Back to Front Page

መከላከያ ሰራዊታችን ምን ይመስላል?ክፍል3

መከላከያ ሰራዊታችን ምን ይመስላል?

ክፍል 3

 

ዑሱማን ሙሉዓለም

ከሐራ-ገበያ

ግንቦት 21፣2012ዓ.ም.

 

ውድ አንባቢዎች በክፍል ሁለት ፅሑፌ በኢህአዴግ የስልጣን ዘመን የኢትዮጵያ ሰራዊት ምን ደረጃ ላይ ደርሶ እንደነበር ገልጨለሁ።አገራችን በፈጣን ዕድገት በነበረችበት ወቅት መከላከያ ሰራዊታችንም ከየትኛውም አጋር ማንኛውንም ትንኮሳ ለመከላከል የሚያስችለው ብቃት ለመገንባት በከፍተኛ ደረጃ ጥረት ተደርል።በዚህም ጠቅላላ ብቃቱ በአካባቢው/በቀጠናውሊነሳ የሚችል ማንኛውም ጦርነት ማስቀረት የሚያስችል /deter ማድረግ የሚያስችል/ ቁመና ተቀናጅቶ ነበር። ጦርነት ማስቀረት ካልቻለ ደግሞ አንድ ትልቅ ጦርነት ሙሉ ለሙሉ ማሸነፍ የሚችልና በተጨማሪም ሌላ ጦርነት በሌላ አቅጣጫ በተመሳሳይ ጊዜ ቢከፈትለትም መክቶ መመለስ የሚችል ብቃት ፈጥሮ ነበር።ይህም ከፅንሰሐሳባዊ የአቅሙ ብቃቱ እና ሞራላዊ አቅሙ ከፍ ያለ መሆኑ ጋር በቀጥታ የሚያያዝ ነው።ተጨባጭ አቅሙም በሰው ሐይል በግዳጅ የተሰለፈው ሐይልና ተጠባባቂ ሐይሉ የተሟላ ነበር።የትጥቅ እና የስንቅ አቅርቦት በአጠቃላይ ዘመናዊ የሎጂስቲክ አቅም በመፍጠሩ ላይ የተዘረዘሩት ጦርነትን ማስቀረትና ጦርነት ካለ አሸንፎና መክቶ የአገሩን ሉዓላዊነት በአጭር ጊዜ ማረጋገጥ የሚችል ወታደራዊ አቅም ያለው ሰራዊት ነበራት ኢትዮጵያችን።አሁንስ?

 

በለውጥ ስም ስልጣን ላይ የወጣው ኮ/ል አብይ የዚህ ሰራዊት አባል የነበረ ቢሆንም ከሬድዮ መገናኛ ኦፕሬተርነት ውጭ በሰራዊት ግንባታና የአመራር ብዙ ልምድ ሳያገኝ ከሰራዊቱ ወጥቶ በሌላ ስራ የቆየ ነው። መአርጉም ለብሄራዊ አስተዋፅኦ ተብሎ በፈጣን የመዓርግ ዕድገት አሰጣጥ ያገኘው ነውኮኔሬልነቱ።በስራው እየተገመገመ ለፍቶ ግሮና ጥሮ የአገልግሎት ጊዜውን ጠብቆ ያገኘው መዓርግ አይደለም።ከላይ ስለ አብይ ያነሳሁት ጠቅላይ ሚኒስተር ከሆነ በኃላ በሱና በሰራዊቱ የነበረው ግንኙነት የሚገርም ነገሮች ስላሉት ነው።መጀመርያ ላይ ሁሉም የበላይ ከፍተኛ መኮነኖች አለቆቹ ስለነበሩ ቀና ብሎ ማየትና ጮክ ብሎ መናገርም አይችልም ነበር። የተለመደው እወዳሃለሁ! የሚለው እንዳለ ሁኖበየግል እያገኘም ልጅህ ነኝ! ምከረኝ! አግዘኝ! ይላቸው ነበር።ትንሽ እንደቆየ ጀነራሎቹን ሰብስቦ ሙሉ ለሊት ሲፀልይ አድሮ ሊሆን ይችላልከናንተ በላይ አላቅም እያለም ስለ መከላከያ ሰራዊት ግንባታና ወታደራዊ ሐሳቦች የተበጣጠሱና በጥልቀት የማያቃቸውን እና እርስበራሳቸው የሚጣረሱ ንግግር አደረገ።የስብሰባው ዓላማ የናንተው ነኝ። ጣልቃ ሳትገቡ በትረ ስልጣኑን ወንበሩን በመቆጣጠሬ አመሰግናለሁ።በተለይም ጀነራል ሳሞራን ማመስገንና ሁላቹሁም ይህንን የሳቸውን አረአያ ተከተሉ ለማለት ነው።ዲሲፒሊናቹሁ አደንቃለሁኝ! እወዳቹኃለሁኝ! ነበረ ንግሩ።ብዙዎቹ መኮነኖች ጨቅላነቱን የታዘቡበት ቀን ነበር። ይሁን እንጂ ለአንዳንደቹ ጊዜ በመግዛት እስቲ እንየው እድል እንስጠው የሚል መንፈስ ግን ፈጥሮለት ነበር።

Videos From Around The World

 

ወደ ዋናው ጉዳይ ልግባና በሦስቱ መመዘኛዎች አሁን ያለው የሰራዊታችን ወቅታዊ አቅም እንገምግም።በፅንሰሐሳብ አቅም በምናይበት ወቅት ይህ በስመ ለውጥ በመጣው የአብይ የውድቀት ለውጥ ምክንያት ሰራዊቱ በአሁን ሰዓት ቀጣይ ጦርነት ከማን ጋር እንደሚሆንናአጠቃላይ የአገሪቱ የስጋት ትንታኔ ምን እንደሆነ አይታወቅም። አገራዊ ስጋት ይኑር አይኑር ግልፅ አይደለም።ግልፅ ባልሆነበት ሁኔታ ደግሞ ሰራዊቱ ብቁ ዝግጅት ማድረግ አይችልም።የለውጥ ሐይል ነን የሚለው ሐይል ያለፈውን እንቅስቃሴ በሙሉ አውግዞ፣ የነበረው የኢትዮጵያ መንግስት ራሱ አሸባሪ ነበር ብሎ፣ ጦርነት የከፈተብንን ኢሳያስ አፈወርቂን የበለጠ ወዳጅ የሚያደርግ እና የህዳሴ ግድብ ግንባታ ለፖለቲካ ፍጆታ ብቻ የተደረገ ነበር ወላሂ! የግብፅ ጥቅም አንጎዳም እናንተ የምትጎዱ ከመሰላችሁ እኛ ተጎድተን ቢሆን የግድቡ የውሃ መያዝ አቅሙን እንቀንሳለን የሚል ፖለቲካል ዲፕሎማሲ በመምጣቱ ሰራዊቱ የተገነባበት የፅንሰሐሳብመነሻው/መሰረቱ የተናደ ሆነ። ለረጅም አመታት የአገራችን አጋር የነበሩ ጎረቤት አገሮች ወደ ጎን ገፍትሮ ከብሄራዊ ጥቅማችን ቅራኔ ያላቸውን አገራትን የሚሰበስብ ግራ የተጋባ ዲፕሎማሲ ተፈጠረ፡፡ ዲፕሎማሲያችን በስጋት ትንታኔ ላይ ስላልተመሰረተ መከላከያም፣ ውጭ ጉዳይም፣ የድህንነት አቅጣቻችንም ፍርስርሱ እንዲወጣ አድርታል።

 

ወታደራዊ ፅንሰሐሳብ መነሻው የአገር ጥቅም ፖለቲካ መነሻ ተደርጎ በስጋት ላይ ትንታኔ ተመስርቶ የሚቀረፅ እንጂ ተራ ንድፈሃሳብ አይደለም።ሌላው ጉዳይ አሁን ያለው ሰራዊት ግዳጁን አያቅም። አብይ ሰራዊቱ ግዳጁን የሚፈፅምበት ፅንሰሐሳባዊ አቅም መሰረቱንና መነሻውን በመናድ አዳክሞታል። አብይ ገና መንግስታዊ በትረ ስልጣኑን በተቆጣጠረበት ግዜ ነበር የነበረው ወታደራዊ መስመር /ዶክትሪን/ መሰረታዊ መነሻው ቆሻሻ ነበር እና የህገመንግስቱ የመጨረሻ ምሽግ ሰራዊቱ አይደለም ህገመንግስት የምንጠብቀው እኛ ፖለቲኮኞች/መንግስት ነን ያለው፡፡ ታድያ ሰራዊቱ ከምን ምሰሶ/ መነሻ ተነስቶ ነው ወታደራዊ ዶክትሪን የሚኖረው? አይታወቅም። አብይ የነበረውን ስህተት ነው ብሎ ተቃውሞ አዲስ ወታደራዊ አስተሳሰብና ወታደራዊ መስመር ሳይተካለት ማሰብያው የተቀማ ሰራዊት አድርጎታል።

 

ይህ የፅንሰሐሳብ ጉዳይ /conceptual component/ ለአንድ ሰራዊት መርሆ፣ ፍልስፍና እና አጠቃላይ መመርያ የሚሰጥና ምን እንደሚያስብ ሳይሆን እንዴት እንደሚያስብ ጭምር አቅም የሚፈጥርለት፣ የመተንተንና የፈጠራና ችሎታ የሚያዳብርበት፣ ነገሮችን በተለያየ አቅጣጫ ማየት እንዲችል የሚያደርገውና ችግር የሚፈታበት ብቃት የሚያጎናፅፈው ነው።ይህ ብቃት አሁን በሰራዊታችን የለም። እዚህ ላይ ሰራዊቱ በዚህ አሰተሳሰብ የሰለጠነና የተገነባ ከነበረ አሁን የት ሄዶ ነው የለም የምንለው? የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል።መነሳቱም ተገቢ ነው።የለም የምለው በሚከተሉት ምክንያቶችናቸው።

 

በመጀመርያ ሰራዊቱን እየመራ ያለው መንግስት ግልፅና አንድ ወጥ የሆነ ስለ ብሄራዊ ስጋት፣ ስለ ብሄራዊ ጥቅም እና ስለ ቀጣይ ሁኔታ ምንም ሐሳብ የለውም። ሐሰብ ብሎ የሚነገረውም ድብቅልቁ የወጣ ነው፡፡ ዛሬ የተናገረውበነገታው የማይደግመው ነው፡፡ በየቀኑና በየሳምንቱ የሚቀያየር በመሆኑ ምኑን ይዘህ ምን እንደምትተው አስቸጋር አድርጎታል።በሁለተኛ ደረጃ ስለ ትናንት 27 ዓመት አንድ ዓይነት ግምገማ የለም።አንዴ ይወደሳል ይመረቃል።አንዴ ጨለማ ይለብሳል።አሁን እየሄድንበት ያለው አዲስ አቅጣጫ ደግሞ አይገለፅም።ሦስተኛው ደግሞ ሰራዊቱ ከመደበኛ ግዳጁና ተልእኮው ወጥቶ ሰላም የለም በተባለበት ቦታ ሁሉ ተበትኗል።የህዝቦችን ጥያቄ ጨፍልቅ እየተባለ በታንክና በመድፍ በሄሊኮፕተር ተጠቅሞ እንዲጨፈልቅ ስምሪት ተሰጥቶት ሳያምንበት በተግባርእየፈፀመ ነው። ሰራዊታችን ከተገነባበት ፅንሰሐሳብና ከባህሪው ውጭ እነዚህ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ሲገባ የነበረው ፅንሰሀሐባዊ ትጥቅ ፈቷል ማለት ነው። ሰራዊቱ የተገነባበት ፅንሰሀሐብ የለም ማለት ነው።ስለዚህ ከህገመንግስት ውጭ የአንድ ግለሰብ ስልጣን ለማራዘም የቆመ ሰራዊት ለማድረግ ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ለማንም ግልፅ ነው።

 

በአሁኑ ወቅት በቆየው የሰራዊቱ ፅንሰሐሳብና በአዲሱ ውሉ በማይታወቅና ግልፅነት በጎደለው አስተሳሰብ መካከል ቅራኔ ተፈጥሮ ሰራዊቱ ምን ማሰብ እንዳለበት እየተነገረውም መቀበል አልቻለም። ሰራዊቱ በለመደው መንገድ እንዴት ማሰብ እንዳለበትናበአገሪቱ ያሉትን ነገሮች በመተንተን በአዲሱ የለውጥ አመራር ነኝ ባዩ ሁኔታ ላይ እምነት የለውም።በስልጣን ያለውም ሐይል በሰራዊቱ ላይ ጥርጣሬ ስላለው እምነት የለውም።በዚህ ሁኔታ አብይ የፅንሰሐሳብ አቅም የጎደለው ሰራዊት ለመፍጠር የነበረውን ሰራዊት ቀስበቀስ የማፍራረስ ስራ ተያይዞታል።ግንቦት ሰባት/አዜማ በአደባባይ ሰራዊቱ መፍረስ እንዳለበት ኢሣት በተባለው ሚድያቸው ጎሮራቸው እስኪደርቅ ተናግረውታል።መቼና በምን መንገድ በሚለው ቢለያዩምአዜማና ፒፒ ሰራዊቱ መፍረስ እንዳለበት ሁለቱም አምነው የማፍረሱ ሂደት ከጀመሩት ቆይተዋል።

 

ሁለተኛው አቅም የሰራዊቱ ተጨባጭ አቅሙ ነው፡፡ በዚህ ረገድ ምንም ለውጥ የለውም እንዳለ ነው።የሰው ሐይሉ፣ የጦር መሳርያ፣ ሌሎች ወታደራዊ ቁሳቁሶች የተሟሉ ናቸው።ከዝግጁነት አንፃር ሲታይ ግን ይህ አቅም ተበትኗል። እንደሚሊሻ ሰራዊቱ በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች ህገመንግስታዊ ባልሆነ ድብቅ ጊዚያዊ አዋጅ ኮማንድ ፖስት በሚል በምስራቅ፣ በደቡብ፣ በምዕራብ ተበትኗል።ገና መsጫ ባላገኘው የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ምክንያትም አሁንም በግንባር ላይ ሰራዊታችን አለ።ትናንሽ ግጭቶችናበአብይ መንግስት ላይ የህዝብ ጥያቄዎች በተነሱ ቁጥር ከዚህ ግንባር ሐይል እየተቀነሰ ወደ ደቡብ ወለጋ፣ወደ ቅማንት፣ ወደ ከምሴ እና ወደ ሌሎች አከባቢዎች እየሄደ ነው።ኢሳያስም ከዚህ ሐይል ተነስቶለት በሐይል በአገራችን ዳርድንብር ላይ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጅት እያደረገ ነው።ባለፉት ሳምንታት ሁለቱ ታረቁ የተባሉ አገሮች ምክንያቱ በልታወቀ ሁኔታ ሰራዊቶቻቸው ምሽግ ገብተዋል።መጀመርያ ምሽግ ገብቶ በተጠንቀቅ የተስለፈው የኤርትራ ሰራዊት ሲሆን ከአዲስ አበባ በመጣ ቀጭን ትዕዛዝ የኢትዮጵያሰራዊትም ምሽግ ገብቷል። ይህ በእንዲህ እያለ በዓለም ያሉ አገራት በኮቪድ-19 ምክንያት በራቸው ዘጋግተው ባሉበት ወቅት ለምን? እና ማንም ሳያቀው ኢሳያስ ኢትዮጵያ ደርሰው ተመልሰዋል።

 

አሁን ደግሞ ጦርነት/ወረራ ሊፈፀምብን ነው እየተባለ ነው። ነገር ግን ወረራ የፈፀመው ወይም ሊፈፅም የከጀለው ሐይል/አገር በግልፅ አልተነገረም።ከአገር ቤትም ባንዳዎች እንዳሉና ማንነታቸው ሳይገለፅ ማስጠንቀቅያ ተሰጥቷቸዋል።የራሴ ግምት ልግለፅ።ጁቢቲን፣ ሶማሊያን፣ ደቡብ ሱዳንን እና ኬንያን ልጠረጥር አልችልም።ግብፅ እና ኤርትራም እንዳልጠረጥር የኮ/ል አብይ ወዳጆች ስለሆኑብን መጠርጠርና መገመት አልቻልኩም።አሜሪካ ወይም ቻይናም እንዳልል ሊያስጠረጥር የሚያስችል ሁኔታ የለም።እኔ የምገምተው የሱዳን መንግስት ነው፡፡ ለረዥም ጊዜ ደንበራችን እናካልል ሲል ቆይቷል።በሱዳን ለውጥ ተካሄደ ተብሎ ባለበት ሁኔታ ደንበር የማካለሉ ሁኔታ የካርቱም አጀንዳ ሆኖ እንደ አዲስ አገርሽቷል።ይህን ተከትሎ ሱዳን ሰራዊትዋን በሱዳን ግዛትዋ ውስጥ ሆኖ ግን በሁለቱ አገሮች ደንበር ላይ አሰልፋለች።ይህን ተከትሎ ችግር ተፈጥራል።የኢትዮጵያ መንግስት በአንድ በኩል ፈትተንዋል ሲል በሌላ በኩል ደግሞ ወረራ ሊፈፅሙብን ነው የሚለው ይህን ይመስለኛል። ነግር ግን የአብይ መንግስት ለምን ማስጮህ ፈለገ ነው? መቼ ነውማስጮህ የጀመረውስ? ብሎ ማየቱ ተገቢ ነው።ማስጮህ የጀመረው ከኤርትራ ጋር ንግግር ከተደረገና ኢሳያስ አዲስአበባ ደርሶ ከተመለሰ በኃላ ነው።ማስጮህ የተፈለገውስ ለምን? ለሚለውም በሰበብ ከኢትዮ ኤርትራ ግምባር ከተሰለፈው ሰራዊት ሐይል አንስቶ ለመውሰድ እንደሚሆን እገምታለሁ።የሴራው አላማም ቦታውን ክፍት በማድረግ ለኢሳያስ የተመቻቸ ሁኔታ መፍጠር ነው።ይህን ግምት የሚያጠናክረው ሌላው መረጃ ደግሞ የትግራይ ህዝብ የመረጠው ህወሓት በህገወጥ መንገድ የስልጣን ዕድሜየን አላራዝምም በከፍተኛ ጥንቃቄ በኮቪድ 19 ሁኔታ ውስጥ በህገመንግስቱ መሰረት ምርጫ አደርጋለሁ በማለቱ በኮ/ል አብይ አህመድ ጦርነት ታውጆበታል።የጦርነቱ አዋጅ ዝግጅት ፈፅመናል ስለሚል ዝግጅቱ በኢትዮ-ኤርትራ ደንበር ያለውን ሰራዊት በማንሳት ትግራይን መቅጣት ወይም ከኢሳያስ ጋር በማበርና በመቀናጀት የትግራይ ህዝብ መምታት የሚለው ነው፡፡ ውጤቱ ምን እንደሆነ በቀጣይ የምናየው ይሆናል።በዚህ ሁኔታ ሰራዊታችን ተጨባጭ አቅሙ በተበታተነበትና የሌለ ስጋት ፈጥሮ አሰላለፉን ለመቀየርና ያለውን ተጨባጭ ስጋት ደግሞ ችላ ብሎ ትርምስ በማስገባት የሰራዊታችን አቅም እያባከነው ነው።ፅንሰሐሳብ የሌለው መሪ ሰራዊትን የሚመራበት አስተሳሰብና አስተሳሰቡን የሚደግፍ አሰራርና ስምሪት ሊኖረው አይችልምና።

 

በቀጣይ ክፍል የሰራዊታችን ሞራላዊ አቅም በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ በዝርዝር አቀርባለሁ።

 

ቸር እንሰንብት!

 

 

ግንቦት 20 በኢትዮጵያ ህዝቦች ልብ ለዘላለም ይኖራል !

 

Back to Front Page