Back to Front Page

ድል ለትግራይ !!!

ድል ለትግራይ !!!

 

ቤቲ ሃይላይ

11-24-20

 

የሚሸነፍ መስሎኝ ራያ ወርጀ

የምጥለው መስሎኝ ወልቃይት ወርጀ

የወደቀ ለቀምኩ ይሄው በገዛ እጀ

መጣልኝ ሳይነጋ ሐዘኑ በደጀ

ደጋግመው ..............🎤

 

ግፉ ግፋ  ሲሉት የቆመ መስሎታል

ሳይገፋ ተገፍቶ መመለስ ቀሎታል

ከኋላና ከፊት ቆረጣው በልቶታል

ቆስሎ ቆስሎ ቆስሎ መታከሚያው ሞልቷል

እንዲያ በል.................🎤

 

ዛላበሳ ብሄድ ሆነብኝ አንበሳ

በሺረ ብሞክር አሳየኝ አበሳ

ዓድዋን ተሻግሬ ደርሸ ነበለት

አልቻልኩም ለመውጣት ሆነብኝ አቀበት

ድገመው ድገመው ............🎤

 

በጦር ብዛት መስሎኝ

የቀን ህልም ዘግኘ

ህግደፍን አምኘ ፋኖን ተማምኘ

አረፍኩት ጉድ ሆንኩኝ እንደ ጉም በንኘ

በልልልልልኝ ..................🎤

 

ህዝቤን ለመሸንገል ድል አለኝ እያልኩበት

አልጋ በአልጋ መስሎኝ ሆነብኝ ሰንሰለት

ለካስ ረመጥ ነው የተጋደምኩበት

ተዋግቱ ገደለኝ የትግራይ አቀበት

እንዲያ በልልልኝ.................🎤

 

የተኛ መስሏቸው መሬት መሬት ብለው

የታገሳቸውን አንበሳውን ገጥመው

እርሳሱ ሲጠና ድል ቢያጡ ደንግጠው

በማይ ካድራ ግፈው  ወደ ሺሬ ዙረው

ዘረፉ ባፋቸው ጀግና ጎበዝ መስለው 

ህፃን አዛውንቱን በጭካኔ ገድለው

እህህህህህ በልልኝ 🎤

ሃይልና ጉልበቴን ሲነጋ እንዱያይልኝ

አዝማሪው እህህህ  እህህህ በልልኝ 🎤

 

ድል ለትግራይ !!!

Back to Front Page