Back to Front Page

የአራት ኪሎ ዘበኞች

የአራት ኪሎ ዘበኞች

ኢዮብ ከጮማ እምኒ

06-15-20


ዘበኞች ... የቤተመንግስቱ ...ቁንጮች
ሦስቱ ... ከሥላሴ በስተጀርባ ... ነዋሪዎች

አንደኛው በግራ ... በባዶየሚኩራራ
በእምቦጭ ... የማይቆጭ ... ለክልሉ የማይራራ
ሆዱወጣ ... ያለ
ከኋላ ተከታይ ... ለመሪነት ያልታደለ
የአራት ኪሎ ... አውደልዳይ
የውሸት ቃል .. አቀባይ

አንደኛዋ በቀኝ ... እንባ የሚቀድማት
ሰላም ስትባል ... አሽሙሩ የሚመስላት
የአራት ኪሎ ... ቅምጥ
የሚኒስቴር ... ቀበጥ
የደቡብ ስም ሲጠራ ...
ወላይታ ሲዳማ ... ጉራጌ ሀድያ
ጋሞ፣ጌዶ ቡርጂ... ስልጤ ሲነሳ
ከምባታ፣ጋምጎፋ ... ዳውሮ ...ሲወሳ
ከአራት ኪሎ ... ሌላ
... ለደቡብ የማትሳሳ

መሀል ... የቆመው ...
በፎቶሱሰ ... የተጠመደው
ንግስነት ... ያሳበጠው
ቁንጮ ካቦ ... መሪው
ነቀምት ሲነሳ ... በላብ የሚጠመቀው
አምቦን ... ጎብኝቶ ሳይሆን ....
ቀጭብሎ... የሚጎነጨው
መሬቷን ላለመርገጥ ... ምክንያት የሚያበዛው
ግራን ቀኙን ሳይሆን... መሀሉን የሚወደው
ለበሻሻ ኦሮሞ ... ጠበቃ ነኝ የሚለው
ከአራት ኪሎ ሳይወጣ ... ኢትዮጵያን የሚነዳው
መቐለ ከተማን... ወንጅሎ የማይጠግበው
... ሦሥቱም ዘበኞች
የፒኮኳዋ ... አምላኪዎች
ከአራት ኪሎ በስተቀር .... ኢትዮጵያን የረሱት
ሰነፍ ቀልደኞች ... አፍራሽ አንኮትኳቶች
ሦሥቱ ... የአራት ኪሎ ... ሱሰኛ ዘበኞች


Back to Front Page