Back to Front Page

የብልፅግና ፓርቲ የሞራልና የፖለቲካ ዝቅጠት

ብልፅግ ፓርቲ የሞራልና የፖለቲካ ዝቅጠት

የሞራል ዝቅጠት ጥልቀቱ የት ድረስ ነው? ጥላቻና የስልጣን ጥም ጥጉስ የት ነው?

 

ፋቶ 26/05/2020

 

የኢትዮጵያ የረጅም ልብወለድ ድርሰት ፈር ቀዳጅ ተብለው በመሃል ሃገር ልሂቃንየሚንቆለጳጰሱት አፈቄሳር አፈወርቅ ገብረየሱስ በጦቢያ መፅሃፋቸው የትግራይን ህዝብ ክብር ለመንካት የሚያውቁዋቸውን ፀያፍ ቃላት ሁሉ ተጠቅመዋል። አፈቄሳር ተብለው የተሰየሙት ሃገራቸውን ኢትዮጵያን ክደው በባንዳነት ለወራሪው የጣልያን ቅኝ ገዥ መንግስት በማደራቸው በጣልያኑ ንጉስ ኡምቡርቶ የተሰጣቸው ሹመት ነው። ጦቢያን የፃፉትም የአፄ ምኒልክን ልብ ለማራራትና ምህረት ለማግኘት በገፀበረከትነት ያቀረቡት ወራዳ ስራ ነው። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ (በፊትም ቢሆን ) በተፃፈና በተሰነደ መልኩ ትግራይንና ህዝብዋን ለማዋረድና አንገት ለማስደፋት በገዥ መደቦች የተደራጀና ተከታታይነት ያለው ሰፊ የስም ማጥፋትና የውንጀላ ፕሮፖጋንዳ ተካሂዷል። የስም ማጥፋትና ታሪኩን የማዛባት ዘመቻው በተራ ግለሰቦች ብቻ የተወሰነ ሳይሆን የመንግስታቱ ቁንጮ መሪዎች፣ ፊደል በቆጠሩ ምሁራን ጭምር ነው። የቅርብ ጊዜ ክስተቶችን ብቻ ብንመለከትየኮሎኔል መንግስቱ ኃ/ማሪያም ትግራይ ለጠመኔ የማትበቃ ድሃ ከሚል እስከ የዘመኑ ፕሮፌሰሮችና ጋዜጠኞች ተጋሩን ካንሰር ብለው በአደባባይ በሰነድና በሚድያ የሰነዘሩት ዘረኛና ነውረኛ ዘለፋዎች መጥቀስ ይቻላል።

Videos From Around The World

ከዚህም በተጨማሪ ታሪኩን ለማዛባት፣ ለማደብዘዝ ብሎም ለመሰረዝ ሲቻላቸው ደግሞ ለመንጠቅ እጅግ በርካታ ፀረ ህዝብ ድርጊቶች በትግራይ ህዝብ ላይ ተፈፅመዋል። ዘመቻና ዝርፊያ ተካሂዶበታል። ርስቱን በተለያየ ጊዜ ተቆርሶ ተወስዶበታል። እንደሁለተኛ ዜጋ ተቆጥሯል። እነዚህን ሁሉ በደሎች ግን አሜን ብሎ ተቀብሎ አያውቅም። ያለምንም ተስፋ መቁረጥ ታግሏል። ጠላቶቹንም ብዙ ጊዜ አሳፍሮ መልሷል። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ታሪክ ይቅር በማይላቸው ከአብራኩ በወጡ ባንዳዎች አሻጥር በርካታ በደሎች ተፈፅመውበታል ኪሳራ አስተናግዷል። ከታሪክ የማይማሩ ጥቂት ሆድ አደር ስልጣን ፈላጊ ወይም ከአፍንጫቸው አርቀው የማይመለከቱ በግል ቂምበቀል የሰከሩ ባንዳዎች አሁንም ከጠላት ተሰልፈው ትግራይን ለመውጋት እየተውተረተሩ ይገኛሉ።ነገር ግን ታሪክ ምስክር ነው ይዋረዳሉ ይጠየቃሉም።ፀሃፊው ከዚህ ቀደምበፃፈው የግል አስተያየትስለ ክህደትና ከሃዲ/ባንዳ ምንነትና በዓላማና በሃሳብ የተለየ አቋም መግለፅና ማራመድ ያለውን ልዩነት በግልፅ ለማስቀመጥና ለማስጠንቀቅ ሞክሯል። መተሳሰሪያዉን (ሊንኩን)በመጫን መመልከት ይችላሉ።

የትግራይ ህዝብ ይህንን ሁሉ የረጅም ጊዜ ውጣውረድ በፅናት አልፎ በተለያዩ ወቅቶች ባደረጋቸው መራራ ትግሎች የሚገባውን መስዋእትነት ከፍሎ ራሱን በራሱ የሚያስተዳድርበት መብት ተጎናፅፏል። የትግሉ ውጤትም ከራሱ አልፎ ለሌሎች ጭቁን የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ተርፏል። ሆኖም ግን መንግስትን ሲመራ የነበረው ኢህአዴግ በተለይ ባለፉት 8 ዓመታት በራሱ ውስጥ በተፈጠረው ዝቅጠትና ብልሹነት በመራራ ትግል የተገኘውን ተነፃፃሪ ሰላም፣ ልማትና ዴሞክራሲ ከሃዲዱ ወጥቶ ወደ ጥፋት አምርቷል። በውስጡ የበቀሉ ቅንቅኖች እየተበላና በውጭ ሃይሎች ድጋፍና ትብብር እየተገፋ ራሱን በራሱ ጠልፎ ሊወድቅ ችሏል። ከዚህ ውድቀትም ብልፅግና የሚባል በጥቂት ቡድኖች የሚዘወር እጅግ አደገኛ የሆነ ፓርቲ በአቋራጭ ስልጣን ላይ ቁጢጥ ብሎ ሃገር በማተራመስ ላይ ይገኛል። ኖአም ቾምስኪ (Noam Chomsky) በአሜሪካ ነጭ ቤተመንግስት (White House) ያለውን ሃይል ለመግለፅ የተጠቀመበትን ሃረግ የአራት ኪሎው ቡድን በትክክል ይገልፀዋል። እጅግ አደገኛ የተደራጀ ነውጠኛ/ወሮበላ/ማፊያ ቡድን!The Most Dangerous Gangster Group!በስልጣን ላይ ያለው ቡድንና አጫፋሪዎቹ ትግራይንና ተጋሩን ለማንበርከክ፣ ለማዋረድና በትግሉ ያረጋገጣቸውን መብቶች ለመደፍጠጥ ያልፈነቀለው ድንጋይ የለም። ለመጥቀስ ያህል፤

         የትግራይ ተወላጆች በማንነታቸው ምክንያት ተፈናቅሏል፣ ንብረታቻው ተዘርፏል፣ ተገድሏል፣ ታስሯል፣ ከመንግስት ስራ ተባሯል እንዲሁም በሃገሩ ተንቀሳቅሶ እንዳይሰራ ተሰናክሏል።

         በዘር ማጥፋት ወንጀል ሊመደብ የሚችል በመንግስት የታቀደና የተቀነባበረ በትግራይ ህዝብ ላይ ያነጣጣጠር የጥላቻና የሃሰት ሰነዳዊ ወይም ዶኩመንታሪ ሰነድ በማዘጋጀት በሁሉም የመንግስትና የፓርቲ ዋና ሚዲያዎችና ማህበራዊ ትስስር ገፆች በማሰራጨት ህዝቡን ለአሰቃቂ የዘር ማጥፋት ወንጀል አደጋ አጋልጦታል። እንደ ኢትዮጵያ ህዝብ አስተዋይነት ባይሆን ኖሮ በትግራይ ህዝብ ላይ ከፍተኛ ሊባል የሚችል የዘር ማጥፋት ወንጀል ይፈፀም ነበር። ነገር ግን በህዝቡ አስተዋይነት ብቻ ሊከሽፍ ችሏል።

         የትግራይን ህዝብ በረሃብ ለመቅጣት በጥቂት የሰከሩ ወጣቶች ድርጊትና በአንዳንድ ባለጌ ፖለቲከኞች አስተባባሪነት ክልሉን ከመሃል ሃገር የሚያገናኘው ዋናውን አውራ ጎዳና እንዲዘጋ አድርጓል። የተዘጋው መንገድ እንዲከፈትም ፍላጎት አላሳየም። ይልቁንም በአፋር በኩል ያለውን መንገድ ለማዘጋትም ተሞክሮ ሳይሳካ ቀርቷል። አንድን ህዝብ በሆዱ በጠኔ ለመቅጣትና ለማንበርከክ አደገኛ ኢሰብአዊ ድርጊት ለመፈፀም ተሞክሯል።

         የትግራይን አመራሮች ለመቀንፀል፣ ለማሰር ወይም አስገድዶ ስልጣኑን ለመቆጣጠርና በሌሎችም ክልሎች እንደታየው በራሱ ምስለኔ ለማስተዳደር እንዲችል የተመረጡ ኮማንዶዎች አሰማርቶ ያልተሳካ ሙከራ አድርጓል።

         የትግራይ ክልል በጀት ቆርጧል፣ የልማት ፕሮጀክቶችን አደናቅፏል፣ ኢንቨስተሮችና ዲፕሎማቶች ክልሉን እንዳይጎበኙ በተደጋጋሚ ከልክሏል።

         የአራት ኪሎው ቡድን የመከላከያ ሰራዊቱን እንደፈለገው ለማሽከርከርና የጥፋቱ ፈፃሚ እንዲሆን፣ ሰራዊቱ ህገ መንግስቱን የመጠበቅ ተልዕኮዉን በነፃነት እንዳይወጣና የራሱን አሻንጉሊት ለማድረግ የነበረውን ዕቅድ እንቅፋት ይሆናል ብሎ የፈራውና የትግራይ ህዝብ ትግል ከፈጠራቸው ምርጥ የጦር ሜዳ ጀግና የሆነውን ጀ/ል ሰዓረንና ሌላው ጀግና ታጋይ ሜ/ጀ/ል ገዛኢ አሰፋን እንዲገደሉ ተደርጓል። የወንጀሉ ዋና አስተባባሪዎችም እንዳይጠየቁ የወንጀል ድርጊቱ ደብዛው እንዲጠፋ ሆነዋል

         በቅርቡም ትግራይ ህገመንግስታዊ መብቷም ግዴታዋም የሆነውን ምርጫ እንዳታካሂድ የሃይል ርምጃ ለመውሰድ ዝቷል። ለልማትና ለሰላም ያላደረገውን ሙሉ ዝግጅት ማድረጉንም በድፍረት ደንፍቷል የሚሰማውም የሚፈራውም የለም እንጂ።

         በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ የኢትዮጵያን መልካም ከማይመኙ የውጭ መንግስታት ጋር በማበርና በመመሳጠር በትግራይ ላይ የደህንነትና የፀጥታ ስጋት ፈጥሯል።በነዚህ ቅጥረኛ ሃይሎችም ጥቃት ለመሰንዘር ሞክሮ በህዝቡ ንቁ ተሳትፎና በፀጥታ ሃይሉ ከሽፎበታል።

         በተለያዩ ወቅቶች የአማራ ክልል መረንየለሽ ደካማ ታጣቂ ሃይል በክልሉ እውቅና እና በአንዳንድ ግብዝ አመራሮች አስተባባሪነት በትግራይ ሉዓላዊ ግዛት ላይ ወረራ ለመፈፀምና ህዝቡን ለማበሳበስ ተሞክሮ በትግራይ ህዝብና የፀጥታ ሃይል ድባቅ ተመቶ አንዳንዴም ፎክሮና ፎቶ ተነስቶ ተንኩሶ ተመልሷል። ሰፊው የአማራ ህዝብም የጥፋታቸው ተባባሪ ላለመሆንም ለማከላከልም ጥረት አድርገዋል።

ጥቃቱና ትንኮሳው ተዘርዝሮ አያልቅም። ለህዝቡ ይፋ ያልተደረጉ ወይም ያልተነገሩ በርካታ በደሎችና ጥቃቶች እንደሚኖሩ ግልፅ ነው። በተለይ ደግሞ በመንግስትና ፓርቲው በሚቆጣጠራቸው ሚዲያዎች በሁሉም አውታሮቻቸው እንዲሁም ፓርቲው በሚደጉማቸው ማህበራዊ ሚዲያዎች እና የተለያዩ የትምክህት ሃይሎች ስር በሚገኙ የመገናኛ አውታሮች የሚነዙት በሬ ወለደ የሃሰት ዘመቻዎች ግርምትን የሚያጭሩ የመንግስትንና የፓርቲውን የሞራል ዝቅጠትና ብልሹነት ፍንትው አድርገው የሚያሳዩ ናቸው። ይህ ለኢትዮጵያውያን ባህል ባዕድ የነበረ ነገር ግን እያገነገነ የመጣ እንደሃገር የደረስንበት የዝቅጠትና የውርደት ጠርዝ የሚያሳይ ነው። የብልፅግና ፓርቲና የመሪው አብይ አህመድ ግልብና ልጓም የለሽ የስልጣን ጥምና ስግብግብነት የደረሱበትን የዝቅጠትና የወራዳነት አረንቋ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ድርጊት ግንቦት 16 ቀን 2012 ዓ/ምበትግራይ ላይ ሆን ተብሎ የተፈበረከ ሃሰተኛ የተቀናጀ የሚዲያ ዘመቻ ተካሂዷል። በሚያሳዝን ሁኔታ ሙከራቸው በአጭሩ ከሽፏል። ነገር ግን የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም እንደሚባለው ቡድኑና አጫፋሪዎቹ ቅንጣት የሞራል እንጥፍጣፊ ስለሌላቸው ሃፍረትም ይሉኝታም የሌላቸው ውዳቂዎች ስለሆኑ መሞከራቸው የማይቀር ነው።

የሞራል ወይም ምግባር ብልሹነት ጥልቀቱ ምን ያህል ነው? የስልጣን ጥማትና ስግብግብነትስ ዳርቻ አለው? ራሱን በራሱ ለማስተዳደር ህገመንግስታዊ መብት ያለው ምንም ያላጠፋ ህዝብና ክልል ለማጥቃት ሰበብ ለመፈለግ ወይም ስም ለማጥፋት ይህን ያህል የወረደ ተራ ዘመቻ ማካሄድ የመንግስትነት ክብርና ሃላፊነት በስህተት ወድቆበት የተሸከመው የአራት ኪሎው ቡድንና አጫፋሪዎቹ ከንቱነትና የፖለቲካ ገልቱነት ገሃድ ከማድረግ ያለፈ ሌላ ፋይዳ አይኖረውም። ለታሪካዊ ትዝብት ግን ያጋልጣል። የማይነጋ መስሎዋት ምኗን ቋት ላይ አደረገች እንደሚባለው ነው። ጠያቂና ፈራጅም ወይም ፍትህ ሰጪ ቢኖር ኖሮ ይህ ድርጊት በህግ የሚያስጠይቅ አደገኛ የወንጀል ድርጊት ነው። ነገር ግን ራሱ ቀማኛ ራሱ ዳኛ በሆነበት ዘመን ፍርዱን ለጊዜው ለህዝብና ለታሪክ መተው ይበጃል። የትግራይ ስራ ጥቃቱን መከላከል፣ ማክሸፍ፣ ገፍቶ ከመጣም በተለደው መንገድ መመከትና ድል ማድረግ ነው። ብልፅግና ፓርቲና ጭፍሮቹና አጋፋሪዎቹ በትግራይና በተጋሩ ላይ ከፈጸሙዋቸው ይቅር የማይባሉ ወራዳና ሃፍረት የለሽ ፀያፍ ድርጊቶች በጥቂቱ እንሆ፤

         ትግራይ ውስጥ የአንድ ሰው በፖሊስ የችግር አፈታት አቅም ማነስ ወይም በሌላ ድክመት የአንድ ሰው ህይወት ማለፍ ለኛ ለተጋሩ ለሰው ህይወት ካለን ክብርና ዋጋ አንጻር የሚያምና የሚያስከፋ ቢሆንም በቀን በብዙ አስሮች በፀጥታ ሃይል በሚገደሉባት ሃገር በመንግስትና በፓርቲ፣በዋና ዋና ሚዲያዎች የተጋነነ መግለጫ ማውጣት ነገር ግን በተመሳሳይ ሳምንት በደቡብ እና በኦሮሚያ ክልል የተፈፀሙ ግድያዎች እንዳልሰሙ ጆሮ ዳባ ልበስ ማለት ከተራ ውንብድና የተለየ አይደለም። በዚህ አጋጣሚ የትግራይ ሚዲያዎች ያለምንም መሸፋፈን መዘገባቸው በለውጥ ላይ መሆናችንን ይመሰክራል። ክልሉም ድርጊቱን በአግባቡ አጣርቶ ለተጎጂዎች ፍትህ እንደሚሰጥ ይጠበቃል። ለሟች ቤተሰብም ፈጣሪ መፅናናትንና ብርታትን ይስጥልን።

         የቆዩና ለሌላ ዓላማ የተደረጉ የሃገር ውስጥና የውጭ ሃገር አመፅ ወይም ሰልፍ ፎቶግራፎችን በማከም እጅግ በወረደ የማመሳሰል ቅጥፈት በትግራይ እንደተፈፀመ አድርጎ የሃሰት ዘገባ በሁሉም የፈደራል መንግስት፣ የአማራ ክልል፣ የብልፅግና ፓርቲ፣ አንዳንድ የኦሮሚያ እና አጫፋሪ ሚዲያዎች (ኢሳት፣ አባይ፣ ዘሐበሻ ወዘተርፈ) በተመሳሳይ ሰዓት አንድ ዓይነት የሃሰት ዘመቻ ከፍቷል። ይህ ተራ ወንጀል ሳይሆን መንግስታዊ ሽብር ነው። ከተገባው የመለወጥ ቃልና ተስፋ አንፃር ምንኛ ያስተዛዝባል? ህዝብ ዝም ቢልም ይታዘባል ጊዜው ሲደርስም ይፈርዳል። የመንግስትና የፓርቲ ቱባ ግን ዱባ (ያውም የበሰበሰ)ባለስልጣናት ስሜታቸው ዋጥ ማድረግ አቅቶዋቸው የተጭበረበሩ ፎቶዎችና መልእክቶች በየማህበራዊ ትስስር ገፃቸው መለጠፋቸው ምን ዓይነት የሞራል ዝቅጠት፣ ግራ መጋባትና ቀውስ ውስጥ መሆናቸውን ያሳያል። በትግራይ የወረዳ ዋና ከተማ ጥያቄ አንግበው መብታቸውን በሰላማዊ መንገድ መጠየቃቸው ትግራይ እንደተናወጠ አድርጎ የሃሰት ዘገባ ማቅረብ በተቃራኒው ግን የሲዳማ፣የወላይታና የበርካታ ዞኖች ያልተመለሱ የክልልነት ጥያቄዎች፣ የሶማሊ ክልል ም/ቤት ትርምስና አሁንም ያልበረዱ የተለያዩ ደም አፋሳሽ ግጭቶች ትንፍሽ የሚል ሚዲያ የለም።

         እጅግ ወራዳ የሚያደርገው ደግሞ የ ETV የከሸፈ ሙከራና ኪሳራ ነው። የትግራይ ህዝብ የራሱ መንገድ ይፈልጋል እንጂ ብልፅግና ፓርቲን ለእርዳታ ከቶ አይጠይቅም። በምስለኔ ወይም በባንዳዎች ከምኒሊክ ቤተመንግስት እንተዳደር አይልም። ባህሉም አይፈቅድለትም። ይህንን ያዘጋጀው ጋዜጠኛ በምን ዓይነት የስነ አእምሮና የህሊና ቀውስ እንደሚኖር አያጠያይቅም። ሌላውን መዋሸት ቢቻል ህሊናንና ፈጣሪን ማታለል አይቻልም። ምናልባትም ለክፉ ደዌ እንዳይጋለጥ ወይም በራሱ ላይ ሌላ ርምጃ እንዳይወስድ ጥበቃ ሊደረግለት ያስፈልገው ይሆናል። ጤነኛ ወይም ሙሉ ሰው ከሆነ ማለቴ ነው።

         ጭር ሲል አልወድም ዓይነት ለምን ትግራይ ሰላም ሆነች? ህወሓት ለምን አልሞተችም ወይም ለምን በትግራይ ህዝብ ቅቡልነት አገኘች? ዓይነት ሸውራራ የክፋት አተያይ የትም አያደርስም ተያይዞ ገደል መግባት ካልሆነ በስተቀር። ይህ ጠፍቶ የማጥፋት ድርጊት የትግራይ ህዝብ አይቀበለውም። እንዲህ ያለ ጭለማ መንገድ በደርግ ጊዜም አክሽፎታል።

እነዚህንና ሌሎች መሰል አፀያፊ ጥፋቶች ሃገርን አስተዳድራለሁ ከሚል መንግስት በራሱ ህዝብ ላይ ሲፈፅም ያውም እጅግ ተራ በሆነ የማጭበርበርና የሃሰት ድርጊት የሌ/ኮሎኔል አብይ አህመድና ጋሻጃግሬዎቹ የሞራል ቀውስና ዝቅጠት እንዲሁም ወሰን አልባ የስልጣን ፍላጎትና ስግብግብነት የደረሰበትን የመጨረሻ ደረጃ ያረጋግጣል። የፈረንጅ ቋንቋ የበለጠ ይገልፀው እንደሆነ deep desperation, degraded morale, confusion and frustration የሚሉትን ይገልፁዋቸው ይሆናል። እንደዚህ ዓይነት የአስተሳሰብና የስነልቦና ደረጃ የወረደ ሰው ወይም ቡድን ደግሞ ለመዋሸት፣ ለማታለል፣ ትላንት የተናገረውን ወይም ያደረገውን ሽምጥጥ አድርጎ ለመካድ፣ ያላደረገውን ፈፀሜዋለሁ ብሎ ለመዋሸት፣ በአንድ ራስ ሁለት ሶስት ኧረ ብዙ ምላሥለመሆን ወዘተ የማያፍር የበሰበሰ ነው። ጂ. አማረ የተባሉ ፀሃፊ Gaslightersበሚል ግሩም መጣጥፋቸው የገለፁዋቸው ባህሪያት የአራት ኪሎውን ቡድንና አጫፋሪዎቹን በደንብ ስለሚገልፃቸው አንባቢያን ፅሁፉን ቢመለከቱት የበለጠ ግንዛቤ ሊያገኙበት ይችላሉ።

የዚህ ፅሁፍ ዋና ዓላማ መንግስት የሚያደርጋቸውን ጥፋቶች ለመዘርዘር አይደለም ምክንያቱም አንድም የሚታወቁ ስለሆነ ሁለትም እነሱ ለፈጠሩት አጀንዳ ምላሽ ለመስጠት አታካራ ውስጥ መግባት አስፈላጊ ስላልሆነ።። ለምን ቢባል ጭራ በመከተል ጠላት በዘረጋው ወጥመድ መግባት ስለሆነ ጥቅም የለውም። ዋናው ጉዳይ ሌ/ኮ/ል አብይ፣አጫፋሪዎቹና ቅጥረኞቹ ይህንን ቅጥፈት የሚያከናውኑት ለምን ዓላማ ነው የሚል ነው። መንግስት በከፍተኛ የቅቡልነት ቀውስ ይገኛል። ከመስከረም 25 2013 በኋላ ሊመጣ ስለሚችል የፖለቲካ ሁኔታም ለመገመት አስቸጋሪ ሆኗል። ኤኮኖሚው ቁልቁል እየተምዘገዘገ ይገኛል። የትግራይ ምርጫ የማካሄድ አጀንዳ ለሌሎች ምሳሌ እንዳይሆን ስጋት ፈጥሯል። የኤርትራው አምባገነን ገዢ የህወሓት እየተጠናከረ መሄድ ወይም ቢያንስ የጠበቁትን ውድቀት (Gameover) መክሸፉ ያበሳጫቸዋል። ደጋፊዎቻቸው ጭምር የሰውየው ያለመታመንና አቅመቢስነትን ላለመቀበል ተበሰጫጭተዋል። ስለዚህ የዘመቻው የአጭር ጊዜግብ የአራት ኪሎው ቡድን ካጋጠሙት ቀውሶች ለመወጣትና ስልጣንን በማራዘም ኢህገመንግስታዊ የፖለቲካ ፍላጎታቸውን ለማሳካት ሲሆንበሌላ ወገን ደግሞ የኢሳያስ ትግራይንና ወያኔን የማንበርከክ የእብሪት ህልም ለማሳካት ትግራይን መበጥበጥ የጋራ አጀንዳ ለማድረግ ነው። አይሳካም እንጂ የድርጊቱ የመጨረሻ ግቡ ሊከሰት የሚችለውን በሃሰት ላይ የተመሰረተ የፀጥታ አለመረጋጋት እንዳለ በማስመሰል የህዝብ ጥያቄ ቀርቦልኛል በማለት ወይም በህዝብና መንግስት መካከል አለመተማመንና ክፍፍል በመፍጠር ጣልቃ ለመግባትና ህወሓትን በመምታት ክልሉን በቁጥጥር ለማድረግ ነው። ይህንን ተፈፃሚ ለማድረግም ዘመቻው የሚከተሉት ዓላማዎች ሊያካትት ይችላል።

1.   በፀጥታ መጓደል እንዲሁም በቅርቡ በሚጠበቀው የህገመንግስት ትርጉም ውሳኔ የክልሎች ምርጫ የማካሄድ መብት በአስቸኳይጊዜ አዋጅ ወይም በሚሰጠው የትርጉም ብይን በማሳበብ የትግራይን ምርጫ ማደናቀፍና ለሌሎች ክልሎችም ማስተማሪያ ማድረግ

2.   የትግራይ ክልል መንስታዊ መዋቅር በብልፅግና ፓርቲ ስር በማዋል ትግራይን ማንበርከክ ወይም የፖለቲካና የደህንነት ቀውስ ውስጥ ማስገባት ብሎም ሃገሪቱን በማን አለብኝነት በፈላጭ ቆራኝነት ሰጥለጥ አድርጎ መግዛት

3.   ከቻለ በህወሓት ውስጥ ስንጥቅ በመፍጠር እርስበርሳቸው እንዳይግባቡ በማድረግ የህዝቡን አንድነት መሸርሸር

4.   ትግራይን ከሌሎች ክልሎች እንዲሁም ህወሓትን ከሌሎች ፓርቲዎች በመነጠል ለጥቃት ማጋለጥ ከተቻለም ህጋዊ የሚመስሉ ህገወጥ ተግባራትን በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት በማፀደቅ የኢኮኖሚ፣ የንግድ፣ የትርንስፖርት፣የመብራት፣የውሃ፣ የባንክና መሰል አገልግሎቶች በማቋረጥ ተፅእኖ መፍጠር ህዝቡም እንዲያምፅና እጁን እንዲሰጥ አቅሙ የፈቀደውን መሞከር በዚህም የፀጥታ ችግርን ሰበብ አድርጎ ጣልቃ መግባት

5.   የግንቦት ያሃ በዓል ህዝቦች እንዳያከብሩት እንዳያስተውሱት አጀንዳ የማስቀየስ ጎናዊ ዓላማም ሊኖረው ይችላል ምክንያቱም ሌላው የረጅም ጊዜ ፍላጎታቸው የትግራይ ህዝብና የወያኔ ሌጋሲ ቀርፎ ማስወገድ ወይም በአምባገነኑ ኢሳያስ አፈወርቂ ምኞት የፖለቲካ እጥበት ማካሄድ።

በትግራይ ህዝብና ክልል በኩል ጣልቃ ገብነትን ለመከላከል ባላቸው የረጅም ጊዜ ልምድና ዝግጁነት እንዲሁም ህዝቡ ካለው ራስን በራስ የማስተዳደር ፅኑ እምነትና አቋም የአብይና ጭፍሮቹዓላማ የመሳካት ዕድል የለውም። ነገር ግን ሃፍረት የሌለው፣ የሞራል እንጥፍጣፊ የራቀውና ቀውስ ውስጥ በመግባት ላይ የሚገኝ አደገኛና ለስልጣን ሲል አቅሙ የፈቀደውን ሁሉ ለማድረግ ከመሞከር ወደኋላ የማይል ሃይል በቀጣይ በሌላ ዘዴ ሙከራ ማድረጉ ስለማይቀር ሁሌም የትም በተጠንቀቅ መጠበቅ የግድ ይላል። ቡድኑ እስካልተወገደ ድረስ ጥፋት ለመፈፀም ወደኋላ አይልም። ሊያስቆመው የሚችለው የትግራይ ህዝብ የማይበገር ፅኑ አንድነት፣ የክልሉ መግስት ዙሪያ መለሽ የመመከትና አስፈላጊሆኖ ሲገኝም የማጥቃት አቅም (ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ዲፕሎማሲያዊ፣ ወታደራዊ፣ ቴክኖሎጂያዊ እና የመረጃ)፣ ከሌሎች ደጋፊ ሃይሎች ያለንን ትስስር/አጋርነት እና ብቃት ያለው አመራር ሰጭነት በተደራጀና በተናበበ መልኩ በቦታው ሲኖር ሲሆን እነዚህ አቅሞች በየወቅቱ የሚዳብሩ መሆን ይኖርባቸዋል። ይህ ጥቃቱ ለማክሸፍ የሚደረግ ጊዝያዊ ወይም ታክቲካዊ ምላሽ ሳይሆን ብቻ ሳይሆኑ ከረጅም ጊዜ ዘላቂ ጥቅሞችና አማራጭ መፍትሄዎች መቃኘት ይገባል።

በርግጥ የጥቃት ሙከራው የትግራይን ህዝብ ስነልቦናና ስብእና ጠንቅቆ ካለመረዳት ወይም ጭፍንነት የሚመነጭ ነው። በመሆኑም ቡድኑና አጫፋሪዎቹ ምንም ቀዳዳ እንዳያገኙ ህዝቡ በላቀ አንድነት፥ የክልሉ መንግስትና ህወሓት ደግሞ በከፍተኛ የዓላማ አንድነትና ፅናት ከመቼውም ጊዜ በላይ በፅናት መቆም ይኖርባቸዋል። የሲቪል ሰርቪሱና መንግስትም ሰላም፣ ልማት፣ ዴሞክራሲ፣ መልካም አስተዳደርና የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ጎን ለጎን በማስኬድ ህዝቡ የመስዋእትነቱንና የድካሙን ተጠቃሚነቱን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል። ህዝቡም ተገቢውን ድጋፍና ትዕግስት፥ ሲያስፈልግም ምክርና ቁንጥጫ ማሳየት ይጠበቅበታል። መንግስት በባህሪው ተቆጣጣሪ ያስፈልገዋል።

ለሁሉም ተግዳሮቶች ሁለመናዊ ዝግጅት!

መቼም ቢሆን ፍትሃዊ ጥያቄ ያነገበ አሸናፊ ነው!

=== // ===

Back to Front Page