Back to Front Page

አሁንስ ወዴት ? ( ሕዚኸ ናበይ)

አሁንስ ወዴት ?  ( ሕዚኸ ናበይ)

ሙሉጌታ በሪሁን ኻብ ሃገረ ካናዳ

 

     በመጀመርያ ይህ ፅሁፍ፣በግሌ እንደ አንድ ትግራዋይ፣በህዝቤ ላይ እየተፈፀመ ያለው የዘር ማጥፋት ዘመቻ በመቃወም ፣ መሆን አለበት ብዬ የማምንበትን ሃሳብ ሳቀርብ፣በትግራዋይነት ስነልቦናዬ ግፍም ገደብ ስላለው በቃኝ ብዬ ስለወሰንኩኝ ነው።

 

በመቀጠል ይህንን ፅሁፍ የራሴ፣ኩራቴ የሆነ ቋንቋ ትግርኛ ቢኖረኝም፣ነገደ አግአዚያን ስለሆንኩኝ፣የግእዝ ቋንቋ ባለቤት እንደመሆኔ መጠን፣ግዕዝ ደግሞ የትግርኛና፣የአማርኛ እናት እንደመሆኑ፣የፈለኩትን በመምረጥ የባለቤትነት ኩራት ስለሚሰማኝ ብቻ ሳይሆን፣ የተቀረው የኢትዮዺያ ህዝብ ታሪክ በማገላበጥ ሃቁን እንዲረዳ በማሰብ ነው።

 

ከምንም በፊት፣ይህ ሁሉ ግፍ በትግራይ ህዝብ ለምን አስፈለገ፧ የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ቅድሚያ፣ የተጋሩና፤የአማራይቱ ኢትዮዺያ ታሪካዊ ማንነት መረዳት ያስፈልጋል።

 

     ኢትዮዺያ የምትባለው ሃገር በንጉስ ሚሊሊክ ከአቢስንያና የጣልያን ጦርነት ከ1886 ባኃላ የተመሰረተች ስትሆን፣ ከዚያ በፊት በሃፄ ዮውሃንስ 4ተኛው ስትመራ የነበረች፣እንደነ ባህረ ነጋሽ፣ ትግራይ፣ በጌምድር፣ ወሎ፣ ጎጃም፣ሸዋ፣ዓፋርና፣ የአርሲን አከባቢዎች የሚያጠቃልል የግዛት ድምበር እንደነበራት ከታሪክ ተረድቻለሁኝ። ከተሳሳትኩኝ ለመታረም ዝግጁ ነኝ። ከዛ በፊት አፄ ቴድሮስም ኢትዮዺያ የሚለውን አሃዳዊ ሃገር፣ ለመመስረት ጥረት በማድረግ ላይ እዳለ ፣በእንግሊዝ ጦር ተሸንፎ፣ የራሱን ሂወት ማጥፋቱ ታሪክ ያስረዳናል።ከዛ በፊት ደግሞ ኢትዮዺያ ወይንም በግዜው አጠራር አቢስኒያ ለ125 ዓመታት፣ የዘመነ መሳፍንት ጊዜ ተብሎ የሚታወቅ መሆነን ታሪክ ያስረዳናል።  በሌላው ገፅታ ስናይ ደግሞ፣የአክሱም ስልጣኔ፣የአክሱም ዘመነ መንግስት ተብሎ የሚጠራ የስርአተ መንግስት ከ2000 ዘመን በላይ ያስቆጠረ ስልጣኔ፣ በወሬ ሳይሆን በማስረጃ መሬት ላይ በሚታዩ ታሪካዊ ቅርሶች፣እንደነ የአክሱም ሃወልት፣የንግስተ ሳባ ፍርስራሽ ቤተመንግስት፣የነ ንጉስ ሮምሓይ ስልጣኔ፣ እንደ ይሓ ቤተመንግስት፣የነ ሃፀይ ካሌብና፣የሃፀይ ገብረ መስቀል ቤተመንግስትና፣ ሌሎች ጭብጥ ታሪካዊ ቦታዎች መጥቀስ ይቻላል። ስለዚህ በታሪክ ይሄ በአማራይቱ ኢትዮዺያ፣የሚቀርበው የባለቤትነት፣የኔነት ውርስ፣ የትግራይ ህዝብ ሃብትና ታሪክ ነው።

Videos From Around The World

 

ታድያ በአሁኑ ስአት፣ኢትዮዺያ እንደ ሃገር ያላትን ወታደራዊ ሃይል፣የ8ቱ ክልሎች ሚልሻና ልዩ ሃይል፣የአማራ ፋኖ፣የአማራ ልዩ ሃይልና ሚሊሻ፣ይህ አልበቃ ብሎ የሻዕብያ፣ሙሉ ሰራዊት፣የአረብ ኤምሬት ሰው አልባ የጦር አውሮፕላን በመጠቀም፣በትግራይ ህዝብ ላይ ከጥቅምት 24 2013 አም ጀምሮ እስከ አሁኗ ደቂቃ ድረስ፣ በአየርና በምድር ህዝቡን እያጠፉት፣የመሰረተ ልማት አውታሮችን፣መንግስታዊና የግል ባለሃብቶች ንብረት በማውደም ላይ ናቸው።  ግን ለምን ?

 

   እንደ ግለሰብም ይሁን እንደ ሃገር፣አንዱን አንዱን ሊያጠፋው የሚነሳሳበት ዋናው ምክንያት ለፅድቅ አለመሆኑ እንኳን ሰው፣ሰይጣን ያውቀዋል፣አማራይቱ ኢትዮዺያም ሆነ የኤርትራው ጭራቅ መንግስት ይህን ሁሉ በደልና ግፍ በአንድ ማህበረሰብ ሲያወርድ፣እረ ተዉ ወገኖቻችን ናቸው ብሎ የተቃወመ፣ አንድ ኢትዮዺዊ እንኳን አለመኖሩ ሲገርመን፣ ጭራሽ ጦርነቱን በመደገፍ የተሰጠው የፖለቲከኞች፣የሃይማኖት መሪዎች ቡራኬና የህዝቡ ድጋፍ መመልከት ግን ከሰብአዊነት የወረደ ተግባር መሆኑና፣ ተጋሩ ኢትዮዺያዊነት የሚለው ዜግነት አሽቀንጥረን የጣልንበት ክስተት ላይ ደርሰናል። እንዲህ ስል ግን ተጋሩ ሆነው ለጥቅምና ለሆዳቸው ሲሉ የደገፉ ሰዎች የሉም ማለቴ አይደለም። ለምሳሌ እንደነ አረጋዊ በርሄ ፣አብርሃም በላይ ፣ስሑል ሚካኤል፣ ሙሉ ነጋ ወ.ዘ.ተ የመሳሰሉ ግለሰቦች ይገኙበታል። ዋናው ጥያቄ ለምን ? እነዚህ ሁለት ግለሰቦችና እነሱ የወከሉት ማህበረሰብ

 

   የትግራይን ህዝብ ከዚህ ምድር ለማጥፋት ለምን ፈለጉ ? ሁለቱም የየራሳቸው ምክንያትና ፍላጎት ስላላቸው ነው። የሁለቱም በየተራ በግል እምነቴና አረዳዴ ለማብራራት እሞክራለሁኝ። ነገር ግን ነፃ በሆነ ሚዛናዊ አስተሳሰብ፣ እምነቴንና ሃሳቤን ለታሪክ ማስቀመጥ ስለምፈልግ፣የግለሰቦች ወይንም የፖለቲካ ድርጅት፣ፍላጎት ወይንም ስሜት ላለመንካት ብዬ የምሸፋፍነው እውነታ አይኖረኝም።

 

   አማራይቱ ኢትዮዺያ፣በኩራት የኔ ብላ የምትመፃደቅባቸው ታሪክ፣ፊደል፣ቁጥር፣ሃይማኖት፣ያሬዳዊ ዜማዎችና ባህላዊ ትውፊቶች ፣ ሁሉም ከ3ሺ ዘመን በላይ ያስቆጠሩ ቅርሶች መሰረታቸው አክሱም፣ ትግራይ ቢሆንም። የባለቤትነት ይዞታቸው ግን የአማራ እንደሆነ ተደርገው ላለፉት 150 ዓመት በግልፅ ፣ ከዛ በፊት ደግሞ ከ13ኛው ክፍለ ዘመን ማብቂያ ፣ ማለት ከንጉስ ላሊበላ በኃላ እያቆጠቆጠ የመጣው የታሪክ ብረዛና ፣ ሃይማኖታዊ ቅጥፈት ላለፉት 700 አመታት የሽዋ አማሮች ፣ በረቀቀ ጥበብ እየሰሩበት መጥተዋል። ከተንኮላቸው አንዱ ንግስናን ከብቃት ወደ ፣ ዘር ሓረግ ለውጠው ፣የራሳቸው የሆነ ንጉሳዊ ሃረግ ከአክሱሙ ንጉስ ምኒሊክ የዘር ሃረግ አለን ብለው ቀጣጥለው ፣ለዚሁ እባባዊ ሰራቸውም ሃይማኖታዊ ድጋፍ በመስጠት፣ለረጅም ጊዜ ሰርተውበት በተለይ ከንጉስ ሚሊሊክ በኃላ ሃይማኖትና ፖለቲካ በማቖራኘት ለ130 ዓመት በአሰቃቂ ሁኔታ ፣የኢትዮዺያን ህዝብ ገዝተዉበታል።

 

    በተለየ መልኩ ግን የትግራይ ህዝብ፣ታሪኩን፣ባህሉን፣ቅርሱን ዘርፈው የማይገባውን ስም በመለጠፍ፣ራሱን አቀርቅሮ፣በማንነቱ አፍሮ ፣ እነሱ የሚሉትን ሳያላምጥ እንዲውጥ፣ያላረጉት ተንኮል፣ያልፈፀሙት ግፍ ፣ያላቀነባበሩት ክህደት የለም። ክህደቶቹስ ምንድናቸው ?

 

    ክህደቶቹ ከላይ የጠቃቀስኳቸው፣ታሪካዊ፡ሃይማኖታዊ፡ባህላዊ፣ብቻ ሳይሆኑ የጀግንነት ሌብነትና፣ቅጥፈትም ያለ ምንም ሃፍረት ሲዘግቡና፣ሲተርኩ መስማትና ማየትም ችለናል። ለምሳሌ አማራይቱ ኢትዮዺያ ፣ ጣልያንን ለመጀመርያ ግዜ በአድዋ ጦርነት ላይ ድል ያደረግን የመጀመርያዎቹ ጥቁር ህዝቦች እኛ ነን እያሉ ያወራሉ። ግን የዚህ ሁሉ ጀግንነት ባለቤት ደግሞ እምየ ንጉስ ሚሊሊክ ነው ይላሉ። እዚህ ላይ አንባብያን ሚዛናዊ ፍርዱ ለናንተ ልተወው። በርግጥ ንጉስ ሚሊሊክ በወቅቱ የነበረ የሃገር መሪ እንደመሆኑ ጥሩውንም ፣መጥፎውንም  ተወቃሹና የሚመሰገነውም እሱ ነው ስለዚህ ጀግንነቱም በማን ይመራ ሁሉም በንጉስ ሚሊሊክ ስም ይሆናል።ነገር ግን ይህ ጦርነት መጨረሻው እንጂ መጀመሪያው አይደለም፣እንደ ኢትዮዺያዊያን ከዛ በፊት የተደረጉት ጦርነቶች ለምን አለመግለጽ ተፈለገ ነው ሚስጢሩ።

 

    ጣልያን በተደጋጋሚ ቅስሙን የሰበሩት ንጉሰ ነገስት ሃጸይ ዮውሃንስ ፬ተኛው ሲሆኑ፣ የጦር መሪው ደግሞ ራስ አሉላ አባነጋ በዶግዓሊ ፣ በስሓጢጥና ፣ በጉራዕ፣ ከዓድዋው ጦርነት በፊት ነው። ለዚህ ነው አማራይቱ ኢትዮዺያ የውሸት ትርክት፣ታሪክ የሌላት የካሃዲዎች ሃገር ፣በሌሎች መስዋእትነት የተገነባች ዘላቂነት የሌላት ካብ ነች። ብትገፋት የምትፈርስ የውሸት ካብ የምለው።

 

ሰለዚህ የተጋሩን ገድል፣የተጋሩን ታሪክ፣ወደ ጎን እየገፋች ፣ ሲያሰኛት እራሷ እንደ ባለቤት፣እየዘባረቀች በውሸት ማንነት የተመሰረተች ሃገር ብትኖር፣ ኢትዮዺያ የምትባለው አገር ነች። ሌላው የታሪክ ውዥንብር ስለ አድዋው ጦርነት ነው። በመሰረቱ በአንድ ሃገር ጦርነት ሲካሄድ ፣የጦርነቱ የመጀመርያው ገፈት ቀማሽ፣ጦርነቱ የሚካሄድበት አከባቢና በስፍራው የሚኖሩ ሕዝቦች ናቸው። በታሪክ እንዳየነው ደግሞ ኢትዮዺያን ለመውረር የመጡ ወራሪዎች፣ ከግራኝ መሃመድና ከዮዲት ጉዲት ውጭ፣ቱርክ፣ግብፅ፣ጣልያን፣ሱዳን እንደ ዛሬው በአማራ ክልል የተወረረውን መሬቷን ለማስመለስ ሳይሆን፣ኢትዮዺያን እንደ ሃገር ስትወርና፣ የበጌምድር ህዝብ እባክህ አፄ ዮውሃንስ አድነን ሲባል ማለቴ ነው፣ምንም ሳያቅማማ ሃገሬን በማለት ሲወድቅና፣ሲዋደቅ የነበረው ግምባር ቀደሙ የትግራይ ህዝብ ነው። ታድያ ያኔ ጣልያን ኢትዮዺያ ስትወርም ፣ከማሃል አገር ሌላው የኢትዮዺያ ጦር እስኪ ደርስ ፣ ያለመታከት ለ7ወር የጣልያንን ጦር ገትሮ የያዘው የትግራይ ህዝብ ነበር። ሚሊሊክ ከሰራዊቱ ጋር ከደረሰ በኃላም፣ለዛ ሁሉ ጦር ስንቅና ደጀን ሆኖ ያስተናገደው የትግራይ ህዝብ ነው። ጦርነቱ ከተጠናቀቀ በኃላ ያጋጠመው የወገን ክህደት፣ ጦርነቱ ከተጠናቀቀ በኃላ፣የሚሊሊክ ጦር ለረጀም ጊዜ ትግራይ ላይ በመስፈር፣የድሃው ገበሬ ከብትና ማር፣እህል ያለ ዩልኝታ እየተቀለበ ቆይቷል፣ በዚህ ምክንያትም የትግራይ ህዝብ ጦርነቱ ካደረሰበት ቀውስ በላይ፣ የሚሊሊክ ጦር ያደረሰበት የኢኮኖሚ ውድቀት፣ለዘመናት በድህነት አረንቋ እንዲማገድ፣ስዉር ተንኮል ተፈፅሞበታል።ግን በኢትዮዺያ ታሪክ ብዙ ባይባልለትም ፣ጉድና ጭራ ከወደ ኃላ ነው እንደሚባለው ወቅትና ግዜውን ጠብቆ እየጠራ መጥቷል።

 

   እዚህ ላይ ሳልጠቅሰው ማለፍ የማልፈልገው፣የኢትዮዽያዊያን ፍርደ ገምድል የታሪክ አፃፃፍን ይሆናል፣እስከ ዛሬ ያነበብኳቸው የታሪክ መፃህፍቶችና ያየኃቸው የቅርስ ቦታዎች፣ መደባዊ ይዘት ያላቸው፣በወቅቱ ላሉት ገዢ መደብ የፖለቲካ ጥቅም ማስፈፀሚያዎች እንጂ ፣ የሃገሪቱን እውነተኛ ታሪካዊ መሰረት የሌላቸው ስለሆኑ ፣ ስርአት ሲቀየር ወይንም ሲፈርስ የሚወገዱ ሆነዋል።ለምሳሌ እኔ ሰለ ኢትዮዺያ ታሪክ እየተባለ የተሰጠኝ ትምህርት፣የአማራይቱ ኢትዮዺያ የነገስታት ታሪክና፣ገድል መሰረታዊ ይዘቱ በአማራይቱ ኢትዮዺያ የተመሰረተ፣የክርስትና ሃይማኖት የተዛባ ትርክት፣ጭራሽ እስልምና የማይታሰብ፣እንደ አረቦች ሃይማኖት ተደርጎ ነበር የምንማረው።

 

    ለምሳሌ በአማራይቱ የሚሊሊክ ኢትዮዺያ፣በብዛት ስማቸው ገኖ ሲነገረንና፣በየአደባባዩ የምናያቸው ሃወልቶች የሚሊሊክ፣የራስ መኮነን፣የሃብተጊዮርጊስ፣ደጃች ባልቻ፣ዘውዲቱ፣እቴጌ ጣይቱ፣ራስ ተፈሪ፣ሌላው ቀርቶ የልጆቻቸውና ሚስቶቻቸው ስዕል በደብተር መልክ አስጠርዘው ስንማር እንደነበርን እኔም ደርሸበታለሁኝ። የነ ኤፄ ዮውሃንስ፣ራስ አሉላ፣ባሻይ አውዓሎም ታሪክ ቢነገርም ለነሱ በሚመች መልኩ ትኩረት እንዳይሰጠው ተደርጎ ይቀርብልን ነበር።እሩቅ ሳንሄድ የክቡር ነብስሄር ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ውለታ እንኳን በኛ ዘመን እንዴት አኩሪ አለም አቀፉ ጭንቅላቱን ሊያጠለሹ እንደሚሯሯጡ የዘመኑ ወጣት ምስክር ነው፣እንዲሁም በአለም የጤና ድርጅቱ አኩሪ መሪ ክቡር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖምን ማየት ይቻላል።

 

ነገር ግን በውጭ ደራሲያን የሚፃፉት መፃህፍት፣ ደግሞ በመጠኑም ከማንቆለዸጣጠስ የተላቀቁ፣ በተቻላቸው መጠን በእድሜ ከገፉ አዛውንቶችና፣ በቦታው ተገኝተው ከሚፅፉት ታሪካዊ ግኝት በመነሳት ስለሆነ፣ ለማመዛዘን እድል ይሰጣል። ለምሳሌ በግሌ ስለ አፄ ቴዎድሮስ ጭካኔና አረመኔነት ፣ያወኩት ከጀምስ ብሩስ መፅሃፍ ነው፣ይህ ፅሃፊ አፄ ቴዎድሮስ ከአጀማመራቸው ጀምሮ፣ ለሃገራቸው የነበራቸው ራዕይና ምኞት፣በህዝባቸው ተቀባይነት ስላላገኘ፣ከህዝባቸው ጋር ተጣልተው፣የህዝባቸውን እጅና እግር እየቆረጡ፣ ህዝባቸው በእሳት ማቃጠልና እስከ ሰዎችን ከገደል መወርወር የደረሱ መሪ ነበሩ ይባላል። አፄ ሃይለስላሴ በ1935 ዓም ኢትዮዺያ ጣሊያን ሲወራት ቤተሰቦቻቸው ጭነው እግሬ አውጪኝ በማለት ሸሽተው እንግሊዝ አገር 5 ዓመት ተሸሽገዋል፣የኢትዮዺያ አርበኞች ካለ መሪ ጣልያንን ድል ሲያደርግ፣ንጉሰ ነገስት ብሎ ሲመለስ ወጊድ እንዳንተ አይነት ንጉስ የለንም ያለው ጀግናው የትግራይ ህዝብ፣ በእንግሊዞች አውሮፕላን በሃይለ ስላሴ ተደብድበዋል ፣ እህሉ ተዘርፈዋል፣የከዳውና የሸሸው ራሱ ሆኖ፣የትግራይ ህዝብ ከዳኝ ብሎ አሳር መከራው አሳይቶታል፣መንግስቱ ሃይለ ማርያም ከራሻ ባገኘው ዘመናዊ ጦር መሳርያ ያለ ምንም ደም ኢትዮዺያ ትቅደም ብሎ፣በስተመጨረሻ ሃገሪቷን ደም በደም አድርጏት ዘርፏት ወደ ዚምቧቤ ሸሸ ። ይህ ነው የአማራይቱ ኢትዮዺያ መሪዎች ታሪክ።

 

   ኢትዮዺያ የ3ሺ ዘመን ታሪክ ያላት ሃገር እያሉ፣ባለቤት የሆነውን የትግራይ ብሄረ ግዕዝ ህዝብ ማግለል፣ መበደል፣ ፍትህ መንፈግ፣የዛሬይቱ ኢትዮዺያ ላለፉት150 ዓመታት የተጠቀመችበት ዘዴ ሲሆን፣ አሁን እየተካሄደ ያለው የዘር ማጥፋት ዘመቻም ፣ የዚሁ ተቀጥላ ፣ የታሪክና የቅርስ ሌብነት፣አንድ አካል ነው። እዚህ ላይ አስረግጨ መናገር የምፈልገው ዋና ነጥብ፣ እኛ ተጋሩ ምንም እንኳን አማራይቱ ኢትዮዺያ እኛን አጥፍታ፣ የኛን ታሪክና ቅርስ ለመጠቅለል ብትፈልግም፣ ያለኛ ፈቃድና መልካም ትብብር፣ የተካሄደ ሴራ፣ ተንኮል፣ ወይንም ክህደት እንደሌለ ግን እንዲሰመርበት እፈልጋለሁኝ። በየወቅቱ ለመጣው በማሸርገድ፣ ከሕዝባዊ ጥቅም ይልቅ ፣ የግል ምቾትና  የስልጣን ፍላጎት ፣ በሚቸርላቸው ጥቅማጥቅም ህዝባቸውን ፣ ከገዢዎቻቸው በላይ ረግጠው የታማኝነትን ክብር፣ ከጌቶቻቸው ማግኘትን የሚሹ እንደየ ወቅቱ ተከስተዋል፣ ዛሬም እያየን ነው።

 

      ስለዚህ ሚሊሊክ አድዋ ላይ በጦርነት አሸነፍኩኝ ቢልም፣ጦርነቱ በተጋሩ መሪነትና ጥበብ በራስ አሉላና፣በባሻይ አውዓሎም ረቂቅ ጥበብ፣ቢጠናቀቅም በወቅቱ ከነበረው የድል አድራጊነት ወኔ በመነሳት እነ ራስ አሉላ፣ራስ መንገሻ፣እነ ባሻይ አውዓሎም እንቀጥል፣ የተቀረውን መሬታችንና፣ወንድሞቻችን የባሕረ ነጋሽ ህዝብ ፣ ነፃ እናውጣ ቢሉም፣አጅሬ ሚሊሊክ በውጫሌው ውል የሸጣትን ኤርትራ ፣በፈረስ ማዩ ውል ተጨማሪ መሬት በመስጠት ትግሪኛ ተናጋሪው ነገደ አግአዚያን ህዝብ፣ ለሁለት ከፍሎ መረብ ምላሽ ኢትዮዺያን ለመግዛት ወሰነ። ሚስጢሩ ጣልያንን ስላሸነፈ ሳይሆን። ያ እንደ ጦር የሚፈራውን ህዝበ አግአዝያን ከፍሎ ታሪኩን፣ባህሉን፣ማንነቱን ለመዝረፍና አደህይቶ፣ቀጥቅጦ፣ረግጦና፣አሸማቆ ለመግዛት እድሉን ስላገኘ ነበር የአድዋ ድል ብሎ ያስተጋባው።

 

    ለዚህም ነው አማራይቱ ኢትዮዺያ ስለ የቀደመው የፋሽስት ጣልያን ሽንፈት ሳይሆን፣ ስለ አድዋው በኩራት የሚተርኩት። አንባቢያን ሆይ የሚያመዛዝን ሕሊናቹህ ተጠቅማቹህ ስለ ሚዛናዊነት ተመራመሩ፣ካልሆነ የአድዋው ጦርነትና፣ የዶግዓሊው ጦርነት ምን ልዩነት አለው ? ኢትዮዺያን የሚውድ ንጉስ ለምን ? ክፋይ አብራኩ የሆነውን የኤርትራ ህዝብ ነፃ ለማውጣት አቅማማ ?  ጅቡቲን ማን ሸጣት ? ኤርትራን ማን ሸጣት ? ማንስ መለሳት ? በምን መልክ ተመለሰች ? ከዛስ ለምን ወደ ጦርነት ገባች ? እነዚህ ሁሉ ጥያቄዎች በሚዛናዊነት መመለስ ስትችሉ አማራይቱ ኢትዮዺያ ከእንግዲህ ላትመለስ ተቀብራለች። ክቡር ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ፣ ከሰራው ረቂቅ ብልህ የመሪነት ብቃት፣አማራይቱ ኢትዮዺያን ቀብሮልን ሄደዋል፣ ለዚህም ስሙን ለዘልአለም በክብር እናስበዋለን። ክፋት፣ተንኮል ጊዜውን ጠብቆ መፈንዳቱ አይቀርም ።

 

   እንደ ግለሰብና እንደ ትግራዋይ፣አሁን ለገጠመን ለዚህ ሁሉ ችግር ተጠያቂዎቹ እኛው ራሳችን ተጋሩ ፣በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ፣ይህን የአማራይቱ ኢትዮዺያ አምነንበት የሰጡንን እያላመጥን፣በራሳችን ላይ የፈጠርነው የውሸት ኢትዮዺያዊነት ቢሆንም ቅሉ፣የተታለልነው ግን አጉል ለሰው ልጅ ያለንን እምነት ነው። ካለፈው ስህተታችን ስለማንማር ነው። ከላይ እንደገለፅኩት ከአድዋው  ጦርነት በኃላ ሚሊሊክ ትግሪኛ ተናጋሪው ህዝብ ለሁለት ከፍሎ ብቻ አላበቃም ፣ትግራይም በመሳፍንቷ ከፋፍሎና አባልቶዋቸው ነው የሄደው፣ለዚህም ነው ለውድቀታችን ቀንደኞቹ ተጠያቂዎቹ እኛው ራሳችን ተጋሩዎች ነን የሚል እምነት ያለኝ ። ይህንን እውነታ ስንረዳ ካለፈው ስህተታችን ለመማርም በቂ ማስረጃ ስለሆነ በቀላሉ እንማርበታለን።

 

   ለምሳሌ አዶልፍ ሂትለር፣አህጉረ አውሮፖ በሁለተኛው የአለም ጦርነት ሲያንቀጠቅጣቸው፣የአሜሪካው ሮዘቬልት፣ የእንግሊዙ ዊንስተን ቸርችል፣ የራሻው ጆሴፍ ስታሊን፣ ምንም በፖለቲካው ቢለያዩም ፣ የወደፊት ህልማቸው፣ እንቅፋት ነው ብለው አስረግጠው የተሰማሙበት ጠላት ደግሞ ሂትለር ነበር። ስለዚህ 3ቱም በፖለቲካ የማይስማሙ አገሮች በጋራ ዘምተው ጀርመንን እንዳልነበረች አድርገው አውድመው ምስራቅና ፣ ምዕራብ ጀርመን በበርሊን ዎል ከፋፍለው እስከ1990 ዓም የገዙዋት፣ በኃላ ግን ጀርመኖች የተዘረጋላቸውን ወጥመድ ተረድተው በጣጥሰው በመጣል እንሆ አሁን ለደረሱበት የዕድገት ማማ ደርሷል፣ ሚሊሊክ ፣ሃይለ ስላሴ ፣ደርግ፣አሁን አብይ አህመድ ወቅቱና ጊዜው ቢለያይም ፍላጎታቸው የጀርመን እጣ ፈንታ ፈርደውብናል። እኛም ያለ ምንም ቅሬታ ለ150 ዓመታት ተቀብለነው ኖረናል ።አሁን ጭራሽ ከምድረ ገፅ ሊያጠፉን፣ ካለ ምንም ሃፍረትና ይሉኝታ ተነስተውብናል ፣እንጥፋ  ወይስ ወጊድ በቃን ባርነት፣በቃን ጭቆና፣ በማለት የራሳችን የሆነች ሃገር እንመስርት ?

 

    እዚህ ላይ በግልፅ አማርኛ መናገር የምፈልገው፣የጀርመን ምሳሌ ያለ ምክንያት እንዳልተጠቀምኩኝና ለምን ሚሊሊክ እንደከፋፈለን ካስረዳሁኝ በኃላ፣የራሳችን ድክመት ደግሞ በጥሞና ፈትሸን፣ ትናንትና አስበን አስልተን የተገበርነው ብሄር ብሄረሰቦች የሚለውን ዝባዝንኪ ፣ ልንማርበት ይገባል የሚል እምነት አለኝ።እንዴት ማለት ? ደግ እኔ የብሄር ብሄረሰቦች መብት ወይም ነፃነትን እደግፋለሁኝ፣አምንበታለሁኝም።ነገር ግን ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ህዝብ የራሱን መብትና ነፃነት እራሱ አፈር ልሶ ፣ መስዋእትነት ከፍሎና ታግሎ ያመጣውን ነፃነት ከሆነ ክብርና ዋጋ ይሰጠዋል። ሆኖም ግን ሌሎች ተሰዉተዉለት የሚሰጠው ነፃነት ግን ያን ያህል ክብር ሰለማይሰጠው። ሊጠብቀውም ግድ የለውም ፣ በአሁኑ ወቅት በኢትዮዺያዊያን የታየው ግብረ ምላሽም የዚሁ ነፀብራቅ ነው ። ስለዚህ ከዚህ በኃላ ፣ የትግራይ ህዝብ ለማንም ህዝብ መስዋእት መሆን የለበትም ለማለት ነው።

 

    ምናልባት ሰዎች የችግር አፈታት ዘዴያችን የተለያየ ነው ብዬ አምናለሁኝ። ለምሳሌ ማርቲን ሉተር ኪንግ የአሜሪካው፣ማህተመ ጋንዲ የህንዱ፣ ኔልሰን ማንዴላ የሳውዝ አፍሪካ፣ሰላማዊ ትግል ብለው ያምናሉ። ማልካም ኤክስ የአሜሪካው እንደግለሰብ፣እስራኤል፣አሜሪካ ደግሞ እንደ አገር ፣ በጉልበታቸው ያምናሉ። አለም ምንጊዜም የጉልበተኞች መናሃርያ ነች ። ተወረህ ተሰቃይተህ ከሞትክ በኃላ የሚገኝ ፍትህ ፣ ዋጋ ቢስ ነው ብዬ አምናለሁኝ ።                                         በአሁኑ ስአት የኢትዮዺያና ፣ የሻዕብያ ወታደሮች ፣ ከአረብ ኤምሬት በሚደረግላቸው ሰው አልባ የአውሮፕላን ድጋፍ ጋር ተጣምረው ፣ ህዝባችን ከተሞቻችን እያወደሙብን ይገኛሉ ፣ አለምም በኤሊ ፍጥነት፣ ምንም አይነት ለውጥ ሳናይባት 52 ቀናት አለፉ ፣ እነ የዲሞክራሲ ጠበቆቹ ፣ አሜሪካኖችም የጦርነቱ አበረታቾች ነበሩ፣ አሁን ሃሳባቸው ቢቀይሩም ፣ የወሰዱት እርምጃ ግን የለም ፣ ለምን ? ምክንያቱም ለነሱ የፍትህ ወይም የዲሞክራሲ ጉዳይ ሳይሆን ፣ የጥቅምና የአሸናፊነት ጉዳይ ነው።

 

     ስለዚህ ይህ ጦርነቱ በአሸናፊነት እንደምንወጣው መቶ በመቶ እርግጠኛ ነኝ። ከዛስ የወደፊት ፖለቲካዊ እቅዳችን ካለፈው ውድቀታችን እንማርበታለን ወይ? ይህ ነው የኛ የተጋሩ የወደፊት ተስፋችን ሊያለመልምልን የሚችል ፅንሰ ሃሳብና ራዕይ። ካልሆነ ለሁሉም ደማችን እያፈሰስን ነፃ ስናወጣ፣ ለራሳቸው ነፃ ያልወጡ ፣ ነፃ አውጪዎች ተብለን የአለም መሳቂያ የማንሆንበት መክንያት የለም ። ነፃነት እየሰጠን ፣ ውለታችን በጥይት የሚከፈለን ከሆነ፣ታሪካችንና መብታችን፣ለሌሎች አሳልፈን እየሰጠን መኖር አንችልም።

 

    እንደ ማሕበረሰብና እንደግለሰቦች ፣ ሌሎች ያልሰሩትና፣ የሌላቸውን እየወረሱና እያባዙ ሲቀጥፉ፣እኛ እንደ ተጋሩ እይደለም ልንጎረን ይቅር፣የራሳችን የሆነውን የኛ ነው ሳንል ቀርተን ፣ እስክንዘረፍ የምናንቀላፋ ሕዝቦች መሆናችን ሃቁ እየተገለጠልን መጥቷል ። የራሳችን የሆኑትን ቅርሶቻችንና ታሪካችን በራሳችን ድክመት በይሉኝታ እየተውን ፣ ሌሎች ያልሆነውን ታፔላ እየለጠፉብን መኖር ያማል፣ይከብዳል። ሻዕብያ ከህወሓት በፊት ለ13 ዓመት ሲታገል ቢቆይም፣በ1970 ደርግ የቀይ ኮከብ ጥሪ ዘመቻ ብሎ፣ ሻዕብያን ለማጥፋት ሲዘምት፣ሻዕብያም በሳህል ተራራ ላይ ተከቦ መሬት ውጪ መሬት ግቢ እያለ ሲጨነቅና፣ ያለውን ዶክመንት አቃጥሎ ሊሸሽ ሲል፣በነብስ የደረሰለት ጀግናው የህ.ወ.ሓ.ት ሰራዊት ነበር፣ ዳሩ ግን በ1977 የመከራ ወቅት፣የትግራይ ህዝብ በድርቅና በጦርነት ሲወረር፣ የእርዳታ መኪኖች በመሬቴ አያልፍም በማለት፣ ሻዕብያ የክህደት ተግባር በትግራይ ህዝብ ፈፅሟል።ነገር ግን የትግራይ ህዝብና መሪው ድርጅት ቂም አልቌጠረም፣ ድርጊቱን ግን አልረሳንም።

 

    ይህ አልበቃ ብሎት ፣ከነፃነት በኃላ ከየትኛውም የአለም ህዝብ በፊት፣የኤርትራ ነፃነት በፍቅርና በአክብሮት እውቅና የሰጠው፣  የትግራይ ህዝብ ነበር፣ሻዕብያ ግን የበላበት ወጨፎ ሰባሪነቱ በተደጋጋሚ ቢያሳይም ፣የባድመን መሬት በመውረርም በተመሳሳይ በደም ቀለበት የተሳሰረው የኤርትራና የትግራይ ህዝቦች ወንድምነት ሊበጣጥሰው ሞክረዋል፣ለዚህም ብዙ ኤርትራዊያን ደጋፊዎች አሉት።

 

    ይህ ሁሉ ግፍና መከራ፣ላጎረሰና ደሙን ገብሮ ስላንተ ነፃነት ለተሰዋ ወንድም ህዝብ ፣የሚከፈል ግብረ መልስ ባይሆንም፣ይባስ ብሎ አሁን ደግሞ ፣ስላንተ ነፃነት ለሞተልህ ህዝብ የህልውና አደጋ ሁነህ ፣በማይመለከትህ አገርና ህዝብ ጣልቃ ገብተህ ፣የወንድምህን ሂይወት መቅጠፍህ አልበቃ ብሎ፣ሃብት ንብረቱን፣ሆስፒታሎቹና፣ትምህርት ቤቶቹን መዝረፍና ማውደም፣በምንም አይነት መንገድ ወደር የሌለው የክፋትና የጥላቻ ጥግ መሆኑ ለመረዳት ይከብዳል። ለምን ተብሎ ለሚጠየቅ ጥያቄ መልስ ያልተገኘለት ጉዳይ ነው። እና እኛስ ምን ስላደረግን ነው ? ይህ ሁሉ ፍርደ ገምድልነት በላያችንና ፣ በህዝባችን ዘንድ የተፈረደብን ? እኛ ተጋሩ እንደ ተጋሩ አካሄዳችንና የፖለቲካ ፍላጎታችን ፣የህዝባችን የወደፊት እድልና ፣የወደፊት የሰላም ዋስትና ፣በሚያስከብር መልኩ የራሳችንና፣የራሳችንን ጥቅም መሰረት በማድረግ መወሰን አለብን እላለሁኝ።

 

    ቅድም እንዳልኩት በጉልበትህ ብቻ በምትኖርባት ዓለም ውስጥ ሆነህ፣ለሌሎች ብለህ የምትከፍለው የሂወት መስዋእትነት ፣በተጠቃሚው ክብር ከተነፈገህ፣የኔ ፣ያንተ ፣ያንቺ ለሌሎች መስዋእት መሆን፣በውለታ ቢሶች እይታና እምነት ደመ ከልብ ሆነናል ማለት ነው። በሻዕብያ ሰራዊት ከትግል እስከ ድል፣ከድል እስከ መንግስትነት፣የተከፈለን ውለታ የደመከልብነት ምላሽ ነው። ስለዚህ የህዝባችን ሰላምና አንድነት፣የወደፊት እጣ ፋንታችን በእጃችን እንደመሆኑ መጠን፣ የኛን ከምድረ ገፅ መጥፋት በተደጋጋሚ የሞከረብን ሃይል፣ እስከ ወዲያኛው መወገድ አለበት ። ጣላትህ እራስህ ማጥፋት ካልቻልክ ፣ማንም ስላንተ የሚሞትልህ የለም። እንደ ተጋሩ አሁንም አጉል ስብዕና፣ፍትህ ፣ ሕግ እያልን ህዝባችን ባናስፈጅ ይሻላል እላለሁኝ። የሚመለከታቸው ሃላፊዎች ውሳኔ የትግራይን ህዝብ ፍላጎት የሚወክል ስለሚሆን ሙሉ እምነት አለኝ።

 

የተጋሩ ስነልቦናዊ ውቅር ፣ ከኢትዮዺያዊያኖች የስነልቦና ውቅር የተለየ ስለሆነ ፣ አብሮ የሚያስኖረን መሰረት የለንም ብዬ አምናለሁኝ። በዝርዝር ለማስረዳት እሞክራለሁኝ

 

 እኛ እንደ ተጋሩ ስነልቦናዊ አረዳዳችንና ፣ የማሕበራዊነት እሴቶቻችን ከሌሎች ኢትዮዺያዊያኖች ለየት ይላል፣ ለምሳሌ ለማንኛውም ትግራዋይ በየትም አገር ይኑር፣የቸገረህን ብትጠይቀው/ቃት ፣ የመጀመርያ ጥረቱ በሱ/በሷ አቅም የሚፈታ ከሆነ ፣ ያለ ምንም ማመንታት ከመንገዱ ውጭ ሄዶ/ዳ የጠያቂውን ፍላጎት ለማሳካት ይጥራል/ለች።

 

    ትግራዋይ የተቸገረን በመርዳት፣በታታሪነት ሰርቶታ የራሱንና እንዲሁም የቤተሰቦቹ/ቿን ሂወት ለመቀየር ሌት ተቀን ይሮጣል/ለች፣ ለሃቅና ለፍትህ አንገቱን/ቷን የሚሰጥ ህዝብ፣ለአላማው/ማዋ የሚሞት፣ በፈራሄ እግዚአብሄር የሚገዛ ቅንና አፍቃሪ ማህበረሰብ ነው። ለሃገርና ለህዝብ ቅድሚያ ከመስጠት ባሻገር ለወገንና ለህዝብ ለውጥ፣ የሂወት መስዋእትነትን ለመክፈል በፀጋ የሚቀበል ቅን ማሕበረሰብ ነው። እዚህ ላይ ስለ አብዛኛው የትግራይ ህዝብ እንጂ እዛና ፣እዚህ ከሃዲዎች የሉም ማለቴ እንዳልሆነ ይታወቅልኝ።

 

   የዚህን ሕዝብ ፍትሃዊነትና ርህሩህነት ወይም ደግሞ ስብእና ተጨባጭ የሆኑ ማስረጃዎች ለመጥቀስ ያህል፣በ፲፯ቱ ዓመት ብረታዊ የትግል ወቅት በጦር ሜዳ ማርኮ አስተምሮ፣አላማውን አሳምኖ ለትልቅ ሃላፊነት ያበቃቸውን የኢትዮዺያ ከፍተኛ ባለሰልጣናትን እንመልከት፣ጀረራል አባዱላ ገመዳ፣ጀነራል ባጫ ደበሌ፣ጀነራል ብርሃኑ ጁላ፣ጀነራል ካሳዬ ጨመዳ፣እና እነ ኩማ ሚዴቅሳ ጥቂቶቹ ናቸው።በሌላው በኩል የትግራይ ህዝብ ቂመኛ ሳይሆን ፣ የበደሉትን ግለሰቦችም ይሁኑፖለቲከኞች፣ከእምነታቸው ውጭ የማያስገድድ ማህበረሰብና ድርጅትም አለው።እነ አረጋዊ በርሄና ግደይ ዘርአፄን በትግሉ ወቅት በአላማ ልዩነት ከሜዳ ወደ ሱዳን የተሸኙ ከፍተኛ የህወሓት አመራሮች ነበሩ።ልጨምርላቹህ፣የኦሮማራ የትግል ጥምረት ከተጀመረ በኃላ በተለይ በአማራ ክልል የነበሩ የትግራይ ተወላጆች፣ከክልላችን ይውጡልን በሚል ዘመቻ፣ከጎንደር ምንምአይነት ልብስና ቁሳቁስ ሳይዙ የተባረሩት የተገደሉ የትግራይ ተወላጆች በሌሊት ሲጨፈጭፏቸው ሸሽተው ወደ ሱዳን በመሸሽ ሂወታቸውን ያዳኑትን እናስታውስ በዛ ቀውጢ ጊዜ የሱዳን ህዝብ ያደረገልን ሰብአዊነት የተሞላበት እርዳታ ለታሪክ ተቀምጧል በአጠቃላይ ከ፸ሺ  በላይ ተጋሩ ከቤት ንብረታቸው ሲፈናቀሉ፣አንድም ኢትዮዺያዊ እረ ተዉ ወንድሞቻችን ናቸው ያለ ግን አልነበረም።     ከዛ በኃላ ምንም እንኳን የአማራ ክልሉን ያህል ዘግናኝ ባይሆንም፣ከኦሮሚያ፣ከጋምቤላ፣ከቤንሻንጉል ክልሎች ተጋሩ በማንነታቸው ሲፈናቀሉና ሲገደሉ፣አንድ ኢትዮዺያዊ ነኝ ባይ ሙሁር ይሁን ፖለቲከኛ የተቃወመም ይሁን ያወገዘ አላየንም።

 

   ሆኖም ግን ይህ ሁሉ ግፍ በትግራይ ህዝብ ላይ ሲፈፀም ፣ወደ ትግራይ የሚሄድ እህልና ሸቀጣ ሸቀጦች፣ በጎች ሳይቀር ታግተው ሲዘረፉ፣የትግራይ ህዝብ ጉያ ውስጥ የነበሩ የመንግስት ሰራተኞች ፣ ነጋዴዎች ፣ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አንድም ኢትዮዺያዊ አልተንገላታም ፣ የትግራይ ህዝብ ትልቅነት፣ለእዩልኝ ወይም ስሙልኝ ሳይሆን የእምነትና የአረዳድ ከፍታ ማሳያ ነው። በቅርቡ ለማመን የሚከብደው የትግራይ ህዝብ ሰብአዊነትና ፣ ርህራሄ ደግሞ፣ አብይ አህመድ የትግራይን ህዝብ ፣ ዘሩን ለማጥፋት በአየርና በምድር ፣ ከሻዕብያ ወታደሮች ጋር ሆኖ ሲያጠፋን፣ይሄ ወርቅና ክቡር ህዝብ፣እንደ ጠላቶቹ መዝቀጥን ሳይሆን በከፍታ ላይ ከፍታን የተካነበት ድርጊት፣ በተምቤን ዓብይ ዓዲ ላይ ደግሞታል ፣ ሊደበድብ የመጣን ሚግ 23 መትቶ ከጣለ በኃላ ፣ አብራሪው ሲዘል አይተዉት፣ተከታትለው በመያዝ ውኃ ለጥሙ፣ሰጥተው ራሱን በውኃ አጥበው ፣ ደግፈው ተሸክመው ለሚመለከታቸው ሃላፊዎች አስረክበዉታል። ይህ ነው የትግራይ ህዝብ የስነልቦና ውቅርና ከፍታ። እስኪ ደግሞ የኢትዮዺያዊያንን እንመልከትና ፍርዱ ለአንባቢያን እተወዋለሁኝ።

 

     ለኢትዮዺያ ብሄር ብሄረሰቦች ፣ ተብሎ በተጋሩ የተከፈለውን የሂወት መስዋእትነት ፣ አሁን ካለው ሁኔታ ጋር ሳነጣጥረው ያሳዝነኛል ይቆጨኛልም፣ ወደ ኃላ ተኬዶ የሚመለስ ቢሆን ፣ ድፍን የትግራይ ህዝብ ሳያቅማማ የልጆቹን ሂወት እንደሚመልሰው እርግጠኛ ነኝ። ምክንያቱም ለገዳይህ ትገድለዋለህ እንጂ ፣ የሂወት መስዋእትነትን የሚያክል የርህራሄና ፣ የደግነት የከፍታ ጠርዝ የሚያስገኘውን ሂወትን ያህል የሚያስከፍል ክብር አትሰጠውም፣ ግን የሰው ልጅ እንዲህ ነው። እኛም እንማርበታለን  ያለፈው ስህተት ሃሳቡም ፣ ድርጊቱም አልስማማበትም፣ ትግራይ ለተጋሩ፣ በተጋሩ ። ከዚህ በኃላ ለዚህች ኢትዮዺያ የምትባል ሃገር ፣ የአንድ ክቡር ትግራዋይ ሂወት ማለፍ የለበትም የሚል ፅኑ አቋም አለኝ፣ ኢትዮዺያ መፍረስ ካለባትም ፣ በራሷ ዜጎች እንዝህላልነት እየፈረሰች ነው። ሃገሪቱ በሙሁር እጦት፣ ሙሁር በወረቀት ሳይሆን ፣ በስነ አእምሮና ፣ በስነልቦና የላቀ ክህሎት ያጣ ምሁር፣የምሁር ደንቆሮ እንጂ ፣ምሁር ተብሎ አይጠራም። ከወሬ በዘለለ ምንም አይነት የሃገር ፍቅር ወኔም ይሁን ስሜት የሌላቸው የሆድ አደሮችና ፣ የስልጣን ጥመኞች ሃገር ነች። ይህች ሃገር የሚሰሩላት እየበላች ፣ የሚገድሏትን የምታጀግን የውሽት፣የቅጥፈት፣የሌቦችና የአመንዝራዎች አገር ነች፣ወንዱም ሴቱም ህሊናው የሸጠ ፣ የሙሁር መካን የሆነች ሃገር ነች፣ቄሱም የሃገር ሽማግሌውም ፣ ዋሽቶ ከማስታረቅ ፣ ዋሽቶ የሚያጣላ ህዝብ የበዛባት ፣ እግዚአብሄር ደህና ሰው አይውጣልሽ የተባለች  ሃገር ነች። ምክንያቱም፣አብዛኛው የኢትዮዺያ ህዝብ አማኝ ነው፣እምነቱም ክርስትና፣ እስልምና፣ዼንጤ፣ገዳ ወ.ዘ.ተ የመሳሰሉ ሃይማኖታዊና ባህላዊ እምነቶችን ያመልካል ። በየትኛውም ሃይማኖትም ይሁን እምነት፣የበደለህን ይቅር በል፣ ጠላትህን እንደራስህ ውደድ፣ የሰው ልጅ ክቡር ሂወት እኔ እንደፈጠርኩት ከኔ ትዕዛዝ ውጭ ማንም ፣ የማንንም ሂወት መውሰድ አይችልም ነው የአምላክ፣ የአላህ፣ የክርስቶስ የምታምኑበት ፈጣሪ ትዕዛዝ። የኢትዮዺያ ህዝብ ግን ወንድሜ በሚለው የትግራይ ህዝብ ላይ ፣ ከሚያመልከው ፈጣሪ ትዕዛዝ ውጭ፣አብይ አህመድ እንዲያጠፋው በሰልፍ፣ በሚዲያ፣ በቤተእምነቶች ድጋፍ ተሰጠው። እረ ተው ፣ ይቅር ለእግዚአብሄር ተባባሉ ፣ እገዝታለሁኝ ያለ የሃይማኖት መሪ ፣ የሌላት ሃገር ኢትዮዺያን ለማየት በቅተናል፣ ይህ እንደ ታሪክ ፣ በተጋሩ ልብና ብዕር ተመዝግቧል ።

 

    አንባቢያን ሆይ ፣ ከብስል ጥሬ አይጠፋም ይባል ነበር ፣ የስው ልጅ ሲሰራ ይሳሳታል፣ ሲሳሳት ደግሞ ይታረማል፣አብረህ ያጠፋሃውን አብረህ ታርመዋለህ፣ ከላይ እንደጠቀስኩት የትግራይ ህዝብ ለፍትህ ወድቆ የተሟላ ፍትህ ያላገኘ ፣ የትግሉ ፍሬ ባመናቸው ግለሰቦች የተቀማ፣ ሂወቱን ከፍሎ ላመጣው ፍሬ እላፊ ይሰጠኝ ወይም ይገባኛል ያላለ ህዝብ ነው ። ሆኖም ሁሉንም ችሎ ቀንደኛ ጠላቴ ድህነት ነው ፣ በማለት ኑሮውን ለማሸነፍ ጎምበስ ቀና ሲል የነበረ ህዝብ ነው። ለዚህም ነበር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን እንደመጣ ፣ የተስፋ ጭላንጭል የታየው።    መቐለ ሊጎበኝ ሲመጣም በክብር ተቀበለው።ኢትዮዺያ ያለ ትግራይ ሞተር እንደሌላት መኪና ናት በማለትም የህዝቡን ልብ መስለብ ችሎ ነበር። አፈ ቅቤ፣ልበ ጩቤው አብይ አህመድ አሊ ግን ፣ የሚያደርገዉን ጠንቅቆ ያውቅ ነበር። ከትንሽ ወራት በኃላ ወደ አሜሪካ ሄዶ ኢትዮዺያ 27 ዓመትጨለማ ውስጥ ነበረች በማለት ፣የተሰሩትን ስራዎች ማጠልሸትና መናድ ጀመረ፣ግድቡን አንቋሸሸው፣ኢንጅነር ስመኘው በቀለን አስገደለው፣ሌሎችም ሌሎችም ፣ ከዚህ በኃላ ያለውን ጉዞ የትግራይ ህዝብና አብይ አህመድ፣ሆድና ጀርባ የመሆን ክስተት እየከረረ ሲመጣ እያሽቆለቆለ ሄዶ፣የነበረው የህ.ወ.ሓ.ት የህዝብ ድጋፍ ከመቅፅበት እንደ አዲስ ማበብ ጀመረ፤ከማታውቀው መልአክ የምታውቀው ሰይጣን፤የሚለውን የአበው ምሳሌ በተግባር ከልጅ አስካዋቂ፣ከሊቅ እስከ ደቂቅ፣በሃገር ውስጥና በውጭ የምንገኝ ተጋሩ፣የፖለቲካ ልዩነታችን ወደ ጎን ትተን ፣የህልውናችን ጠንቅ የሆነውን ጠላቶቻችንን መለየትና በጥንቃቄ መከታተል ጀመርን ፣ ወደጅና ጠላቶቻችንም አየን።

 

    በዚህች አገር ዜጎች ላለፋት 10ዓመትና ካዛ ወዲህ የታየ ጉድ፣ የሃገሪቱ ባለስልጣናት ላለፉት 25 ዓመታት የተገኙ ድሎችና፣የፖለቲካ ቀውሶችም ይሁን የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ፣ እኩል ተጠያቂዎች መሆናቸው ቢታመንም፣የአብይ አህመድ የሽግግር መንግስት ግን ጥፋቱን ሁሉ ለህ.ወ.ሓ.ት፣ የለውጡ ድሎችና የሃገሪቱ ጥሩ ጥሩ አመርቂ ውጤቶች  የሱ የስራ ውጤቶች እንደሆኑ በሚቆጣጠራቸው ሚዲያዎች ማስተጋባት ሲጀምር ፣ የኢትዮዺያ የጨለማ ጉዞ መጀመሩ ግልፅ በሆነ መንገድ ማየት ችለናል።

 

 እስኪ ዘርዘር አድርገን እንመልከታቸው በሃገሪቱ በሚዘገንን ሁኔታ በባለስልጣናት እውቅና , ግብረሶዶምነት ተስፋፍቷል ፣ ህዝቡ ሳያላምጥ የሚውጥ  ስለሆነ ማንም መጥቶ ያታልለዋል ይዋሸዋል፣ ታስታውሳላቹህ ዶ/ር ኢንጅነር ሳሙኤል የሚባል ወሮ በላ ፣ ሌላዋ ከእንግሊዝ አገር የመጣች አጭበርባሪ ፣ እኔ እህተ ማርያም ነኝ ብላ ስታሞኛቹህ እና መንግስታቹህ፣ የቤተክርስቲያን አለቆቻቹህን ፣ ዻዻሳቹሁን ስትሳደብ ፣ሃይ ባይ በሌለባት ሃገር ሁሉም የፈለገውና ያሻው ይፈፅማል።

 

   ፖለቲከኞቻችሁን ተመልከቱ ማንም እየመጣ ይወክላቹሃል፣ አንድ ቀን ግን ስለ መብታቹህ ሲጮህ ወይም ሲታሰሩ አይታዩም ፣ አሁን አሁን ጀዋር፣በቀለና ልደቱ እየታጋፈጡላቹህ ነው፣ ሃገሪቱን በተለይ ደቡብ ሕዝቦችን እዩ ማንም እየመጣ ፣ነብይ ነኝ እያለ ሙድ ይይዝባቸዋል፣ በካራቴ ይጥልዋቸዋል፣ ኢትዮዺያ ትልቁን የሰው ልጅ ክብር የምትነፍግ ሃገር ሆናለች። ወደ ደብረ ማርቆስ ለስራ የሄዱ የሃገር ሃብት የሆኑ 2 ዶክተሮችን በድንጋይ ተቀጥቅጠው ተገድለዋል። የሰው ልጅ ያለ ምንም ጥፋቱ በድንጋይ ተቀጥቅጦ መሞት አንሶ ፣ ተገድሎም ተዘቅዝቆ ተሰቅሎ ሲጨፈር በሻሸመኔ አይተናል ። የሃገር ፍቅርና ክብር ማለት ለሰው ልጅ ሰብአዊነት ተነፍጎ ፣ መሬት የሚመለክበትና ፣ለመሬት ሲባል ሰው የሚጨፈጨፍበት ሃገር ኢትዮዺያ እያየን ነው። ለጋ የሆኑ ከደምቢደሎ ዩኒቨርስቲ ልጃገረዶች ለመማር ሄደው የሚታፈኑባት፣የጦር አዛዦቿ በጠራራ ፅዕሃይ የሚገደልባት፣የቱን ዘርዝሬ የቱን ልተው፣ ስለዚህ በኛና በኢትዮዺያዊያን፣ያለው የአስተሳብና የስነልቦና ውቅር ሰማይና መሬት ነው፣የሚለው አመለካከቴ እላይ በዘረዘርኳቸው ጭብጥ ለማስረዳት ሞክሬያለሁኝ።

 

   ይህን ሁሉ ግፍ የተሸከመች ሃገር በትግራይ ህዝብ ላይ ጦርነት ስታውጅ የደገፍክ ህዝብ፣ ካናንተ ብዙም አንጠብቅም፣የሚያልፍ ቀን የማይረሳ ጠባሳ ትቶ ያልፋል ነውና፣ኢትዮዺያ ለትግራይ ህዝብ ፣እንደ ባዕድ ህዝብ፣ ከባዕድ ሃገር ጋር አብራ የዘር ማጥፋት ጦርነት አውጃብን፣ አላበቃችም የትግራይ ህዝብ አንጡራ ሃብት የሆኑ ፋብሪካዎች እንደነ አልመዳዳ ጨርቃጨርቅ፣ አዲስ መድሃኒት፣ ሳባ እምነ በረድ፣ የቆዳ የዘይት፣ በትንሹ ልጥቃቅሰ፣ ሆስፒታሎች ፣ትምህርት ቤቶች፣ አምቡላንሶች ፣ የመንግስትና የግል ባለሃብቶች ንብረት ተዘርፏል፣ ባንክ ፣ መብራት፣ ውሃ ፣ትራንስፖርት፣ኮምኒኬሽን የመሳሰሉት ወድሟል።

 

ለምን ይህ ሁሉ ግፍ በትግራይ ህዝብ ተፈለገ ?እንግዲህ ለዚህ ነው አሁንስ ወዴት (ሕዚኸ ናበይ) በማለት ጥያቄዬን ያቀረብኩት።ይህንን ጥያቄ መመለስ የምንችለው ደግሞ እኛ ተጋሩና፣ተጋሩ ብቻ ነን።

 

     በግል እምነቴ ላለፉት 150 ዓመታት ኢትዮዺያን ያስተዳደሩ ስዎች ኢህአዲግን ጨምሮ፣ንጉስ ሚሊሊክ በአድዋው ጦርነት፣ንጉስ ሃይለ ስላሴ ፣ በማይጨው ጦርነት፣መንግስቱ ሃይለማርያም በ17 ዓመት የትግል ጦርነት፣ኢህአዴግ ህወሓት ባስተዳደረበት ወቅት ለትግራይ ህዝብ አደላ እንዳይባል የሌሎች ክልሎችን ያህል ያልለማ ክልል ቢኖር ትግራይ ክልል ነው።አሁን ደግሞ የአብይ አህመድ መንግስት ፣ ከአምባገነኑ የሻዕብያ መንግስት ጋር ተባብረው እየጨፈጨፉን ነው። እዚህ ላይ ሳልጠቅስ ማለፍ የማልፈልገው ኢትዮዺያን በግልጽና በስውር እያፈራረሱ ያሉት አማራዎች ናቸው። እስከነ ምሳሌው (ጅራፍ እራሱ መትቶ እራሱ ይጮሃል) እንደሚባለው። የአማራ ሰፋሪዎችና ተስፋፊዎች ፣ በአሁኗ ስአት ኢትዮዺያን እያመሱ ያሉት አማሮች ሲሆኑ፣ ባላቸው የሚዲያ ብዛትና ፣ በያዙት ፖለቲካዊ ስልጣን ተጠቅመው፣ እራሳቸው እየገደሉ ተገደልን ብለው እሪ ይላሉ፣ እራሳቸው አፍነው ህዝባችን አማራ በመሆኑ ታፈነ ይላሉ(ለምሳሌ የደምቢ ደሎ ሴት ተማሪዎች)እነሱ ራሳቸው የሌላውን ብሄር በተለይ ትግራዋይና ፣ ኦሮሞ እያፈናቀሉ፣ ተፈናቀልን ይላሉ ፣ እራሳቸው ህዝብን በገጀራ ገድለው ህዝባችን በገጀራ ተጨፈጨፈብን ይላሉ፣ ጥሩ ማስረጃ በሃረርና፣በማይ ካድራ የሰሩትን ግፍ መጥቀስ ይቻላል። ብዙ ጉድ መጥቀስ ይቻላል። ግን እስከ መቼ የሚለውን ጥያቄ ለማንሳት ያስገድደናል።

 

   አሁን አለም በቴክኖለጂ አንድ በሆነችበት ወቅት፣በ21ኛው ክፍለ ዘመን እኛ ራሳችን ከዘመኑ ፖለቲካ ጋር መገለባበጥ ይኖርብናል፣በአሁኑ ወቅት ትግራይ እንደ ሃገር ልትቆም ትችላለች የሚል ስነልቦናዊ እምነት በያንዳንዱ ትግራዋይ ጭንቅላት ውስጥ መቀረፅ አለበት ብዬ አምናለሁኝ።ምክንያቱም ለሃገረ ትግራይ ውልደት እስከ ሂወት መስዋእትነት ለመክፈል የተዘጋጀ አስተማማኝ ወጣት ትውልድ አለ፣ከምንም ከማንም በላይ የተደራጀ ህዝብ አለ፣ተራራ ፈልፍሎ ጥሮ ግሮ መለወጥን የሚመኝ ታታሪ ህዝብ አለ፣ለወቅቱ በትግራይ አቅም ፣የትግራይን እድገት ማፋጠን የሚችል የተማረ የሰው ሃይል አለ፣በማንኛውም ስአት ሃገሩ ትግራይ ነፃ ሃገር ብትሆንለት ጨርቄን ማቄን ሳይል ገብቶ ሃገሩን መገንባት የሚፈልግ ዳያስፖራ አለ፣በጀግንነት በእሳት ተፈትነው ጦርነትና ሃገርን መምራት የሚችሉ የፖለቲካና ወታደራዊ መሪዎች አሉ ፣የወቅቱን የአለም ፖለቲካዊና አለም አቀፍ ዲፖሎማሲ ተረድተው ትግራይን እንደ ሃገር መገንባት የሚችሉ ሙሁሮች አሉ ፣ውድ ተጋሩ አንባቢያን  ትግራይ በአሁኑ ስአት በኢትዮዺያ ስር ስለሆነች እየገጠመን ያለው ችግር አለም እኛን እንደ ሃገር ስለማታውቀን ብቻ ነው።ሃገረ ትግራይ ሆነን ስንወጣ ታሪካችን፣ባህላችን፣ቅርሶቻችን፣የጀግንነት ታሪኮቻችን ሁሉም እራሳችን ችለን እንደፈለግነው በምንችለው ሰንደን ለዓለም ህዝብ የምናቀረበው አንዱ የገቢ ምንጫችን ሲሆን ዛሬ የወደሙት ፋብሪካዎቻችንናራ ሆስፒታሎቻችን ወ.ዘ.ተ በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚተኩ ናቸው።የ1977ቱ ችግርና መከራ አሸንፎ የወጣ ህዝብ፣ይህንን መከራ ያቅተናል ብዬ አላምንም፣እንደ ተጋሩ ወገባችንን ጠበቅ አድርገን አላማችንን እንደምናሳካ ለደቂቃም አልጠራጠርም፣ከሁሉም ከሁሉም በላይ ግን የጠላቶቻችን ምኞትና ፍላጎት ጠንቅቀን እስከ ተረዳንና፣ወዳዘጋጁልን ወጥመድ እስካልገባንና፣እንደማንገባም እርግጠኛም ነኝ።

 

   አለም የጉልበተኞች መሆኗን ጠንቅቀን መረዳት ያስፈልጋል።አለም ከኛ ምን ትፈልጋለች፣እኛስ ለአለም ምን ማቅረብ እንችላለን ? በአለም ውስጥ ካሉ አገሮች በመሬት ስፋትና በህዝብ ብዛት ከኛ ያነሱ ህዝቦች አሉ፣በተፈጥሮ ሃብት የኛን ያክል ያልታደሉ ህዝቦቦች አሉ ፣ምንም አይነት የባህር በር ሳይኖራቸው ፣በዘመኑ ቴክኖለጂ የበለፀጉና ጥሩ አቅም ያላቸው ሃገራት ሞልተዋል፣ ተጋሩ ለተጋሩ ብቻ ብለን ጉልበታችንና ጊዜያችን ወደ ራሳችን መመንዘር ስንጀምር፣ያኔ ሁሉም ቀልቡና ምኞቱ ወደኛ ይሆናል፣ድሃ ማንም አይፈልገውም ፣ ፈሪና ቦቅቧቋ ማንም አይጠጋውም ጭራሽኑ መሳለቅያ ይሆናል።እኛ ተጋሩ ለ53ቀናት የኢትዮዺያ፣የኤርትራ፣ፎጣ ለባሽ ቀጥ አድርገን በመያዛችን እነዚህ ህዝቦች ማናቸው ተብለን፣አለም ትግራይ ማን እንደሆነች የት እንደምትገኝ አለም አወቀን ሁሉም በኤሊ ፍጥነት ቢሆንም አኩሪ ገድልና ታሪክ ግን እየተሰራ ነው።

 

ትግራይ ትዕወት፣

 

ኽብሪን ሞገስን ብእንተ ትግራይ ንትኳሽሑ ንዘለኹም እሕዋትን አሓትን።

 

ኽብርን ሞገስን በብእዋኑ ምእንተ ዓዶም ትግራይ ሂወቶምን አካሎምን ንዝገበሩ ኹሎም።

 

የቐንየለይ

Can reached at mba1277@gmail.com

 

 


Back to Front Page