ ነበር ። የኋላ የኋላ የሶማሊያ የማስፋፋት ፖለቲካ እየተቀለቀለ በመሄድ የክልሉ ህዝብ ትግል  በአግባቡ አልተረዳነውም ። ይህ አሁንም በክልሉ የሚነሱ ጥያቄዎች  በአዲስ አበባ አይን የሚጠረጠሩ ናቸው ።የሶማሊ ህስብ አትዮጵያዊ ሆኖ  በእኩልነት  የታየው  በአሁኑ ፌደራል ህገ መንግስት ነው ። ይህ ታሪክ መከለስ አይቻልም። የአሁኑ የክልሉ መሪ ታሪክን በመከለሰ የብሄር ጭቆና የሚባል ነገር እንደልነበረ ሲናገር ከመስማት የሚያሳፍር ነገር  የለም።በእርግጥ የሰውየው ስልጣን የሚመነጨው ከሶማሊ ህዝብ ሳይሆን ከአዲሳበባ በመሆኑ እንዲያ ማለቱ  ከግሉ ጥቅም ጋር የተያያዘ መሆኑ የታወቀ ነው ። የሰውየው ትልቁ ችግር የሶማሊ ክልላዊ መንግስት በማፈርስ ተባባሪ መሆኑ ነው ።ክልሉ የጀገኖች መፍለቅያ የመሆኑ ያህል አልፎ አልፎ ከህዲ ይታጣበታል ማለት አይደለም ።   አብዲለ ዛሬ እስርቤት በመሆኑ ብዙ ማንሳት ተገቢ ባይሆንም  ችግር አልነበርውም ማልት ኝ አይቻልም ።ነገር ግ ን  የአብዲለ መንግስት  አካባቢውን ወደ ልማት  ጎደና ያስገባ  ነበር ። ክልሉ የልማት ተቋዳሽ ሆኖ አያውቅም ።ክልሉ Military Garrison  እንደነበር  የሚዘነጋ ሰው ይኖራል ብዬ አልገምትም ። ሶማሊ ከልል ትልቅ ዩንቭርስቲ፣ አይሮፕላን ማርፍያ  ትላልቅ የመሰኖ ፕሮጀክቶች  ወዘት አይተናል ። በራሱ ቋንቋ መማሩ ትልቅ አብዮት  ነው የሶማሊ ህዝብ አሁንም ነጻነቱ ሊመለስለት ይገባል። ህዝቡ በመረጣው ሊተዳድር ይገባዋል።መብቱ ነው ። ይህን የማይቀበል ወገን ጽረ አትዮጵያ መሆኑ መንገር አለብን። የአብዲለ መንግስት ጥፋት ኑሮት ከነበረም በህጋዊ መንገድ መያዝ ነበረበት ።የህዝቡ መብት  በአስቸካይ ካልተመለስ ትንሽ ቆይተን ጦሱን መክፈላቻን አይቀርም ።በመተማመን ለመገንባት የተጀመርው ስራአት  ከፍተኛ ጥርጣሬ የሚፈጥር ወንጀል መሰተካከል አለበት። ማመን ያለብን አንድ ሙስጤፌ የሚባል አጉራዘለል ሳይሆን  የክልሉን  ህዝብ ነው ።

 

 

የኦሮምያ ፖሎቲክ  በመሰረቱ የእኩልነት ጥያቄ ነው ። በኦሮሞ ስም የተደራጅ ድርጅቶች በሙሉ በመሰላቸው የኦሮም መብትን የማረጋገጥና የማሰከበር ነው ።የኦሮሞ ሊህቃን መካከል ተቃርኖ መኖሩ ማየቱ ተቃሚ ነው ። በአሁን ወቅት አሃዳዊ አስተሳሰብ የተጠናወታቸው ግለሰቦች የመጡት ከኦሮምያ መሆኑ ዳግም እወነታን እንድነመረምር ተገደድን ። ከኦሮምያ አካባቢ ብሄር ጠል ፖለቲካ እንዴት ሊፈጠር ቻለ ። በእውን የኦሮሞ ፖሎቲካ  አሃዳው አስተሳሳብ የማበቀል ዕድል አለው ።ይባስ ብሎ አሃዳኢው ቡድን የተወለደው   በኦህዲድ   ማህጸን መሆኑ ሲታይ  ደግም  ደጋግመን እንድጠይቅ እንገደዳለን ሌላው ገርሚ ነገር የኦሮሞ ታግዮች  ሌላ ተኪ ድርጅት ሳያበጁ የነበራቸው ድርጅት  ኦህዲድ በማፍረስ  ስትራተጂክ ስህተት የፈጸሙበት አካሄድ  ስንመለከት  አሁንም ተጨማሪ  ጥያቄ  ማንሳቱ  ተገቢ ይሆናል ። መቸም ቢሆን የአትዮጵያ የፖለቲክ ተቃርኖ እንደማይለወጥ እያወቁ መታለላቸው እንቆቁልሹ በቀላሉ አይመለስም። ኦቦ ለማ ለታሪክ ያበቁት ድርጅት እስኪከስም ድረስ ዝምታ መምረጣቸው ለምን ይሆን።እንደኔ አሁንም አልዘገይም ።የኦህዲድ ትልቁ ችግር  በነፍጠኛ  አራሙቻ መወረሩ  ነበር።እነዚህ ግለሰቦች  የትሮይ ፈረስ  ሆነው  ሆነው ድርጅቱ እንዲፈርስ ደሉተዋል ።የኦሮምያ ታጋዮች በኢህ አዲግ ማመጻቸው ተገቢ ነበር ። ሆኖም የአሮሚያ ህዝቦች ጻማ ተነጥቀዋል ።የለውጡ መሪ የነበሩት ኦቦ ለማም ዛሬ የት እንዳሉ አይታወቅም ።ቲም  ለማ የሚባል  ዛሬ በ አብይ ተተክተዋል ። ኦሆዲድ የበላው የትምክህት ቡድን  ኦነግ ን  በተራው እየቆረጠመ ይገኛል ።ይባስ ብሎ አሁንም የገዢ ቡድኑ ውትፍ ነቃዮች ከኦሮም ነባር ታጋዮችም  እያየን ነው ። ነገሩ የሽረሪት  የህይወት ኡደት  እሆነ ነው

 

የኦሮምያ  ፖሎቲካ ለፌደራል ስራአቱ የማዕዝን ድንጋይ ነው እያለን በመጨረሻ ጽረ ፈደራል ስር አት ኦህዲድ ከተባለው የፖለቲካ ቡድን ፈደራል ስራአቱን የሚያፈርስ ነቀዝ ወይም ትል ይፈጠራል ብሎ የገመተ አልነበረም።  የኒዮ ነፍጠኛ  ሊህቃን ትልቁ ህልም የኦሮሚያ ምድር ነው ።በቀደም ዘመን በኦሮምያ የነበርው የወላጆጃቸው ጋሻ መሬት ያስታውሳሉ። አሁንም መሬት ይሸጥ ይለወጥ በሚል ፖሊሲ  ሊዘርፋት ይፈልጋሉ ።ቶሎ ካልተሰተካከል በስተቀር የሚቀር አይሆንም ።አሮሚያን ማፈርስ ያሰፈለገበት ዋና ምክንያት የአማራ ሊህቃን ፍላጎት ለማርካት ነው ።ሊህቃኑ  አራት ፋላጎቶች አሉዋቸው ። የመጀመሪያው የፖለቲካ ስልጣን ሲሆን  ሁልትኛው   የኦሮሚያ መሬት ነው። 3ኛው ደግሞ   ባህልና ቋንቋ መጫን  ነው ። 4ኛው  ደግሞ  የአሮሚያን ሃብት ለመቆጣጠር  ነው ።ኦሮምያ ከተቆጣጠሩ ደግሞ ባገኙት ሃብት አላማቸውን በሌሎች ብሄሮች ለመጫን ነው ።በመጨረሻም  የቀደሞ  አስተዳደር ከነሙሉ ክብሩ መመልስ ይሆናል ። የአሁን የአብይ መንግስት ትልቁ የቤት ስራም  የአሮጌው ስራአት  ማሰመለስ ነው  ።

  የአብይ ቡድን ኦህዲድን አብዝቶ ይጠለው ነበር ። ይህ ብቻ ሳይሆን አብይ የኦነ ግ ተቀባይነት ያሰቀናዋል ። ይህን ለመገዳድር ወደ ኦዲፓ  የስም ለውጥ ቢያደርግም  ኦነግ ጋር መወዳደር አልተቻለም ። የኦሆዲድ ይዞ ወደ ህዝብ በመቅረብ ኦነግ ን መውዳድር እንደማይቻል በመገንዘብ ድርጅቱን  የማፈርስ እርምጃ  አብይን  በስልጣን ከማቆየት ጋር የተያያዘ ነው ። ሆኖም አሮጌ ፋርሽ የመጣፍ ጉዳይ በመሆኑ ድርጅት መፍጠር የሚቻል አልሆነም። የአሮምያ ፖሎቲካ  ለመቆጠጠር ኦቦ ለማንም  የማምከን  እርምጃ የዚሁ ሂደት አካል ሆነ ።በመቀጠልም የአሮምያ አስተዳድር በታማኞች ቁጥጥር የማዋል እርምጃ ተወሰድ። ከኦቦ ለማ በኋለ ኦሮምያ  በወታደራዊ አስተዳድር ቁጥጥር ውስጥ ትገኛለች ።ዛሬ በአሮምያ  የጦርነት ቀጠና ተለውጣለች ።ለኦሮሞ  ህዝቦች መብት የሚታገሉ የፖለቲካ ቡድኖች   አመራሮችና  አባላት እሰርና ግድያ  እጣቸው  ሆነዋል።ያሳዝናል ።እዚሁ ድጃችን በደል እያየን አይተን እዳላየን ሆነናል ።

 

የኦሮም ድርጅቶች የማክሰም ሂድት ኦህዲድ ላይ አላቆመም ። አሁንም ቀጥለዋል። ፈተናው ለኦሮም ድርጅቶች  ብቻ  ከሰማይ የመጣ ቅጣት እንድልሆነ ግ ን ማየት ያሰፈልጋል ።  የተጠላው ነገር ብሄረትኝነት ነው። ከሁሉም የተጠላው ግ ን  በተለይም የኦሮም ብሄርተኝ ነት ነው ። የጦርነት አዋጁ  በሁሉም ቢሆንም አሀዳዊ ሃይል በቅደሚያ  አመድ አደርገዋለሁ ብሎ የተነሳው የኦሮሞ በሄረተኝ ነትን ነው ። እነ ኦቦ ለማ ከነበራቸው የትግል ልምድ ለምን እንደተዘናጉ ግራ ያጋባል ። ቢያንስ የትምክህት ፕሮጀክት የሚያውቁት ነው ። በመሆኑም የብሄር ድርጅቶች እንዲፊርሱ ታቅዶበት የሚሰራ ነው ። ሁሉም ብሄራዊ ድርጅቶች ዕጣቸው ተመሳሳይ ነው ።

 የአብይ ቡድን የኦነግን ተወዳጅነት መቋቋም ስለአቃተው  ከተቻለ ማጥፋት ካልተቸለ ደግሞ አመራሩን በማክሰም መቆጣጠር  ነው ።የሌሎች የኦፌኮም ዕድልም ተመሳሳይ ነው በዚሁ ቀመር የኦነግ  አመራር  ከፊል እስር ከፊሎቹ ደግሞ  የቁም እስር ላይ ይገኛሉ። ኦነግ በኦሮምያ ተወዳጅ እና የትግል አርማ በመሆኑ ሁሉም ይመኘዋል።ኦነግ ነፍጠኛውም ሊቆጣጠርው ይመኘዋል ።የአብይ ቡድን የኦነግ የአሮሞ ፖለቲካ  አንቀሳቃሽ ሞተር  የትግል አባትነት  ለመውረስ እየታተረ ነው። ሆኖም በአሮምያ ኦነግ ን ያህል ተደማጭነት ያለው ድርጀት የለም።ኦህዲድም ቢሆን አሮምያ ይህ ሁሉ አመታት ሲያሰተዳድር ሰው ልብ መግባት ሰላልቻለ  የራሱን መጠርያ የተጠየፈበት ሁኔታ ተመለክተናል።የድርጁት አባላትም ቢሆኑ ቆዳቸው ሲፋቅ ኦኖጎች ናቸው ሲባባሉ ነበር ። ድርጅቱ  ሲመሩ የነበሩ  ግለሰቦችም በተሰጣቸው ሃላፊነት አመዛዝነው ከመስራት ይልቅ ኦነግ ን ተመኝተው በድብቅ ሲያገለግሉ ነበር ። የአሁኑ የአብይ ቡድን ፋላጎት ግ ን  አነግ አጥፍቶ  የድርጅቱ እሴት መውረስ ነው ።አሁን የኦነግ  አመራር በራሱ ምስለኔዎች ሊቆጣጠረው እየሞከረ ነው ። ኦፌኮም ቢሆን ከአብይ ሴራ ነጻ ነው ማለት አይቻልም። የኦቦ በቀለ ገረባ እና የጅሃር መታሰር ምክን ያት  ተመሳሳይ ነው ።ጁሃር ተወዳጅ ፖለቲከኛ ነው  ። የጁሃር ተወዳኝ ነት ሀገራዊ ነው። ለዚሁም ጁሃር  በእንጭጩ ከፖለቲካው ምህዳር  ለማስወገድ  የተሸረቡ ሴራዎች የሚታውቁ ናቸው ።በአብይ  የኒዮ ነፍጠኛ ዘመን    አባ ገዳዎቹም  ቢሆኑ   ስበዕናቸው  ጠብቀው መኖር የሚቻለቸው አይመስልም ።የተፈልገው ነገር የእምዩ ምኒሊክ ያልተሳክ ፕሮጀክት ማሰፈጸም ነው ።ሁሉንም በሃይል የማንበርከክ ፍላጎት ነው ።የብሄር ብሄርሰቦች  የእኩልነት ጥያቄ ማንሳት ጽረ ኢትቶጵያዊነት  ተደርጎ ተወስደዋል 

አማራ ክልል ዲሞክራሲያዊ አመራር ማምክን፤

 ከአማራ ማህበርሰብ  እልፈ አዕላፍ  ዲሞክራት ታጋዮች ያፈራ ማህበርስብ ቢሆንም  በአሁን ውቅት አንገታቸው እንዲደፍ  የማያቋርጥ  ዘማቻ ሲደረግባቸው እያየን ነው ። በአሁን ወቅት  የትምክህት ትርክት የተቋወመ   የአማራ ተወላጅ  ስሙ ሲብጠለጠል እያየን ነው ።ሆኖም ዲሞክራቶች  የፖለቲካ ስልጣን የህዝብ ነው እያልን አሁንም ተሰፋ ሳንቆርጥ ትግላችን ይቀጥላል ።በአማራ ክልል አመራሮች የተፈጸመው ወንጀል ታሪክ የሚረሰው አይደለም።ወንጀሉ የተፈጸመው በርሱ የለውጥ መሪ ነ ኝ በሚል ግለሰብ ነው።የአማራ ክልል አመራር የተገደሉበት ምክ ን ያት የለውጥ ሃይል ነኝ ባዩን ስለሚገዳድሩት ብቻ አልነበረም።በዋናነት በክልሉ ነጻ አስተዳድር ለመመስረት የነበራቸው ህልም ለማክሸፍ ነው።ሰዎቹ በአቅም የተሻሉ ነበሩ። በየመድረኩም ጠንካራ ክርክር ሲያካሂድ ተሰተውለው ነበር።የአትዮጵይ ተስፋም ነበሩ። መፈንቅለ መንግስታዊ ግድያ የህዝብን ህልም መንገድ ላይ ያስቀረ ነው። ከመፈንቅለ መንግስት በሃላ በክልሉ የራሱ መስተዳድር የለውም። በአብይ የሚመራ አስተዳደር ነው።የደም ካሳ እንዲሆን ጎርጎራ ፕሮጀክት ቢታሰብም የሚልዮኖቸ ተስፋ የመመለስ ስራ ይቀራል ። የሁላችንም ሃላፊነት ነው ። ሁሉም መዳን የሚችለው ሲተባባር ብቻ ነው ። ከዚህ ክልል የወጡ የፖሎቲካ ሰዎች የሚከተሉት የአሃዳዊ ፖለቲካ አስተሳሰብም አማራን በሌሎች እንዲጠረጠር እና እንዲጠቃ እየተደረገ ነው። ሁሉም ብሄር ቤረሰቦች ማወቅ ያለባቸው ጉዳይ የጭቀኑ አማራ  ዕጣ ፈንታ ከሁልም ጋር ተመሳሳይ መሆኑ ነው ። ለዚሁም በአካባቢያቸው ያለውን ከሌላ ብሄር የመጠውን ወገናችን መጠበቅ እንድላብን ነው ።

ዲሞክራሲዊ ብሄረተኝ ነት ፤

በአሁን ወቅት በአንድነት ሃይሎች  ወይም የዘመኑ ነፍጠኞች ዋነኛ ጠላት ተደርጎ የተወስደው  ህወሃት እና የትግራይ ህዝብ ነው ። ትግራይ የአገራችን የዲሞክራሲያዊ ብሄርተኝ ነት ትልቁ ምሽግ  ወይም ደጀን ነው ።በዚህ ምክን ያት  ህወሃት እንዲፈርስ  እና እንዲሸነፍ ያልተደርገ ሴራ የለም።ኢሳያስ እና አብይ  ህወሃትን ግጠው ቢውጡት ደስ ባላቸው ።ስሙም ራሱ ያስደነግጣቸዋል ።  በኢህ አዲግ  ውሀደት  ሽፋን  ህወሃትን ለማፍረስ ተጎንጉኖ ከሽፈዋል ።ማፍረስ የተፈለገው   ብአዴን / ኦሆዲድ  አልነበረም። የተባሉት ድርጀቶች ቀደመው  በህዝቦች ትግል  የፈረሱ ነበሩ ።በይፋ  ከመፍረሳቸው በፊት  የድርጅቶቹ አመራሮች   ከአዲስ አባባ ውጭ የሚንቀሳቀሱበት ዕድል አልነበረም ። የውህደቱ ዋና አላማ ህወሃትን በማፍረስ ለአቶ ኢሳያስና  ለ ኒዮ ነፍጠኞች ገጸ በረከት ለማቅረብ ነበር ። ከዚሁ በተጨማሪ የእነ አብይ ህልም የትግራይ ከልል መንግስት ለመቆጣጠር ነበር  ።ሆናም ህወሃት   ሴራዎች   በማክሸፍ የራሱን ቁመና ጠብቆ ተሻግረዋል ብቻ ሳይሆን የፈደራል ሃይሎችን የማሰባሰብ አቅምም ፈጥረዋል  ።ህወሃት  የብልጽግና የጭፍለቃ ተንኮል ሲያከሽፍ ከኢሳያስ ተንኮልም አምለጠዋል ። አብይና ኢሳያስ   የትግራይ ዲሞክራሲያዊነት ብሄረተኝነት ያለ መሪ  ድርጅት በማስቀረት በመቀሌ ከተማ  ፈንድሻ እና ቄጤማ ተነሰነስላቸው ሽር እንዲሉ ነበር። በድል አድራጊነት  መቀሌ አደባባይ ላይ  ሸር የማለት ህልም የትግራይን ህዝብ ብሄራዊ  ማንነት በማሳጣት  መታሰቡ አሳዛኝ ያደረግዋል ። ህወሃት የሚጠላው በትላንትና ድሉና የነገ ተስፋ  በመሆኑ ነው ። ካላቹህ ህወሃት  የነገ  ፓርቲ ነው  ። ህወሃትን ማፈረስ ሲያቅት  በሰራውና ባልሰራው  ወንጀል እንዲሸማቀቅ በማድረግ ከፖሎቲካ ምህዳሩ መሽኘት ነው ። አሁንም ከሌሎች ዲሞክራሲያው ብሄረተኞች ጋር የፖለቲካ ጥምረት እንዳይፈጥር ትግራይ መሄድ በወንጀል የሚታይበት ደረጃ ተደረሰዋል ። በጣም የሚያሳዝነው የፖለቲካ  ሀሁ የማያውቁ የብልጽግና  ቡድን መሪዎች ዲሞክራሲያዊ ብሄረተኞች የህዝቦች ዲምክራሲያዊ አንድነት ዋሰትና መሆናቸው እየታወቀ ለእንገልት መዳረጋቸው ነው ። መቀሌ ደረሰው የተመለሱ አንዳንድ የፈዳራል ጥምረት አባላት ለአብይ  ጥቃት ተጋለጠው ይገኛሉ። በትግራይ ላይ የተሸረቡ ሴራዎች የህዝብ ጎርፍ ፈጥረው  አስመራንና  አዲስ አባባ  እንድሚያጥለቀልቁ   በእርግጠኝ ነት መናገር ይቻላል።

ፓርቲና ምርጫ

በአፍሪካ  የመንግስትን ስልጣን  ሃብትና  አቅም የተቆጣጠረ የፖለቲካ ቡድን በፖለቲካ ምርጫ  ለማሸነፍ ጉልበት የሚገኝበት ዘመን አልፈዋል ።ያለንበት ዘመን የ ህዝብ ፖሎቲካ የተጀመረበት ዘመን ነው ማለት ይቻላል ። በአገርችንም የህዝብ ተቋውሞ መንግስትን ለመለወጥ አስችለዋል ።  በመሆኑም በስልጣን ያለ ቡድን እንደ ትላንቱ ኮሮጆ ሰርቆ በስልጣን ይቆያል ማለት አይቻልም ። በመሆኑም ለፍትሃዊ እና ነጻ ምርጫ መዘጋጃት የማይታለፍ ነው ። አገራችን ህዝቦች በነጻነት መሪዎቻቸውን  መምረጥ አለባቸው ። ከዚህ ውጭ  ሰላም  እና አገራዊ ይሁንታ የሚባል ነገር አይኖርም ። በግዚያዊ ሁኔታዎች መባዘንም መዘባነንም አይገባንም ። ፓርቲዎች እና የፖለቲክ ቡድኖች ግለሰቦች አንድን በሌላው ጫም በመግባት  መረዳት እና መረዳዳት ያስፈለጋል ። አንድ ሰው በአገር ጉዳይ በግልም ይሁን በቡድን ያገባዋል ብለን ማሰብ አለብን ። የፖልቲክ ቡድኖቸ ተደራጁት ለስልጣን ብቻ ሳይሆን ለመፍትሄም ጭምር ነው ብለን ማሰብ ሊጠይቀን  ነው ።

 የብልጽግ አካሄድ አደገኛ ነው ።ሁሉንም የ ፖልቲካ ቡድኖቻን የኢኮኖሚ ጥገኛች  ለማደርግ  ጥረዋል ።ቡድኖቹ ነጻ ህልውና እንዲኖራቸው ያስፈለጋል ።ይባስ ብሎ አንዳንዶቹን የመንግስት ተሻሚዎች  ሆነዋል ።ከተሻሚዎች መካከል ዶክተር አረጋዊ በርሄ ናቸው ። አዲሱ ተሻሚው  የህወሃትን ታጋዮችን መቀሌ የመሸጉ ሲሉም አደመጥኩ።ለነገሩ ሰውየው ከእጅ አይሻል ዶማ ናቸው ።ዶክተሩ ለመመረቅያ የጻፍትን መጽሃፍ አንዴ እጄ ገብቶ አንብቤ የተገነዘብኩት ሳስታውስ ሁሌም ይገርመኛል።በመጽሃፋቸው እንዳሰፈሩት  ህወሃት እሳቸው እስከነበሩብት ግዜ  ድርስ የተከተለችው የትግል ስልት ትክክል ነበር ።ህወሃት ስህተት የጀመረችው እሳቸው ከሸሹበት ግዜ ጀምሮ እንደሆነ ነግረውናል  ።ይህን ከነብብኩ በኋላ እሳቸውን መገምት አስቸጋሪ አልሆነብኝም። ዶክተሩ ለ አብይ ጸሎት እንዲያደግላቸው በስብሰባ ሲጠይቁ ብዙ ሰው ሲሰቀጥጠው ይሰማል።ሰውየው የተመኙትና  ቃል የተገባላቸው  በሙስጦፌ ዘዴ ትግራይ እንደነበር  የሚናገሩ ሰዎች  ሰምቻላሁ። እንግዲህ የአሁንዋ ሽመት ማስተዛዘኛ መሆንዋ ነው ።  አንድ ቁም ነገራቸው ግ ን ኤርትራ ሂደው ለሻዕብያ ግብር ይዘው አለመቅረባቸው  ነው ። ኢህሃዲግ ህወሃት ለመጣል ኢሳያስ ጋር አልሄድም ።ምስክርነት ለራስ ነው ።

አምባገነኖች ይህም ይከጅለቻው ንሮዋል/ 

 የአብይ መንግስት ዲሞክራሲያዊ እንደሆነ  ሊነግረን  እየሞከር ነው ።አብይ ዲሞክራት ከሆነ አምባገነንነስ ለማን እንስጠው።ዲሞካራሲ አንድ  መሰረታዊ መለኪያው የፖሎቲካ ስልጣን በህዝባዊ ምርጫ መያዝ  ነው ።ተቋዋሚዎችም ከገዢው ቡድን እኩል መወዳደርያ ዕድል አግኝተው በነጻ ምርጫ መሸናነፍ ሲችሉ ነው። አብይ በእጅዋ የሚሰጥ የሌላት  እናት አንጀትዋ  ከአለት ይደነድናል  የሚሉት አባባል ይገልጸዋል ። ሩቅ ሳንሄድ ምርጫው ሲራዘም  የስልጣን ክፍተት እንዳይፈጠር  ሁሉም ያሳተፈ ባለአደራ መንግስት ይመስረት ብለው ሃሳብ ያቀረቡ የፖሎቲካ  መሪዎች  ዛሬ እስርቤት ላይ ናቸው ።የሃጫሉ ግድያ ሰበብ የታሰሩ የኦሮም ታጋዮች ያጠፍት ጥፋት ቢኖር  ለሰላማዊ ሽግግር ስለታገሉ ነው ። አብይ ይችን  ለማስተናገድ አቅም የለውም ። የአብይ ቡድንም የዲሞክራሲ እንጥፍጣፊ  የለውም የሚባልውም ለዚሁ ነው ።

የአሃዳዊ መንግስት ስራአት ከፌዳራል ስር አት በተለየ ዲሞክራሲያው እንዳልሆነ አዲሱ ሶፊስት ህገ ወጥ አብይ መከራከሪያ ነጠብ ይዞ ብቅ ማለቱ ይገርማል ።ጉዳዩ  ወደ ትንተና ከመገባቱ በፊት ይህ ጥያቄ  ምን አመጣው  ያሰብላል። እንደው የአገሬ ሰው  ውረድ አልመታህም ሲለው ውረድስ እሺ አልመታህምን ግ ን ምን አመጣው አለ ይባላል። ሰውየው በህገወጡ የቀደሞ የፓርላም ስብስብ ይህ ጥያቄ ራሱ አንስቶ ራሱ ለመመለስ የፈለገበት  ለምንድነው።እኔ  ፌዳራል ስር አቱ ለማፍረስ ዳር ዳር እያለ ነው እላለሁ ።ለነገሩ የቀረው ነገር ጥቂት ነው ።የጭፍለቃ እና የማፈርስ ፖለቲካውን እያገባደደው ነው ።አሃደዊ መንግስት ዲሞክራሲያው ሊሆን ይችላል ።በአገራችን አሃዳዊ ዲሞክራሲያው አይደለም ብሎ የተከራከረ የለም።አይኖሩምም። ሲውድን፣ኖርወይ ፣ጋና፣ አየርላንድ  እያለን አሃዳዊ መንግስታት ዲሞክራሲያዊ እንደሆኑ ማየት እንችላለን። ነገር ግ ን ፈደራል ስራአ ት እንዲሁ በምርጫ የተከሰተ ሳይሆን  በተለያዩ አስግደጅ የፖለቲካ ሁኔታዎች አማካይነት ነው ። በመሰረቱ ፈደራል ስራአት የብሄር ብሄረሰቦች ብዝሀነት ባለባቸው አገራት  የሚነሱ የማንነት ጥያቄዎች ለማስተናገድ በድርድር የሚገነባ ስር አት ነው ።የባህል እና የማንነት ብዙህነት ያለባቸው አገራት የፌዳራል ስራአት ይመርጣሉ። በዘመናችን የአሀዳዊ መንግስትም ቢሆን በነበሩበት መቀጠል የማይችሉበት ሁኔታ ደርሰዋል። በመሆኑም የአህዳዊነት ዘመን አክትመዋል።የአገራችን ህልውና  ከፌዳራሊዝም መለየት አይቻልም።

 

አለቀ ደቀቀ፤ሟርት አይደለም፤

የመጨረሻ ሰአት ላይ ነን። የኤርትራው አምባገነን መንግስት  ከአብይ ጋር በማበር ትግራይን የመማራክ  ጦርነት እና አብይን የማዳን  ሴራዎች  እየተጣጦፈ ይገኛሉ  ። ወገን አብይና አገራችን ለይተን ማየት አለብን ነው።ህዝባዊ ትግል እንቀላቀል ።ይህ ጦርነት በመንግስትና በኢትዮጵያ ህዝቦች መካከል የሚካሄድ ይሆናል ።የኦሮምያ ወጣቶች ትግል ላይ ናቸው ። በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች  ጦርነት ተጀምረዋል ። አይጦች አሁንም ጽረ ህገ መንግስት ግብራቸውን እንዲያቆሙ ተግላቸን እናጽና ።

በድል ማግስት ያገናኘን፤

 


Back to Front Page