ግልፅ ደብዳቤ ለኢፌዲሪ ህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባላት

 

Tignen Tidmek 02-21-20

 

እንደሚታወቀው ለአምስት አመት አገራችን ለማስተዳደር የተመረጠው ኢህአዴግ እንደሆነ የኢትዮዽያ ህዝብና እናንተም የምታውቁት ጉዳይ ነው ። ኢህአዴግ የተመረጠበት ዋናው ምክንያትም ያነገበው የፖለቲካ ሪኦተዓለም እሱም አብዮታዊ ዴሞክራሲ ነው እናንተ የኢፌዲሪ ህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባላትም የተወከላችሁበት መሰረታዊ ምክንያት ይህንን ዓላማ ለማስፈፀም ነው ከዚህ በተጨማሪም የአገራችን ከፍተኛ ስልጣን ያላችሁ አካል ናችሁ ማንኛውም ባለስልጣን ከዚህ ፓርላማ በምንም ተአምር ሊበልጥ አይችልም በአገራችን የህገመንግስት ጥሰቶች እንዳያጋጥሙም በከፍተኛ ደረጃ ክትትልና ቁጥጥር የማድረግ ሃላፊነት በናንተ ላይ ነው የተጣለው   የኢትዮዽያ ህዝብ ወክላችሁ በተወካዮች ምክርቤት የተቀመጣችሁበት ዓላማና ተልዕኮም መንግስት የሚደርጋቸው እንቅስቃሴዎችን መከታታል ፣ ህጋዊነታቸውን ማረጋገጥ ፣ የህግ ጥሰቶችን ማስተካከል ፣ ወዘተ ይመስለኛል

 

Videos From Around The World

ታድያ አሁን ያለው ተጨባጭ ሁኔታ ስናየው በርካታ የህገመንግስት ጥሰቶች እየተፈፀሙ ያሉበት ወቅት ያለን ይመስለኛል ለምሳሌ ያህል በስረ አስፈፃሚው አካል ከተለያዩ አገሮች እየተፈፀመ ያለው ውሎች ምክርቤቱ የሚያውቀውና የተስማማበት አይመስለኝም ከነዚህ ስምምነቶችም አንዳንዶቹ ያገራችን ሉአላዊነትና ክብር የሚደፍር ሊሆኑ ይችላሉ ።ይህን ዓይነት የህግ ጥሰት ሲፈፀም ፓርላማው ጠቅላይ ሚኒስትሩን በጥብቅ መጠየቅ ያለበት ይመስለኛል ።በጠራራ ፀሃይ የህዳሴ ግድባችን ምርጥ ማኔጀር ላገሩ ሌት ተቀነ በበረሃ ላገሩ ግድቡን ለመፈፀም እየተጋ በነበረበት ጊዜ በሴራ ሲገደል ፣ ብርቅዬ ጄነራሎቻችን በሴራ ሲገደሉ ፣ ከፍተኛ የክልል አሰተዳዳሪዎች በሴራ ሲገደሉ ፣ የጃዋር መሓመድ ጠባቂዎች ለተመሳሳይ ግድያ አይነት ለመፈፀም የሚመስል አይነት ድርጊቶች ሲከሰቱና እነዚህን ያሴረና ግድያውን የፈፀሙ በቁጥጥር ስር ውለው ፍርድ ሲገኙ አላየንም የፍርዱ ሁኔታና ዘገምተኝነት ስናየው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጀምሮ ተሳትፎ ያላችው መሆኑን የሚያስጠረጥር ዱጋይ ሆኖ እያለ ፓርላማው በገለልተኛ አካል እንዲጣራና ሃቁ እንዲወጣ ፓርላማው ያደረገው የሚረባ እንቅስቃሴ አላደረገም በጣም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ተፈናቅሎ የሚላስ የሚቀመስ አጥቶ የድረሱልኝ ጥሪ በሚያሰማበት ጊዜ ፓርላማው በተወካዮቹ በኩል ጉዳዩን ለማወቅ ብሎም አስቸኳይ መፍትሄ እንዲያገኝ እቦታው ድረስ ሆዶ ማየትና ማጣራት ሲገባው ይህ ነው የሚባል እንቅስቃሴ ሲያደርግ አልታየም የህዳሴው ግድብ በተመለከተ አገራችን አሁን ያለችበት ሁኔታ መሰረት ወደ ድርድር የሚስገባ እንዳለሆነና ስንረጋጋ ማድረግ ውይም ደግሞ ከዚህ በፊት በተነደፋው በናይል ተፋሰስ ሃገሮች ብቻ መታየት አለበት የሚል አቋም መያዝ ሲገባ የኢትዮዽያን ጥቅም በማያስከብር ሁኔታ የሶስተኛ ወገን ባለበት ድርድር እየተካሄደ ፓርላማው ዝም ብሎ ማየት በጣም አሳዛኝ ነው

በተጨማሪም ደቡብ ክልልና ምዕራብ ኦሮምያ የህዝብ ተወካዮች በማያወቁት ሁኔታ በኮማንድ ፖስት እየተዳደረ ነው ያለው ለዚህም ፓርላማው ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጠርቶ በጥብቅ መጠየቅ ያለበት ይመስለኛል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢትዮዽያ ህዝብ ስም የተገኘ በቢልዮን የሚቆጠር ብር ለቤተመንግስትና ለመሳሰሉት ማስዋብያ ሲያዝና ወጪ ሲያደርግ ህገ መንግስታዊ ጥሰት መሆኑ ታውቆ ፓርላማው ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጠርቶ በጥብቅ መጠየቅ ያለበት ይመስለኛል የመከላከያ ተቋማችን ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደፈለጉት በአጭር ጊዜ በጣም ብዛት ያለው ወታደራዊ አመራር በጥሮታ ሲያስወግድ አሁን ካለንበት ሁኔታ ጋር ስናገናዝበው በእውነት ኢትዮዽያን ለመጥቀም ነው ወይስ ማዳከም ብልን ብንጠይቅበኔ እይታ ሆን ተብሎ የነበረውን ጠንካራ መከላከያ ሰራዊት የማዳከም ስራና ለጠቅላይ ሚኒስትሩተላላኪ የሆነ መከላከያ ሰራዊት የመፍጠር አካሄድ መስሎ ይታየኛል ። ታድያ ይህንን ጉዳይ እንደ ኢትዮዽያዊ ፓርላማው ሊያንገበግበው አይገባም ? ለዚህም ፓርላማው ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጠርቶ በጥብቅ መጠየቅ ያለበት ይመስለኛል በአጭር ጊዜ በርካታ የሚኒስትሮች ሹምሽር ማካሄድ ውጤታማነቱ ሳይፈተሽ እንዲሁ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የማሾም ስልጣን ስላለው ብቻ ለሹምሽር ሚኒስትሮችን ለሹመት ሲያቀርብ ያለምንም አሳማኝ ምክንያት ፓርላማው እንዲሁ መራቂና አፅዳቂ ብቻ መሆን ያለበት አይመስለኝም ከዚህም አልፎ በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በህጉና ስርዓቱ መሰረት ወደ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ሳያቀርብ ሚኒስቴር እንደሾመ ፣ ይህንንም ምን ያህል ለፓርላማው ያለው ንቀት በግልፅ ያሳየበት ሁኔታ ነው የሚያሳየው ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ክህገ መንግስት ውጭ ወደ ተወካዮች ምክርቤት ሳያቀርብ ሚኒስቴር ሾመው ከጨረሱ በኃላ ተሹሞ ያለቀለት በድጋሚ ወደፓርላማው በሚያቀርብበት ጊዜ ፓርላማው ጠቅላይ ሚኒስትሩን መገሰፅ ፣ ይቅርታ እንዲጠይቅ ማድረግና የመሳሰሉት እርምጃ መውሰድ ሲገባው መርቆና አፅድቆ ማለፍ ፓርላማው ማድረግ የነበረበትን አላደረገም

 

እነዚህንና የመሳሰሉት የህግ ጥሰቶች በተከታታይና በስፋት እየተፈፀሙ የኢትዮዽያ የህዝብ ተወካዮች እያዩ እንዳላዩ መሆን በከፍተኛ ደረጃ የተወከሉበትን የህዝብ አደራ ያለመፈፀም ብቻ ሳይሆን ለወከሉት ህዝብም መካድ እንደሆነ ያመላክታልታድያ የተወካዮቻችን አይተው እንዳላዩ ሰምተው እንዳልሰሙ መሆን ፣ የዜጎች ሰቆቃ ቢያንስ በከፍተኛ ደራጃ መቀነስ እየተቻለ ተወካዮቻችን የተጣለባቸው ሃላፊነት ባላመወጣታቸው በአገሪቱ ከፍተኛ ችግር እንዲከሰት እንደመተባበር ይቆጠራል እነዚህ ጥቂት ለአብነት ያህል የተጠቀሱት እንደ የተወካዮች ምክርቤት አባል አላወቅኩም አልሰማሁም ፣  እንደ አንድ ጉዳይ ተነስቶ አያውቅም እንዳትሉ በተላያዩ ማህበራዊና ዓለማቀፋዊ ሚድያዎች በተደጋጋሚ ሲራገብ እንዳለ ስለሚታወቅ ማመካኘት እንደማትችሉ ብትገነዘቡ ጥሩ ይመስለኛል እኔ እንደ አንድ ኢትዮዽያዊ ዜጋ ከአንድ የህዝብ ምክርቤት ተወካይ የምጠብቀው ስብእና ንቁና ጠንካራ ፣  ለህዝቦች ሰላም ፣ ነፃነት ፣ ዴሞክራሲና ፍትህ ለማስከበር በቆራጥነት ከስሩ ያሉትን ስራ አስፈፃሚ አመራሮች ሁሉ የሚጠይቅና የሚያስተካክል እንጂ ስሜቱ የተሰረቀ ፣ ይህንን ከተናገርኩኝ ስራ አስፈፃሚው በሰበብ አስባብ ሊያስረኝ ፣ ሊያንገላታኝ ይችላል ፣ ወዘተ ብሎ የሚሰጋና የፈሪ ስብዕና ያለው ሰው አይደለም ስለዚህ ከምርጫም በኃላም ቢሆን እያንዳንዱ የፓርላማ ተወካይ የኢትዮዽያ ህዝብ የጣለበትን ከፍተኛ የህዝብ አደራ ባለመወጣቱ መጠየቅ እንዳለበት ብሎም ከፍተኛ የሚባለው ቅጣት ሊጠብቀው እንደሚችል መገንዘብ ያለበት ይመስለኛል ስለዚህ ጨው ለራስህ ብለህ ጣፍጥ እንደሚባለው እያንዳንዱ የህዝብ ተወካይ ውሎ አድሮ ከመጠየቅ ስለማያመልጥ እስከ የሂወት መስዋዕትነትም ቢሆን በመክፈል የአገራችን ህገ መንግስትና ሉአላዊነት እንዲከበር መጣር እንዳለበት እገነዘባለሁ

በአሁኑ ወቅት የሰው መብት መረገጥና የህገ መንግስት ጥሰቶች ሲፈፀሙ ከማንኛውም ኢትዮዽያዊ ዜጋ በላይ ሊያንገበግበውና ሌት ተቀን መስራት ያለበት እያንዳንዱ የምክርቤት አባል ይመስለኛል ታድያ ይህንን ወቅት እንዲሁ እንደማንኛውም ወቅት ዝም ብሎ መመልከት የህዝብ ተወካይ በህዝብ የተጣለበትን ከፍተኛ አደራ እንዳልተወጣና እንደ ተራ ግድፈትም መታየት ያለበት አይመስለኝም ስለዚህ እኔ እንደ አንድ ኢትዮዽያዊ እያንዳንዱ የህዝብ ተወካይ የተመደበለት አምስት ዓመት ወደ መገባደዱ ቢሆንም ከተገባደደ በኃላ በህግ እንዲጠየቅ መደረግ አለበት የሚል አስተያየት አለኝ በህግ እንዲጠየቅ አስተያየት የምሰጥበት ዋና ምክንያትም ለመጪው ጊዜም ማንኛውም የህዝብ ተወካይ የተጣለበትን የህዝብ አደራ ገሸሽ በማድረግ የግል ፍላጎቱንና ስሜቱን እንዳያስቀድም ስለሚረዳ ፣ አስፈፃሚው አካልም እንዳሰኘው ህግ እየጣሰ ፈላጭ ቆራጭ እንዳይሆን ፣ ፓርላማው የበላይ አካልና ስራ አስፈፃሚውም ለፓርላማው የሚታዘዝ እንዲሆን ፣ የህዝብ ተወካይም እውነተኛ የህዝብ ተወካይ መሆኑን የሚያጠናክር ስለሆነ እያንዳንዱ የህዝብ ተወካይ ባለፉት ዓመታት በፓርላማው በተጨባጭ የነበረውን መፋዘዝ ወይም የህዝብ አለኝታና ዘበኝነት በውል ተመርምሮ አስፈላጊውን የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ በህግ መጠየቅ አለበት

ሌላው በጣም የሚያሳስበው ጉዳይ ደግሞ በቅርቡ እንደሰማነው እያንዳንዱ የምክርቤትአባልም እንደሚያውቀው ኢህአዴግ ፈርሰዋል የሚል ነው ለአምስት አመት አገራችን ለማስተዳደር የተመረጠው ኢህአዴግ እንደሆነ የኢትዮዽያ ህዝብና እናንተም የምታውቁት ጉዳይ ነው ። ኢህአዴግ የተመረጠበት ዋናው ምክንያትም ያነገበው የፖለቲካ ሪኦተዓለም ማለትምአብዮታዊ ዴሞክራሲ ለመተግበር በምርጫ ወቅት ለህዝባችን ቃልኪዳን ስለገባችሁ ነው እናንተ የኢፌዲሪ ህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባላትም የተወከላችሁበት መሰረታዊ ምክንያት ይህንን ዓላማ ለማስፈፀም ነው ኢህአዴግ ፈርሰዋል ከተባለ በአሁኑ ሰዓት በምክርቤቱ ተቀምጣችሁበት ያለው ወንበር በየትኛው የህግ አግባብ ነው? ከአራቱም የኢህአዴግ ፖለቲካ ፓርቲዎች ሶስቱም ማለትም ከህወሓት በስተቀር ወደ ብልፅግና የሚባልአዲስ የፖለቲካ ፓርቲ አዲስና የተለየ የፖለቲካው ሪኦተ ዓለም ፣ ከአብዮታዊ ዴሞክራሲ ውጭ የሆነ ሪኦተዓለም የሚያራምድ ፓርቲ ተቀላቅላችኃልስለዚህ እያንዳንዱ የሶስቱ ተቀላቃይ ፓርቲዎች በተወካዮች ምክርቤት ወንበር መቀመጥ ከህግ ጥሰት በላይ ነው የተቀላቃይ ፓርቲ አባላት ወደ ብልፅግና ከተቀላቀላችሁበት ጊዜ አንስቶ እንደ የፓርላማ አባል የመቀመጥ ህጋዊ መሰረት የላችሁም ስለዚህ ከዛች ቀን ጀምሮ የሚደረጉ ውሳኔዎች ህጋዊነት አይኖራቸውም ክዛች ቀን ጀምሮ ለምታደግሩት እንቅስቃሴ በኢትዮዽያ ህዝብ ንብረት ያለህጋዊ መሰረት መጠቀም ሰለሚሆን ከተጠያቂነት ማምለጥ አይቻልም

በኔ አመለካከት ሁለት አማራጭ ያላችሁ ይመስለኛል 1ኛ በፓርላማው ለመቀጠል ኢህአዴግነታችሁ መልሳችሁ ፕሮግራማችሁም አብዮታዊ ዴሞክራሲ መሆኑን በመግለፅና ለኢትዮዽያ ህዝብ  ከፍተኛ ይቅርታና ድጋፍ እነዲቸራቹ በማድረግ በነበረው የተወካዮች ምክርቤት ወንበር መቀጠል2ኛ አሁን ተቀምጣችሁበት ያለው ወንበር ልትቀመጡበት የህግ መሰረት ስለሌላቹ በክብር መልቀቅ ከዚህ ውጭግን በፓርላማው በመቀጠል የአገሪቱን ሃብት የመጠቀም መብትም ስለማይኖራችሁ ከወዲሁ መገንዘብ ያለባችሁ ይመስለኛል ከዚህ በኃላ የሚደረገው ማንኛውም የምክርቤት ውሳኔ ህጋዊነት የሌለው መሆኑን አውቃችሁ ህግ የማክበር ተግባር እንደማንኛውም ተራ ዜጋ የበኩላችሁን እንድትወጡ ለማሳሰብ እፈልጋለሁ

 

ቸር እንሰንብት !!

tidmektignen@gmail.com

 

 

Back to Front Page