Back to Front Page

መከላከያ ሰራዊታችን ህዝባዊነቱን ሊያረጋግጥ ይገባል! (ክፍል አንድ)

መከላከያ ሰራዊታችን ህዝባዊነቱን ሊያረጋግጥ ይገባል!

 

(ክፍል አንድ)

 

በመቹ ቱሳ 08-28-20

 

ለዴሞክራሲ ግንባታና ለአገር ሁለንተናዊ እድገት ሰላም ወሳኝ ነው፡፡ በአገራችንም ላለፉት 27 ዓመታት ሰላም በመስፈኑ ለፌደራላዊ ስርዓቱ መጠናከር ዋልታና ማገር ሆኖ ዘልቋል፡፡ የአገራችን ሉአላዊነትና ሰላም ለአፍታም ጥያቄ ውስጥ ሳይገቡ በንቃት እንደተጠበቁ መዝለቃቸው ያደባባይ ምስጢር ነው፡፡ የዚህ ሁሉ አለኝታና ዘብ ደግሞ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችን እነደነር ጠላትም ሆነ ወዳጅ አይክደውም፡፡

 

ቀደም ሲል የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከአገሩ አልፎ ድንበር ተሻግሮ የሌሎች አገራትን ሰላም በማስከበር ረገድ የማይረሳ ታሪክ ያስመዘገበ ብርቅየ ሰራዊት ነው፡፡ ከዚህም የተነሳ ከኢትዮጵያውያንም አልፎ የአፍሪካ ህዝቦች አለኝታነቱን በተጨባጭ አስመስክሯል፡፡

 

ጀግንነቱን የዓለም ህዝብ የመሰከረለት፤ በመልካም ወታደራዊ ሥነ ምግባር የታነጸ ከፍተኛ ዝባዊነትን የተላበሰ አኩሪ ገድሎችን ያስመዘገበ መከላከያ ሰራዊት እንደሆነ ማንም አይክደውም፡፡ ሰላምን ለማስከበር በተሰማራበት አካባቢ ሁሉ በህዝብ ከፍተኛ ከበሬታንና ፍቅር እየተቸረው የመጣ ሰራዊት ነው፡፡ በሶማሊያ፡ በሱዳን፡ በሩዋንዳና በላይበሪያ የሰራቸው መስተንክራዊ ተግባራት ምንግዜም ከህዝብ ልብ የሚጠፉ አይደሉም፡፡

Videos From Around The World

 

በሶማሊያ ሲንቀሳቀስ የነበረውን አልሸባብ የተሰኘው አሸባሪ ቡድን በመደምሰስ፤ የሶማሊያ ህዝብና መንግስት ያደርጉት የነበረውን አገርን መልሶ የመገንባትና የልማት ተግባራትን በመስዋእትነቱ እንዲረጋገጥ እድርጓል፡፡ በአገሪቱ ጠንካራ ይዞታ የነበረውን አልሸባብ የተባለውን የሽብር ቡድን ድል በመቀዳጀቱም በተባበሩት መንግስታትና በሶማሊያ የአፍሪካ ሰላም አስከባሪ አሚሶም በኩል ለአኩሪ ተግባሩ ሽልማት እንደተበረከተለት ይታወቃል፡፡

የዓለማችን ህዝቦች ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ያላቸው አድናቆት ከፍተኛ መሆኑን ብዙዎች መስክረውለታል ብዙዎችም ጽፈውለታል፡፡ ከእነዚህም አንዱ ሮበርት ቤክሁሰን ነው፡፡ ይህ ጸሃፊ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት በጣም ዝቅኛተኛ በጀት የሚጠቀም ሆኖ በጣም ከፍተኛ ብቃት ያለው ሠራዊት ነው፡፡ በከፍተኛ ተጻብኦና አለመረጋጋት ባለበት ቀጠና የምትገኘው አገሩን ሰላም በአስተማማኝ ያረጋገጠና ከባእዳን ጠላቶች ጥቃት መጠበቅ የቻለ ሠራዊት ነው ሲል አስፍሯል፡፡አገሪቱ የአፍሪካ ቀንድ የኢኮኖሚ ልማት ማዕከል ለመሆንና ፈጣን እንዲሁም ተከታታይ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማስመዝገብ የቻለችውም ሰራዊቱ የአገሩን ሰላም በማስጠበቁ ነበር፡፡ መከላከያ ሰራዊቱ ከአመሰራረቱ ጀምሮ ህዝባዊነት የተላበሰ ለእውነት ራሱን አሳልፎ የሚሰጥና የሚሰዋ ስለሆነ በህዝቦች ይሰጠው ያለው ክብር ከፍ ያለ ነው፡

 

ነገር ግን ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ በአገሪቱ ሰላም ሲደፈርስ ህገ መንግስቱ በአሃዳዊያን ቡድኖች ሲሰረዝና ዝደለዝ ሰርዓት አለበኝነት በአገሪቱ ነግሶ ሰዎች በማንነታቸው ምክንያት በድንጋይ ተቀጥቅጠው ሲገደሉ ተዘቅዝቀው ታስረው በአስከፊ ሁኔታ ተደብድበው ሲሞቱ፣ ለአመታት ያፈሩት ንብረት ሲቃጠልና ሲወድም፣ መንግስት ፈላጭ ቆራጭ ሆኖ እገሌን እሰር እገሌን ግደል እያለ ማፊያዎችን ሲያሰማራ ግን መከላከያ ሰራዊቱ የማዶ ተመልካች ሆኗል የሚሉ የበርካታ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች አመለካከትና እምነት ሆኗል፡፡

 

በአገሪቱ ህገ መንግስት አንቀጽ 87 ንኡስ አንቀጽ 1 ላይ የሰፈረው የአገሪቱ መከላከያ ሰራዊት የተመጣጠነ የብሄሮች ብሄረሶብና ህዝቦችን ተዋጽኦ የያዘ መሆን ይኖርበታል የሚለው ድንጋጌም አገሪቱን የሚመራው መንግስት ባለፉት ሁለት አመታት በግላጭ ጥሶታልል፡፡ በርካታ የካበተ ልምድ ያላቸው የሰራዊቱ አባላት በማንነታቸው ብቻ ከሰራዊቱ እንዲባረሩ ተደርጓል፡፡ ቀደም ሲል ከኤርትራ መንግስት ጋር በነበረው እልህ አስጨራሽ ጦርነት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከቱ የአገር መከላከያ ሰራዊትና የደህንነት አባላትም ያለአግባብ በእስር እንዲማቕቁ ተደርገዋል፡፡

 

በሌላ በኩል ደግሞ በዚሁ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 5 ላይ የአገሪቱ መከላከያ ሰራዊት ከማንኛውም ከፖለቲካ ፓርቲ ውግንና ነጻ ሆኖ ህገመንግስታዊ ስርዓት የመጠበቅ ተልእኮ ተሸክሞ ስራውን ያከናውናል የሚል ድንጋጌ ቢኖርም አብዛኛው ህዝብ እያነሳ ያለው ስጋት የመከላከያ ሰራዊቱ ለአምባገነኑ የአብይ አህመድ መንግስት ተገዢ ሊሆን ይችልል የሚል ስሜት ተበራክቷል፡፡

 

በተመሳሳይ አንቀጽ በንኡስ አንቀት 4 የተቀመጠውም የአገር መከላከያ ሰረራዊት ለሕገመንግስቱ ተገዢ ይሆናል የሚለውም መንግስት በራሱ አፍራሽ መንገድ እየሄደ በመሆኑ ይህንኑ የሚቃረኑ በርካታ ተግባራት ታይተዋል፡፡ የአገሪቱ መከላከያ ኢታመዦር ሹም ተገድሏል፤ የክልል ከፍተኛ አመራሮች በጠራራ ፀሃይ ተረሽነዋል የአገሪቱን ህገመንግስት በአሃዳዊያን ጨፍላቂ አስተሳሰብ አደጋ ላይ ወድቋል፣ እየፈረሰም ይገኛል፡፡ አገሪቱ የብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦችን መብት በማፈን አሃዳዊና አምባገነን ስርዓት ለማስፈን እየተሰራ ይገኛል፡፡

 

በመሆኑም በየትኛውም የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ላልተወከለ የውጭ ሃይሎች ተላላኪ ሆኖ አገሩን ለሸጠ የአገር ሉአላዊነትና ብሄራዊ ጥቅም አሳልፎ ለባእዳዊያን ለሰጠና በለውጥ ስም ነውጥን እያስፋፋ ላላ ቡድን በዝምታ መመልከት የለበትም የሚል ትንታኔ በበርካታ ሙሁራን ይሰጣል፡፡ ከዚህ አልፎም የራሱ ዜጎች የሆኑ ህዝቦች የዘር ማጥፋት ስራ እያከናወነ ይገኛል፡፡

 

ለዚህ ደግሞ ሩቅ መሄድ ኣያሻም፡፡ በቅማንት፡ በሶማሌ፡ በደቡብ፡ በኦሮሚያና በወላይታ ህዝቦች ላይ እየደረሰ ያለውን የግፍ ጭፍጨፋ ማየት በቂ ነው፡፡ ይህ በእርግጥም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ህዝባዊነቱን ረስቷል ማለት ያስችላልን? ይህ ማለት ግን ሁሉንም የመከላከያ ሰራዊት አባላትን የሚመለከት አይደለም፡፡ በለወጥ ስም ስልጣን የተቆናጠጠው አሸባሪ ቡድን ጋር በመሆን በህዝብ ላይ ግፍ አየፈጸሙ ያሉትን ጥረት የመከላከያ ከፍተኛ አመራሮችና የእነሱ ታዛዦችን ነው፡፡ ሌሎች ህዝባዊ አመለካከት ያላቸው ግን እምቢ ወደ ህዝባችን አንተኩስም ብለው ራሳቸው መስዋእት እስከመሆን ደርሰዋል፡፡ ለዚህ ማሳያ የሚሆነው የወላይታ ተወላጅ የሆነው የመከላከያ ሰራዊት አባል ነው፡፡

 

ህገመንግስቱ ከተጣሰ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ለግድያ ለእስር ለእንግሊትና ለስቃይ እየዳረጉ ባሉበትና አገር ለባእድዳን ተላልፋ በተሰጠችበት በአሁኑ ወቅት መከላከያ ሰራዊቱ በዝምታ መመልከት አይኖርበትም የሚል አንዱ እየተነሳ ያለ ትችት ነው፡፡ አገር ከፈረሰች ሕገመንግስቱ ከተቀደደ መከላከያ ሰራዊቱ ስራው ምንድን ነው? ብለው የሚጠይቁ ዜጎች በርካታ ናቸው፡፡

 

አዎ እውነት ነው፡፡ መከላከያ ሰራዊታችን የዜጎች ስቓይ ይብቃ ማለት አለበት፡፡ የአገሪቱ ህዝቦችን ጥያቄ እንዲመለስ ሃላፊነቱን መወጣት ይጠበቅበታል፡፡ የህዝቡን አብይ አህመድ ይውረድልን ብልጽግና ፓርቲ አልመረጥነውም አይመራንም የሚለውን የህዝብ ጭሆት በመስመት የነውጥን ሃይል ከስልጣን በማስወገድ ህዝባዊነቱን ዳግም መላበስና የህዝብ አለኝታ፡ ዋስና ከለላ መሆኑን በተግባር ማረጋገጥ ይኖርበታል፡፡

 

በአሁኑ ጊዜ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የኦሮሚያ ህዝብ የድረሱልን ጥሪ እያስተጋባ ይገኛል፡፡ የአገሪቱ ህገመንግስት ተጥሷል የአገሪቱ ሉኣለዊነት ተደፍሯል ይህንን አምባገነን አሃዳዊ መንግስት ለማውረድ በሚናደርገው ትግል መከላከያ ሰራዊቱ ከጎናችን ይቁም ለአምባገነን መንግስት ማገልገሉን ያቁም የሚሉ ጥሪዎችን እያሰማ ይገኛል፡፡

 

የደቡብ ህዝቦችም በተመሳሳይ መልኩ የድረሱልን ጥሪ ማቅረብ ከጀመሩ ሁለት ድፍን ዓመታትን አሰቆጥረዋል፡፡ የትግራይ ህዝብም ይህ መንግስት የብሄሮች፡ ብሄረሰቦችና ህዝቦችን መብት ደፍጥጦ አሃዳዊ መንግስት ለመመስረት አልሞ እየተንቀሳቀሰ ያለ ጥገኛ ቡድን መሆኑን ገና ከጥዋቱ አስታውቆ የኢትዮጵያ ብሄሮች፡ ብሄረሰቦችና ህዝቦች አንድ ሆነው እንዲታገሉት በተደጋጋሚ ጥሪውን ሲያቀርብ ቆቷይል፡፡ አሁንም ትግሉን አጠናክሮ ቀጥሎበታል፡፡

 

በሶማሌ፡ በቤንሻንጉል ጉሙዝ በአፋርና በአማራ ያለው ህዝብም ተመሳሳይ ጥያቄ እያቀረበ ነው፡፡ እንግዲህ መከላከያ ሰራዊታችን የህዝብን የድረስልን ጥሪ ወደጎን ትቶ እስከመች አምባገነኖችን ስታዘዝ ይኖራል? መከላከያ ሰራዊታችን ይህንን ማድረግ ካልቻልክ በታሪክ ተጠያቂ መሆንህ አየቀሬ ነው፡፡

 

 

 

Back to Front Page