Back to Front Page

የሰራዊቱ ህዳሴ ግድብ መወጮ በሌ/ኮ አብይ ትዕዛዝ ለአሽብራቂ ፕሮጀክቱ ወስዶታል

 

የሰራዊቱ ህዳሴ ግድብ መወጮ በሌ/ኮ አብይ ትዕዛዝ ለአሽብራቂ ፕሮጀክቱ

በእውነቱ ትዝብት (/ጄነራል)  09-16-20

የኢፊዲሪ መከላከያ ሰራዊት የህዳሴ ግደብ መሰረተ ድንጋይ ከተጣለበት ጊዜ ጀምሮ እሰከ አሁን ለ8ኛ ጊዜ በአንድ ዓመት የአንድ ወር ደመወዙ እያዋጣ ይገኛል ፡፡ አሁን ሌ/ኮሌኖሉ ገበታ ለሀገር የሚባል ህዝባዊ ያልሆነ ፕሮጀክት ያለ ዕቅድ በሰሜት ጀምሮ ገንዘብ ሲያጣ ለፈደራል መንግሰት ሰራተኛች አስገድዶ ደመወዙ እየወሰደበት ይገኛል ፡፡ በመከላከያም የአንድ ወር ደመወዝ በአጭር ጊዜ ከ3 ወር- 6 ወር እንዲቆረጥ ተወሰናል፡፡ የሚገርመው ጉዳይ ግን ሰራዊቱ አቅምና ፍላጎት የለንም ብሎ አሸብራቂ ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ በመቀወሙ ያለ ፍላጎቱ በትእዛዝ የህዳሴ ግድብ መወጮ ከመንግሰት ካዝና ምንም ተጠያቂነት ወደሌለው አሽብራቂ የግለሰብ ፕሮጀክት አዙሮታል ፡፡

Videos From Around The World

በዚህ ምክንያትም ሰራዊቱ መርዳት ካለብን በስው ሰራሽና በተፈጥሮ ጉዳት እየደረሰበት ያለ ህዝብ እንጂ ለቅንጦት ፕሮጀክት ሞራላዊ፤ ሀይማኖተዊና ህጋዊም ግዴታ የለብንም ብሎ አቋም ወሰዳል ቢሆንም ገንዘቡ በግድ ተቀርጣል፡፡ ይህ የሚያመለክተው ከገንዘቡ በላይ ለአንድ ሰው ጊዛዊ እወቅና ሲባል ሰራዊቱ ሲቸገር ማይት ከባድ ነው፡፡ አሁን ሰራዊቱ መገንዘብ ያለበት የአንድ ሰው የበላይነት በሰዎች ሂወት ፤ገንዘብና ንብረት ምን ያህል ፈላጭ ቀራጭ እንደሚሆን ይህ በቂ ምሳሌ ነው፡፡

የገንዘብ ማዋጣቱ ተግባር ሁለት አላማ ነው ያለው ነው የመጀመርያውና ዋነኛው ሰራዊቱ ካለው የሰው ኃይል ብዛት አንፃር ብዙ ገንዘብ በመሆኑ ሰራዊቱ በአጭር ጊዜ እንዲከፍል በማሰገደድ ለፕሮጀክቱ ፍፃሚ ወሳኝ ነው አለበለዝያ ብሮጀክቱ በወቅቱ አያልቅም፡፡ እዚህ ላይ የሚነሳው ጥያቄ የትኛው ፕሮጀክት ነው አገራዊ ህዳሴ ወይስ አሸብራቂ መናፈሻ ? ገበታ ለሀገር የሚባል ፕሮጀክት የማን ነው ? ፕሮጀክቱ የኢትዮጵያ ህዝብ ቅድሚያ የሚሰጠው ነው ወይሰ የሌ/ኮ አብይ የቅደሚያ ቅድሚያ ፕሮጀክት? የሚሉ ጥያቄዎች መልስ እንፈልጋለን ሲል ሰራዊቱ በርካታ ጥያቄዎች አንስተው መልስ አላገኘም ፡፡ ሁለተኛ አላማ ሰራዊቱ የብልፅግና ፖለቲካና የጠ/ሚኒትሩ ደጋፊ ነው ለማለት ህ/ሰቡን ለማደናገር ነው፡፡

 


Back to Front Page