Back to Front Page

ጊዜ መስተዋት ነው ፡ ነው ዪላሉየትግራይ ፳፩፪ ምርጫ

ጊዜ መስተዋት ነው ፡ ነው ዪላሉ

የትግራይ ፳፩፪ ምርጫ

በቀለ ብርሃኑ. September 6, 2020

 

ሰሞኑን የታደለች ሃይልማርያምን ቆንጆ መጽሃፍ ኣንበብኩኝ፥፥ የብርሃነ መስቀልን ብሩህ ጭንቅላት፤ የትግሉ ሂደትና ውስጣዊ (በባለቤትነትዋ ልታውቀው የቻለችዉን አውነታዎች )ትግሎችን ኣካፍላናለች፤፤ኣንድ አጅጉን ያስተዋልኩት ነገር ከብሄረ _ትግራይ የፈለቁት ኣብዮተኞች ለኢትዮጵያ የነበራችው ፍቅር፤ አምነትና የማይነቃንቅ ጽኑ አምነት ነበር። ብርሃነ መስቀል፤ ዘርኡ፤ ተስፋይ ደበሳይ፤ ቢንያም_ ከብዙው በጥቂቱ ለመግለጽ_ ለኢትዮጵያዊነት የተሰዉ ታጋዮች - (የትግሉ መሪዎች ማለት ይሻላል_ - ነበሩ።አኔም ራሴ የነዚሁ ጀግኖች ደቀ፡መዝሙር ነበርኩ። አንደኔ ኣይነቶች ኣሁንም በሂዎት አንዳሉ ኣምናለሁ።

Videos From Around The World

ያሁኑ ዘመን “ኢትዮጵያውያን” ግን የኔን ኢትዮጵያዊነት አያደበዘዙብኝ አንደሆነ አየተሰማኝ ነው። ይህን ኣዲሱን ስሜቴን ኣልወደድኩትም፤፤ ስሜቴን መደብቅ ግን ደግ ስላልመሰለኝ ነው መግለጹን የወደድኩት። የድሮው መሪዎቼ በሂዎት ቢኖሩ ምን ይሰማቸው ይኖር ይሆን ነበር??አኒህ ‘አትዮጵያዊ’ ለመሆን ማንነህን መክዳት ኣለብህ የሚሉትን _ ዘመን ኣመጣሽ ነገሮች_ አንደኔው ቢያይዋቸው ምንስ ይሰማቸው ይሆን? ለኔ አየተሰማኝ አንዳለው ኢትዮጵያዊነታቸው ይደበዝዝባቸው ነበር ይሆን?

ይህ አንደ መንደርደርያ የሞነጫጨርኩት ነገር የትግራይን የምርጫ ሂደት ስመለከት ነው። በነገራችን የትግራይ ምርጫ ሂደትና ዝግጅት ከኣገሪቱ ኣጠቃላይ ሁነታና ከጊዜው ኣጭርንት ኣንጻር ሲታይ አስካሁን ድረስ ኣጥጋቢ በሆነ ሁነታ ላይ ይገኛል የሚል አምነት ነው ያለኝ። የያኔው ወጣት ድርብርብ ጭቆናዎችን ለማስውገድ ሲል ሂዎቱን አስከመስጠት ድረስ ተፋለመ። መረት ላራሹ፤ ለብሄር_ብሄረሰቦች ነጻነት፤ ለሴቶች አኩልነት _ ባጠቃላይም ለህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ኣንድነት ብሎም ታገለ። ነገሮች በከፊልም ቢሆን ተፙልተው አዚህ ደርሰን ነበር፤፤

ባሁኑ ጊዜ ግን አጂግ በሚያስደንቅ ፍጥነት የብሄር አኩልነት ማለት ኣገር ማፍረስ ነው የሚሉ ሃይሎች ተፈጥረው በሌላ በኩል ደግሞ አናቱ የመረቁት ለንግስናው ሲል ብቻ ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር የሚታትር መሪ ኣንድነት ተመስርቶ ኢትዮጵያዊነትን የሚሸረሽር ሃይል ተፈጥሮ ኣገሪቱ በመተራመስ ላይ ትገኛለች፤፤

በዚህ ታሪካዊ ሂደት ላይ ያገር መሸርሸሩን ሂደት በማፋጥን ላይ የሚገኘው ያማራው ልሂቅና የፖለቲካ መሪዎች ሆነው አናገኛቸዋለን። ይህን ስናገር አየቀፈፈኝ ነው። በርካታ የኣማራ ምሁራንና ደግ ኣሳቢ ወዳጆች ኣሉኝ። ይህን ስል አንደት ይሰማቸው ይሆን የሚል ስጋት ይሰማኛል። ግን ሃቁን ማውጣት የበሽታውን ማዳን ኣንድ ሂደት ነውና መናገር የግድ ይላል።ብዙ ያማራ ልሂቃን የዚህ ኣገር ኣፍራሽ ሂደት ኣካል ባይሆኑም ዝምታችዉን ኣለማፍረሳቸው ብስማቸው አየተነገደ ዝም ማለታቸው ቢያንስ ቢያንስ የመፍተሄው ኣካል ኣለመሆናቸው ግልጽ መሆን ይኖርበታል።

በሌላ በኩል ደግሞ ጠባብና አንጭጭ ኣስተሳሰብ ያላቸው ጠባቦች በታሪክ የተፈጸሙትን የማስፋፋት ጦርነቶች ሁሉ በኣማሪኛ ተናጋሪው ብቻ አንደተፈጸመ_ ከዚያም ኣልፎ ድሮ ለተፈጸሙት የመስፋፋት ሂደቶች ላስከተሉት ሰቆቃ ሁሉ ያሁኑን ኣማሪኛ ተናጋሪ ተጠያቂ የማድረግ ኣባዤ ይህንን ከፍተኛ ያገሪቱ ቁጥር ህዝብ ላይ ቅሬታ አንድሚያሳድር መገንዘብ ጠቃሚ ይሆናል።

ወደ ትግራይ ምርጫ ስመለስ ኣዳዲስ ክስተቶችን በማየቴ በመጠኑም ቢሆን ተደናግጨ ነበር። ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን መገንባት ነብርና የኔ ህልም ኣዲሱ በውጭም ዪሁን ባገር ዉስጥ ያለ ትንሽ የማይባል ወጣት ስለ ሃገረ _ ትግራይ ምስረታ ኣስረግጦ ሲናገር፤ ሲጽፍ፤ ሲስብክ ስሰማ ትንሽ ግራ ተጋብቸ ነበር።

ከቀናትና ከሳምንታት በሁዋላ ደጋግሜ ሳየው ግን ኣልፈርድባቸውም፥ በታታሪነቱ፤ በታማኝንቱ፤ በ አምነቱ ዪታወቅ የነበረው ትግራዋይ፣ ያንን ፋሺስታዊ ፡ልጆችን ገድሎ አናቶችን የጥይት ዋጋ ስያስከፍል የነበረ መንግስት ደሙን ኣፍስሶ ያሽቀነጠረ የያኔው የትግራይ ወጣት ሌባና የቀን ጅብ ሲባል ካልፈለጋችሁማ ምን ምርጫ ኣለኝ ብሎ ወደ ነጻ ሃገር ምስረታ ቢያዘነብል ኣልፈርድበትም።

ባይሆን ትልቅ ሃገራዊ መግባባት ያለቡት ለሁሉም የምት ሆን በጅማሮ የቀረችዉን፣ በተለያዩ የታሪክ ኣጋጣሚዎች የተቆራኙትን ህዝቦችዋን ኣስተሳስራ በህግ የምትገዛ ኢትዮጵያን መመስረቱ የበለጠ ጠቃሚ አንደሆነ ነው የኔና የመሰሎቼ ሚና መሆን የሚገባው ብየ ኣስባለሁ። በርግጥ ጊዘው ደግ ኣይዶለም። ዱርየዎችና ወኔ የከዳቸው ግለሰቦች ያገሪቱን መዘውር ይዘው ከግራ ወደ ቀኝ፣ ከላይ ወደታች አያንገራገጩ ቁም፡ስርዋን አያሳዩዋት ነው። ግን አስኪያልፍ ያልፋል ሆኖ ነው አንጂ ሁሉም ነገር መስመሩን መያዙ ኣይቀርም።

አስከዚያው ግን ለትግራይ ምርጫ ሁሉንም በጎ ነገሮች አመኛለሁ። ምርጫው በተሳካ ሁነታ አንደሚያልቅም ተስፋየ የላቀ ነው።ዪህ ቅጥ ኣምባሩ የጠፋበት መንግስት ጋዜጠኞችና ታዛቢዎችን ኣላስገባም ብሎ ቢያንገራገርም ምንም ነገር ሊቀይር አንድማይችል ወዳጅ ካለው ቢመክረው ዪበጅ ነበር። ዳሩ ተላላኪ ምን ወዳጅ ኣለው?

በዚህም ምርጫ የትግራይ ፓርላማ የተለያዩ ኣስተያየቶችን የሚያንጸባርቅ ሆኑ አንዲኣልቅ ምኞቴ ነው፤፤

ሰላም ለክለላችን፤ ለሃገራችን

 


Back to Front Page