Back to Front Page

የኣስተዋዮቹ ስጋት (በ12-07-2010ዓ/ምእንደተፃፈ)

የኣተዋዮ ስጋት (በ12-07-2010ዓ/ምእንደተፃፈ)

 

ዳንሾ ሄሮን

(09/10/2012 ዓ/ም)

 

ከታች እንዲታነቡት እምጋብዛችሁ ፅሁፍ በ12/07/2010 ዓ/ም፤ ዶ/ር ዓቢይ ኣህመድ የኦህዴው ሊቀመንበርነት ሲሰጣቸውና ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆነው ከመረጣቸው በፊት በነበሩ ሳምንታት ውስጥ የተፃፈ ነበረ። በዚሁ ቀን በኣይጋ ፎረም የተለጠፈ ማወቅ ይበጃል የተባሉ ፀሃፊ የውሸት ዘመን በሚል ርእስ ያስነበቡን ፅሁፍ ነው። የፅሁፉ ኣንዱ ንኡስ ርእስ የጠቅላይ ሚኒስትርነት ጉዳይ ይል ነበር። ፀሃፊው በዚህ ንኡስ ርእስ ዶ/ር ዓቢይ ከመረጣቸው በፊት ምን መከሩን፤ ዛሬ ድረስስ ምን ተፈፀመ የሚለውን ለማነፃፀር ያክል ታነቡት ዘንድ ጋብዣቹለሁኝ።

 

የጠቅላይ ሚኒስትርነት ጉዳይ

 

በቅርቡ የአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ከስልጣን የመልቀቅ ጥያቄ ማቅረባቸው ተከትሎ ስለ ቀጣዩ የሀገራችን ጠ/ሚኒስትር ብዙ አነጋጋሪ ጉዳዮች ተነስተዋል። አንዳንድ ግለ ሰቦች ካደረባቸው ኩፍኛ ጠ/ሚኒስተር የመሆን ጉግት አባዜ ከወዲሁ ነገሮችን በማመቻቸትና የማይገባቸውን የአመራር ቦታ ላይ በመቆናጠጥ ጠ/ሚኒስትር የሆኑ ያክል ውዥምብር ፈጥረዋል። በርግጥ እነዚህ ሰዎች ኢህአዴግ በመተካካት ሂደቱ ላይ የፈፀማቸው ስህተቶች መገለጫ ናቸው። ስለ እነዚህ ግል ሰዎች የግል ስብእና ያለኝ ጥያቄ ከመሰንዘሬ በፊት አቶ መለስ ዜናዊ ከዚህ ዓለም በሞት በተለዩን ሳምንት በማስታወሻ ደብተሬ (diary) ያሰፈርኩት አጭር ፅሁፍ ላካፍላችሁ።

Videos From Around The World

25/12/2004 ዓ/ም

በርግጥም ይህ ሰው ታላቅና ድንቅ ነበር። ኢትዮጵያ በሃዘን ልቧን ተሰብሯል። ለመሪዋን ጥልቅ ፍቅር እንዳላት ለዓልም መስክራለች። በዚያ ያልጠብቅነው አሳዛኝ አጋጣሚ ሀገር ማለት ህዝብ ነው። የሚለውን ሃቅ በግልፅ ተገንዝበናል። . . . . . .

በአቶ መለስ ዜናዊና ድርጅታቸው ኢህአዴግ አመራር ኢትዮጵያ ከድህነት አረንቋ የሚያስወጣት መንገድ በመያዝ በሁለት እግሯ መራመድ ጀምራለች። በዚህ መንገድ ስትራመድ ወደ ኋላ የሚትመለስበት ዕድል የላትም። ምክንያቱም መመለሻ መንገዱ ተዘግቷል። የኢትዮጵያ ህዝቦች በሙሉ በአንድ ቃል ዘግተውታል።

ኢትዮጵያ በዚህ መንገድ ስትራመድ በፈጣን ሩጫ፣ ወይም በቀስታ በመራመድ፣ ወይም ደግሞ ቀስ ብላ እያረፈች እየተራመደች፣ እንደገና እያረፈች እየተራመደች ትጨርሰዋለች። የአረማመድዋ ፍጥነት የሚወስን አንድ ታሪካዊ ሃላፊነት ለኢህአዴግ አመራርና አባላት ተጥለዋል። እያንዳንዱ የኢህአዴግ አመራር ይሁን አባል ለስልጣን ሳይጓጓ፣ ለጥቅም ሳይጓጓ፣ እንዲሁም ለዝና ሳይጓጓ ፍፁም መስዋእትነት የሚከፍልበት ጊዜ ከማንኛውም ጊዜ በበለጠ አሁን ሁነዋል። ስለሆነም ይህ ለኢትዮጵያ በፍጥነት መራመድና አለመራመድ ወሳኝ ጉዳይ ነው። ህዝቡ ቢሆን በአንድ ቃል ወስኗል።

የታላቁ መሪያችን አቶ መለስ ዜናዊ የነበረው ህዝባዊ ሃላፊነት በመረከብ ሀገሪቱን ለወደፊቱ የሚመራ አካል የሃላፊነቱ ቦታው እሳት መሆኑ ከወዲሁ መገንዘብ ይኖርበታል። ይህ ቦታ በከፍተኛ ደረጃ ጠንክሮ መስራትን፣ ፍፁም የህዝብ አገልጋይ መሆንን፣ ፍፁም ሀገራዊ ወገንተኝነትንና የሀገር ጥቅም ማስቀደምን፣ በከፍተኛ ደረጃ የአመራር ክህሎትንና ዕውቀትን መገንባትን፣ እንዲሁም ጥንካሬና ብርታትን የሚጠይቅ መሆኑ መገንዘብ ያስፈልጋል። ይህ ካልሆነ እሳቱ በጣም ይፋጃል። በተአምር እረፍት አይሰጥም።

የክቡር ታላቁ መሪያችን አቶ መለስ ዜናዊ ነፍስ መንግስተ ሰማያት ያዋርስልን!! አሜን!!ይላል ማስታወሻው።

እንግድህ ይህን የድያሪ ማስታወሻ ይዘትና አሁን ያለው በአንዳንድ የኢህአዴግ አመራሮች የጠ/ሚኒስትርነት ስልጣን ሽኩች ሀገሪቱን ካለችበት ሁኔታ በማገናዘብ ልቦናችሁን ይመዝነው። አሁን ባለው ሁኔታ ይሁን የወደፊታዋ ኢትዮጵያ የሚመራ አካል ብስለት፣ የአመራር ችሎታ፣ ለቦታው የሚመጥን ስብእና የፖለቲካ አቅም ከሌለው አስቸጋሪ ነው። በማስተዋሻው እንደተገለፀው ወንበሩ እሳት ነው። ትክክለኛ አመራር ካላገኘ የኢትዮጵያ ህዝብ ዕረፍት አይሰጠም። ለዚህ ቦታ ያለአቅምህ መንጠራራትም አያስፈልግም። ከኔ ብሔር ይሁን ከኔ ወገን ይሁን ብሎ መንጫጫትም አያስፈልግም። ጠቅላይ ሚኒስትርነት የአቅም እንጂ የወረፋ ጉዳይ መሆን የለበትም። ህዝብ መንግስት እንዲመራ ሃላፊነት የሰጠው ድርጅት ከሁላችንም ይሻላል ብሎ ያሰበውን መሪ ያስቀምጠልን። ይህ ካልኩ ዘንዳ ጠ/ሚኒስትር ካልሆነ እየተባለ የሚዘመርላቸውን ስለ ዶ/ር አብይ አህመድ ግራ የገባኝ ነገር አለ።

ዶ/ር አብይ አህመድ የተባሉ ሰውዬ በቅርቡ በwikipedia website (https://en.wikipedia.org/wiki/Abiy_Ahmed_Ali) የተለጠፈው ስለሳቸው የሕይወት ታሪክ የሚገልፅ ፅሁፍ ተመልከቱ። የሚገርመው ነገር የኢመደኤ ዋና ዳሪክተር ሁነው አያውቁም። ኤጀንሲው ከተፀነሰ ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን የኢመደኤ ዋና ዳሪክተር ሜ/ጀነራል ተ/ብርሃን ወ/አራጋይ ናቸው። በዚህ ሕይወት ታሪካቸው በሚገልፅ ፅሁፍ በ1980ዎቹ መጀመርያ ብ15 ዓመታቸው ትግል ውስጥ እንደ ገቡ አስነብበውናል (በ1976 ተወለዱ፤ በ1991 ኦህዴድ ተቀላቀሉ)። ይህም ነጭ ውሸት ነው። እኔ እስከማውቀው ድረስ በኢህአዴግ ሰራዊት ለመሰለፍ ከ18 ዓመት በላይ መሆን የግድ ስለነበረ። እንህ ሰውዬ ታድያ ተኪ ናቸው? የሚደንቅ መተካካት!!

በጣም የሚገርመኝ ነገር እሳቸውና ከጎናቸው ያሉ የኦህዴድ ባለስልጣናት በተቋዋሚ ምድያ፣ በማህበራዊ ምድያና በዩቱዩብ ጀብደኞች ሲደነቁና ሲሞገሱ እናያለን፣ እንሰማለን። ታድያ እነዝህ ሰዎች የኢህአዴግ አመራር ከሆኑ እንዴት ከተቋዋሚዎች ጎራ በተለየ አድናቆት ይጎርፍላቸዋል። እነዚህ ሰዎች የኢህአዴግ መለዮ ለብሰው ኢህአዴግን የሚያጠቁና ህገ መንግቱን በኃይል ለመናድ ከሚፈልጉ ወገኖች ጋር የተሰለፉ ይመስላሉ። እንድህ ከሆነ ኢህአዴግ እንዴት እንድህ የመሳሰለ የአስተሳሰብ እንክርዳዶች መለየት አቃተው። ምናልባት የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጥ በዓይነ ቁራኛ የሚመለከቱና መበታተንዋን የሚመኙ ወገኖች ተልኮ በማወቅ ይሁን ባለማወቅ አንግበው የማተራመስ ኃይሎች አካል ስለመሆናቸውና አለመሆናቸው ኢህአዴግ እርግጥኛ ነው ወይ?

በኢትዮጵያዊያን ሶማሌና በኦሮምያ ህዝብ መሃከል ግጭት በማጋጠሙ ምክንያት በሚያዛዝን ሁኔታ ዜጎች ሕይውታቸውን አጥቷል፣ የአካል ጉዳተኞች ሁነዋል፣ አሰቃቂ ግድያ ተፈፅሞባቸዋል፣ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል። ዶ/ር አብይና ግብረ አበሮቻቸው ሃላፊነታቸው ከመወጣት ይልቅ ጉዳዩ ላልዋለበት አካል ስያላክኩ ቆይተዋል። ይህን አስከፊ ግጭት በወጉ መቆጣጠር ያልቻለ አመራር ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ሹመት ሲጓጓ የሚያስገርም ቢሆንም፤ ጉዳዩ ያነሳሁበት ዋናው አንግል ግን ከላይ የገለፅኩት የህዝባዊ ወገንተኝነት ጉዳይ ነው። በከፍተኛ አመራር ተቀምጠህ ነገር ግን በህዝብ መሃከል አለመግባባት በሚፈጠርበት ወቅት ሚዛኒህ ስተህ ጎራ ከለየህ እንዴት በህዝቦች መሃከል መተሳሰርን፣ መተማመንና ፍቅርን ልታመጣ ትችላለህ። ምህዋሩ የሳተ አመራር፣ ከፍትህ ሚዛንና የህግ የበላይነት መርህ ጨርሶ የራቀና ያፈነገጠ አመራር እንዴት ኢትዮጵያዊያን መምራት ይችላል?

በእኔ እምነት አመራር በተቻለ መጠን ለሁሉም ህዝቦች ዕኩል ወገናዊ አስተሳሰብ ሊኖሮው ይገባል። ብሔር፣ ብሔረሰብና ህዝብ በዕኩል ዓይን ማስተዳደር መቻል አለበት። አመራሮች በብሔር ሰበብ ከወንጀለኞች ጋር ጎራ ለይተው በህዝቦች መሃከል የሚያጋጥም ግጭቶች የሚያባብሱ ከሆኑ እንዴት ሰላምና አብሮ የመኖር እሴት ሊረጋገጥ ይችላል? በሚናስተዳድረው ብሔር፣ ብሔረሰና ህዝብ በወንጀለኞች አስከፊ ግፍ ሲፈፀም፣ ለምን ተመሳሳይ ግፍ በሌላው ብሔር ወይም ብሔረሰብ እንድደርስ እንፈቅዳለን? ለምን አስቀድመው ግፍ የፈፀሙ ወንጀለኝች ተባብረን በህግ ፊት አናቀርብም? ለምንስ የህዝብ አመራር ተብለን የወንጀለኞች ዋሻ እንሆናለን? ይህን ጉዳይ ለሌሎችም የኢህአዴግ አባል ድርጅቶችም የሚመለከት ይሆናል።

በዶ/ር አብይ አመራር ስፍር ቁጥር የሌለው ዝርክርክነትና ለከፍተኛ እልቅት፣ ለሰላም እጦትና የእርስ በርስ ጦርነት ሊያስከትል የሚችል የጎላ የአመራር ክፍተት የሚፈጠር ይመስለኛል። የኔ ጥያቄ የጠቅላይ ሚኒስትሪነት ጉዳይ ብቻ አይደለም። ይዘውት የመጡና አሁንም የያዙት የአመራር ቦታ ስእብናቸው ለዚህ ቦታ የሚመጥን አይመስለኝም። ስለሳቸው በአይጋ ፎረም ብዙ አንብያለሁኝ። በወሬም ደረጃ ብዙ ይባላል። በአመራር ችሎታ፣ በመልካም ስነ-ምግባር፣ በአስተሳሰብ ብስለትና ምጥቀት ሳይሆን በውሸት፣ በማጭበርበር፣ በግበረ ስጋዊ ሰሰኝነት፣ ወዘተ የሚታወቅ ሰው ፤ አሁን ለተቀመጠበት ማማ ይገጥማል ወይ? ሰፊው የኦሮምያ ህዝብ የሚወክለው ድርጅት ልቀ መንበርመሆን ማለት እንዴት በጨበጣ? በጣም በአስተሳሰብ የበሰሉና አስተዋይ አመራሮች ያሉበት ኦህዴድ እንዴት በአጭበርባሪዎች ሊናጥ ቻለ? ለማንኛውም ኢህአዴግ ለነዚህ ጥያቄዎች ተገቢ ምላሽ መስጠት እንድችልና እንዝህ ችግሮች መፍታት የሚያስችል የበሰለና ጥበብ የተሞላበት አመራር መስጠት የሚችል ጠ/ሚኒስትር መምረጥ እናዳለበት አፅንዖት ሰጥቸ ሃሳቤን ለመግለፅ እወዳለሁኝ።

 


Back to Front Page