Back to Front Page

የጄነራሉ ፖለቲካ ወገንተኝት (ክፍል አንድ)

የጄነራሉ ፖለቲካ ወገንተኝት

ከትዝብት በእውነቱ

8-3-20

መከለካያ ስራዊት በህገ መንግሰቱ አንቀፅ 87 (5) የመከላከያ ሰራዊት ተግባሩን ከፖቲካ ድርጅቶች ወገናዊነት ነፃ በሆነ አካኃን ያከናወናል ይላል ፡፡ በዚህ መሰረት ሰራዊቱ በግልፅ የፖለቲካ አባል በመሆን ንቁ ተሳታፊ ባይሆንም ተግባሩን ግን ሙሉ በሙሉ ከፖለቲካ ተፅኖ ውጪ ሆኖ አያወቅም ፡፡ በለውጥ ስም ሌ/ኮ አብይ ወደ ስልጣን ከመጣ በኃላ በመከላከያ ትልቅ ሪፎርም እንደተሰራ በሚድያ ሲለፈፍ ነበር ፡፡ ከዚህ ውስጥም መከላከያ ሰራዊት ተግባሩ ከፖለቲካ ወገንተኝነት ፍፁም ነፃ ሆኖ ማከናወን እንዳለበት ውይይት ተደርገዋል ፡፡ ከዚህ በመነሳት ሚታዩ የነበሩ ምልክቶችና አዝማምያዎች መስተካከል እንዳለበት ውይይት ተደርጎበታል

ሌ/ኮ አብይ ስልጣን በያዘ በማግሰቱ በመከላከያ የተሰራ ነገር ቢኖር የሰራዊቱ አመራር ማደከም ፤ ቆይቶም በተለይ በጀነራሎችና ሲንየር ኮሎኔሎች የተደመሩና ያለተደመሩ ብሎ በመፈረጅ የውሰጥ መቋቋር በመፈጠር ውሰጠዊ አንድነቱ ማደከም ነበር ፡፡ በዚህ ምክንያትም ቀድመን ተደምረናል በማለት ባልተለመደ መልኩ ከማዕርጋቸውና ኃላፊነታቸው በላይ በቀጥታ ከሌ/ኮ አብይ እየተገናኙ ተቋሙን ህግና ስርአት አልባ አደረጉት ፡፡ ለዚህም ያለ እወቀታቸው፤ልምዳቸውና ያለ ጊዚያቸው በመደመራቸው ምክንያት በዚህ አመት የተሰጠው የጀነራሎች ማዕርግ አምበሻበሻቸው ፡፡ ልክ በደርግ ጊዜ የበሩት ከወታደራዊ ዕዝ ሰንሰለት ውጪ ለፓርቲው ቀጥታ ተጠሪ የነበሩ መኮንንኖች ለሰራዊቱ ወድቀት ቀዳሚ ነበሩ ፡፡ ስለሆነም አሁን ኮ/ል አብይ ሰራዊቱ ከፓርቲ ወገንተኝነት ነፃ ሊያደርገው ይቅርና ጀነራሎች የግሉ አሽከር /ተገዢ ሆናል፡፡

የሰራዊቱ አመለካከት ድሮውም ቢሆን በፖለቲካ ተፅኖ የነበሩት ከፍተኛ አመራሮቹ ናቸው ፡፡ አሁንም ለውጥ እየተባለ ከፍተኛ ጄነራሎቹ ናቸው ፡፡ በአሁኑ ባለው የአገሪቱ ፖለቲካ ቀውስ ከዚህ በፊት ከነበረው በባስ ሁኑታ በግልፅም በስውርም የአንደ ፓርቲ ወክለው መግለጫ እየሰጡ ውሰብስብ ፖለቲካ ውስጥ እየዳከሩ ያሉት ከፍተኛ ጄነራሎቹ ናቸው ፡፡

Videos From Around The World

 

ባለፉት ሁለት አመት ሰራዊቱና ከፍተኛ አመራሩ በህገ መንግስቱና በመከላከያ አዋጅ 1100/11 አንፃር ምን ይመስላል ?

የመጀመርያው ግልፅ የፖለቲካ ጣልቃ ግብነት

ከኦቦ ለማ የውህድ ፓርቲ ተቋውሞ ማግሰት የነበረ ውይይት

በመጀመርያ ማንሳት የምፈልገው መከላከያ ሚኒስትሩ ከኦቦ ለማ የውህድ ፓርቲ ተቋውሞ ማግሰትና ወደ ውጭ አገር ለስራ እሀድ ታህሳስ 22 መሄድ ተከትሎ ሰኞ ታህሳስ 23/2012 ዓ.ም ያለምንም ዝግጅትና የተደራጀ ፅሁፍ ለሁሉም አመራርና ከፍተኛ መኮነን በጋራ ውይይት ተደረገ ፡፡ አከታትሎም ወደ ሁሉም አባል ወይይት ተደረገ፡፡ በውይይቱ የተካተቱት አጀንዳዎች ሁለት ናቸው በአዲሱ ሰራዊት መተዳደርያ ደንብና የፖለቲካ ውይይት ናቸው፡፡በመሆኑመ ሁሉም ኦቦ ለማ ከመምጣቱ በፊት አለቀ ይህ ፖለቲካዊ ሽፍጥ ነው ፡፡

በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ያልወጣ የሰራዊት መተዳደርያ ደንብ ልክ እንደ ውህድ ፓርቲ በጥድፍያ ለሰራዊቱ ከዛሬ ጀምሮ ረቂቅ ደንቡ ተግባራዊ ይሆናል ብሎ ከህግ ውጭ ማወያየት ለምን አስፈለገ ፡፡ የውይይቱ ዋና አላማ የውህድ ፓርቲ መስረታ ህገ መንግስታዊ ነው ብሎ ማስረፅና ብልፅግና ማስተዋወቅ ነበር ፡፡ አዲሱ የመተዳደርያ ደንብ እንደ ዋና ወይይት መስሎ የቀረበው ለውይይቱ መግብያ ነበር ፡፡

የጥድፍያ ውይይት አላማው የኦቦ ለማ ውህድ ፓርቲ የመቃወም አቋም በሰራዊቱም ይንፀባረቀል የሚል ስጋት ስላለ ውህድ ፓርቲው ስልጣኑን ለማራዘም የሚወስደው ማንኛውም ኢ-ህገመንግሰታዊ እርመጃ ሰራዊቱ ተባባሪ እንደሆን ለማሰገደድ ነው ፡፡ በፖለቲካ ውይይቱ ማጠቀለያ በየጦር ክፈሉ የተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች በቀጥታ ቪድዮ ኮንፈረስ ለጄኔራል ብርሁኑ ጁላ ቀርበዋል ፡፡ በመሰረቱ ግን የሰራዊቱ ህገ መንግስታዊ ነክ ውይይቶች አጀንዳ የመቅረፅ ና ውይይት በበላይነት የመምራትና ማጠቃለል የመከላከያ ሚ/ሩ እንጂ ከፍተኛ ጄነራሎች ስራ አይደለም ፡፡ በመከላከያ አወጅ ቁ/1100/2011 አንቀፅ 23(1) ሚኒስትሩ ሰራዊቱ ለህገመንግሰቱ ተገዢ መሆኑንና ለህገ መንግሰቱ በፅናት መቆሙን ያረጋግጣል ይላል፡፡ ሆኖም ጄ/ብርሀኑ በህግ ከተሰጠው ስልጣን ውጪ ሁሉም የመከላከያ ስራ ከሌ/ኮ አብይ አልፎ እየተገናኘ አገረና መከላከያ ሰራዊቱ እያመሰ ይገኛል፡፡

ቀጥሎ ከሰራዊቱ በሁሉም ክፍሎች ከተነሱ ጥያቄና አስተያየት ሰራዊት ለምን የፖለቲካ ውይይት ይወያያል የሚል ቀዳሚ ነበር ፡፡ ፖለቲካ የፖለቲከኞች እያለን ፤ህገ መንግሰት ጠባቂ ነን እያልን በሌላ መንገድ ደግሞ ወቅታዊ ሁኔታ በሚል ሰበብ የአንድን ፓርቲ አስተሳሰብ ማስረፅ ትክክል አይደለም የሚል ጠንካራ መልዕክት በቪድዮ ኮንረፈሱ ተላልፋል ፡፡ አወያዩ ጄ/ ብርሁኑ ለተነሳው ጥያቄ ከህገ መንግሰት አንቀፅ 87 አንፃር ምንም አይነት መልስ ስለሌላቸው በቁጣና በንዴት የያዙት ማሰታወሻ ጠረጰዛ ላይ እየወረወሩ እንዴት ይህ ውይይት ፖለቲካ ይባላል በማለት ጥያቄውን በቁጣና በማስፈራራት አልፈውታል ፡፡

በመጨረሻ ስለ ራሰቸው ህገመንግሰት ጠባቂነት ብዙ ተናግረው መድረኩ ዘጉት ፡፡ መልዕክቱም ህገ መንግሰት ጠባቂነት ማለት ለባለተራው ብልፅግና ማንኛውም ትዕዛዝ ፈፅሙ እኔም እየፈፀምኩ ነው ማለታቸው መሆኑ ሁሉም ገብቶታል በአጭሩ ተደመሩ ነው፡፡ ቁጣው በየክፍሉ ያወያዩት አመራሮች ጥያቄው የራሳቸው ጭምር አድርገው ማቅረባቸው ነበር ፡፡ ያኔ ውይይቱ ፖለቲካዊ ነው ብለው የተቋወሙትም ቀስበቀስ በምደባ ፤በማዕርግ ፤ ጡረታ ማውጣት ፤ በአለም አቀፍ ግዳጅ ምክንያት ዘወር ማድረግ ወዘተ ዘዴ በመጠቅም ተፅኖ ፈጥራል፡፡ ይህ አካሄድ ግዳጅ ምን ያህል አንደሚጎዳ መገመት አያስቸግርም እንዲያውመ ጠላት መጣ መጣ በሚባልበት ጊዜ ወይም ይህ ጠላት መጣ መጣ የሚለው ሙሉ በሙሉ እንደሚባለው የፖለቲካ ዲስኩር ነው ማለት ነው ፡፡ በኔ እምነትና ትንታኔ 100 ፐርሰነት ውሸት መሆኑ የመከላከያ ሁለንታናዊ እንቅስቃሴ ማየት በቂ ነው፡፡

ጄነራሉ ብርሁኑ በተግባራቸው የፖለቲካ ወገንተኛ ናቸው፡፡

1.   ከዚህ በፈት በ2011 ዓ.ም ስለ ኦነግ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ የሰጡት መግለጫ እንን አሁን በመቶ የሚቆጠሩ ተዋጊ ይዞ ይቅርና በሽግግሩ ወቅት 30 ሺህ ጦር ይዞ ምንም አለመጣም አታስቡ አሁን ይደመሰሳል ብለዋል ፡፡ በአገሪቱ ምርጫ ቦርድ የተመዘገበ ፓርቲ መዝለፍ ምን ማለት ነው፡፡ የሽግግር ጊዜ የነበረ ሁኔታ የኦነግ ስህተት ብቻ ነበር ወይ? አሁን ማንሳቱስ የመከላከያ ተግባርና ኃላፊነት ነው ? ለዚህም ነው ጄ/ብርሀኑ ለኦነግ ትዕግስት አያስፈልገውም በማለት በጥድፍያ ወደ ጦርነት የገቡት፡፡ ቢሆንም 100 ወታደር ለመደምሰስ በርካታ ክፍለጦር፤ መከናይዘድና ሄሊካፕተር አሰማርተው ሁለት አመት አልበቃቸውም፡፡ ጄነራሉ በሚድያ ወጥተህ ለአነግና ደጋፊው አስፈራራ የሚል ፖለቲካዊ ትዕዛዝ ሲሰጣቸው ወጥተው ዘራፍ ብላል ቀጥሎም 100 ሽፍታ ለመደምሰስ በሺዎች የሚቆጠር ህዘብ ላይ ከባድ ጉዳት እንዲደርስ አድርጓል ፡፡ እንደዛ ባይሆን ኑሮ 100 ሽፍታ ማጥፋት አልቻልክም ተብለው ይጠየቁ ነበር ቢያንስ የተራዘመላቸው ጡረታ ጊዜ ያበቃ ነበር ፡፡ ስለሆነም ምክንያቱ ሽፍታ የሚሉት መደምሰስ አይደለም ፖለቲካዊ ተልዕኮው የኦሮሞ ህዘብ ትግል በማደከም ሰልጣን ላይ ለመቆየት ነው፡፡ የሀጫሉ ግድያ፤ የጁሀርና በቀለ እሰር ለ2 አመት ሲፈፀም የቆየው ፖለቲካዊ ተልዕኮ አንዱ አካል ነው፡፡ በየትኛው ወታደራዊ ፈሊጥ ነው 100 ሽፍታ ለመደምሰስ በሜካናይዘድና አየር ድጋፍ የታገዘ እግረኛ ጦር የሚዘምተው ፡፡

 

2.   ጄነራሉ በ2011 ዓ.ም መከላከያ ሚ/ር ለህዘብ ተወካዮች ም/ቤት ሪፖርት ሲያቀርቡ ኦነግ ለማጣጣል ብለው በውትደራና ሂወቴ ውስጥ በወለጋ የደረሰ ጭፍጨፋ በውትድረና ሂወቴ አይቼ አለውቅም ብለዋል፡፡ ቀጥለውም በቅርቡ በቪድዮ ዶክመንታሪ እናቀርባለን አሉ የዋልታ ፌክ ዶክመንታሪ መሆኑ ነው፡፡ ይህም በኮ/ል አብይ ኦነግን በተገኘ መድረክ ማሳጣት የሚል የተሰጣቸው የፖለቲካ ተልዕኮ ማስፈፀም ነው ፡፡ ዶክመንተሪ ስርቶ ኦንግ ማጋለጥ በየትኛው መለክያ ነው የመከለካያ ስራ የሚሆነው፡፡ የጄነራሉ ድርጊት ኦነግ በኦሮሚያ ተቀባይነት እንዳያገኝ ለገዢው ፓርቲ ፖለተካ ድጋፍ ማድረግ ነው፡ ይህም ኮ/ል አብይ የኦሮሞ ትግል የማዳከም ስራ አካል ነው ፡፡ አሁን እየሆነ ያለው ለነፃነቱ የሚተገል ኦሮሞ የተለያየ ስም እየሰጡ ማሳደድና ለህብረ ብሄር ፈደራል ስርዐት የሚታገሉ አካላት ማደከም፤ማሰር፤መግደል ፤ማግለል፤ድምፃቸው እንዳይሰማ ወዘተ ማድረግ ተቋማዊ መሆኑ መለስ ብሎ ማየት ያስፈልጋል፡፡

 

3.   በ2011ዓ.ም ቤተመንግሰት ለጥቅማጥቅም መብት ለመጠየቅ የሄዱት የታጠቁ ወታደሮች በኃላ መፈንቅለ መንግሰት ነው ሲባል ጄ/ብርሀኑ አዲስ አበባ ያለው በሙሉ መኮንን ሰብስበው ያለ ምንም መረጃና ማስረጃ መፈንቀለ መንግሰቱ ያቀናበረው ግንበት ሰባት በአቋራጭ ስልጣን ለመያዝ ነው ብላል ፡፡ ምክንያት ብለው ያቅረቡትም አንዱ አንዱ ጥያቄ የግንቦት ሰባት ፖለቲካ አቋም ነው ሲያራምዱ የነበሩት ስለሆነም አይቀጡ ቀጣት ያገኛሉ አሉ፡፡ ጄነራሉ ግንቦት ሰባት የቤተ መንግሰት ወዳጅ መሆኑ ሳያውቁ ነው የተናገሩት፡፡ ጄኔራሉ ከቤተ መንግሰት የተሰጣቸው ፖለቲካዊ መልዕክት ሳያቅማሙ ማስተላፍ ብቻ ነው የሚያውቁት እንጂ የአገሪቱ ውስብስበ ፖለቲካ በፍፁም አይረዱትም፡፡ በኃላ ግን ግንቦት ሰባት ማሳጣት ሌ/ኮ አብይ የማይወዱት መሆኑ ከቤተ መንግሰት ሲነገራቸው ግንቦት ሰባት ለቀቅ በማድረግ ኦነግና ሌሎች አካላት ሽፍታ እያሉ ላይ ማሳጣትና መፈረጅ ቀጠሉ ፡፡ ስለሆነም ጀነራሉ ግልፅ የፖለቲካ ጣልቃ ገብነትና አንድን ፖርቲ ድጋፍ እየቀጠሉበት ይገኛሉ ፡፡ ሰራዊቱም ሁሉም አይነት ሚዲያ ስለሚዳስስ ከሳቸው በላይ ፖለቲካዊ ንቁ መሆኑ አለማወቀቸው ይገርማል ፡፡

 

4.   በወለጋና ጉጂ አከባቢ ለረጅም ጊዜ መንግሰት የስልክና ኢንተርኔት ተዘግቶ ነበር፡፡ ከኮቪድ 19 ጋር ተያይዞ በአክቲቪስቶችና አለም አቃፍ ሰብአዊ ድርጅቶች ስልክ መከፈት አለበት ብለው ተፅኖ ሲያደርጉ ነበር፡፡ ጄ/ብርሀኑ በሚድያ ብቅ ብለው ወለጋ ሰላም ነው ኮሽ የለም ስለሆነም ስልክ ተለቃል አሉ ፡፡ ቀጥለውም የተለመደው ማጣጣል ታጣቂዎቸ ሬድዮ መገናኛ እንካን የሌላቸው ተራ ሽፍቶች ናቸው አሉ፡፡ ይህ ለፖቲካ ፍጆታ ነው፡፡ መሬት ያለው ግን ከፍተኛ ውግያ በመሆኑ ሰራዊቱም በማያቀርጥ የእርስ በርስ ውግያ እየተሰላቸ ነው ፡፡ እንዲህ ባሉ በማግሰቱ የቀጠሉት ግጭቶች ከየት መጡ ስለሆነም ስልኩ የተለቀቀው በአለም አቀፍ ተፅኖ ነው፡፡ የሰጡት መግለጫም ወታደራዊ ኦፕሬሽን ሳይሆን የፖለቲካ ስራ ነው ፖለቲካ ስራ ድግሞ የወታደር ስራ አይደለም፡፡ ሁሌ መንግሰት ፖለቲካዊ ኪሳራ ሲደርሰበት ያለ ሙያቸውና ተልዕካቸው ሁኔታዎቸን ለማድበስበስ በሚድያ ብቅ ይላሉ፡፡

 

5.   ጄ/ብርሀኑ ግንቦት 15 ወታደራዊ ኣመራር በመኮንኖቸ ክበብ ሰብሰበው እኛ እንደ ግብጽ እና ሱዳን ሰራዊት ፕሮፈናል መሆን ኣለብን ብለው ሲናገሩ ሁለቱም ሀገራት ሰራዊቱ ስልጣን በሀይል መያዙን ለማሳወቅ ነበር ሰልጣን መፈለጋቸው በግልጽ የተናገሩበት እና ውስጥ ለውስጥ ሰው እያደራጁ እንዳሉ እንደ ተነቃባችው ሰላወቁ ካሁን አሁን ኮ/ል ዓብይ ያጠፋኛል በማለት የተሰጠው ሳያላምጥ ይውጣል።

 

6.  ኦቦ ለማ፤ጀነራል አደም ሚና በመከላከያ ምንድ ነው?

በጀ/ብርሀኑ የሚደረጉ ፖቲካዊ መግለጫዎቸና ማስፈራርያዎች የመከላከያ ተግባር ቢሆን ኑሮ የተቋሙ የመጀመርያ ሰው ኦቦ ለማ ነበር ሚደያ ላይ በተደጋጋሚ መቅረብ የነበረበት ሆኖም ኦቦ በኮ/ል አብይ ከካራንቲን ከመጀመሩ በፊት ካራንቲን ገብታል ይባስ ብሎ በአዳማ ቀብር ስነስርአት ሀዘናቸው የገለፁበት መልዕክት በOBN እንዳይተላፍ ተደረጋል ይህ ኮ/ል አብይ ተግባር ተሰሚነት ያለቸው ኦሮሞዎች ድምፃቸው በማፈን የኦሮሞ ትግል ማጥፋት ነው ፡፡ የአሁኑ የሀጫሉ ግድያ ተከተሎ የመጡ ቀውሶች የተፈፀሙ ናቸው ድምፁ እንደይሰማም OMN ተዘግታል የኦሮሞ ህዘብ ማጥቃት በአሀዳውያን ተቋማዊ ቅርፅ ይዛል ስለሆነም ድንገት አይደለም 2 አመት ሙሉ በጁሀርና ብሄርተኛ ኦሮሞዎች የነበረ ዘመቻ መለስ ብሎ ማስታወስ ጠቃሚ ነው፡፡ በብልፅግና የተንኮል ፖለቲካ ጄ/አደም እንደ ጠ/ኢታማዦር ሹም ፊት ለፊት እንዲታይ አይፈለግም ሁሉም ነገር ከመጋረጃ በስተጀርባ እንዲጨርስ ያደርጋል ፡፡ ኮ/ል አብይ ለጀ/ብርሀኑ አንተ ነህ የተሻልክ ሰለሚለው እውነት ይመስለዋል ከስልጣኑ በላይ የሆኑትን ውሳኔዎችን እንዲወሰንም ይፈቅደለታል ሆኖም ኮ/ል አብይ ሁሉም ነገር አስቀድሞ ከጀ/አደም የጨረሰው ነው ለጀ/ብረሀኑ የሚነግረው ጀ/አደም የተሰጠው ፖለቲካዊ ተልዕኮ የሚያሳካው ጀ/ብርሀኑ ወደ ፊት በማምጣት ስለሆነ እንደ ፈረስ እንዲጋልብ ይፈቅድለታል፡፡ ለዚህ ነው ጀ/ብርሀኑም የኮ/ል አብይ /ብልፅግና/አሀዳውያን /ተንኮል ለማሰፈፀም ግንባር ቀደም ሆኖ ኦሮሞን የማደከም ታሪካዊ ስህተት እየፈፀመ ያለው ፡፡ አሀዳውያን ሀይሎች በያሉበት ሆኖው ደግሞ መከላከያ ሚ/ርና ም/ጠ/ኢታማዦር ሹም ኦሮሞ ተቆጣጠሩት ይላሉ ሆኖም ይህ ስልጣን ኦሮሞን ለማጥፋት መሆኑ በቅርቡ መከላከያ ፈፅሞታል ብሎ አመንስቲ ኢንተርናሽናል ያቀረበው ሪፖርት ማየ ት በቂ ነው፡፡

7.   በቅርቡ የብልፅግና ኢ-ህገመንግስታዊ ስልጣን ማራዘም ተከትሎ በአገሪቱ ያሉ ተፋካካሪ ፓርቲዎች የጋራ ምክክር በማድረግ መፍተሄ እናምጣ ብለዋል ካለሆነ ግን ከመስከርም 2013 በሀላ የተመረጠ ህጋዊ መንግስት የለም ብለዋል ፡፡ ኮ/ል አብይ አርፋቹ ተቀመጡ ካልሆነ ጦር በማዝመት እገድላሎህ፤ ህፃን አዛውንቱ ደምበደም ትሆናለቹህ ብለዋል ፡፡ ታድያ ጄ/ብርሀኑ የኮ/ል አብይ ማሰፈራራት አከታትሎ የተለመደው ፖለቲካዊ መግለጫ የሰጠው ፡፡ በአገሪቱ መጪው 2013 መስከረም የሚደረግ ህዝባዊ አመፅ በሀይል እንጨፈልቃለን ብሎ አስፈራርታል፡፡ ከዚህ በኃላ የሚመጡ ሁሉም መስከረም ቢሆን ምንም ኮሽ የለም ብልፅግና ለዘአለም እንዲኖር እናደርጋለን የሚል ፖለቲካዊ መግለጫ ነው የሰጠው ፡፡ ይህ መግለጫ አንቀፅ 87 (5) ህገ መንግሰት ይጥሳል፡፡ ለዚህም ነው ብልፅግና ያለ ፖለቲካዊ ውይይት ጀ/ብርሁኑ ተማምኖ ስልጣኑ ያራዘመው ፡፡ ስለሆነም ጀ/ብረሁኑ ይህ የአገር ሰራዊቱ ለብልፅግና ፖለቲካዊ ማሰፈፀምያ በማድረግ እዚህም እዛም ግጭት ውሰጥ አታስገባው፡፡ ጄ/ብርሀኑ እንካን የዚህ አገር ውሰብሰብ ፖለቲካ ልትገምት ቀርቶ በውትድርና ሙያህ 100 የማይሞላ የወለጋ ሽፍታ (ራሱ እንደገለፀው) በሳምንት ይጠፋሉ ብለህ ገምተህ ይሄው ሁለት አመት አለፈው ፡፡ ስለዚህ እንደ ኮ/ል አብይ በጉልበት አታሳብ፡፡ ነገ ሌላ ቀን ነው፡፡

8.   በአመንሰቲ ኢንተርኛሽል ለመከላከያ ሰራዊት በሰብአዊ ጥሰት የቀረበው ወቀሳ ሰራዊቱ ሊወያይበትና ሊታረምበት ይገባል፡፡ ይህ ካልሆነ ሰራዊቱ ቀጣይ ሰብአዊ መብት ጥሰት ለመፈፀም እየተዘጋጀ እንደቆየ ባለው በአሁኑ ቀውስም በስፋት እየተሳተፈ ይገኛል ፡፡ ከለውጡ በፊት በሻሸመኔ፤ ሞያሌና ሌሎች አከባቢዎች ከህግ አግባብ ሰላማዊ ሰው የገደሉ ተብለው በመከላከያ ትብብር ፍ/ቤት ቀርባል የተማላ ባሆንም ( ጀ/ሳሞራ ሊመሰገኑ ይገባል) ፡፡ ታድያ አሁን ምንድ ነው ዝም ማለት ? የሚጠየቅ አመራርና አባል ካለ ይጠየቅ ካልሆነ በመከላከያ ሰራዊት ያለተፈፀመ ከሆነ ለህዘቡ መግለፅ የግድ ይላል፡፡ የመከላከያ ስም ለማጥፋት አይደለም ማንም የሰራዊት አባል ሲያጠፋ ግን በግለሰብ ደረጃ ተጠያቂ መኖር አለበት አለበለዚያ ግን ሰብአዊ መብት ጥሰቱ ተቋማዊ/መንግሰታዊ /ሽፋን አለው ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ የሰራዊቱ ተቀባይነት ዘጭ ይላል፡፡ ቀስበቀስም ለአገርና ህዘብ ይጎዳል ስለሆነም ተጠያቀነት መስፈን አለበት፡፡

 

9.   በቅርቡ ኮ/ል አብይ ጄነራለች ሰብስቦ የሚሰጣቹ ማንኛውም ትዕዛዝ( ህጋዊም ህገወጥም) ጥያቄ ሳትጠይቁ ትፈፅማላቹ ብላል በሚድያ፡፡ በሚድያ ያስተላለፈውም ሆን ብሎ ለኢ/ያ ህዝብና ፖለቲካ ፓርቲዎች ለማስፈራራት ነው ፡፡ አርፈህ ቁጭ በል ሰራዊቱ ይጨፈጭፈኃል ነው መልዕክቱ፡፡ በህገመንግስታዊ ስርአት ያላቸው አገሮች ሰራዊት ህጋዊ ትዕዛዝ ብቻ ይፈፅማል፡፡ የአሜሪካው ነውጠኛ ፕሬዚዳንት ትራምፕ በቅርቡ በአንድ ጥቁር አሜሪካዊ ሞት ምክንያት የተቀሰቀሰው አመፅ ለመቆጣጠር በከተሞች የአሜሪካ መደበኛ ሰራዊት እንዲገባ የሰጠው ትዕዛዝ ህገወጥ ትዕዛዝ ብለው ጄነራሎቹ እንዳይፈፀም አድርገውታል፡፡ በኛ አገር ግን ኮ/ል አብይ ጄነራሎች ስብስቦ ፔሬድ(በቃ የኔ ቃል አንድ ይበቃል) እያለ ያስፈራራል ፡፡ መልእክቱም እንደ ደርግ እምቢ ያለ ሰው ጥይት አጉርሰው መሆኑ ነው፡፡ በዚህ እሳቤ የሚመራ ወታደር ለጦር ሜዳ የሰለጠነው መከላከያ ሰራዊት ሙሉ ትጥቅ አስታጥቆ ወደ ሰላማዊ ከተሞች እየተሰማሩ ጉዳት እያደረሰ ያለው፡ ስለሆነም ኮ/ል በለውጡ ማግሰት የመንግሰት አሸባሪ ነበር ሲል የገለፀው አባባል በበለጠ አጠናክሮ ቀጥላል ፡፡

ቀጥሎም እንዚህ ጄነራሎች ወደ ታችኛው አመራርና አባል እየወረዱ ፈፅም የተባልከው ሁሉ ፈፅም (ግደል፤እሰር፤ግረፍ ወዘተ) ፔሬድ ማለት ጀምረዋል፡፡ ጮህ ብለው ባይናገሩም የማይቀበሉት ቀላል ቁጥር አይደለም ለዚህም ነው በሁለት አመት 100 የወለጋ ሽፍታ መደምሰስ ያልተቻለው ፡፡

ለማጠቀለል የሰራዊቱ ከፍተኛ አመራሮች የኮ/ል አብይ አምባገነናዊ አገዛዝ ለማሰቀጠል ኢ-ህገመንግስታዊ ድርጊት መፈፀምና ማሰፈፀም ተባባሪ መሆን ለአገርም ለእናንተም ጠቃሚ አይደለም፡፡ ስወየው እብድ መሆኑ የሰራዊቱ አመራሮች በቅርብ ታውቁት አላቹ ፡፡ ለምሳሌ መካከለኛና ከፍተኛ አመራሮች ቤተ መንግሰት ጠርቶ በ2011 የተናገረው የሰራዊት ተልዕኮ ድንበር መጠበቅ ነው ህገ መንግሰት መጠበቅ አይደለም ብላል ስለዚህ ጉዳይ እንድተናገሩም እድል አልሰጠም ፡፡ ይህ ያደረገበት ምክንያት ጀ/ስአረ ህገ መንግሰት እየጠቀስ የፓርቲ ጣልቃ ገብነትን እንዲስተካከሉ በኮ/ል አብይ ድርጊት ከፍተኛ ተቋውሞ ነበረው ይህ በሁሉም አመራር ይታወቀል፡፡ በዚህ ምክንያት ነው ስለ ህገመንግሰት መጠበቅአያገባህም/ አያገባቹሁም እናንተ ደንበር መጠበቅ ብቻ ነው ተግባራቹህ ብላል በአደባባይ፡፡

ትንሽ ቆይቶ ከጄ/ስአረ መስዋእትነት በኃላ ደግሞ በቤተ መንግሰት ከፍተኛና መካከለኛ አመራር ስብሰባ ጠርቶ ህግ መንግሰት ጠባቂ አይደላቹሁም ያልኩት ተሳስቼ ነበር ጄ/ ስአረ ከስብሰባ በሃላ በአካል ተወያይተን ትክክል አለመሆኔ ተግባብተናል ብላል አሁንም ስለዚህ ጉዳይ እንድተናገሩ እድል አልሰጠም ፡፡ ታድያ መከላከያ ሰራዊቱ የህገ መንግስት ጠባቂ መሆኑ ለመረዳት ጄነራሉ መሞት ነበረባቸው?፡፡ አሁን ደግሞ ጄነራሎቹ ሰብስቦ የህገ መንግሰትም የአገርም ጠባቂ አይደላቹሁም የኔ በጊዜ ያለተገደበ ንጉሳዊ ስልጣን ጠባቂ ናቹህ ፔሬድ፡፡አሁንም እንድተናገሩ እድል አልሰጠም፡፡

መጀመርያ ስልጣን እንደያዘም የጦርነት ሀ ሁ (ABC) ጄነራሎች ቁጭ አድረጎ ስልጠና ሰጠ/ቀደዳ/ እንደ ዋልታ ዶኩመንተሪ በሁሉም ሚደያ ተላለፈ ለራሱ ግለሰባዊ እወቅና ለማግንነት ስል ጄነራሎቹን በአለም ህዘብ ፊት እጅግ ዝቅ አደረጋቸው ፡፡ልብ በሉ አሁንም እንድተናገሩ እድል አልሰጠም፡፡ ታድያ ግብፅ የኢ/ያ ከፍተኛ ጄነራሎች ያኔ የጦርነት ሀ ሁ (ABC) ሲማሩ አይታ ይሁን የምትደነፋው ምክንያቱም አንዳንዶቹ ሳያውቁት ቀርተው ሳይሆን እሱን ለማሰደሰት ብለው እንደ ተማሪ ይፅፉ ነበር ፡፡ ታድያ እናንተ ምንድ ናቸህ ራሳቹህ ጠይቁ? ፤ በየጊዜው የኮ/ል አብይ ዲስኩርና ድራማ እያያቹ እሰከመቼ ? ለምንስ አትጠይቅ ይባላል ? ለምንስ ለወታደር በሚድያ ያስፈራራል? ለምንስ ውይይት ብሎ ጠርቶ ራሱ ብቻ ተናግሮ ይሄዳል? መልሱ ለእያንዳንዱ ሰራዊት አባል ይመለከታል፡፡

ሰራዊቱ ማወቅ ያለበት በመከላከያ ወይም በክልል ልዩ ኃይል የህዘብ አመፅ ፤ የህዘብ ጥያቄ መቆጣጠር በፍፁም አይቻለም ቀውስ ማባባስ ግን ይችል ይሆናል፡፡ ስለሆነም ሰራዊቱ ብልፅግና ፓርቲ ወደ ሰለጠነ ፖለቲካ ውይይትና ድርድር እንዲመጣ ከተፈለገ ሰራዊቱ ለፖለቲካ መጠቀምያ መሆን የለበትም፡፡ ጄ/ብረሁኑም ብልፅግና እየተከታተለ ፖለቲካዊ መግለጫ መስጠት የለበትም ፡፡ ካልሆነ ፊልድ ጃኬት አውልቆ ወደ ብልፅግና ይግባና ጠ/ሚ ይቀበለው ፔሬድ ፔሬድ ፔሬድ፡፡

Back to Front Page