አንተ እንጂ አንተ
ካሳ በቃሉ
04/30/2020
አንተ እንጂ አንተ፡...
ደሞ ማንስ ካንተ ብሶ
የምትነጥቅ የሰው ለቅሶ፡
አንተ እንጂ አንተ.....
ይሁዳን ያስናቅክ ይሁዳ
ጓዶችህን የምትነክስ፡እምነትህን የምትከዳ
ላሰፈሰፈ ጠላት፡ምስጢር የምትሸጥ፤የምትረዳ
በቃልህ የማትገኝ፡መንታ ምላስ ቀዳዳ
ደሞ ባንተ ብሶ ባንዳ?!
የአገር ሞት ማሳያ አብነት፡ሃፍረት፡የታሪክ እዳ
አምሳያ የሌለህ ባንዳ!!!