Back to Front Page

ሰሜን እዝን እንደ ምክንያት

ሰሜን እዝን እንደ ምክንያት

ግዜ ለኩሉ 12-11-20

አሁን በትግራይ ላይ እየተካሄደ ያለው ጦርነት ብዙ ሰው የሚረዳው "ሰሜን እዝ ጥቃት ደረሰበት" በሚለው ትርክት ነው። እውነት ሰሜን እዝ ተጨፍጭፈዋል? እውነት የጦርነቱ መነሻ የሰሜን እዝ ጥቃት ነው? የሚሉትን በዘርዘር ለማስቀመጥ እሞክራሎህ።

የጦርነቱ መንስኤ ለመረዳት ግን ጦርነቱ የተጀመረበት ግዜ መቼ እንደሆነ በግልፅ ማስቀመጥ ግድ ይላል። ባለፉት ሶስት ኣመታት ማለትም አብይ ወደ ስልጣን ከመጣ በትግራይ የተከሰቱ ነገሮች የትግራይ አንድነት መጠናከር እና በትግራይ ህዝብ  ላይ ግልፅ የሆኑ ጥቃቶች ነበሩ። እነዚህ ጥቃቶች ግን አይን አፍጥጠው የወጡ ግዜ  እንጂ በድንገት የተከሰቱ ኣልነበሩም። ከመንሻው ለማየት

በትግራይ ህዝብ ጦርነት ከተጀመረው ቆይተዋል

በትግራይ ህዝብ ላይ የተለያዩ መንግስታት በተለያዩ ዘመን ጦርነት ተከፍቶበት ተጨፍጭፈዋል። ለዚህም በሚኒሊክ ከፋፋይነት ትግርኛ ተናጋሪዎች ለሁለት እንዲከፈሉ ተደርገዋል፡ በኋይለስላሴ ግዜ በእንግሊዝ የውግያ አዎሮፕላኖች በመታገዝ ተጨፍጭፈዋል እንዲሁም በድርግ ለ17 ኣመት ጦርነት ተከፍቶበት በድል ተወጥተዋል። ወደ አሁኑ ጦርነት አጀማመር እና መቼ እንደተጀመር ዝርዝር ስንገባ

Videos From Around The World

1.  በትግራይ ህዝብ ላይ የመዝመት እና እንደ ጠላት ተቆጥሮ የማጥላላት፡ እንደ ሌባ መቁጠር፡ መሪ ድርጅቱን እና ህዝቡን ሳይለዩ አንድ ላይ የመኮነን ላለፉት ሰላሳ አመታት የተሰራባቸው ስራዎች ናቸው። ትርፍ ከፍሎ ትርፍ ባይጠይቅም ይህ ህዝብ ግን አገሪቷን እንደዘረፈ፡ የአውሮፓ አኗኗር እንደሚኖር እና ይኼውም የሆነበት ምክንያት ከኢትዮጵያ በተዘረፈ ሀብት ብቻ ሳይሆን ከኢትዮጵያ አፈርም ጭምር እየተጫነ ወደ ትግራይ እንደሚሄድ ሲዘመትበት ነበር። ትግራዋይ ልጆቹን ገብሮ ሰላማዊት፡ በተከታታይ እድገት ያስመዘገበች እና አንገቷን ቀና አድርጋ በአለም መድረክ የምትናገር ኢትዮጵያ እንድትፈጠር መሰረት ያስቀመጠው ስድሳ ሺ ልጆቹን ገብሮ በመቶ ሺዎች አካለ ስንኩል ሁነውበት  በድህነት ዘበኛ ደርግ ባደረገው መራራው ትግል ድል አድርጎ ሲሆን፡ ይህ ህዝብ  ምስጋና ሳይሆን ነጋ ጠባ ጥላቻ፡ ስድብ፡ ማጥላላት እና ኩነኔ ተቸረበት። የትግራይ ህዝብ ጠላቶች እንደ ኣሽን በፈሉ ሚድያቸው ቤቱ፡ የሚሄድበት መንገድ፡ ተራራው እና ጋራው በወርቅ እንደተነጠፈ አድርገው ሳሉቱ። የሚገርመው ግን እነዚህ ሚድያዎች በዘመነ መንግስቱ ኋይለማርያም እንኳን ሊፈጠሩ ለመፈጠርም የማይታሰቡ መሆናቸው ነበር።

2.  የትግራይ ህዝብ የማጥፋት ዘመቻ ከአምስት አመት በፊት በ2008 ዓም በግልፅ እንደ አዲስ  ተጀመረ። የትግራይ ተወላጆች ከጎንደር እና ከመተማ ጥረው ግረው ያፈሩት ሀብት በመዝረፍ እና በማቃጠል እንዲገደሉ እና እንዲባረሩ ተደረገ። ከ30000 በላይ ተጋሩ ባዶ እጃቸው ተባረሩ። የሞቱት ፈጣሪ ይቁጠራቸው። በግልፅ "95 ሚልዮን ለ5ሚልዮን" የሚል ዘመቻ በኢሳት ቲቪ (ይህ በሌ/ኮል አብይ ለሲሳይ አጌና እንደ ጀብድ ተቆጥሮ እውቅና ተሰጥቶታል)ተከፈተባቸው። በግልፅ "30 ሚልዮን ለ5 ሚልዮን" የሚል የቁጥር ስሌት " አምስት ሚልዮን እንኳ የአማራ ህዝብ የትግራይ አምስት ሚልዮን ህዝብ ገድሎ ቢሞትብን ሀያ አምስት ሚልዮን የአማራ ህዝብ  በሰላም ይኖራል" የሚለው የከንቱዎች የዘር ማጥፋት ዘመቻ ተዝምቶባቸዋል። "የትግራይ ናቸው"  የተባሉት የቋማት ላይ ጥቃት ደርሰዋል። በአክስዮን የተቋቋመው የሰላም ባስ  አክስዮን ማህበር ንብረት የሆኑት አውቶብሶች ተቃጥለዋል።

3.  ወደ ትግራይ የሚወስዱት የፌደራል መንግስት መንገዶች ተዘግተዋል። የትግራይ ህዝብ በአፋር አድርጎ (እድሜ ለአፋር መንግስት እና ህዝብ) በሀሩር እና በፀኋይ እንዲጓዝ ተደርገዋል። ወደ ትግራይ የሚጓዘው እህል እና እንስሳት ተዘርፈዋል። የትግራይ ህዝብ ምንም እንደሌለው ተድርጎ አስርቦ ለመግደል ተሞክሯል።

4.  ተደጋጋሚ የጦርነት ትንኮሳዎች በወልቃይት እና በፀገዴ በኩል ተካሂደዋል። ይህም በርስት አስመላሽ ኮሚቴዎች አጃቢነት በአማራ መንግስት የተከናወነ ነበር።

5.  ሌ/ኮል አብይ አህመድ በአንቴኖፍ ኮማንዶ በመላክ የትግራይ መንግስት አመራሮችን ልክ እንደ ሱማሌው ኦፕሬሸን አይነት በቁጥጥር ስር ለማዋል ተሞክሮ ከሽፈዋል።

6.  የመንግስት በጀት ብቻ ሳይሆን በውጭ እርዳታ የሚመጣው የሴፍት ኔት እርዳታ ከልክለዋል።

7.  ለተማሪዎች የሚውለውን የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ (ማስክ) ከልክለዋል።

8.  መንግስት ትግራይን ለመውጋት አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉ በአብይ በአደባባይ ተነግረዋል። አዎ የድሮንና የሪፓብልክ ኋይል በድብቅ እንዳዘጋጀ እና አሁን ደግሞ ሪፓብሊካን ግዳጁ እንደጨረሰና ወደ ሰራዊቱ እንደሚቀላቀል በፓርላማ ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪ ግን

8.1      ትግራይ ምርጫ ከተደረገ ጦርነት እንደሚኖር በግልፅ ቋንቋ "እናቶች እንዳያላቅሱና ህፃናት እንዳይሞቱ" በማለት ሌ/ኮል አብይ አስቀድሞ ተናግረዋል።

8.2      የትግራይ መንግስት መሪዎች ለመያዝ በሚደረው ኦፕሬሸን የሰሜን እዝ ለማሳተፍ የአመራር መቀያየር እና የተለያዩ ግዳጆች ታማኝ ለሚላቸው የሰሜን እዝ አባላት ተሰጥተዋል።

8.3 የተለያዩ የመክላከያ ክፍሎች በተለይ ልዩ ኋይሉ በጎንደር በኩል እንዲጠጋ ሲደረግ ሌሎች ክፍለ ጦሮች በራያ በኩል እንዲጠጉ ተደርጎ እንደ ነበር ፀሀይ የመታው ሀቅ ነበር።

8.4 በኤርትራ በኩል የሚገባ ኋይል ወደ አስመራ አጓጉዘዋል። ለሚገባው ኋይል አስፈላጊው ሎጂስቲክስ  አስቀድሞ ወደ አስመራ ተጓጉዘዋል። በተጨማሬም በጦርነቱ ለሚሳተፉ የሻእብያ ወታደሮች የሚውል 15000 የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ደንብ ልብስ ወደ አስመራ ተጓጉዘዋል። ይህም የኤርትራ ሰራዊት አስቀድሞ ጦሩነቱ  ላይ እንደሚሳተፍ መታቀዱ ያሳያል።

8.5      ጦርነቱ በተጀመረበት ምሽት የትግራይ መንግስት አመራሮች ለመያዝ ያልተሳካ ኦፕሬሽን በሁለት አንቴኖፍ በተላኩ አየር ወለድ ወታደሮች ተከናውነዋል። ወድያው ደግሞ የትግራይ መንግስት ራሱን የመከላከል እርምጃ ሲወስድ ሌ/ኮል አብይ ያዘጋጀው ኋይል (የአማራ ምልሻና ልዩ ኋይል ጨምሮ) ጥቃት እንዲጀምር ትእዛዝ ሰጠ። የምክር ቤት ውሳኔም አልጠበቀም።

የሰሜን እዝ አልተጨፈጨፈም

"ህወህት ሰሜን እዝ ጨፈጨፈ፡ ልብሳቸው ኣውልቆ የሞቱት ቀብር ነፈጋቸው፡ እራቆታቸው ወደ ኤርትራ ላካቸው" እየተባለ ኢትዮጵያውያን እንዲያለቅሱ እና ጦርነቱ እንዲደግፉ የተሰረገው በውሸት ድራማ ነው። ለዚህ ማረጋገጫ ሁለት ምክንያቶች አቀርባሎህ።

1.  የሙርከኛው ጀነራል ባጫ ደበሌ ትወናዎች

1.1 "የሰሜን እዝ አባላት በትግራይ ተወላጆችና የኦኔግ ባንዴራ ይዘው እልል እያሉ በኦኔግ ሸኔ ተጨፈጨፉ"

1.2      " የተጨፈጨፉት እራቆት አውጥተው መቃብር እንኳ ነፈጓቸው"

1.3      " ሰራዊቱ ልብሱ አውልቀው እራቆቱ ወደ ኤርትራ ልከውት የኤርትራ ሰራዊት ልብሱ አውልቆ አለበሳቸው።" (ቀድሞ መጨፍጨፋቸው መንገሩን መቼ እንደረሳው አላቅም።

1.4      "ሰራዊቱ ራሱን አደራጅቶ ለውግያ ዝግጅቱ አጠናቅቆ ዛሬ ማታ ወይም ነጌ ጥዋት ከሸራሮ እስከ ዛላንበሳ ድል ሲያደርግ ታዩታላችህ።" (ሌላ ውሸት፡ እዩት ተጨፈጨፈ፡ እራቆቱ ተላከ የተባለ ሃይል ነው)። በተባለው ቀን የተባሉት ቦታዎች መያዝ ባይችሉም።

2   የትግራይ መንግስት የሰሜን እዝ አባላት ተንከባክቦ እና ደህንነታቸው ጠብቆ በመቆየት ለአለም አቀፍ ቀይ መስቀል ማህበር አስረክበዋል

የሰሜን እዝ አባላት የትግራይ ህዝብ እና መንግስት በእንክብካቤ በመያዝ ከጀነራል እስከ ተራ ወታደር ለቀይ መስቀል በማስረከብ ወደ ኢትዮጵያ መንግስት እንዲገቡ አድርገዋል። ነገር ግን  መንግስት ከቤተሰቦቻቸው እንኳ ሳይገናኙ መልሶ ወደ ጦርንውት እየላካቸው ነው። አብይ እስከ ኣሁን በጦርነት የተማገደው አልበቃ ብሎት አሁንም እነዚህ የኢትዮጵያ ህዝብ ያጭበረበረት ተጨፍጨፉ የተባሉት ወታደሮች ወደ ጦርነት እየማገዳቸው ነው። ስለዚህ ገዳያቸው አብይ ነው። ህውህት ጀነራል ሳይቀር በከብር ለቀይ መስቀል አስረክበዋል። መንግስት ግን "ከጁንታው አስለቀቅኩኝ" በማለት ዳግም በምንታ ምላሱ እየዋሸ ነው። ህወህት ጨፍጫፊ ቢሆን ለምን እስከ አሁን አቆያቸው?

ስለዚህ በትግራይ ህዝብ እና መንግስት የተከፈተው ጦርነት ሰሜን እዝ ሽፋን በማድረግ ውስጠ ሚስጥሩን የሚያውቀውን ጀነራል አደም ከኋላፊነት ገለል በማድረግ  ኢትዮጵያውያን በማታለል የተከፈተ ጦርነት ነው። ጦርነቱ  በህግ ማስከበር ሽፋን ለግለ ሰብ ስልጣን እና ለግዛት ተስፋፊ የአማራ ባለስልጣናት የመሬት  ማስመለስ እና ባደረ ቂም ለመወጣት የፈለገው የኤርትራ መንግስት   በቅንጅት የተከናወነ ጦርነት ነው። ሰሜን እዝ እንደ ምክንያት ተደርጎ የተከፈተው ጦርነት የሰው ሂወት ቀጥፈዋል፡ ሀብት በልተዋል፡ ትግራይ እና የትግራይ ህዝብ አውድመዋል። የሰላሳ አመት እቅድ ለግዜውም ቢሆን ተሳክተዋል። መጨረሻው ግን ትግራይን በመግደል የምትኖር ኢትዮጵያ አትኖርም። ብትግራይ ሞት የምትጠፋ ኢትዮጵያ እንጂ በትግራይ ሞት የምትበለፅግ ኢትዮጵያ አትኖርም። ያን ግዜ  በኢትዮጵያ ሞት የትግራይ ትንሳኤ እውን ይሆናል።

 


Back to Front Page