Back to Front Page

ይድረስ ፍልስፍና እና ድንቁርና ለተቀላቀለቦት ለዶ/ር ዳኛቸው

ይድረስ ፍልስፍና እና ድንቁርና ለተቀላቀለቦት ለዶ/ ዳኛቸው

 

ሙሉጌታ ወልደገብርኤል (ስትራቴጂስት) 08-22-20

 

የፍልስፍና አስተማሪ ወይም ተማሪ መሆን ማለት፥ ስለማታውቀው ነገር አዋቂዎችን መጠየቅ፤ መጻሕፍትን ማጥናት፣ መመራመርና ማገላበጥ፤ በርዕሰ ጉዳዩ በተጨባጭ የደረስክበት ነገር ሳይኖር የቀረ እንደሆነ ደግሞ በዘፈቀደ አፍን ከማላቀቅና ነገርን ከመዘበራረቅ አንደበትህን መግራት መቻል እንደሆነ ጠቢባን ምስክርነታቸውን ይሰጣሉምነው ዝም ብላችሁ ብትኖሩ ይህ ጥበብ በሆነላችሁ ነበርእንዲል መጽሐፍ። አንድም፥ሰነፍ ዝም ቢል ጠቢብ ሆኖ ይቈጠራል፥ ከንፈሩንም የሚቈልፍ ባለ አእምሮ ነው ይባላልሲል ጠቢቡ ሰሎሞን የርቁን ቅርብ አድርጎ እንዳመሳጠረው።

 

እኚህፈላስፋነኝ ብለው የሚያስቡና የሚያኑ፤ በየመድረኩምፈላስፋተብለው የሚጠሩ፤ በአዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ የፍልስፍና መምህር የሆኑ ግለሰብ፥ በዋልታ የቴሌቪዥን ጣቢያ በሳልሳዊት ባይነሳኝ አዘጋጅነት የሚቀርበው የእንነጋገር ፕሮግራም ላይ ከሌሎች ተጋባጅ እንግዶች ጋር ቀርበው ሰሙኑ የተናገሩት በፕሮግራሙ አዘጋጅ ሳይቀር ተቃውሞ የገጠመው፤ መጽሐፍ፥በመላሳቸውም ሸንግለዋል፤ የእባብ መርዝ ከከንፈሮቻቸው በታች አለእንዲል የዶ/ ዳኛቸው ከላይ ሲታይ መልካም የሚመስል ዳሩ ግን እብሪተኛ እምነትና አስተሳሰብ የወለደው የሁከትና የግርግር፣ የጥፋትና የእልቂት ከፋፋይ ሃሳብ፤ ምንጭና የተናጋሪው የፍስልፍናቸው ጥቅልቀትና ስፋት ከራሳቸው አንደበት በተገኘ ዐረፍተ ነገር እንመረምራለን።

Videos From Around The World

 

የተረተኛው ፈላስፋ ተረት ተረት በቅዱሳት መጻሕፍት እውቀት ሲመዘን

 

ያነበቡትን ሳይጠይቁና በሚገባ ሳይመራመሩ እንዲሁ ተቀብለው ለመትፋት የተጣደፉ በአዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ የፍልስፍና አስተማሪ / ዳኛቸው a stands for alfa o stands for omega አልፋና ዖሜጋ። a አልፋ ነው o ኦሮሞ ነው ያነበብኩትይላሉ። ክለውም፥በግሪክ ሜተሎጂ a እና o በተገናኘ ቁጥር የምድር ስርዓት አይደለም የሰማዩን ስርዓት ይገለባበጣል!” ነበር ያሉት የንቀት በሚመስል አነጋገራቸው። በርግጥ ከዚህ አባባላቸው የተነሳ ከፕሮግራሙ አጀጋጅ የተሰነዘረውሰማኒያ ስድስት ብሔሮች ያሉበት አገር ምናልባት አልፋና ኦሜጋ ሁለቱ ብቻ ናቸው ብለን ስንሄድ...” የሚለውን የመልስ ምትፈላስፋውያልጠበቁት ምት በመሆኑ በሚገባ ሚዛናቸው እንዳሳታቸው ዶክተሩ አዘጋጅዋን ለማሳጣት የተጠቀሙባቸው ቃላቶች እማኝ ናቸው። በዚህ አጋጣሚ፥ የፕሮግራሙ አዘጋጅ ሳልሳዊት ባይነሳኝ ያሳየችው የሞያ ብቃትና ግልጸኝነት ላማመስገን እወዳለሁ። አሁን ወደ ሐተታው እንግባ፥

 

1.      ለሀገርና ለትውልድ ፊደል ቀርጻ የሰጠችው፤ የዝማሬ፣ የታሪክ፣ የእምነት፣ የመጻሕፍት፣ የፊደላት ወዘተ ብቸኛ ባለቤት የሆነችው ጥንታዊትና ታሪካዊት ቤተ ክርስትያንችን አልፋ ብላ ስትጽፍ አልፋ፥ ዖሜጋ ብላ ስትጽፍ ደግሞኦሜጋብላ ሳይሆን ዖሜጋ ብላ ነው የምትጽፈው። ይህ አንድ ተራ ምእምን አንድም ሰንበተ ክርስትያን የማይስተው ሐቅ ነው። በርግጥ አንድ መንገደኛ ሰው ባልዋልበትና ባላለፈበት እውቀት ከመሬት ተነስቶ ነገርን ለማፋለስ ቢበረታና እንዲሁ በትዕቢት ቢናገር የሚደንቅ አይደለም። ብዙ ምሑራን ባሉበትና ባፈራው በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ስምና ሽፋን እንዲህ ያለ የወረደ ነገር በአደባባይ ሲሰማ ግን የተቋሙን አቋምና ህልውና አደጋ ላይ ለመሆኑ አመላካች ነው።

 

2.      አልፋእናዖሜጋሁለቱም የግሪክ የመጀመሪያና የመጨረሻ ቃላቶች ናቸው። አልፋና ዖሜጋ የሚል አባባልም በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ጉልህ የሆነ ስፍራ የሚይዝና ትርጓሜውም፥ በመለኮታዊው ባህሪውና ህልውናው ማንም የማይመስለውና የማይጋራው፣ ቀዳሚና ተከታይ የሌለው፣ ሰማይንና ምድርን ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣ፣ ፍጥረታት ሁሉ አሳልፎ በዙፋኑ በክብር የሚቀመጥ፣ መጀመሪያና መጨረሻ የሌለው እግዚአብሔር አምላክ ማንነት ለመግለጽ ጥቅም ላይ የዋለ አባባል ነው፥አልፋና ዖሜጋ፥ ፊተኛውና ኋለኛው፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝእንዲል። ይህ ፈጣሪን የሚገልጽ አባባል (አልፋና ዖሜጋ) በማንኛውም ዓይነት ሁኔታ ፍጡርን ለመግልጽ ቋንቋውን መጠቀም ከአላዋቂነት ያለፈ እግዚአብሔርን መሳደብ ይሆናል።ፈላስፋነኝ ብለው የሚያምኑ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር የሆኑ / ዳኛቸው የተባሉ ግለሰብም እያደረጉት ያለው ይህ ነው።

 

3.      ሌላው ዶክተሩ፥ አልፋ ዖሜጋ ሲባል ስለ ተባለ ከማለት ያለፈ የቃሉ ክብደት በአግባቡ እንዳልገባቸው ከሚናገሩት ነገር መረዳት ይቻላል። ባይሆን ኖሮ፥ አልፋና ዖሜጋ የሚለው ኃይለ ቃል አጠቃቀምና ትርጋሜ በትክክል የገባው ሰው አማራ ኦሮሞ ማለት ነው በማለት ራሱን በአደባባይ ለማዋረድ አይደፍርም።

 

4.      እኚህ ግለሰብ (/ ዳኛቸው) ኢትዮጵያ ፈሪሃ እግዚአብሔር ያላት፣ አገረ እግዚአብሔር ናት! ተብሎ በሚነገርላትና የኢትዮጵያ አምላክ እየተባለ ብዙ የተዘፈነላት አገር እምብርት ላይ ተቀምጠው እንደ ጥላ የሚያልፈውን ፖለቲካቸው ለማጣፈጥ አስበው በእግዚአብሔር ላይ አፋቸውን ሲያላቅቁ በጓዳ ተደብቀው ሳይሆን በመንግሥት ሚድያ በአደባባይ ነው። በዚህ ድርጊታቸው የተቃወማቸው ሆነ ቅሬታውን የገለጸ አንድም ሰው የለም። ለምን? ምክንያቱ ግልጽ ነው። ይኸውም፥ ግለሰቡ መስማት ስለ ምፈልገውን ነገር (ኦሮ-ማራ) እስከ ተናገሩ ድረስ እግዚአብሔርም ቢሆን የቻሉትን ያህል እያብጠለጠሉ ቢናገሩና ቢወርፉትም ጉዳያችን ስላይደለ ነው። አንድም፥ እግዚአብሔር - እግዚአብሔር የምንለው ነገር ለእኛ ለኢትዮጵያውያን እንደየ አስፈላጊነቱ የምንጠቀምበት ከአምስተኛ ጎማ የዘለለ ሌላ ትርጉም ስለሌለው ነው። ባይሆን ኖሮ ዶክትሩ ይህን የሰይጣን ቋንቋ (አዎ! ሰይጣን ቋንቋ አለው፥ ሀሰት ተብሎም ይታወቃል) ለማስተጋባት ባልደፈሩ ነበር።

 

5.      ጥያቄው፥አልፋእናዖሜጋከዚህ ቀደም የት ነው የተገናኙ? መገለጫ ባህሪያቸው ምንድ ነው? ምንስ ይመስላሉ? አካላዊ ናቸው ወይስ መናፍስ? የት ቦታ፣ ምንስ በሚባል ሰፈር? ተገናኝተው የሚያውቁ ከሆነ ደግሞ የመገናኘታቸው ዓላማ ምን ነበር? ማንስ ነበር ያገናኛቸው? ተገናኝተው የጣሉትንስ ማንን ነበር? የተከሉትስ ምን ተብሎ ይታወቃል? በመገናኘታቸው፥ በምድርም ሆነ በሰማይ የተፈጠረው ነውጥስ ምን ነበር? ከመገናኘታቸው የተነሳ በሰማይም ሆነ በምድር የተፈጠረው አዲስ ስርዓት ምንድ ነው? ከዚያ በኋላስ የት ገቡ? መገኘታቸውስ ወዴት ነው? ፍለጋቸውስ የሚያውቅ ማን ነው? ይህ እኔና እርስዎ የምንመልሰው ጥያቄ ሳይሆን፥ በግሪክ ሜተሎጂ a እና o በተገናኘ ቁጥር የምድር ስርዓት አይደለም የሰማዩን ስርዓት ይገለባበጣል!” ሲሉ ሐሰታቸውን ያስተጋቡብን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲፈላስፋሊመልሱት የሚገባ ጥያቄ ነው።

 

6.      የሰማይና የምድር ስርዓት መናወጥ የሚባለው፥ ፀሐይ ስትጨልም፣ ጨረቃም ብርሃንዋን አልሰጥም ስትል፣ ከዋክብት ከሰማይ ሲወድቁ፣ የሰማያትም ኃይላት ሲናወጡ፣ የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ሲታይ፣ የምድር ወገኖች ሁሉ ዋይ ዋይ ሲሉ፣ የሰው ልጅንም በኃይልና በብዙ ክብር በሰማይ ደመና ሲመጣ ሲታይ ነው (ማቴ 2429)ኦሮ-ማራየሚባለው የቃላት ፖለቲካ ሲፈጠር ዶክትሩ እንዳሉት ከፍ ሲል ከዘረዘርኳቸው ምልክቶች አንዳቸውም አልታዩም። የዘንዶ ምላስ የተዋሰ፣ የጠጠር ወርዋሪና የኮከብ ቆጣሪና አምላኪና አድናቂ፣ እንደ ክፉ ደብተራ ያልተጻፈ የሚያነብና የሚያነበንብ ሐሰተኛ ሰው ሲቀደድ ግን ምክንያታዊ መሆን አይጠበቅብኝም! ብሎ ስለሚያምን የፈለገውን ተናግሮ ህዝቡን ያስጨበጭባል። እውነቱን በማስረጃ አስደግፎ የሚሞግትና የሚናገር ደግሞ በጠላትነት ይፈረጃል።

 

7.      ዶክተሩ ሥርዓት እያሉት/የሚሉት ያለው የመንግስት ለውጥ (አብዮት) ከሆነ፥ ምድራችን የህልውናዋ ያህል ስፍር ቁጥር የሌለው የመንግስታት ለውጥ ያስተናገደች ምድር ናት። ይህ ሁሉ ሲሆን ግን በሰማይ የተፈጠረ አዲስ ነገር የለም። የተገለበጠ መንግስትነት ሆነ የተናወጠ ሰማያዊ ስርዓት የለም። ታድያ፥ በቦስተን፣ በፓሪስ፣ በዩክሬይን፣ በሞስኮ፣ በቺሊ፣ በኢራን፣ በቱኒዝያ ወዘተ በዓለም 196 የዓለማችን ከተሞች በዘመናት መካከል የተፈጠረው የስርዓት ለውጥ አማራና ኦሮሞ በተጠቀሱት አገራት ከተሞች መገናኘታቸው ነበርን? አንድም ምድር ማለት ኢትዮጵያ ማለት ካልሆነ በስተቀር። ለውጡ የዕብደት መናገሻ መሆኑን ሳስበው ለድሃ የኢትዮጵያ ህዝብ አዘንኩለት።

 

8.      ጎበዝ፥ ድምጸቱ ስለተመቸንና ስለሚመስል ብቻ ቃላትን እያጋጨን ይህ ማለት ነው ለማለት የሚቃጣን ሰዎች ከሆን እንደ አገርም እንደ ህዝም አደጋ ላይ ነን። እንደ / ዳኛቸው እምነትና ዝሩው ፍልስፍና፥ አገራችን ኢትዮጵያ በአሁን ሰዓት ትገኝበት አሰቃቂ ሁኔታ ውስጥ ልትገባ የቻለችው ይወት የሆነችው ወሓት ወደ መቐለ ስለነካቸው ነው የማለት ያህልም ነው የሚሆነው።ማለት አማራ፤ማለት ኦሮሞ ማለት ነው ብለን የምናምን ከሆነማለት ህይወትን የሚመሰጥ ህወሓት የማይሆንበት አንዳች ምክንያት የለውም። ይህ ሁሉ ግን ፍልስፍናን ከመውደድ የሚመነጭ እውቀት ሳይሆን የእውቀትና የጥበብ የማስተዋልም ድርቀት የሚያስከትለው ድንቁርና ነው።

 

9.      ሌላውን ሁሉ ትተን፤ 1983 / በሶቬት ህብረት ኦክስጅን ሲተነፍስ የነበረው ወታደራዊ የደርግ መንግሥት ሲደረመስ በአዲስ አበባ በመስቀል አደባባይ ማን ከማን ቢገናኝ ነው? በርግጥ አንድ ጊዜ በሐሰት በሽታ የተከልፈ እብሪተኛ ሰው 83 ድልም ቢሆንየኦሮ-ማራየድል ውጤት ነው ከማለት ወደኋላ አይልም። እኔ የምጠረጥረው ግን ምናልባትም ዶክተሩየግሪክ ሜተሎጂሲሉ ያሉትን ነገር የግሪኮች ትምህርት በጥልቀት በሚገባ ሲይገባቸው እንዲሁ በመረዳቸው ልክ እየተናገሩ እንደሆኑ ነው የማምነው።

 

ምንድ ነው እየሆነ ያለው

 

አገር ካልተበተነች አላምንም ካልሆነ በስትቀር ለጊዜያዊ የፖለቲካ ጥቅም ማግኛ ተብሎ፥ የአክሱም፣ የይሓ፣ የገረዓልታ ስልጣኔ መገኛ፤ የውቅር አብያተ ክርስትያናት፣ የያሬድ ጣዕመ ዜማ፣ የግዕዝ ቋንቋ ምንጭ፤ የአድዋ ታሪክ ማህጸን የተሸከመና ኢትዮጵያን እንደ አገር በመገንባት ረገድ የአንበሳ ድርሻ ያለው የትግራይ ህዝብና ክልል በማግለል የሚደረገው ማንኛውም ዓይነት እንቅስቃሴ ማንንም የማይበጅ መሆኑን ምጡ እያየነው ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ የቱንም ያህል የህወሓት መሪዎች ቢጠላና ቢቃወም የትግራይ ህዝብ ኢትዮጵያዊነት በተመለከተ ግን ሊጠራጠር ቀርቶ አስቦትም አያውቅም። እንደ / ዳኛቸው ያሉ በአጉል ትምክህትና ያልተፈተነ እውቀት የተለከፉ በጣት የሚቆጠሩ ግለሰቦች ግን የትግራይ ህዝብ ብቻም ሳይሆን ሌላውን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች እንደ ህዝብ ሊቆጥሩት ቀርቶ የባሪያ ያህል ክብር ነፍገው አፋቸው በአደባባይ ሲያላልቁ ማየትና መስማት ንጹህ አየር የመተንፈስ ያህል የተለመደ ሆኗል።

ምንድ ነው እየሆነ ያለው? ለሚለው ጥያቄ እየሆነ ያለው እኔው ልንገሮት። መጽሐፍ፥ በድን ባለበት በዚያ አሞሮች ይሰባሰባሉ እንዲል፤ / ዳኛቸው እና መሰል በትዕቢት የተወጠሩ ግለሰቦች፤ በባለተራዎቹ በእነ ታዬ ደንደአና አወሉ አብዲ ፊት ሞገኝ ለማግኘትና ደጅ ለመጽናት፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ለማጭበርበና ለማወናበድ ሆነ ብለው በሚፈበርኩትና በሚፈጥሩት ተረት ተረት እንጀራቸውን ለመጋገርና ለማብሰል መሰለፋቸውን እንጅ የዶ/ ዳኛቸው ተለላ አባባል አንድም ባለአእምሮ ኢትዮጵያዊ የሚቀበለው እውነታ አይደለም። ይህን ዓይነቱ አመለካከት ከአባ ዱላ ገመዳ ጋር አብሮ መቀበር ያለበት የጥፋት አስተሳሰብ ነው።

 

አገራችን ኢትዮጵያ በዚህ ሰዓት የሚያስፈልጋት፥ ሲጠግቡ የሚመርቁ ሲራቡ የሚራገሙ፤ የስራና የደመወዝ ጭማሪ ለማግኘት ሲሉ ብቻ ህዝብን እንደ እንጀራ የሚበሉ፤ እንደ በልዓም ቀለብ እየተሰፈረላቸው አፋቸውን የሚያላቅቁ፤ ህዝብ በህዝብ ላይ የሚያነሳሱና ደም የሚያቃቡ፤ ትውልድ የሚያጨናግፍና መቀመቅ ውስጥ የሚከት አስተሳሰብ የጸናባቸው የደም ሰዎች ሳይሆን፥ ሰላምንና አንድነት የሚያወርድ አስታራቂ ሃሳብ ያላቸውና የሚያቀርቡ ዜጎች ነው። በቋንቋ፣ በባህል፣ በአስተሳሰብ፣ በታሪክ፣ በስልጣኔ፣ በወግና በልማድ ልዩ ልዩ የሆነው ህዝቡ ልዩነቶቹን አቻችሎ በጋራ በሰላም፣ በእርስበርስ ወዋደድ፣ በመከባበርና በመተባበር ሊያኖር የሚችል ሃሳብ፣ እምነትና አስተሳሰብ ያላቸው ጭምት ዜጎች ነው የሚያስፈልገን።

 

የእነ / ዳኛቸው እና እያጋጩ እግዚአብሔር ሰይጣንን ገጨ የሚለው ነጠላ ዜማ አይደለም የሚያፈልገን። የዶ/ ዳኛቸው ዓይነቱ የተጀመረውን የሐሰትና የፕሮፓጋንዳ ትርክት ወደላቀ ደርጃ የሚያሸጋገር ማንንም የማይጠቅም የወረደ አስተሳሰብና ውሃ የማይቋጥር ዲቃላ ፍልስፍና ፍርፋሬ ለመልቀም የሚነገርና አድርባይነት የወለደው የጭንቀት ሃሳብ ከመሆኑ ያለፈ ሌላ ምንም ትርጉም የለውም። እንዲዚህ ዓይነት ከፋፋይ፤ የባላጥና ሰንበላጥ የምዋርት ንግግር የምድርን ፍሬ የሚበላ የእርግማን ውጤት መሆኑን አውቀን ሁላችን በአንድ ድምጽ ልንቃወመውና ወጊድ ልንለው ይገባል።

 

ውቅቱን እየጠበቁ ፍርፋሬ ለመልቀም የማይቆርጡትና የማይቀጥሉት የሌላቸው አእምሮአቸውን ያጡ ግለሰቦች የሚሉት ሁሉ እየሰማን የአጀንዳቸው ሰለባ እንዳንሆን በዚህ አጋጣሚ ወንድማዊ ምክሬን ለመለገስ እወዳለሁ። በድፍረትና በትዕቢት በመናቅም በጻድቅ ላይ የሚናገሩ የሽንገላ ከንፈሮች ሁሉ ዋጋቸውን ይቀበላሉና። የእኚህ ግለሰብ ጸብ ከህወሓት መሪዎች ጋር ከሆነ ደግሞ ከህወሓት መሪዎች ጋር መጨረስ። የህወሓት መሪዎች ከህዝቦች ሆነ ከአገር ታሪክ የሚያገናኘው አንዳች ነገር የለውም። ድንቁርና ካልሆነ በስተቀርም ነገርን መቀላቀል ፍልስፍና ሊሆን አይችልም።

 

እናመገናኘታቸው ፈጃቸው እንጅ አልበጃቸውም

 

ይህ የምለው መሰረት የሌለው፣ የተምታታ፣ በእውቀት ያልተፈተነ፣ ጥበብና ማስተዋል የሚጎድልበት፥ ጉንጭ አልፋ የዶ/ ዳኛቸው ያልበሰለ ፍልስፍና መሰረታዊ ስህተት ለመጠቆም እንጅሆነከኦሮሞና ከአማራ ህዝቦች ጋር የሚያገናኝ አንዳች አመክንዮ እንደሌለ ቀደም ሲል በሰፊው ግልጽ አድርጌለሁ። እንደ ዶክትሩ እምነትና አባባል የመጀመሪያ ፊደሎችሁሉ አማራንሁሉ በተመሳሳይ ኦሮሞን የሚወክል ከሆነ እነዚህ በመገናኘታቸው ደግሞ የሚፈጠር ነውጥ አለ ከተባለ በርዕሱ እንደገለጽኩትእናመገናኘታቸው ፈጃቸው እንጅ አልበጃቸውም።

 

በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ አቤሮንና ኦን (ልብ ይበሉ፥ የአቤሮን የመጀመሪያ ፊደልሲሆን የኦን ደግሞነው) እነዚህ ሁለት ወገኖች መገናኘታቸውና መምከራቸውን በሙሴ ላይም ማመጻቸውን ያስተምራል (ዘኅ 161) ውጤቱ፥ ምድር አፍዋን ከፍታ ዋጠታቸው ከዚህ የተረፉትንም በመቅሰፍት መታቸው ነው የሚለው። በርግጥ ይህን ዓይነቱ እውቀት፥ የሰሙትንና ያነበቡት ሳይጠይቁ፣ ሳያጣሩና በሚገባ ሳያልምጡ ለመትፋት የሚጣደፉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፍልስፍና አስተማሪ የሆኑ / ዳኛቸው ዓይነቱ ሰው ይህ የተሰወረ እውቀት ነው። ምን ነው? ቢሉ፥ እንዲህ ያለ ነገር እንዳለ ቢያውቁ ኖሩ ሰውዬው የቃላት ድርደራው ቤት ስለመታ ብቻ ቤት ለማፍረስ ተራ የቃላት ጨዋታ ለመጫወት አይቃጣቸውም ነበር።

 

ፍልስፍና ምንድ ነው? ፈላስፋስ ማን ነው?

 

መጽሐፍመጻሕፍትንና የእግዚአብሔርን ኃይል አታውቁምና ትስታላችሁእንዲል፤ አንድ ሰው፥ ከደሙ ጋር ያለተወሃደ፤ አንድም፥ በተውሶ የተገኘ እውቀት ብቻ የተሞላ እንደሆነ ግለሰቡ ለጥፋት እንጅ ለልማት እንደማይሆን ታሪክ ምስክር ነው። ከራስ የማይመነጭ፣ ስንሸምትም ቢሆን ከማነብነብ ያለፈ በእውነተኛ ጥረትና ልፋት ገንዘባችን ያላደረግነው እውቀት ሁሉ ያልበሰለ ምግብ የመመገብ ያህል የሚያቅለሸለሽ ነው የሚሆነው።

 

ጥሎብንፈላስፋነኝ ብሎ የሚያስብ፣ የሚያምንና ተብሎም እንዲጠራ የሚሻና የሚናፍቅ የሦስተኛ ዓለም ሰውብሎ አፉን የሚከፍተው በክህደት ነው። ፈላስፋነቱ ሊያሳየን የሚፈልገው አንዳች የኃይማኖት መጻህፍት ሳይማርና ሳይመረምር ስለተባለ ብቻ ዘሎ እግዚብሔር ላይ ነው ጦሩን የሚያነሳው። ለመሆኑ፥ ፍልስፍና ምንድ ነው? ፈላስፋስ ማን ነው?

 

የቃሉ ትርጓሜ ሰዎች የሚፈሩትና የሚያስቡት ያህል ውስብስብ ያለ አንድም የማይደረሰበት ነገር ማለት ሳይሆን፤ ፍልስፍና ማለት፥ ጥበብን መውደድ ማለት ሲሆን ፈላስፋ ተብሎ የሚታወቀው ደግሞ ጥበብን ፍለጋ ልቡን የሰጠ ሰው ማለት ነውከሰማይም በታች የተደረገውን ሁሉ በጥበብ እፈልግና እመረምር ዘንድ ልቤን አተጋሁእንዲል ጠቢቡ ሰሎሞን። ይህ ዓይነቱ ጥበብ፥ አስተዳደራዊ ሊሆን ይችላል የሙዚቃ ችሎታና ተመስጦ ሊሆን ይችላል። የመድኃኒት ቅመማ ሊሆን ይችላል የጦር መሳሪያ አንድም አዳዲስ የጦርነት ስልት ማመንጨት ሊሆን ችላል። ጥበብን መውደድ፥ የሰው ልጅ ህይወትን በቀጣይነት ለመምራትና ለማስቀጠል ያስችለው ዘንድ በየዘርፉ የሚፈጥራቸው ጥልቀት ያላቸው አስተሳሰቦችና አመለካከቶች ሁሉ የሚያካትት ነው።

 

ፍልስፍና ሲባል፥ የዕለት እንጀራ የማያበላኝ፣ ህይወት የማይሰጠኝ፣ ራሴን ጠብቄ በሥርዓት እንድኖርና እንድመላለስ ካላደረገኝ፤ በአንጻሩ፥ አባ/እናት አንድ ብር ካለህ/ እስቲ እይልኝ እያለ እንደ ብቅል መንገድ ላይ የሚያሰጣኝና መንገደኛ ለማኝ፣ አእምሮውን ያጣ ዕብድ፣ፈላስፋተብሎ ለመታወቅ የተጋባበት መጥፎ ስሱን ለማስታገስ ከቤተ መጻህፍት የህዝብና የመንግስት ንብረት እየመነተፈ የሚቸረችር ሌባ፣ የእናቱን መቀነት እየፈታ ጫት ቤት ተዘፍዝፎ የሚውል አስቸካሪ ሰው፣ የአገርና የወገን ሸክም፣ በሽተኛ፣ በጫት በሲጋራና በካቲካላ የጠሰጠሰና የተበሳሳ ሳንባና ኩላሊት ባለቤት የሚያደርገኝና የሚያሸክመኝ ከሆነ፥ እንደዚህ ዓይነት ትምህርት ለምኔ? ምንስ ይበጀኛል? ኢትዮጵያ ውስጥፈላስፋነኝ ብለው የሚያስቡ፣ የሚያምኑና ተብለውም እንዲጠሩ ብዙሐኑ የፍልስፍና ተማሪዎችና መምህራን ነን የሚሉ ግለሰቦች ተለይተው የሚታወቁበት ህይወት ይህ ዓይነቱ ረብ የለሽ የደከረተ ህይወት ነው። ይህ ደግሞ ከግብዝነት ያለፈ የእውነተኛ ፍልስፍና ውጤት ሊሆን አይችልም።

 

ፍልስፍናም ቢሆን እንደ እግዚአብሔር ያለ ፈላስፋ የለም

 

መጽሐፍ፥ከእናንተ ጥበበኛና አስተዋይ ማን ነው? በመልካም አንዋዋሩ ስራውን በጥበብ የዋህነት ያሳይ። ነገር ግን መራራ ቅንዓትና አድመኛነት በልባችሁ ቢኖርባችሁ፥ አትመኩ በእውነትም ላይ አትዋሹ። ይህ ጥበብ ከላይ የሚወርድ አይደለም፤ ነገር ግን የምድር ነው፥ የሥጋም ነው፥ የአጋንንትም ነው፤ ቅንዓትና አድመኛነት ባሉበት ስፍራ በዚያ ሁከትና ክፉ ስራ ሁሉ አሉና። ላይኛይቱ ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጽሕት ናት፥ በኋላም ታራቂ፥ ገር፥ እሺ ባይ ምሕረትና በጎ ፍሬ የሞላባት፥ ጥርጥርና ግብዝነት የሌለባት ናትእንዲል፤ እውነተኛ ፍልስፍና፥ ጸጉርህንና ጺምህን በማስረዘም ጨበሪ የሚያደርግና የሚያስመስል፣ አሸንክታብ የሚያስረዝም፣ ጨርቅ የሚያስጥል፣ አፍህን በትዕቢትና በዕብሪት እንድትከፍት የሚያደር

በማታውቀው ርዕሰ ጉዳይ ላይ እየገባህ እንደገባህ በመምሰል ያልገባህን ነገር መናገርና ነገርን እንድትቀላቅልና ያለ እውቀት ምክርን እንድታጨልም የሚያደርግ አይደለም። እውነተኛ ፍልስፍናና የተፈተነ እውቀት ከዚህ ሁሉ ዕድል ፈንታ የለውም። የፍልስፍና አባትና ፈጣሪ የሆነው እግዚአብሔር ይባረክ! እውነተኛ ፈላስፋ ከዚህ ሁሉ የቅቤ ገበያ የመሰለ ግርግር፣ ከአመጽ፣ ከጸብ፣ ከሁከትና ከመከፋፋል ጋር ምንም ክፍል የለውም። ሰው ሰውን እንዲያከብር ሳይሆን ሰው በሰው ላይ እንዲነሳ ጸብን የሚዘሩና በውሸት ዲስኩር አመጽን የሚቀሰቅሱ እንደእነ / ዳኛቸው ዓይነቱ ግለሰቦች የሰለጠነባቸውእውቀትየሚሉት በሽታ ምንጭ ቅንዓትና አድመኛነት የወለደው የምድር፣ የሥጋና የአጋንንት ሃሳብ እንደሆነ ለሁሉም ግልጽ ሊሆን ይገባል። ምን ነው? ቢሉ፥

 

·         እውነተኛ ፍልስፍና፥ ነፍስን የምታጠፋ ሳትሆን ነፍስን የምትመልስና የምታለመልም ንጽሕት ናት፤

·         እውነተኛ ፍልስፍና፥ የሐሰት ነጋሪት ሳትሆን ምስክርነትዋ የታመነ ነው ሕጻናትን ጠቢባን ተደርጋለችና፤

·         እውነተኛ ፍልስፍና፥ ክፉና ጣማማ ሳትሆን ሥርዓትዋ ቅን ነው ልብንም ደስ ታሰኛለችና፤

·         እውነተኛ ፍልስፍና፥ የጨለማ መንገድ ሳትሆን ብርሃን ናት ዓይንን ታበራለችና፤

·         እውነተኛ ፍልስፍና፥ አዱለአዊ ሳትሆን እውነትንና ቅንነት የምታድርግ ናት አንድነትን ትፈጥራለችና፤

·         እውነተኛ ፍልስፍና፥ ከወርቅና ከክቡር ዕንቍ ይልቅ የተወደደች፣ ከማርና ከማር ወለላ ይልቅ የጣፈጠችም ናት።

 

አንድ ሰው የተማርኩ የተማራመርኩ ነኝ ብሎ ሲያበቃ፥ የተጣሉትን ለማስታረቅ፣ ለማቀራረብና ለመዳኘት ዕርቀ ሰላምን የሚያወርድ ብልጫ ያለው ማለፊያ ሃሳብ ይዞ ከመቅረብ ይልቅ ህዝብ በህዝብ ላይ እንዲነሳ፣ እንዲያምጽ፣ እርስበርሱ እንዲናከስና እንዲጠፋፋ አድሎአዊና ከፋፋይ የሆነ ሃሳብ የሚያስተጋባ፤ አንዱን አጀግኖ ሌላውን የሚያኮስ ተናጋሪፈላስፋተብሎ ሳይሆን መታወቅ ያለበት እንዲህ ዓይነት እብሪተኛ ሰው የሲዖል አጋፋሪ ተብሎ ነው መጠራት ያለበት። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እነዚህ ዓይነት የታሪክ፣ የህግ፣ የፖለቲካ፣ የፍልስፍና መምህራን ነን ባዮች ጸብ ጫሪ ግለሰቦች ካላጸዳና ካልጠራረገ መንግስትነቱ አትጸናም።

 

በመጨረሻ፥ ቀደም ሲል፥ ፍልስፍና ምንድ ነው? ስንል ፍልስፍና ጥበብን መውደድ፣ ማሰላሰል፣ ማውጣና ማውረድ፤ በጥበብና በእውቀት ደስ መኘትና ለፍለጋው ልብን መስጠት ነው ብለናል። እውነተኛ ፈላስፎችም፥ በጸብ ጫሪነታቸው ሳይሆኑ በትዕግስታቸው፣ በዝግታቸው፣ በትህትናተኛውና በሰላም ወዳድነታቸው ተለይተው እንደሚታወቁ ተመልክተናል። በአንጻሩ፥ፈላስፋነኝ ባዩ የዶ/ ዳኛቸውና መሰል ደቀ መዛሙርቶቻቸው አንጻራዊ ማንነት በተደጋጋሚ በአደባባይ የሚስተዋለውን ከፋፋይ፣ ምቀኝነትና አድመኝነት የወለደው የሁከትና የአመጽ፣ የትዕቢትና የእብሪት አነጋገር ተመልክተናል። እንግዲህ ምርጫው የእኛ ነው። መልካም የሚመስል ዳሩ ግን ትክልል ያልሆነ ተረት ተረት እየፈጠሩ መርዛቸውን የሚረጩ የአድርባዮች ትምህርት እየተከተልን ሰላማችን ማጣትና እርስበርስ መጠፋፋትን ወይም እንደእነ / ዳኞቸው ዓይነቱ የደመወዝና ጭማሪና ስልጣን ፍለጋ የማባለውን ለማለት ሃፍረት የማያውቃቸው፣ ነገር አቀጣጣዮችና እሳት አከፋፋዮች ወጊድ በማለትና በመቃወም የአገራችን ሰላምና የህዝባችን ደህንነት መጠበቅ የእኛ ድርሻ የሚሆነው።

 

E-mail: mahbereseytan@gmail.com

 


Back to Front Page