Back to Front Page

ለአቶ ሊላይ ኋይለማርያም ፡-ልጨምርልህ

ለአቶ ሊላይ ኋይለማርያም ፡-ልጨምርልህ

ደስታ ረዳ

(ነሀሴ 16/2012)

*በፋና በአማርኛ ቃለ መጠየቅ ስታደርግ ሰምቼ ብዙ ነገር ስለረሳህ ልጨምርልህ። የኢትዮጵያ ህዝብ የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖሮው የሚከተሉት ላስታውስህ።

* አንተ ተገደሉ ያልካቸው ታጋዮች ቁጥር ግን ለምንድርነው ያን ያህል ያሳነስካቸው?

* እንዴ፡ ኤርትራ 20 ሺ ተገደለ ትላለህ እንዴ? ለመሆኑ ኤርትራ የሄዱት የብርጌዶች ቁጥር ረስተሀቸው ነው? ወይስ የአንድ ብርጌድ የሰው ኋይል አታውቀውም ነበር? እዚህ ላይ በጣም ተሳስተሃል። ምን ብርጌድ ተመለሰ እና 20 ሺ ሞተ የምትለው? እንዴ ደግሞ እኮ የምትነግረን ህውህት በክፍለ ጦር እና ብእዝ የተደራጁበት ዘመን በ1974/75 ዓም ነው። እናማ ሁለት መቶ ሺ ልትል ነው? አንተ ያልከው ቁጥር እኮ በቃ ህወህት የላከችው ሃያ ብርጌድ ብቻ ነው ማለት ነው?

* በህወህት የተገደሉ ታጋዮች ቁጥር ራሱ በጣም ኣሳንሰኸዋል። ማን የሚባል ታጋይ ቀረ እና? ህወህት አዲስ ኣበባ ሲቆጣጠር እኮ 13 ክፍለ ጦሮች ነው የነበሩት። እናማ የእያንዳንዱ ክፍለ ጦር ኣባላት ብዛት ስንት እንደ ነበሩ ረስተኸው ነው? እንዴ የአቦይ ስብሃት ቤተሰብ ብቻ ኮ ነው የነበሩት። አቤት ግን የኣቦይ ስብሃት ቤተሰብ ታጋዮች ምን ያህል ሃይለኞች ነበሩ? በአንድ በኩል የራሳቸው ታጋዮች እየገደሉ ሲጨርሱ በሌላ በኩል ደግሞ የደርግ ሰራዊት መደምሰሳቸው!

* አንተ ግን ትገርማለህ። እንዴት የሃውዜን ህዝብ ህወህት እንደ ደመሰሰችው ረሳኸው። በራስዋ ጦር ኣይሮፕላኖች ኣድርጋ ኣይደለም እንዴ በገበያ ቀን የደመሰሰችው! ትረሳለህ መሰለኝ? ምን ይሄ ብቻ። የየጭላ፡ የውቅሮ፡ የመቀሌ፡ የማይጨው፡ የመርሳ፡ የሃሙሲት ድብደባውዎች እኮ በወያኔ ጀቶች ነበር።

* አንተ ግን በጣም በጣም ትገርማለህ? መርሳት ጀምረሃል መሰለኝ። "አዲስ አበባ 40 ሺ ታጋዮች በረንዳ ኣዳሮዎች ኣሉ" ያልከው ግን ምን ሁነህ ነው? እንዴ እነዛ በአቦይ ስብሃት በረሀ የተረሸኑት ዳግም ተነስተው በረንዳ አዳሪ ሁነው በየመንገዱ የታጋይ ፎታቸው ለጥፈው እየለመኑ ኣላፊ ኣግዳሚው ያስቸገሩት ማን ሆኑ እና እነዚህ የምትረሳው? ግን ሜቴክ የአአ በረንዳ አዳሪዎች  አዋሽ እየወሰደ ሲያሰለጥን ታጋዮቹ እየለየ ሳይወስድ መቅረቱ እንዴት አልወቀስከውም? ሜቴክ ራሱ የአቦይ ስብሀት መሆኑ ረሳኸው እንዴ?

* አቶ ሊላይ ግን ስለ ራስህ ማውራት ስለማትፈልግ ሁነህ ነው በ1968 ታግለህ በ1971 ዓም ጋንታ መሪ ነበርኩኝ ያልከው? እንዴ ረሳኸው እንዴ በዛን በመሰለ ወታደራዊ ቁመናህ በአጭር ግዜ የኋይል አመራር ስትሆን? ማእከላይ ኮሚቴ እንደ ነበርክስ እንዴት ሳትናገር ቀረህ? ኣዎ ስለራስህ መካብ ደብሮህ ይሆናል።

* ደግሞ አንተ እኮ ወደ ደርግ የገባኸው ከትግል ከድተህ ሳትሆን፡ በነበረህ ወታደራዊ ቁመና አአ መጥተህ ሂልተን ሆቴል ሁነህ ኣመራር ልትሰጥ ነው። እንዲያውም የሰራኸው ጀግንነት እንዴት ወደ ስለላ ስራ ታወርደዋለህ? የአንቦ ውግያ፡ የሚሌ ቆረጣ፡ የመራኛው ውግያ፡ የደብረ ዘይት ከበባ አንተ አይደለም እንዴ የመራኸው? ደግሞ እኮ አንተ "ከወያኔ ከድቼ ወደ ጠላት በመግባት፡ ጠላትን እሰልል ነብር" ስትል ራስህ ሰው እንዲጠረጥርህ እያደረግክ ነው። እንዲህ እማ ኣታድርግ፡።

* ስማ አቶ ሊላይ፡ ደግሞ "ባለ 22 ክፍል ከአአ የበለጠ የትም የማይገኝ የአቦይ ስብሃት ቤተ መንግስት ኣለ" ያልከው፡ እንዴ ምን ነው ወደ 22 ክፍል ብቻ ኣወረድከው? 22 ክፍል ታድያ ቤተ መንግስት ይባላል እንዴ? አላየኸውም ማለት ነው። አቦይ ስብሃት በመቀሌ፡ ማጨው፡ ውቅሮ፡ ተንቤን፡ አዲግራት፡ አኽሱም፡ ሽሬ እና ሑማራ ያስገነቡት ቤተ መንግስት አላየኸውም? ወይ ትዋሻለህ ወይ አላየኸውም?

* የህወህት ዋና ገዳዮች ስብሃት ነጋ፡ አረጋዊ በርኼ እና ግደይ ዘረአፅዮን ነበሩ ያልከው ግን የሆነ ጥርጣሬ አሳደረብኝ። አንተ የወያኔ ሰላይ ነህ እንዴ? አረጋዊ በርሄ እና ግደይ ዘረአፅዮን የተደመሩ መሆኑ እያወቅክ እንዴት እንደዛ ትላለህ? ደግሞ እነሱ ኮ በ1980 ዓም ነው ከትግሉ የወጡት። እዚህች በጣም ጠረጠርኩህ።

መታሰብያነቱ፥- ለአቶ ሊላይ ኋይለማርያም

ግልባጭ፥- ለፋና ቲቪ

 


Back to Front Page