ያ የገደልከው ...
ኢዮብ ከ ጮማ እምኒ
12-5-20
ያ የገደልከው ... ብሄር አለው ...
... ስም አለው ... ዘር አለው ...
ያ ... የገደልከው ... የሞተው የማይናገረው
ቋንቋ አለው ... እምነት አለው ...
... አባት አለው .. እናት አለው ..
ያ … የገደልከው ... ወገን አለው ባህል አለው ...
... አገር አለው !
ያ … ያ… የገደልከው ... ሬሳ አይደለም የማይናገር
የማይጽፍ ማይመዘግብ ... የማያይ የማይሰማ
ያ… ያ…የገደልከው ... ታሪክ አለው
ያ የገደልከው ... ሬሳ ያልከው ያፌዝክበት ...
... ያናናቅከው ... ሬሳ አይደለም ... ህያው ነ ው
ያ… ያ… ሬሳ ያልከው ... የረሳኸው ...
... ተነስቷል ... ታጥቋል
አልሞተም ... ሬሳ አይደለም
ትግራይ ትዕወት !!!
|