Back to Front Page

መከላከያ ሰራዊታችን ህዝባዊነቱን ሊያጠናክር ይገባል! (ክፍል ሁለት)

መከላከያ ሰራዊታችን ህዝባዊነቱን ሊያጠናክር ይገባል!

 

(ክፍል ሁለት)

 

ገመቹ ቱሳ 08-30-20

 

አንድ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ ለመከላከያ ሰራዊታችን ያለውን ንቀት አንጸባርቋል፡፡በአሁን ወቅት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት መፈንቅለ መንግስት ማድረግ አይችልም፡፡ ይህንን ማድረግ እንዳይችል አድርገን አዋቅረነዋል ሲል አጽንኦት ሰጥቶ ተናግሯል፡፡ በሌላ ወቅትም የሰራዊቱን ከፍተኛ አዛዦች ሰብስቦ እናንተ ፈጽሙ የተባላችሁትን መፈጸም ነው፡፡ ፐሬድ፡፡ ሲል በንቀትና በትእዛዝ መልክ ተናግሯል፡፡

 

Videos From Around The World

ከዚህ ንግግር የሚንረዳው የኢትዮጵያን መከላከያ ሰራዊት የአገርን ሉአላዊነትና ህገመንግስቱን የመጠበቅ ሃላፊነቱን ወደጎን ትቶ ለአንድ አምባገነን ተገዢ እንዲሆን ያለውን ፍላጎት ነው፡፡ ይህንን ፍላጎት እውን ለማድረግም በሰራዊቱ ላይ የተለያዩ ደባዎች እየፈጸመ መጥቷል፡፡ ይህ ግን ፈጽሞ ሊሆን አይችልም፡፡

 

እርግጥ ነው ተገቢ ባልሆነ መንገድ ወደ ከፍተኛ ስልጣን የወጡ፣ እጃቸው በደም የጨቀየ፣ አእምሯቸው በጥላቻ የታወረ፣ አርቆ ማሳብ ያቃታቸውና የህዝብን አደራ የረሱ አንዳንድ የሰራዊቱ ከፍተኛ አመራሮች ከአብይ አህመድ ጋር መቆራኘታቸው እሙን ነው፡፡

 

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የብሔሮች፣ ብህረሰቦችና ህዝቦች ወገን እንጂ የኣሃዳዊያንና የትምክህተኞች መሳሪያ እንደማይሆን መላው የኣገሪቱ ህዝብ ይተማመናል፡፡ ሆኖም ግን በተለያዩ ጫናዎች ወደ ህዝብ ጥይት የሚተኩሱ ኣንዳንድ ኣባላት የሉም ማለት አይቻልም፡፡ እነዚህ አባላት ከእንደዚህ ዓይነት ተግባር ሊቆጠቡ ይገባል፡፡ ካልሆነ ግን ነገ ተወቃሽ ከመሆን አልፎ በታሪክ ተጠያቂ መሆናቸው የማይቀር ሐቅ ነው፡፡

የሰላምና የልማት ሃይል የሆነው መከላከ ያሰራዊታችን ለህዝቡ ወግኖ በህዝቡ ላይ ተገቢ ያልሆነ ጫና የሚያሳድር ማንኛውንም ወገን በመመከትና በመከላከል የሰላም ኣጋርነቱን በማረጋገጥ ፀረ ሰላም ሃይሎችን ይወጋል እንጂ በሰላማዊ መንገድ ጥያቄ የሚያነሱ ወጣቶችና የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ላይ መሳሪያ አያነሳም፡፡ እንደዚህ የሚያደርግ ከሆነ ህዛባዊ ኣመለካከቱ መሸርሸሩን መገንዘብ ይገባል፡፡

የመከላከያ ሰራዊታችን በኣሃዳዊያን የሚመራውን የፌደራል መንግስት ለማስወገድ በሚደረገው ህዝባዊ ተቃውሞ ኣካል ሆኖ ህዝቡን ማበረታታትና ኣምባገነኑን መንግስት ከስልጣን ተወግዶ ስልጣኑን ለህዝብ እስኪያስረከብ ድረስ ከህዝቡ ጎን በመሰለፍ ህዝባዊ ውግንናዉን ማስመስከር ይኖርበታል፡፡ ውግንናው ለሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ እንጂ ለነውጠኛ ቡድን ሊሆን ኣይገባም፡፡

የመከላከያ ሰራዊታችን ህዝባዊነቱን ማረጋገጥ የሚችለው ደግሞ ወደ ህዝብ ጥይት ኣልተኩስም በማለት ይሆናል፡፡ በተለይም ደግሞ በኣሁኑ ወቅት ህዝባችን በተለያዩ ችግሮች በተከበበ ወቅት የመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ያስፈልገዋል፡፡ በአንድ በኩል ህዝቡ በድህነት ኣረንቋ ውስጥ ሆኖ እየተሰቃየ ይገኛል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ እንደልቡ ተዘዋውሮ ሮጦ ሰርቶ እንዳያድር ኣንድም የሰላም እጦት ሌላም ኮቪድ 19 ከፍተኛ መሰናክል ፈጥረውበታል፡፡ በመሆኑም መከላከያ ሰራዊታችን ድጋፉና ውግንናው ለህዝብ እንጂ የሕግ የበላይነት ማስከበር በሚል ሽፋን ስልጣኑን ለማራዘም ለሚሯሯጥ ኣሃዳዊ ኣገዛዝ ሊያግዝ ኣይገባም፡፡

በኣሁኑ ወቅት የፌደራል መንግስት እየሄደበት ያለው ኣካሄድ የዴሞክራሲ ምህዳሩን የሚያሰፋ ሳይሆን ፋሺሽታዊ የደርግና የሂትለር ኣካሄድ በመሆኑ መከላከያ ሰራዊታችን ይህንን በመገንዘብ ህዝብን ሊደግፍ ይገባል፡፡ የአገራችን ሁኔታ የሚገመግሙ የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚያስቀምጡት የእነ ሳዳም ሁሴንና የመሓመድ ጋዳፊ ታሪክ በኢትዮጵያ እየተደገመ መሆኑን ነው፡፡

በሰላማዊ መንገድ መብቱ እንዲከበርለት የጠየቀን ህዝብ በውይይት ዴሞክራሲያዊ በሆነ መልክ ምላሽ መስጠት እየተቻለ መንግስቱ ሃይለማርያም ያደርግ እንደነበረው የወቅቱ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ኣህመድ ምላሽ ጥይት ሆኗል፡፡ ይህ ድርጊት አሁን ያለው መንግስት ምን ያህል ፋሺሽትና ጨካኝ እንደሆነ በተግባር ኣሳይቷል፡፡

ዶ/ር ኣብይ አህመድም ሆነ በዙሪያው የተሰበሰበው የነፍጠኛ ቡድን ከኢትዮጵያ ህዝብ አብራክ የተፈጠረ አይመስሉም፡፡ ከህዝብ አብራክ መውጣቱን የከዳ ንጉሳዊ ጨቋኝ ኣመለካከትና ፍላጎት የተቆራኘው ኣምባገነናዊ ቡድን ነው፡፡ ይህ ነፍጠኛ ንጉሳዊ ኣመለካከት የያዘ ቡድን የትኛውንም ህዝብ ሊወክል ኣይችልም፡፡ አሁን ስልጣን ላይ ያለው ቡድን የኦሮሞም ሆነ የአማራ ህዝብ ወኪል አይደለም፡፡ ሊሆንም አይችልም፡፡ ሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦችንም ኣይወክልም፡፡

በመሆኑም ኣሁን ስልጣን ላይ ያለው ቡድን የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ጠላት እንደሆነ መገንዘብ ያሻል፡፡ የህዝቦችን ኣንድነት ለማጠናከር ሳይሆን ኣገሪቱን ለመበተን እና ለማፍረስ የመጣ ሃይል መሆኑ ባለፉት ሁለት ዓመታት በተግባር ታይቷል፡፡ የህዝቦችን ደም መጣጭ መሆኑንም አስመስክሯል፡፡

ይህ ቡድን የአገሪቱን ሰላም፣ ዴሞክራሲና ልማት ለማረጋገጥ የሚሰራ ሳይሆን የውጭ አገራት መንግስታት ተላላኪና ጥገኛ በመሆን የአገሪቱን ሉኣላውነት ኣሳልፎ የሰጠ ከሃዲ ቡድን መሆኑን መከላከያ ሰራዊታችን ሊገነዘበው ይገባል፡፡ እስካሁን በፈፀማቸው ተግባራት ሲታይ ጭር ሲል አልወድም አይነት ፍላጎት እንዳለው መገንዘብ ኣያዳግትም፡፡ ከኣፄዎች ከንጉሳውያን እና ከኣምባገነናውያን የወረሰው ቀረርቶ፣ ድንፋታ፣ ማስፈራራት የሚቀናው ፍፁም ገዳይና በደም የተጨማለቀ ቡድን ነው፡፡ በተንኮልና ሴራ የተሞላ ሀገር እንደ ሀገር ለመምራት ምንም ዓይነት እቅድ የሌለውና አገሪቱን ለማፈራረስና ኣጥፍቶ ለመጥፋት የተዘጋጀ የዘመኑ ዳግማዊ ደርግ ነው፡፡

ለዚህም ነው ቡድኑ በዚህ አጭር ጊዜ እጆቹ በደም የጨቀዩት፡፡ በርካታ ብርቅዪ ዜጎችን በጭካኔ የገደለው፤ ኣሁንም ቢሆን በዚያ አላበቃም መግደሉን ቀጥሎበታል፡፡ ይህ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል የሚል ኣባዜ የተጠናወተው ኣምባገነናዊ ቡድን ለፍርድ መቅረብ ይኖርበታል፡፡

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሆይ የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ከተደፈጠጡ፣ የአገሪቱ ህገመንግስት ከተሻረ፣ የአገሪቱ ሉአላዊነት ከተደፈረ ምን ትጠብቃለህ? ህዝባዊ አደራህን ለመወጣት መነሳት ይኖርብሃል፡፡ በአብ ይአህመድ የሚመራውን አሃዳዊ መንግሰት በማስወገድና ስልጣኑን ለህዝብ በማስረከብ ታሪካዊ ሃላፊነትህን በመወጣት ህዝባዊ ውግንናህን የምታስመሰክርበት ወቅት አሁን ነው፡፡

 

ከአብይ አህመድ የተለጠፉ አንዳንድ አባላትም ቢኖሩም ሃይል የሰፊው መከላከያ ሰራዊት ነው፡፡ መከላከያ ሰራዊቱ በብሄርም ሆነ በሃማኖት ሳይለያይ አንድነቱን አጠናክሮ አገርን እየበተነ ያለውን የነውጥ ቡድን ከህዝብ ጎን በመሰለፍ ፈጥኖ ሊያስወግደው ይገባል፡፡

 

አብይ አህመድና የብልጽግና ፓርቲ አገርን አስይዞ ቁማር እየተጫወተ ቆሞ መመልከት ይብቃ፡፡ መከላከያ ሰራዊታችን ህዝባዊነቱን ሊያድስ፣ የአገሪቱን ሉአላዊነት ሊታደግና ከአገሪቱ ብሄሮች፣ ብሄሮችና ህዝቦች ጎን በመቆም አምባገነኑን አገዛዝ በማስወገድ ዳግም ህዝባዊነቱን ሊያረጋግጥና የህዝብ አለኝታነቱን ሊያስመሰክር ይገባል፡፡ በመሆኑም የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት ቆም ብሎ በማሰብ ከህዝብ ጎን በመሰለፍና የዚህን አምባገነን ቡድን የስልጣን ዕድሜ በማሳጠርና በማስወገድ ህዝቡ የእኔ የሚላቸውን መሪዎች እንዲመርጥ በማስቻል ታሪካዊ ሃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል፡፡

 

 

 

Back to Front Page