Back to Front Page

ወድቆ መነሳት-የህወሓት ምስጢር

ወድቆ መነሳት-የህወሓት ምስጢር

አለም ወርቂ  7-18-20

ምንድነው ህወሓት ሁሌ እንደ አልአዛር ከመቃብር ተነስቶ ህይወት የሚዘራው? አበቃለት ሲባል ማለትም የጸሃይ ባት ቁመና ይላበስና ዙሮና ተመልሶ እንደ ጥዋት ጸሃይ ይደምቃል! ምስጢሩ ምንድነው?

ጥሩ ትንሽ ከሆነ ማህበረ ሰብ የወጣ የህወሓት ድርጅት እንዴት በኢትዮጵያ ተጽእኖው የገዘፈ ሆነ!?

ምንድነው ብዙ የኢትዮጵያ ምሁራን የህወሓት ነገር ሁሌ እንቆቅልሽ የሚሆናቸው? ድርጅቱ ተዳከመ ሲሉ ጠንክሮ ያገኙታል። ሞተ ብለው ሲጨፍሩ ህይወት ዘርቶ ያዩታል! ምክንያቱ ምን ይሆን?

Videos From Around The World

ኢትዮጵያ ምድር ባለፉት 45 አመታት ብዙ የፖለቲካ ድርጅቶች ብቅ ብለው ጠፍተዋል ኣልያም ተዳክመዋል። ደርግ፡ ኢህ አፓ፡ መኢሶን ጀብሃና ኢዲህ በምሳሌነት መጥቀስ ይቻላል። ህወሓት ግን ለ17 አመታት በመታገል ስርኣት ኣፍርሶ፣ መንግስት በመሆን ለ27 አመታት ዘልቀዋል። ኢትዮጵያም በሚገርም ሁኔታ ቀይረዋል። አሁንም ህይወት ያለው ድርጅት ሁኖ እሰከ አሁን ተጠናክሮ በመቀጠል ላይ ይገኛል። እንደ ድሮው መላው ኢትዮጵያ ባያስተዳድርም መላው ኢትዮጵያውያንን ግን ከማንም ድርጅት በላይ እያነጋገረ ይገኛል። የሰው ቀልብ የሚስበው ስለ አብይ ሲነገር ሳይሆን ስለ ህወሓት ጉዳይ ነው። ለምን?

የድርጅቱ ጥንካሬ የሚመነጨው ከየት ነው ለሚለው የተለያየ መልስ ቢኖርም በኔ ግምት ግን የሚከተሉት ናቸው።

1.      ያመነበት አጥብቆ የመያዝ ባህል በትግራይ ማህበረሰብ ውስጥ ስር የሰደደ ባህል ነው። ይህ ጥሩ/ጠቃሚ ባህል ድርጅቱ ለችግርና ፈተና እጁ እንዳይሰጥ በጣም የጠቀመው ይመስለኛል። ይህ የጽናት ባህል ሌሎች ብዙ ድርጅቶች ብዙ ቁም ነገር ሳይሰሩ ሲበታተኑ ህወሕት ግን ተራራ ሁኖ እንዲቆምና እንዲሁም በምድረ ኢትዮጵያ የገዘፈ ተጽእኖ ፈጣሪ እንዲሆን አርጎታል።

 

2.      የድርጅቱ የረጅም ጊዜ ልምድ ረጅም እድሜ እንዲኖረው ረድቶታል። በትግል እያለና እንደ መንግስት ሁኖ መስራት ከጀመረ በኋላ ያገኘው የፖለቲካና የአስተዳደር ልምድ ቀላል አይደለም። ለዛም ነው ሌሎች ድርጅቶች ሲደናበሩ ህወህት ግን መቼና ምን ማድረግ እንዳለበት ጠንቅቆ የሚያውቀው። ለዚህ ይመስላል ከኢትዮጵያ አልፎ የአፍሪቃን ቀንድ ፖለቲካ ዘዋሪ/ሹፌር ይሆናል ተብሎ የሚታማው።

 

3.      በድርጅቱ ውስጥ የበቀለው ጠንካራ ዲስፕሊን ለድርጅቱ ትልቅ ጉልበት ሁኖታል። በዚሁ የተነሳ በኢትዮጵያ ያለው ማናቸውም የፖለቲካ እንቅስቃሴ በእርጋታና በጭምትነት ለማየት የረዳው ይመስለኛል።

 

4.      በመጨረሻም ኢትዮጵያውያን ተሰባስበው የተሻለ የፖለቲካ ድርጅት ባለመፍጠራቸው የተነሳ ህወሓት ባገሪቱ ምድር አሁንም ረጅም እድሜና ተጽእኖ ፈጣሪ ሁኖ እንዲቀጥል አድርጎታል።

የህወሓት ትንሣኤ

ባለፈው ጊዜ ህወሓት ከስልጣን አባረርነው፣ ድል ኣድርገናል ብለው ባንዲራቸውን ከፍ አድርገው ከፍ ባለ ድምጽ የፎከሩና የሸለሉ አሁን የት አሉ? ቆይቶ ሲታይ ክልላቸው እንኳ በትክክል መምራት የማይችሉ ድኩማን ሁነው ተገኝተዋል።

ጨዋታው ኣልቋል [Game Over] ያለው ኢሳያስም አሁን ስልጣኑን ለማስጠበቅ በጭንቀት ላይ ነው።

27 አመት ጨለማ ነበር ያለው አብይም እንኳን የተሻለ ሊያመጣ ቀርቶ የነበረው ብርሃንም በራሱ አመራር ድክመት ምክንያት ስለጠፋበት እየተደናበረ ይገኛል።

ሌላው ጊዜው ራሱ ከህወሓት የወገነ ይመስላል

 አብይ በራሱ ድክመት ከጊዜ ወደ ጊዜ በህዝብ የነበረው አሜኔታ እተሸረሸረ ይገኛል። በሃጫሉ ሞት ምክንያት በኦሮሞ ቤት በጣም ተጠልተዋል። ህወሓትና ኦነግ ሃጫሉን እንደገደሉ አድርጎ ለህዝቡ ቢደሰኰርም የኦሮም ልብ መግዛት አልቻለም። ይህ ክስተት ለህወሓት ትልቅ የፖለቲካ ትርፍ ሲሆን ለአብይ ግን ትልቅ ኪሳራ ነው! የአማራ ፖለቲከኞችም ቢሆኑ ወያኔ እንዲያጠፋላቸው ብቻ ነው የሚደግፉት እንጂ አገር የመምራት ብቃት እንደሌለው ከጥዋቱ አይተውታል።

የህወሓት ጥበብ ጠላትን በደንብ መገምገምና ከዚያ በኋላ ከህዝብ እንዲነጠል መስራት ነው። ጠላቱን ከህዝብ መነጠሉን ሲያረጋግጥ ሰይፉን ከአፎቱ ይመዛ።

አብይ አሁን በመድረቅ ላይ የሚገኝ ኩሬ ውስጥ የሚኖር አሳ ይመስላል። ውሃው እያለቀ ሲሄድ አሳው በቂ አየር ስለማያገኝ መወራጨት ያበዛል። የምናየውና የምንሰማው የየቀኑ ጭሆትም ሆነ ርግማን ከዚሁ የተነሳ ነው። ከእንግዲህ አብይ ተረት የሚሆንበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም። ህወሓት ግን አሁንም ከማናቸውም ጊዜ በላይ ተጠናክሮ ወጥተዋል። ጠላቶቹም እግሩ ላይ እንደወትሮም ይወድቃሉ። ህወሓት አሸናፊ ጠላቶቱም ተሸናፊ አድርጎ አሁንም ታሪክ ይዘግበዋል። የወድቆ መነሳት ምስጢርም ግቡ ማሸነፍ መሆኑን ይነገራ!

ህወሓት አሁንም ያገሪቱ መሪ የጨበጠ ይመስላል

የፌደራሊስት ሃይሎች አሁንም ህወሓት ያገሪቱ ሹፌር እንዲሆን ይፈልጋሉ ።

ሂደቱ የሚያመለክተው አሁንም ህወሓት የአፍሪቃ ቀንድ ፖለቲካ የሚዘውር ይመስላል።

መገለጫው ምንድነው ለሚለው፡

1.      አብይ በራሱ ጅልነትና በተከታዮቹ እውቀት ማነስ ወደ መቃብር እየወረደ ይገኛል።

2.      ኢሳያስም እጣ ፈንታው ከአብይ ህልውና የተሳሰረ ስለሆነ ከመሞት አይድንም።

3.      በኢትዮጵያና በአፍሪቃ ቀንድ አካባቢ እንደ ህወሓት ጥንካሬና ልምድ ያለው ድርጅት የለም።

ኣብይ አሁን ተደላድሎ እንዳሰበው መግዛት እንደማይችል የገባው ይመስላል። ያለው ምርጫ ወይ እስከ መጨረሻ ጉልበት ተጠቅሞ መግዛትና ሲሸነፍ መሸሽ ወይም ካሉት የፖለቲካ ድርጅቶች ተነጋግሮ መፍትሄ መፈለግ ነው።

 

 

 


Back to Front Page