Back to Front Page

አንዳንድ ግንዣቤዎች - በድጋሚ

አንዳንድ ግንዣቤዎች - በድጋሚ

 

ካሁን በፊት የጻፍኩት መልእክት ጠቃሚነት ኣለው ብየ ስላሰብኩ ከጥቂት ነጥቦች ጋር አነሆ፡

 

July 31, 2020

 

በቀለ ብርሃኑ                                                  ዲሰምበር 7፣ 2019

 

 

ክ ጥቂት ቅናት በፊት አያ ዮሃንስ አበራን  (PHD) አንበብኳቸው፡ አደነቅኳቸውም።

 

የ አቶ ዮሃንስ አበራ ን ጽሁፎች በጉጉት ነው የምጠብቃቸው። እውነት፤ ግልጽነትና ሩቅ አሳቢነትን ያንጸባርቃሉ። በጣት ከሚቆጠሩ ላገሪቱ ከሚጨነቁ የኢትዮጵያ ምሁራን ቀዳሚ ናቸው እላለሁኝ።  እግዜር ከሳቸው ጋር ይሁን።

 

ስለ ህወሓት ሳስብ ሁል ጊዜም የሚያበሳጨኝ የትግራይ ህዝብ ቅንጣትም ብትሆን ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ የተሻ ጥቅም ሳያገኝ አገኝ እየተባለ በማንም ጎሰኛ ሞራሉ እስኪዳሸቅ  (ይቅርታ በቀሉ እንኳን የሚዳሽቅ አይመስለኝም) ድረስ ሲሰደብ፤ ሲታማና የጥላቻ መአት ሲወርድበት - የህወሓት ዝምታ እጂግ ዘግናኝና ክፉ ነበር። ከዚህ ድርጅት ጋር ምንም ግኑኝነትና የፖለቲካ ወገንተንነት ባይኖረኝም ይህ ዝምታው እንደሚያሳስበኝ አጋጣሚውን ሳገኝ ሳልገልጽላቸው አላለፍኩም። ለእውነት መቆም ሁሌም የህሊና ነጻንት ይሰጣልና።

 

እንደኔ ከሆነ ህወሃት ካጠፋቸው ነገሮች ሁለት ጽንፍ አካሄዶች የታዩኛል።

 

ባንድ በኩል ከላይ የተጠቀሰው ትግራዎት በሌላው ሲገለሉ፤ የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ ሲዛባቸው የተግባሩ ተባባሪ እስኪመስል ድረስ ጆሮ ዳ ልበስ ብሎ ዝም ማለቱ ሲሆን በሌላው ጽንፍ ደግሞ ኢትዮጵያን ከድህነት አረንቋ ለማውጣት የሚደርገወን ያክል ስለ ኢትዮጵያዊነት - የኢትዮጵያ አንድነት የሚደርገው የፕሮፓጋንዳ ደካማነት ነው። 

Videos From Around The World

 

ተግባር ከ ቃላት ይበልጥ ይናገራል የሚሉት አባባል አለ። መሰረታዊ እወታነት አለው ቢባልም በኔ እይታ አባሉ ጎዶለነት አለው።  ለጊዜውም ቢሆን የተደጋገመ ዉት እውነትን ይቀብራታል።  በ ኢትዮጵያ የሆነዉም ይሄው ነው።

ተግባር በቃላት ካልታጀበ/ ካልተገለጸ ዉጤቱ በቀላ አይታዪም።  ህወሓት መራሹ ኢሃአደግ አንዱ ትልቁ ጉድለቱ ይህ ነበር። ስራዎቹ ሁሉ ኢትዮጵያዊ ዘግነትን በጽኑ መሰረት እንዲመሰረት የሚረዱ ናቸው ብሎ ካልለፈፈ፤ ሀብረ-ብሄራዊነት አቃፊ ያላደረገ ኢትዮጵያዊነት ላሳር ነው ብሎ ካላወጀና ካልሰበክ በየ መንደሩ የገነባቸው ትምህርት ቤቶችና የህክምና ጣብያዎች፤ መንገዶች፤ የመብራት ሃይል ግንባታዎች፤ ፋብሪካዎች ራሳችው ይመሰክሩልኛል ብሎ ማስብ ብቻ ራሱ በቂ እንዳልሆነ ኣሁን ያለው ያገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ ይመሰክራል::

 

ባንድ በኩል የዚያን ዘመን ትውልድ መውቀስ ከባድ ነው። የያኔው ታጋይ ሃይል እውነትንና ህዝባዊ አላማን አንግቦ ነበር የተነሳው። በኔ እይታ ያሁኑ ትውልድ ያፈራቸው የፖለቲካ መሪዎች ኣብዛኞቹ ጊዚያዊ ጥቅምን፤ ዝናን፤ እውቅናን ለማግኘት የሚሯራጥ ይህንን ለማግኘት ሲልም ሸፍጥና ክፋትን እንደመሳርያነት የሚጠቀም ዘመን አመጣሽ ሃይል ነው። ኣሁን ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ መገንዘቡ በቂ ነው፡

 

ፖለቲከኞቻችንን እዩዋቸው። በነሱ እይታ በእውነት የተመሰረተ የሃሳብ ልዕልናን መነሻ ያደረገ የሰነፎች ፖለቲካ ነው።  የቀን ጅቦች ሲሉ ጠ/ሚኒስቴሩ፤ ኦሮ-ማራ ለታክቲክ ነው የተጠቀምነው በማለት ሌሎች ህዝቦችን ያገለለ ጥላቻን እነ አንቶኔ ሲሰብኩ፤. በጥላቻ ነቀርሳ የታመሙት እነ እምቧ ያለው ባደባባይ ዘራፍ ሲሉ የሚታያቸው የዛሬ ዝናቸው እንጂ ለዘመናት አብሮ የኖረዉን ህዝብ ፍላጎት ማሳካት አይደለም።  ያ ያኔ ቀረ።

 

ሰሞኑን የ ዋለሊኝ መኮንንን 50ኛ ዓመት መታሰቢያ በቴለቪዥን ስከታተል ነበር።  ያኔ - ያኔ ከ50 ዓመት በፊት ዋለሊኝና ጓዶቹ ኢትዮጵያ የ ብሄሮች እስር ቤት ነች ሲሉ: መሬት ላራሹን ሲሰብኩ፤ ያኔና ከዚያ በፊት የነበሩትን ከፉ ያገዛዝ ስራቶች ሲተነትኑና ስያጋልጡ ለቅንጦት አልነበረም።  ከዝያ ብኋላ የመጡና የነዝያን ግፈኛ ስርዓቶች ያላዩና ወይም ተጠቃሚ የነበሩ የነዋለልኝን መሰረታዊ አበርክቶ ለማሳንስ የሚሞክሩ ሰዎች ስመለከት እጅጉን ደመመኝ። ደግነቱ ያኔ የነበሩ የድሮው ወጣቶች ያሁኑ አዛውንቶች በጥልቅ ትንተናቸው አዲሶቹን ሲያርሙ ማየቴ መንፈሴ ተረጋጋ።

 

በዚሁ ስብሰባ አንድ ምናልባትም ያልተገነዘባችሁት የሰማሁትን ላካፍላችሁ።  ሰውየው "አልባሌ" ወጣት ቢሆን አይገርመኝም ነበር።  የ ኤኮኖሚክስ (ዶር) ምሩቅ ወጣት ይመስለኛል የጠ/ሚኒስትሩ አማካሪ ይመስለኛል።  አንድ ፎረም ዉስጥ የአብይን "ነጻ ገበያ " ስያራምድ ነበር ያየሁት።

 

ወደ ነገሩ ልግባና በግርድፉ እንዲህ አለ።  ያኔ ዋለልኝ ያንን ጽሁፍ እንዴት አድርጎ ሊጽፈው ቻለ።  እንግሊዝኛው በጣም የመጠቀ ነው። አብሮት የፈረንጅ ጸሃፊ ሳይኖር አይቀርም - ዓይነት ነገር።

ያን ስሰማ እጁጉን አዘንኩኝ።  እንዲህ ያለ አመለካከት ያላቸው ወጣቶች ናቸው አገር የሚመሩት..

 

እነ አያ አበራም በፈረንጆች እየታጀቡ ይሆን የሚጽፉት??  የያኔው ዩኒቨርሲቲ ካሁኑ -ብያንስ ቋንቋን በሚመለከት- እጅግ የላቀ እንደነበር አለማወቁ ገረመኝ።  የበርሃነ መስቀል ረዳን፤ የ አዲስ ህይወትን ጽሁፎች፤ የUSUAA   የ አውሮፓና አለም አቀፍ ተማሪዎች፤ ወዘተ.. ይህ አዲስ ምሁር እንዳላያቸው እርግጠኛ ነኝ።

 

እንግዲህ እንዲህ አይነቶቹ ናቸው ዘመናዊ አማካሪዎች፤ መሪዎች፤ የሃሳብ ምንጮች። ይህችን አገር ፈጣሪ ይጠብቃት።

 

ጊዜው አሁን ነው። ይህ ተደጋግሞ ተነግሯል።  ኢትዮጵያ ወይ ትወድቃለች (አሁን ባለችበት ሁኔታ ዳግም ላታንሰራራ ) ወይም በፍጥነት ካለችበት ገደል አፋፍ ማፈግፈግ።

 

ምርጫው የህዝቡ ነው።  በግልጽ የሚታየኝ ያለው የትግራይ ህዝብና ዉስጧ ያሉ ፓርቲዎች የመድህኑ ተጨባጭ ሃይል ናቸው።  ሌላዉም ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል የዚህ ህዝብና ፓርቲዎቹ አጋር በመሆን አገሪቷን ለማዳን ከመጓዝ ሌላ አማራጭ ያከተመ ይመስለኛል።

 

የትግራይ መሪዎች ከነብዙ ጉድለቶቻቸው የተደራጁ የኢትዮጵያ መድህኖች ሆነው አየተገኙ ነው፥፥  ባሁኑ ጊዜ ኣምባገንነቱ ለሁሉም ሰው ግልጽ የሆነለት ያዲስ ኣበባው መሪ ሁሉንም ኣይነት የሰላማዊ ተቃውሞ ኣራማጆችን ወደ ከርቸሌ ልኳቸዋል፤፤

ከንግዲህ በዚህ ሰው በኩል የሚመጣ ኣገር ኣዳኝ መፍትሄ አንደማይኖር  ቁርጣችንን ያወቅን ይመስለኛል።

 

ትግራይ ዉስጥ የሚካሀደው ምርጫ በሁሉም ኣገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ መታገዝ ኣለበት፥  ምርጫዉም የሁሉንም ተሳታፊ ፍላጎት ከሞላ ጎደል ማሟላት ይኖርበታል፤ ማለትም ግልጽና ፍት ህ የተላበሰ መሆን ይገባዋል።

 

ምርጫዉን በሚመለከት ፡ በተለይ የ proportional representation ኣስፈላጊነት የምለው ይኖረኛል።

 

ላሁኑ በዚህ ላብቃ።

 

አስከዛው ሰላም ለሁሉም

 

 

 

Back to Front Page