|
ከቻይና ልምድ የምንማረው ምርጫን ለማስቀረት ነው እንዴ? 23/07/2012 ዓ/ም ኮሮና ቫይረስ በቻይና ዉሃን ግዛት በወረርሽኝ መልክ ከተከሰተበት ግዜ ጀምሮ የዓለም ስጋት ሁኖ ቀጥልዋል።ከ800,000 በላይ የዓለማችን ህዝቦች በቫይረሱ መያዛቸው እና ከ38,000 በላይ ህዝብ ደግሞ ለህለፈት መዳረጉንም የተላያዩ የብዙሃን መገናኛ ዘግበውታል።አሁንም አገሮች የሚከተሉት ሪኦተ ዓለም(አይዶሎጂ)፣የእምነት መሪዎች እና አማኞች ፈተና ሁኖ ቀጥልዋል።አሁንም አደግን በለፀግን እያሉን የነበሩት አገሮች የኛ ፈለግ ካልተከተላችሁ ወዮላችሁ እያሉን የነበሩት አሁን በኮረና ቫይረስ ምክንያት የሚዩዙት የሚጨብጡት አጥተዋል።ጣርያ የነካው እድገታቸው በሺ በሚቆጠር ህዝብ ከሞመት ግን ሊታደገው አልቻሉም።አሜሪካ እና የአውሮፓ አገሮች በዚህ በኩል ተጣቃሽ ናቸው።በኮረና ቫይረስ በጣልያን ለህልፈት የተዳረገው ከ10000 በላይ ደርሰዋል።የዓለማችን ቁንጮ የሆነችው አሜሪካ ከቻይና በልጣ ከ3400 በላይ ህዝብ በሞት ተነጥቃለች።አሁንም መቆጣጠር አቅቷት ኮሮና ቫይረስ በመከላከሉ ረገድ ቫይረሱ አስቀድማ ከታየባት ግን ደግሞ ፈጥና ለመከላከል ከቻለችው አገር ቻይና ጋር ተባብራ ለመስራት አቅዳ እየተንቀሳቀሰች ነው።ግን ቻይና በፍጥነት ለመካላከል የቻለችው የዓለማችን ቁንጮ አመሪካ ኮሮና ቫይረስ ለመካላከል ያቃታት ለምንድ ነው?የሚለው ብዙዎቹ እያነሱት ያለ ጥያቄ ነው።
የተፈጥሮ አደጋ ወረርሽኝ ወዘተ በማንኛውም አገር ሊታይ የሚችል ክስተት ነው።በሚደርሰው የተፈጥሮ አደጋ እና በወረርሽኝ ምክንያት ይብዛም ይነስም ዜጎች ሊሞቱ ሊፈናቀሉ ይችላሉ።በዓለም መንግስታት ልዩነት የሚመጣው ግን በተከሰተው የተፈጥሮ አደጋ ወይም ወረርሽኝ ሳይሆን በህዝባቸው ላይ በሚደርሰው አደጋ አፈታት ላይ ነው።የዓለም መንግስታት ገሚሰቹ በተፈጥሮም ይሁን በወረርሽኝ ምክንያት ሊከሰት የሚችለውን አደጋ አስቀድመው በመተምበይ አልያም ከተከሰተም ፈጥነው ህዝባቸው ለማዳን የሚያስችል እርምጀዋች ሲወስዱ ገሚሰቹ የዓለም መንግስታት ግን ችግሩ ከመድረሱ በፊትም አይጠነቀቁም ከደረሰም ህዝባቸው እያለቀ ደንታቢሶች ሁኖው ይቀጥላሉ።ይህ የሚሆንበት ምክንያት መንግስታትና ህዝቦች ከሚከተሉት ሪኦተ ዓለም የሚመነጭ ነው።የምትከተለው ሪኦተ ዓለም ለህዝብ የወገነ ሲሆን የምትከተለው ስርዓት የምታወጣው ፖሊሲ እና ስትራተጂ ለህዝብ የወገነ እንድሆን አቅደህ ትሰራለህ ትተግበራለህም።የምትከተለው ሪኦተ ዓለም ለህዝብ ያልወገነ ከሆነ ግን ለህዝብ አስበህ ማቀድ እና መተግበር የሚታሰብ አይደለም።ኮሮና ቫይረስ ከመከላከል አንፃር እየታየ ያለው ልዩነትም ይህኑኑ እውነታ ያረጋግጣል።የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከል የቻሉ የኤስያ አገሮች ደቡብ ኮርያን ጨምሮ በአብዛኛው የልማታዊ መንግስት አስተሳሰብ የሚከተሉ እና እየተገበሩ የመጡ አገሮች ናቸው።በምዕራቡ ዓለም ሚድያ ይህንን ሓቅ ለማድበስበስ ይሞኩራሉ።የኤስያ አገሮች ኮረና ቫይረስን በፍጥነት ለመቆጣጠር የቻሉት ከአሁን ቀደም ዶርሷችው ከነበረ ወረርሽኝ ትምህርት ማግኘች በመቻላቸው ነው በማለት ከዋናው ጉዳይ እንድንወጣ እያደረጉን ነው።ከአሁን ቀደም የተገኝ ትምህርት ካለ ጠቃሚ አይደለም የሚባል አይደለም።እንኳን ለደረሰበት ላልደረሰባቸው አገራትም ጠቃሚ ልምድ እስከሆነ ድረስ መማር ይገበቸው ነበር።ይሁን እና ልይነቱ እሱ አይደለም።በኤስያ ያሉ አገሮች የልማታዊ መንግስት መርሆች ስለሚከተሉ ኮረና ቫይረስም በመከላከሉ ረገድ የልማታዊ መንግስት ፖሊሲ ነው የተከተሉት።የልማታዊ መንግስት መለያ ባህርያት ፈጣን እድገት፤ልማት የሞት ሽረት፣የተመረጠ የተቀናጀ የመንግስት ጣልቃ ገብነት ወዘተ ናቸው።በቻይናም በሌሎች የኤስያ አገራት ኮሮና ቫይረስ ከመከላከል ኣኳያ የታየ ተግባር ይህ ነው።የተመረጠ የተቀናጀ የመንግስት ጣልቃ ገብነት።ቻይና በጣት በሚቆጠሩ ቀናት ሆስፒታሎች ገንብታ ኮሮና ቫይረስ ለመከላከል ስራ አዋለች።ይህ የተመረጠ እና የተቀናጀ የመንግስት ጣልቃ ገብነትን ያሳያል። በአውሮፓ እና በአሜሪካ ኮረና ቫይረስ መከላከል ያልቻሉበት ምክንያት እድገታቸው ከኤስያ ልማታዊ መንግስታት ስላነሰ ነው?አይደለም።ከኤስያ ልማታዊ መንግስታት በላይ የገንዘብ እጥረት ስለገጠማቸው ነው?ይህም አይደለም።አሜሪካ እና አውሮፓ ከኤስያ ልማታዊ መንግስታት ያነሰ የቴክኖሎጂ እድገት ስላላቸው ነው?ይህንንም አይደለም።የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጉድ እያደረጋቸው ያለ በሚከተሉት የነፃ ገበያ አስተሳሰበቸው ነው።ለ99% ህዝባቸው ከመጨነቅ ይልቅ ለ1% ዜጋቸው ብቻ ስለሚጨነቁ ነው፡፡የኢኮኖሚ ማነቃቅያ መደጎምያ ወዘተ ተብሎ የተሰጠው 2 ትሪልዮን ዶላር ለአመሪካ ህዝብ በኮረና ቫይረስ ከሞሞት ሊታደገው አልቻለም።የ2 ትሪልዮን ድጎማ ሓሳቡ ሲነሳ በኮረና ቫይረስ ምክንያት ለህልፈት የተዳረጉ አሜሪካውያን ከ1000 አይበልጡም ነበር።2 ትሪልዮን ዶላር ድጎማ ከፀደቀ በኋላ በቫይረሱ የሞቱ ዜጎች ከ3400 በላይ ደርሰዋል።2 ቲርልዮን ዶላር እንደቻይና ለኮረና ቫይረስ መከላከል ስራ በቀጥታ ህዝቡላይ ቢውል ኑሮ ምን ያህል ሂወት መታደግ እንደሚቻል መገመቱ አይከብድም።በመንግስት ወጪ ሆስፒታል የገነባች ቻይና የኮረና ቫይረስ ምርመራ በነፃ አገልጋሎት የሰጠች ቻይና የፊት መሸፈኛ ጭብል በነፃ ያሰረጨች ቻይና ምንያህል የቻይና ህዝብ ሂወት ታድጋ የዓለም ህዝቦች ሂወት ለመታደግ ደፋ ቀና መላትዋ በመመልከት የአመሪካ 2 ቲርልዮን ዶላር ምን ያህል የአሜሪካውያን ሂወት መታደግ ይችል እንደነበር ማስላት አይከብድም። ኮሮና ቫይረስ በመከላከሉ ረገድ በኢትዮጵያ ውስጥ እየታየ ያለው ልዩነትም በዓለም ዓቀፍ ደረጃ እየታየ ያለ ልዩነት መልክ መያዝ ጀምረዋል።በኢትየጵያ የፌዴራል ስልጣኑ የተቆጣጠረው ሓይል የምዕራቡ ዓለም የነፃ ገበያ ኣስተሳሰብ የሚከተል ሓይል ነው።ይህንን ሓይል ኮሮና ቫይረስ በመከላከል ረገድ እየወሰደው ያለው እርምጃ ከምዕራባውያኑ አገራት በብዙ መልኩ ይመሳሰላል።የአሜሪካ መንግስት 2 ትርልዮን ብር ለኢኮኖሚ ማነቃቅያ መደብኩኝ ብሎ ዜና ሲያስነግር የዐብዪ መንግስትም በተማሳሳይ 15 ቢልዮን ብር መመደቡን በሚድያዎቹ አስነገረ።የአሜሪካ ፕረዚዳንት ዶናል ትራምፕ አንድወር በማይሞላ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በማስወገድ ታሪክ አደርጋሎህ ሲሉ በዐብዪ የሚመራ የሳንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስተር የኮሮና ቫይረስ መድሃኒት አገኘን የኢትዮጵያ ህዝብ እንኳን ደስ አለህ ብሎ ኮሮና ቫይረስ የመከላከሉ ስራ በኢፋ እንዲገደል አደረገ።ከዚህ በተጨማሪ የአዲስ አበባው ጠቅላይ ሚኒስትር እንደ የአሜሪካው ስርዓት በለሃብቶች ለማወደስ ሲል ለኢትዮጵያ ሙሁራን በኢፋ ሰደበ።አሁን ደግሞ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ምርጫ በተያዘለት ግዜ እንዳማይካሄድ በሚድያ አስነገረ።ይህም ሁኖ በአሜሪካም በኢትዮጵያም ስርጭቱ ማስቆም አልተቻለም አይቻልልምም።ምክንያቱ ግልፅ ነው።የኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመግታት የህዝብ ውግንናን ይጠይቃል እና። የኢትዮጵያ መንግስት ከፀረ ህዝብ ተፈጥረው የሚመነጭ ኮረና ቫይረስን ወረርሽኝ ለመግታት ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ ማድረግ አይፈልግም።ይልቁንም ወረርሽኙ የሚቀጥልበት ተግባራዊ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል።በድብቅ ወረርሽኙ እንዲቀጥል እያደረገው ያለ ስራ ለጊዝየው ትተን በግልፅ የሚታይን ተግባራቱ አተኩረን እንመልከት፡፡የመጀመርያው የኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ ከታየበት ሰዓት ጀምሮ ኮሮና ከአዲስ አበባ ውጭ ወደ ሌሎች ክልሎች እንዳይዘመት ለማድረግ የሚያስችሉ እርምጃዎች ከመውሰድ ይልቅ ዝምታውን ነው የመረጠው።አሁን በኦሮምያ በአማራራ ክልል የኮሮና ቫይረስ ታማሚዎች መገኘታቸው የመንግስት ደንታ ቢስነት መገለጫዎች ናቸው።ከዚህ በተጨማሪ በዓለም ጤና ድርጅት ጥረትና የኢትዮጵያ ማህበራዊ ሚድያዎች ተነሳኝነት የኢትዮጵያ ህዝብ ኮሮና ንፅህና በመጠበቅ ማህበራዊ ርቀትን በመጠበቅ እንዲከላከለው በሚቀሰቅሱበት ወቅት ሆን ብሎ ኢትዮጵያ የኮረና ቫይረስ መድሃኒት ሰራች ብሎ በመቀስቀስ የህዝብ ኮሮና ቫይረስን የመካለከል እንቅስቃሴን እንዲኮላሽ አድርገዋል።ይህ የኢትዮጵያ ህዝብ መከፈል የለለበትን ዋጋ እንዲከፍል የሚያደርግ ነው።የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ምርጫው በተቀመጠለት ግዜ ሰሌዳ እንደማይካሄድ የገለፀበት አግባብም መንግስት የኮረና ቫይረስ ስርጭት ለመግታት ቁርጠኝነት እንደሌለው ማረጋገጫ ነው። የአራት ኪሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብዪ አሕመድ ምርጫ ቦርድ መግለጫ ከመሰጠቱ ቀደም ብሎ ከቻይና ልምድ ትምህርት በመውሰድ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመግታት እንደሚሰሩ ተናግረው ነበር።የቻይና ተመኩሮ የሚጠቅመው ምርጫ ለማስቀረት ሳይሆን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በፍጥነት በመግታት ምርጫው በታቀደለት ግዜ እንዲካሄድ ለማድረግ መሆን አለበት።ቻይና ኮረና ቫይረስ በፍጥነት በመግታት የህዝቧን ኑሮ ለመሻሻል ነው እየተጋች ያለችው።ከዚህ ኣልፋም ቻይና ለዓለም ህዝብ ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመታደግ ነው እየሰራች ያለቺው።የኢትዮጵያ ህዝቦች የኮረና ቫይረስ ወረርሽን በፍጥነት በመግታት ህገ መንግስታዊ ስርዓት የሚከበርበትን የህገመንግስቱ መገለጫ የሆነውን ምርጫ ማካሄድ ይጠብቅብናል።
የዐብዪ መንግስት በትምህርትነት እየወሰደው ያለው ልምድ የልማታዊ መንግስታት ተሞኩሮ ሳይሆን የአውሮፓ እና አሜሪካ ነው።የአሜሪካ እና የአውሮፓ ልምድ ደግሞ ህዝባቸው እንደቅጠል ከመርገፍ ሊታደጋቸው አልቻለም።የዐብዪ መንግስት የአውሮፓ እና አሜሪካ ህዝባቸው ሊታደግ ያልቻለውን ልምድ ወደ ኢትዮጵያ በማስመጣት የኢትዮጵያ ህዝብ እንደቅጠል እንዲረግፍ በማድረግ ምርጫ የማይካሄድባት ኢትዮጵያን ለመፍጠር ነው እየተሯሯጠ ያለው። ከዐብዪ መንግስት በተፃራሪ ተሰልፋ የኮረና ቫይረስ ለመግታት እየተጋች ያለችውን ክልል ትግራይ ናት።ትግራይ በልማታዊ ዲሞክራስያዊ አስተሳሰብ የሚመራ መንግስት ባለቤት ነች።የትግራይ ልማታዊ ዲሞክራስያዊ መንግስት ለትግራይ ህዝብ አብዝቶ ይጨናቃል።በኮረና ቫይረስ ሊደርስበት ከሚችል እልቂት ለመታደግ ሌትተቀን እየሰራ ነው።የማእከላይ መንግስት ሴራ እያከሸፈ ወደፊት መራምዱን ቀጥለዋል።የትግራይ ልማታዊ ዲሞክራስያዊ መንግስት የኮሮናን ቫይረስ ስርጭት ለመግታት የሚያካሂደውን እንቅስቃሴ አጠናክሮ መቀጠል አለበት ልክ እንደ ኤስያ ልማታዊ መንግስታት።የኢትዮጵያ ህዝብ ከትግራይ ልማታዊ ዲሞክራስያዊ መንግስት ልምድ ትምህርት መውሰድ ይገባዋል።የዐብዪ መንግስት አሽቀንጥሮ በመጣል የኮሮናን ቫይረስ ስርጭት መግታት ከኢትዮጵያ ህዝብ የሚጠበቅ ተግባር ነው። የልማታዊ ዲሞክራስያዊ መንግስት መከላከል ማእከል ያደረገ የጤና ፖሊሲ ተግባራዊ በማድረግ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በፍጥነት እንግታ!
|