Back to Front Page

የብልጽግና የቀብጸ ተስፋ እርምጃ ግብአተ መሬቱን ከማፋጠን የዘለለ ተጽእኖ አያመጣም

የብልጽግና የቀብጸ ተስፋ እርምጃ ግብአተ መሬቱን ከማፋጠን የዘለለ ተጽእኖ አያመጣም

በስዒድ መሐመድ 10-05-20

ባለፉት ዓመታት በተከታታይ የፈጠራ ትርክቶች የትግራይን ህዝ ከሌሎች ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ለመነጠል አሁን ራሱን ያነገሰውና በትግራይ ህዝብ መካከል የኖሩ፣ በትግራይ ምድር የተማሩ፣ ከትግራይ ህዝብ ጋር የተዛመዱ የተዋለዱ የተጎዳኙ ሀሀሉም የማይክዱት አንድ እውነታ አለ። የትግራይ ህዝብ ፍጹም በኢትዮጵያውነቱ የማይደራደር፣ በትግራዋይነቱና በማንነቱ የማያመነታ፣ መብቱን ለማንም በማንኛው ችግር ላይ እንኳን ቢሆን አሳልፎ የማይሰጥ ኩሩ፣ ጀግና፣ አዛኝ፣ ርህሩህ፣ ታማኝ በጠቅላላው ወርቅ የሆነ ህዝብ ነው።

ይህ ህዝብ ሰላሙን ጠብቆ ኑሮውን ለማሸነፍ ደፋ ቀና ይላል። ይሁን እንጂ ያለ ስሙ ስም፣ ያለ ስራው ስራ፣ ያልሆነውን ምስል እየፈጠሩ ከሌላው የአገሪቱ ህዝቦች ጋር ለማጋጨት የብልጽግና ቡድኖች ብዙ ጥረዋል።

Videos From Around The World

ስልጣኔን በሃይ አስቀጥላለሁ በሚል ከፍተኛ ወታደራዊ ዝግጅት እያደረገ ያለው "መልከ ጥፉን በስም ይደግፉ" እንዲሉ ብልፅግና በሚል መልካም ስም የሚጠራው ከፋፋይ፣ ደም መጣጭ አምባገነን ቡድን ሕገመንግስቱን እስከነ ጭራሹ ቀዶ ለመጣልና ንጉሳዊ ስርዓትን ለመትከል አፍራሽ ተግባራቱን አጠናክሮ ቀጥሏል።

በተለይ ይየዚህን እኩይ ምግባ ተባባሪ አንሆንም ያለውን የትግራይን ህዝብና ሀወሓትን ለማንበርከክ ያልተማሰ ጉዱጓድ የለም። ህወሓት የትግራይን ህዝብ ከአምባገነኑ የደርግ የብቀላ ተግባር መከላከል የቻለችውና ለአብይ አህመድ ያልተንበረከከችው በህቡ ያላሳለሰ ጽናትና ድጋፍ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደስልጣን ከመጡበት ዕለት ጀምሮ በትግራይ ህዝብ ያልተሸረበ ሴራ የለም። አሁንም ድረስ በትግራይ ህዝብ መሪዎቹን በመምረጡ ሕግ ተጥሷል በሚል ከእውነት የራቀ ምክንያት አምባገነኑ መንግስት ወታደራዊ እርምጃ ለመውሰድ እየፎከረ ይገኛል።

እጅግ አሳኙ ነገር የክልሉን ሰላም ያስከበረ ህዝብ ፀረ ሰላም፣ ለሕገመንግስት የቆመን ህዝብ ኢሕገመንግስታዊ፣ 2 ነጥሸሸብ 7 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ወጥቶ ያካሄደው ምርጫ የጨረቃ፣ የጨረባ ምርጫ እና ሕገመንግስት የጣሰ በሚል ለማጣጣል ብሎም ለመሰረዝ መሯሯጥ እውነትም አብዲ ዒሌ አንድ ወቅት እንዳለው "ለቅሶው ከፍየሏ በላይ ነው" ፌዴራል ስርዓቱን በማፍረስ አሃዳዊ ንግስናን ማረጋገጥ ነው። በትግራይ ህዝብ ላይ የያዙትን የጥፋት እቅድ የማይቀይሩ የትግራይን ህዝብ ለመውጋት በጦር ሃይል ለማንበርከክ ያስችላል ያሉትን እርምጃ ሁሉ እየወሰዱ የመጡና በመጨረሻዋ ሰዓት ሞት አፋፍ ላይ ሆነውም የቀቢጸ ተስፋ እርምጃ ከመውሰድ ወደኋላ አይሉም ግን አይሳካላቸውም።

የቀን ህልም ቢሆንም ሕገመንግስትን ያፈረሰ አምባገነን መንግስ በሕግና በሕግ የሚጓዘውን የትግራይ ህዝብ በሃይ ለማንበርከክ ሲያሴረው የነበረውን ተግባር አጠናክሮ የራሱን የሞግዚት አስተዳደር ለትግራይ ለመመደብ ሽርጉድ እያለ ይገኛል።

ይህንን ሃይልን የመጠቀም እቅድ ሕገ-መንግስታዊ ስርዓቱን አደጋ ላይ በሚጥሉ አካላት ላይ እርምጃ ለመውሰድ ሕገ-መንግስታዊ መሰረት አለ በሚል የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አደም ፋራህ በይፋ የትግራይ ህዝብ ላይ ጦርነት አውጀዋል።

አፈጉባኤው ሃላፊነት በጎደለው መንገድ

ህዝብ የመረጠውን የትግራይን ሕግ አውጪና ሕግ አስፈጻሚ መታገድ አለበት ብለዋል። ይህ ግለሰብ የራሳቸውንና የመሰሎቻቸውን ስልጣ ከህዝብ ይሁንታ ውጭ ማራዘም አልበቃ ብሏቸው ለትግራይ ክልል ከፌዴራል መንግስት አስተዳዳሪ እንልካለን እያሉ ነው።

የፌደራል የፀጥታ አካላት በትግራይ ህዝብ ላይ በማሰማራት ክልሉን መቆጣጠር፣ ይህንን ተከትሎ ደግሞ ለፌደራል መንግስት ተጠሪ የሆነ ጊዜያዊ መንግስት ማቋቋም አለብን ሲሉ ጦርነት አውጀዋል።

ነገሩ "የሚሉሽን በሰማሽ ገበያም ባልወጣሽ" አይነት ነው። ህዝቡ ላይ ያለውን እውነታ አለመገንዘብ ወይም ሆን ተብሎ አገሪቱን መበታተን እንደሆነ ህዝቡ በውል ይገነዘባል።

እውነትም ይህ የአብይ አህመድ የንግስና ዘመን ዘመነ ግርምቢጥ ነው። እውነቱን ውሸት ውሸቱ እውነት የሆነበት፤ ነገሮች ሁሉ ተገለባብጠው የሚተረኩበት ያልሰራ የሚሞገስበት የሰራ የሚወቀስበት ዘመን ሆናል።

እስኪ በእውነቱ ከሆነ ሰላም የደፈረሰው ትግራይ ክልል ነው? አስራ ሰባት ባንኮች በጠራራ ፀሐይ የተዘረፉት በትግራይ ነው? 3 ሚሊዮን ህዝብ በሁከትና ግጭት ከቀየው የተፈናቀለው በትግራይ ነው? በአስር ሺዎች በእስር የተዳረጉት ትግራይ ውስጥ ይሆን? ሰው በብሄሩ ምክንያት ተዘቅዝቆ የተሰቀለው በትግራይ ምድር ነው? በየቀኑ ቀይ ሽብር በኦሮሚያ ወጣቶች ላይ እየፈፀመ ያለው ህወሓት ይሆን? የወላይታን ንፁሓን ዜጎች በጠመንጃ እየፈጀ ያለውስ ማን ነው?

ሰዎች በብሄራቸው ምክንያት ከመንግስት ስራ እንዲባረሩ

ለበርካታ ዓመታት ወልደው ድረው ከኖሩበት ቀየ ንብረታቸው እየተዘረፉ እዲሰደዱ የተደረገው በትግራይ ይሆን? ይህ ሁሉ የፈጸመው ህወሓት የተፈጸመው በትግራይ ከሆነ እንደሚትሉት ህወሓት ይሰቀል ብለን በፈረድን ነበር ዳሩ ግን ይህነን ያደረገውና እያደረገ ያለው በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የሚመራው ብልጽግና ነው።

በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በሶማሊያ፣ በአፋር፣ በወላይታ እና በሲዳማ ህዝብ ላይ የተፈጸመውና አሁንም የቀጠለው ኢሰብኣዊና ኢሕገመንግስታዊ ድርጊት በጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድና በብልጽግና ቡድን የተፈጸመና አሁንም የቀጠለ ነው። ስለሆነም ሁለቱ ይታነቁ እንጂ "የአብየን ወደ እምየ" የሚለው አባባል ውሃ አይቋጥርም። አይሰራም።ለዚህ ደግሞ ፈራጁ ህዝብ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ በየአካባቢው ድምጹን እያሰማ ነው።

የብልጽግና ቡድን አይመራንም ህገወጥ ቡድን መሆኑን በግላጭ እየመሰከረ ነው። በዛሬው በኢረቻ በዓል በአዲስ አበባ አብይ ገዳይ ነው ስልጣኑ ይልቀቅ አይመራንም የታሰሩ ፖለቲከኞች ይፈቱ ድምጻቸው ለዓለም ህዝብ አሰምተዋል። አዎ ብልጽግና ከመስከረም 25 ቀን 2013 ዓም በኋላ ህጋዊም ሞራላዊ ቁመና አይኖረውም። የቀብጸ ተስፋ የመጨረሻ እርምጃ ለመውሰድ እንዳቀደ በአፈ ጉባኤው በኩል መልእክቱን አስተላልፏል። የብልጽግና የቀብጸ ተስፋ እርምጃ የአብይ አህመድንና የአጃግሬዎቹን ግብአተ መሬት ከማፋጠን የዘለለ ተጽእኖ አያመጣም።

Back to Front Page