Back to Front Page

ኣስተያየት በዶክተር ዮሃንስ ኣበራ ግንዛቤዎች

 

 

ኣስተያየት በዶክተር ዮሃንስ ኣበራ ግንዛቤዎች

 

በቀለ ብርሃኑ May 12, 2020

 

ይህ ጽሁፍ ዶር ኣበራ ዮሃንስ የጻፉትን መልአክት ተንተርሶ የተጻፈ ነው፥፥ ኣንባቢው በርከት አንዲል በሚል በኣማርኛ መሞከሩ የሚሻል ስልመሰለኝ ልምዱ ባይኖረኝም አነሆ፦

 

ዶክተር ዮሃንስ በጣም የምከታተላቸው ጸሃፊና ተንታኝ ናቸው፥፥ በብዛት የሚያቀርቧቸው ኣስተያየቶችና ኣስተሳሰቦች ከኔው ጋር ይመሳሰላሉ ወይም ይቀራረባሉ፥፥

 

ስሞኑንን ስለኢትዮጵያና ትግራይ ኣንድነት የጻፉት ቁም ነገር በጥሞና መታየት የሚገባው ነው፥፥ ስለዚህ ጉዳይ ወደፊት ኣጭር ነገር ለማለት አፈልጋለሁ፥፥ ለጊዜው ዋናው መገንዘብ ያለብን ነገር ግን የትግራይ ኢትዮጵያዊነት ፍጹም መሆኑ ነው፥፥ ማንም ተነስቶ በዘለፈንና ባስፈራራን ቁጥር የምናፈገፍግ ከሆነ ሌሎች ችግሮች በመጡ ቁጥር በተመሳሳይ ሁኔታ ላይ ላለመገኘታችን ዋስትና ኣይኖረንም፥፥

 

Videos From Around The World

የዛሬው ኣስተያየቴ ምርጫን በሚመለከት የጻፉትን ይመለከታል፥፥ የምርጫ ማዘግየቱን ሃሳብ በተከፋፈለ ልብ ሳልቀበለው የምቀር ኣይመስለኝም፥፥ የኔ ምክንያቶችና ኣማራጭ መፍትሄ ግን ትንሽ ለየት ዪላል፥፥

ፒፒ ፓርቲና ህውሓት ላይ ያለኝ አይታም ከ ኣመሪካና አትዮጵያ አንግሊዝኛ በላይ ነው ብየ ገምታለሁ

 

ለመነሻ ይሆነን ዘንድ ፈደራሊዝምን በሚመለከት የኢትዮጵያውያን ኣመለካከት ወይም ኣረዳድ ኣንድ ኣይመስለኝም፥፥ የፈረንጆቹን የፈደራል ኣወቃቀር ከሆነ የምንከተለው አያንዳንዱ የፈደርሽኑ ኣካል የሆነ ክልል ወይም ግዛት የሚኖረው መንግስት ከፈደራሉ መንግስት በምንም መልኩ የተለየ ነው፥፥ ኣንድ ኣይነት የፖለቲካ አይታ ያላቸው ሆነው ከተገኙ ይህ ያጋጣሚ ጉዳይ ነው፥፥ ለምሳሌ ያክል በፈድራሊዝም ብዙ የማትታማው ኣሜሪካ አንኳ ፈደራል (ማአከላዊ) መንግስቱ የሚተዳደረው በኣክራሪዎች አኩሌታ የሚሆኑት ግዛቶች ደግሞ በለዘብተኞች ነው የሚተዳደሩት።

 

፩፥ መሰረታዊ መነሻ ሃሳብ

 

)= ልብ አንበል፤ ክልላዊና ፈደራላዊ ፓርቲዎች የተለያዩ ናቸው። ኣንድ ፓርቲ ባንድ ጊዜ ክልላዊም ፈደራላዊም መሆን ኣይችልም። ህውሓት፤ ባይቶና ሌሎች ትግራይ ዉስጥ የሚፎካከሩት ፓርቲዎች ተጠሪነታቸው ለክልላቸው ነው፥፥

)=በፌደራል ደረጃ መሳተፍ የሚፈልጉ ሃይሎች ከሌላ ተመሳሳይ ኣስተሳሰብና ፕሮግራም ካላቸው ቡድኖች ጋር በመስማማት ኣገራዊ ፓርቲ መመስረት ዪኖርባቸዋል፥ ለምሳሌ ኣገራዊ ፈደራሊስት ፓርቲ፤ የኢትዮጵያ ዲሞክራቲክ ፓርቲ፤ የብልጽግና ፓርቲ፤ ወዘተ

በዚህ ላይ መስማማት ካለን በሚቀጥለው ድምዳሜ ላይ ልንስማማ የግድ ነው፥ ይህም ብልጽግና ፓርቲ አንኳን ሳይመረጥ ተመርጦም ትግራይን ማስተዳደር የማይችል መሆኑ ነው፥፥ በፈደራል ደረጃ ግን ትግራይ ዉስጥ ገብቶ ቅርንጫፎችን መክፈት ዪችላል፥፥

አንግዲህ ኢትዮጵያ ዉስጥ ኣዲስ ኣሰራር ካልተፈጠረ በስተቀር ይሀ የፈድራሊዝም ሃሁ ማንም ፖለቲከኛ ኣስቀድሞ ሊያውቀው የሚገባ መመርያ መሆን ኣለበት።

የነ ኣቶ ነቢዩ ስሑልና የጠቅላይ ሚኒስትሩ ኣስተሳሰብ ከዚህ አይታ በመነሳት ቢቋጭ ይበጃል ባይ ነኝ፥፥ ለሁሉም ልክ ኣለው፡

ለዚህም ነው የህውሓትና ብጽግና ልዩነቶች ከኣማሪኛ ና ኣመሪካንኛ አንግሊዝኛ ባሻገር የመሰለኝ።።

 

) የምርጫ ጉዳይ፤

አውነትን የምንሻ ኢትዮጵያውያን ባንዳንድ ጉዳዮች ላይ መስማማት የሚኖርብን ዪመስለኛል፥ የኢትዮጵያ መንግስት ምርጫውን ያራዘመው በኮረና ቫይረስ ምክንያት ብቻ አንዳልሆነ ማመን ተገቢና ኣስፈላጊም ነው፥ ምርጫ ለማድረግ ዝግጁነትና ፈቃደኝነት ኣልነበረዉም። በዚህ ላይ ብዙ ማለት ጊዜ ማባክን ስለሆነ አንለፈው።

ኣሁን አዚህ ደርሰናል፥ ፈደራል መንግስቱ ምርጫን ኣሻፈረኝ ብሏል፥፥ ህግ የማይገዛው ስለሆነ በዚህ ላይ አንካስላንትያ መግባቱ ኣያስኬደንም፤፤

በኔ አይታ የትግራይ ክልል ብቻውን የኢትዮጵያ ደሞክራሲ ብቸኛ ታጋይ በመሆን ለጭዳ መቅረብ ያለበት ኣይመስለኝም፤፤ ትግራይና የትግራይ ህዝብ ለብዙ ኣመታት ያለ ኣንዳች መካች ሲታማ፤ ሲሰደብ፤ ሲዶለትበት ቆይቶ ኣሁን በክፉ ሃይሎች ፕሮፓጋንዳ የጥላቻ ቀለበት ዉስጥ ገብቷል። ኣሁን ይበቃል መባል ኣለበት፥፥

አናም ህወሓት ባገር ደረጃ ኣሁን ምርጫ መካሄድ ኣለበት የሚለዉን ኣቋሙን ማስተካከል የኖርበታል፥፥ ይህንንም ለማድረግ ከተመሳሳይ ሃይሎች ጋር ድርድር የግድ ነው፥፥ ነገሮችን ማርገብ የሚጠቅመው ዋናው የትግራይን ህዝብ ፡ ያ ሳይበላ በላ ተብሎ የሚታማዉን ህዝብ ነው።

 

ምርጫዉን በሚመለከት ኣንድ ነገር በጥሞና መታየት ኣለበት፥ ይህዉም ምርጫ ከኮረና በሁዋላ የሚሉት ኣስተሳሰብ ነው፥፥ ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ ኣይታደርም፥፥ ኮሮና ቫይረስ መችና አንዴት አንደሚሄድ የሚያውቅ ሰው የለም፤፤ አንደማንኛውም የ ፍሉ (ጉንፋን) ኣይነት ዘላቂ ሊሆን ይችላል ወይም ሊጠፋ ዪችላል። አናም አንዲህ ኣይነቱ አሳቤ ልቅ (open-ended) መሆን የለበትም፤፤ ስለዚህም ከፈደራል መንግስቱ ጋር የሚደረጉት ድርድሮች ይህን ያገናዘበና ያም አስኪሆን ድረስ መንግስት የሚሰራቸው ነገሮች ዉስን አንዲሆኑ መረዳቱና ማስረዳቱ ተገቢ ዪሆናል።

 

ክልላዊ ምርጫ

ዶክተር ዮሃንስ ኣበራ በትግራይ ዉስጥ፡ የምርጫው ዉጤት (በዲሞክራሲ አጦትም ዪሁን ህወሓት ባሁኑ ጊዜ ባገኘችው ቅቡልነት)አርግጠኛ በሆነበት ጊዜ ምርጫ ማካሄድ ፋይዳ አንደሌለው ሞግተዋል፥፥ ያካባቢዉን ሁኔታ ባላውቀዉም ሙግቱ ዋጋ አንዳለው ዪገባኛል፥፥ ኣከራካሪ ነው፤ ግን ከላይ ልገልጸው አንደሞከርኩት አኔም ብሆን ትግራይን ከኣውሎ ነፋሱ ዓይን (eye of the storm) ለመክላክል ሲባል ኣገራዊው ምርጫም ክ
ላዊ ምርጫ ቢዘገዪም ጉዳቱ ከባድ ኣይሆንም ብየ ኣስባለሁ፤፤

 

በሌላ በኩል ሲታይ የተጻፉ ኣገራዊና ክልላዊ ህጎች ማንም አንዳሻው የሚሽራቸው ከሆነ ኣገር የለምና ኣማራጭ ህጋዊ መፍትሄዎች መሻት የግድ ነው። ስለዚህም ለትግራይ ህዝብ ኣማራጭ የሚሆን ምን ህጋዊ ኣማራጭ ኣለ ብሎ ማሰብ ተገቢ ነው። ይህ ህጋዊ ኣማራጭ ለትግራይ ህዝብ ጥሩ የዲሞክራሲ ልምድ ይሰጠዋል ብየ ገምታለሁኝ።

 

ጊዜያዊ ኣማራጭ፤

 

አንደሰማሁት ትግራይ ዉስጥ ኣራት ፓርቲዎች አንዳሉ አሰማለሁ። የኔ የመፍትሄ ሃሳብ በነዚህ ዙርያ ያጠነጠነ ነው፥ ይህዉም ኣራቱ ፓርቲዎች ተደራድረው አስከሚቀጥለው ምርጫ ድረስ ትግራዪን አንዲያስተዳድሩ ነው፤፤ ይህ ኣካሄድ ኣዳዲስ ፓርቲዎች ኣስተዳደራዊ ልምድ አንዲቀስሙ ከማድረጉም በላይ የፖለቲካ ምህዳሩን በማስፋት በኩል በጎ ሚና ዪጫወታል ባይ ነኝ፤፤

ህጋዊ ኣማራጭነቱና ዝርዝር ጉዳዩን በሚመለከት የህግ ኣዋቂዎች ቢያክሉበት መልካም ነው በሚል ነገሬን ልቋጭ።

 

 

Back to Front Page