Back to Front Page

ከመጋረጃ ጀርባ… የፍትህ ደባ!

ከመጋረጃ ጀርባየፍትህ ደባ!

የፍትህ ስርአቱ፤ ስርአት አልበኛ ትርምስ! ህግ የለሽ አረመኔነት! ከመጋረጃ በስተጀርባ ምስክርነት ለፍትህ በቂ ከሆነ በቃ ላንቃችን ይዘጋ! ትንፋሻችን ይቋረጥ! ፍትህ የሚባል የለም፡፡

አርፈን እንቀመጥ!”  የእስረኞች ቃል!

                                                                                             በርሀ ሃይላይ 09-25-20

ይህ መስማት ለአንድ በፍትህ ስርአቱ ሚና ለነበረው ሰው መራራ የሂወት ፅዋ ነው፡፡ ፍትህ ዕኩልነትን ካላረጋገጠች በጭፈን ፍርድ ጥቂቶች ይጨቆናሉ! አገር ይፈርሳል! ሰው ከውልደቱ እሰከ እልፈተ ሞቱ ድረሰ የመብትና ግዴታዎች ባለቤት ነው፡፡ ነገር ግን ከህግ ይልቅ በፈጣሪ ላይ ያለን እምነት ይጠነክራል:: ምንም እንዃ በህግ ልገዛ የሚል የፀና እና ወደ ባህል የተሸጋገረ አስተሳሰብ ባይኖረውም የህዝቡ ባህል ከእምነቱ የተቀዳ እንደመሆኑ የመከባበርና የመቻቻል እንዲሁም እውነትን የመፈለግ ስነልቦና አለው፡፡ አንድ ማሕበረሰብ በሰላም እንዲኖር አስፈላጊ ከሆኑ ነገሮች አንዱ በሕግ አግባብ መኖር ነው፡፡

Videos From Around The World

የዛሬ ፅሁፌ ይሃው የእስረኞች ቃልና ሕገ መንግሥትና ሌሎችም ሕጎች እንዲከበሩ ዜጎች ሁሉ መብቶቻቸው ሲደፈሩ ማስከበር እንችላለን በማለት እምነታቸው የተረጋገጠ እንዲሆን የመንግሥት ሥልጣን አካላትም ሕጎችን ተከትለው መንግሥታዊ ኃላፊነቶቻቸዉን እንዲወጡና በጥቅሉ የሕግ የበላይነት በሕብረተሰብ ዉስጥ አብሶ ፍሬ እንዲያፈራ ጠንካራ የሆነ የፍርድ ቤት መዋቅር ተዘርግቶ ሕግን የተከተለ የዳኝነት ተግባር መከናወን አማራጭ የሌለው መንግሥታዊ ተግባር ነው ብለው ለሚያምኑ ከመጋረጃ ጀርባ የፍትህ ደባ ተጠየቅ ለማቅረብ ነው፡፡ እርግጥ ነው! በሰለጠኑት ሀገሮች ዉስጥ ይህ ተግባር በመንግሥትና በሕብረተሰቡ ዘንድ የቁጣ ማዕበልና አመፅ ይቀሰቅሳል፡፡ እኔ የምወዳት ሀገሬ ላይ ግን የሞት ፅዋ ይደግሳል፡፡

ነፃና ገለልተኛ የፍትህ ስርአት ማለት በህግ ብቻ መስራት ማለት ነው፡፡ በህግ የበላይነት ስር ባሉ መንግስታት በእኩል የሚያገለግል፣ በህግ የተገዛ ነፃና ገለልተኛ የሆነ ነው፡፡ የህግ የበላይነት በሌለበት ሁኔታ ስለ ፍትህ ብዙ ማውራት አስቸጋሪ ነው፡፡ አሁን እኛ ሃገር ያለው የጭቆናና በህግ ልገዛ የሚል አስተሣሠብ አልባ ነው። ህዝቡን አንቀጥቅጦ ለመግዛትና ለምዝበራ ሂደት ብቻ ነው ህጉ ጥቅም ላይ የሚውለው፡፡ ነፃና ገለልተኛ ተቋማት የሉም፡፡ ይህ በሆነበት ሁኔታ የግለሰቦች ነፃነትና የፍትህ ስርዓቱ እንኳንስ ፍትህ ሊሰጥ ቀርቶ ገለልተኛነት እንዴት ይታሰባል? ዳኞች ሙሉ ነፃነት አላቸውን? ሰብአዊ ፍርሃትና የግለሰባዊ አምባገነንነት ችግር ባለበት ሁኔታ ነፃና ገለልተኛ መሆን እንዴት ይቻላል? እነዚህ ሁሉ በሌሉበት ስለ ህግ የበላይነት ብዙ መናገር አይቻልም፡፡

1.  ወዴት? ፍርድ ቤት ለፍትህ ደባ!

ወንጀል የአንድን ማህበረሰብ ህልውና አደጋ ላይ የሚጥል ሳንካ ነው፡፡ ወንጀል ሲፈፀም ተጠያቂነት ሊከተል ይገባል፡፡ ነገርግን አጥፊን በመለየት አካሄድ ያላጠፋን ሰው እንዳይጠየቅና ንፁህ ሰው ያለጥፋቱእንዳይቀጣ ጥንቃቄ መደረግ አለበት፡፡ በዚህ መርህ መሰረት ማሰረጃ ከሳሸም ይሁን ተከሳሸ ለሚያቀርቡት ጥያቄ ፍርድ ቤትን እውነተኛ ውሳኔ እንዲሰጥ ከሚያግዙ ነገሮች አንዱና ዋንኛ ማረጋገጫ ነው:: በእኛ ኣገር የሕግ ስርዓት በመሰረቱ ማስረጃ ማቅረብና ምስክሮችን መመርመር የዓቃቤ ሕጉና የተከሳሹ ሃላፊነት ቢሆንም ፍርድ ቤቱም ሰፋ ያለ ሚና እንዳለዉ ማየት ይቻላል:: ፍርድ ቤቱ በምስክር ኣቀራረብና ምርመራ ያለው ሚና ሰፊ ነዉ፡፡ የማስረጃ አቀራረብ ህግን ተከትሎ እንዲፈፀም ስርአት ተበጅቶለታል:: ዋናው አላማም የዜጎች ሰብአዊ መብት እንዳይጣሰ መከላከል ሲሆን አፈፃፀሙም ህገ መንግስታዊ መርህ ጭምር የተበጀለት ነው፡፡ ማንም ሰው ጉዳዩን የማየት የመረዳት የማሰታወስ የመግለፅና እውነቱን ለመናገር ግዴታ እንደሚገባ እሰካወቀ ድረስ በህግ ብቁ ማሰረጃ ነው ተብሎ የህግ ግምት ይወሰዳል:: ይህም ማለት አካለ መጠን አለመድረሰ ወይም በህግ የተከለከለ ሰው ካልሆነ በቀር ማንም ከምሰክርነት አይከለከለም:: አዕምሮው ጤነኛ የሆነ ማንም ሰው በህግ ፊት ቀርቦ የማሰረጃነት ቃሉን የመሰጠት ተፈጥሯዊ የሆነ መብትና ግዴታ ያለው ሰለመሆኑ የኢፌዲሪ ህገ መንግስት በአንቀፅ 20 (4) ያሰቀምጣል::

በተከሳሹ ላይ የቀረበው ክስ መሰረት ባለው ፍሬ ነገር ላይ የተመሰረተ መሆን አለመሆኑን ለማረጋገጥ የግድ ምስክር መቅረብ ይኖርበታል፡፡ ይህ አስፈላጊ የሆነበት ምክንያትም በዘመናዊው የዳኝነት አሰራር ሓቁን አንጥሮ ለማውጣት ብቸኛው መንገድ በመሆኑ ነው፡፡ መንግሰት አንድን የወንጀል ክስ ከመመስረቱ በፊት ተፈፀመ የተባለው ድርጊት በሕግ የሚያስጠይቅ መሆኑንና የሚያስጠይቅ ነው ቢባል እንኳ ማስረዳት የሚቻል መሆኑን ማረጋገጥ ይጠበቅበታል፡፡ በኢፌድሪ ህገ መንግሰት አንቀፅ 20 (1) (4) መሰረትየተከሰሱ ሰዎች በመደበኛ ፍርድ ቤት ግልፅ በሆነ ችሎት የመሰማት መብት አላቸው፡፡ የቀረበባቸውን ማናቸውም ማስረጃ የመመልከት፣ የቀረቡባቸውን ምስክሮች የመጠየቅ መብት አላቸው፡፡በተቃራኒው የህግ የበላይነት ላለመኖሩ ማሳያ የሚሆኑት የሃገሪቱ ህገ መንግስቱንና ህገ-መንግስታዊ ስርአቱን በማክበርና ለማስከበር፣ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በሙስና፣ በሽብርና በሰብአዊ መብት ጥሰት ጥበቃ፣ በአገር ሉአላዊነትና ደህንነት ስራ የተሰማሩ ብሔራዊ ጀግኖች በመሸለም ፋንታ ተከሰው ላለፉት ሁለት አመታት እነሱ በእስር፣ ቤተሰባቸው በማህበራዊ እና ኢኮነሚያዊ ቀውስ ይገኛሉ፡፡ በዚህ ሳይበቃ አሁን ደግሞ ከማጋረጃ በስተጀርባ ምስክር እንዲሰማ በማለት ባልተለመደና ከህግ ውጪ መስከረም 5 12 19 እና 26 ፍርድ ቤቱ አዟል፡፡

 

2.  እንኳንስ ፍትህ ገለልተኛነት እንዴት ይታሰባል?

የመስከረም 5 12 19 እና 26 ከመጋረጃ ጀርባ የፍትህ ደባ የሚጀምረው ከሳሽ ዓቃቤ ሕግለምስክሮች ጥበቃ ለማድረግ ማንነታቸውና አድራሻቸው እንዳይገለጽ የወንጀል ምስክሮችና ጠቋሚዎች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 699/2003 አንቀጽ 4 ( እና ) ማንነታቸውና አድራሻቸው እንዳይገለጽ፣ ወይም እንዳስፈላጊነቱ በመጋረጃ በስተጀርባ ሆነውና ተሸፍነው ማንነታቸው ሳይገለጽ ምስክርነታቸውን እንዲያሰሙመደንገጉን በመጠቆም፣ የተከሳሾች ‹‹ምስክሮች ማነነታቸው ይገለጹልን›› ጥያቄን ተቃውሟል፡፡

ዓቃቤ ሕግ በዋናነት ተቃውሞውን ያቀረበው ምስክሮቹ ከመሰከሩ በኋላ በተከሳሾች ዘመዶችና ወገኖች ጥቃት ይደርስባቸዋል በማለት ነው፡፡ ተከሳሾቹ በበኩላቸው ባነሱት የመቃወሚያ ክርክር ለምስክሮች ደኅንነት ተብሎ ማንነታቸውና አድራሻቸው ለተከሳሽ እንዳይደርስ ሊደረግ አይገባም ህገ መንግስታዊ የመከላከል መብት ይንዳል በማለት ተቃወመዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ የሁለቱን ተከራካሪ ወገኖች ክርክር ካዳመጠ በኋላ ተከሳሾች ያቀረቡት ‹‹የምስክሮች ዝርዝር ይሰጠን ማንነታቸው ይገለፅልን በታማኝነታቸው ላይ የፍትህ ክርክር እናድርግ›› ጥያቄ፣ ከምስክሮች ጥበቃ አዋጅ አንፃር የምስክሮች ስም ማንነት ለተከሳሾች መገለፅ በምስክሮች ሕይወት ላይ አደጋ ያደርሳል ወይስ አያደርስም የሚለውን ፍርድ ቤቱ በማስረጃ ከማጣራቱ በፊት፣ የተከሳሾቹ ጥያቄ ሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 20(4) መሠረት፣ የምስክሮች ዝርዝር ተገልጾ ቢሰጣቸው በምስክሮቹ ላይ አደጋ እንደሚደርስ ማረጋገጥ ቢቻል፣ ተከሳሾች ማንኛውንም ማስረጃ እንዳያውቁ መከልከል ይቻላል አይቻልም የሚለው የሕገ መንግሥት ትርጉም በመዘንጋትና በአንቀጽ 20 (4) ምስክሮችን በሚመለከት የተደነገገው የተከሰሱ ሰዎች የቀረቡባቸውን ምስክሮች የመጠየቅ መብት ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ እንጂ፣ የምስክሮችን ስምና ማንነት ማረጋገጥ መብት የሚሰጣቸው አለመሆኑን ወይም ግዴታ የሚጥል አለመሆኑን አሳውቋል፡፡

ተከሳሽ የምስክሮችን ስምና ማንነት ማረጋገጥ መብት ፍትሐዊ የሙግት አካሄድን ከማሳካት ይልቅ፣ ምስክሮችን ለአደጋ የሚያጋልጡ ሁኔታዎች እንዳይፈጸሙ አስቻይ ሁኔታዎችን ለመፍጠርና በሕጎች አግባብ እንዲወሰን ለማድረግ ተከሳሾች በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 20 (4) መሠረት የምስክሮችን ማንነት ጋር የተያያዘ መርህ በመናድ የቀረበለትን የሕገ መንግሥት መብት ውድቅ ማድረጉን አሳውቋል፡፡ 

3.  የዳኝነት ስርዓት ፍትህ ማስፈንን መጻረር!

በመሰረቱ ዓቃቤ ሕግ ማቅረብ የሚችለው በወ/////ቁጥር124 መሰረት ባቀረበው ዝርዝር ላይ የተጠቀሱትን ምስክሮች ነው፡፡ የሚጠሩትን ምስክሮች ዝርዝርና የሚያስረዱትን ነገር ለተከሳሹ እንዲገልፅ የሚገደድበት ምክንያት ደግሞ ተከሳሹ ለመከላከል እንዲችል ሁኔታው እንዲመቻችለት ለማድረግ ነው፡፡ ምንም እንኳ በአሁኑ ጊዜ መለኮታዊ ሃይልን አለመፍራት እየሰፋ መሄዱ፣ በመለኮታዊ ኃይል ስም የሚደረግ የዕዉነት ማረጋገጫ የሚያስጨንቅና ዕዉነትን ብቻ ለመናገር የሚገፋፋ መሆኑ እየቀነሰ ቢመጣም ምስክሮች የምስክርነት ቃላቸውን ከመስጠታቸው በፊት መማል ወይም እውነትን ለመናገር ማረጋገጥ አለባቸው፡፡ ይህ ስነ ስርዓት ተደረገ ለማለት ብቻ የሚደረግ ሳይሆን ተከሳሽን ጥፋተኛ ወይም ነፃ የማስደረግ ውጤት ስላለውና እውነቱን ኣለመመስከር ወይም በሓሰት መመስከር በወንጀል ሕግ ስለሚያስጠይቅ የወንጀል ሕጋችን በቁ 453 ቀርቦ መመስከር በፍትህ አደባባይ ትልቅ ግምት ሊሰጠው የሚገባ ነው፡፡

 

ማሰረጃን ምክንያቶችን በማንሳት መቃወም ይቻላል:: ለምሳሌ በወንጀል ስነ ሰርአት ህግ ቁጥር 146 መሰረት ዐቃቤ ህጉ ወይም ተከሳሹ ማሰረጃ ሊሆን አይገባም በማለት መቃወሚያ ማቅረብ የሚችሉ መሆኑ ተደንግጓል ይህም ማለት ማሰረጃው የጥቅም ተካፋይነት የችሎታ ማጣት የወንጀል ተካፋይነት ወይም ሌላ ምክንያቶችን በማንሳት ፍርድ ቤት ቃሉን እንዳይቀበል መቃወሚያ መጠየቅና የሚቀርቡ ጥያቄዎች ላይ ተገቢ አለመሆንን በመቃወም ማቅረብ የሚቻል መሆኑን ያሰረዳል:: የወንጀል ምስክሮችና ጠቋሚዎች ጥበቃ ኣዋጅ ቁጥር 699/2003 አንቀፅ 2 (1) (2) መሰረትጠቋሚ ወይም ምስክርማለት በወንጀል ምርመራ፣ በወንጀል ክስ ወይም በወንጀል ማጣራት ሒደት መረጃ ወይም ምስክርነት የሰጠ ወይም ለመስጠት የተስማማ ከሚኒስቴሩ (ጠቅላይ ዓቃቤ ሀግ) ጋር የጥበቃ ስምምነት የተፈራረመ ምስ ክር፣ ጠቋሚ ወይም የምስክር ወይም የጠቋሚ ቤተሰብ አባል ነው፡፡

በጣም በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ሰብስበው ካጎሩ በኋላ ጥበቃቸውም ሆነ ጉዳያቸው ከመደበኛው የፍርድ ቤት መዋቅር ውጭ በልዩ ቁጥጥር ታፍነው እንዲቆዩ ከማድረጋቸውም በላይ የወንጀል ምስክሮችና ጠቋሚዎች ግዴታና መብት በህግ የተወሰነ ነው፡፡ በወንጀል ምስክሮችና ጠቋሚዎች ጥበቃ ኣዋጅ ቁጥር 699/2003 አንቀፅ 4 እና 5(3) መሰረትሊሰጥ የታሰበው ጥበቃ በሌላ ሰው መብ ትና ህጋዊ ጥቅም ላይ የሚያስከትለው ጉዳት መመርመር አለበት፡፡ ጉዳት የሚያስከትል ሆኖ ሲገኝ በፍፁም አይፈቀድም፡፡

ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ተጠቃሚን ከመኖሪያ ስፍራው ለጊዜው ወይም ለዘለቄታው በአገር ውስጥ ወይም በውጭ አገር በሚያዘጋጅለት ቦታ ማስፈርን ወይም የጥበቃ ተጠቃሚው ነጻነትን የሚያሳጣ ቅጣት በመፈጸም ላይ ከሆነ ቅጣቱን በመፈጸም ላይ ካለበት ቦታ ወደተዘጋጀለት ሌላ የቅጣት መፈጸሚያ ቦታ ማዛወርን የሚመለከት የጥበቃ እርምጃ፣ የጥበቃ ተጠቃ ሚን ግላዊ መረጃዎች በከፊል ወይም በሙሉ ከአዲስ ሁኔታ ጋር እንዲስማማ አድርጎ ማስተካከል፣ ለጥበቃ ተጠ ቃሚ ስውር ጥበቃ ማድረግንና የረጅም ርቀት የመገናኛ መሣሪያ በመጠቀም በመኖሪያ ቤቱ ላይ የሚደረግ ቴክኒካዊ ቁጥጥርና ቀረጻን፣ ለራስ መጠበቂያ የነፍስ ወከፍ መሳ ሪያ መስጠት፣ የመሳሰሉት ግዴታዎች ሳይወጣ የምስክሮች ጥበቃ ሕገመንግስቱን እና ስለ ምስክሮችና ጠቋሚዎች የወጣ አዋጅን በሚቃረን መልኩ በድብቅ እንዲደመጡ መፈቀዱ ተገቢነት የለውም፡፡ ተጠርጣሪዎች ለምስክሮች ጥያቄ የማቅረብ መብታቸው ተገድቧል፡፡ ፍትህ ለጉልበተኞች ተላልፎ ተሰጥቷል፡፡ ምናልባትም በግል ቂም በቀልም እየተያዙ የገቡ ኣልነበሩም ነበር ለማለት ኣይቻልም፡፡ ቂመኛው ማን እንደሆነ ታሪክ ይናገራል፡፡ ብቻ ፍርዱን ለእግዚኣብሄር መስጠት ይሻላል ምክንያቱም ኣማራጭ ስለሌለ ነው፡፡

ታድያ በምን አግባብ ነው ከመጋረጃ በስተጀርባ ምስክርነት መፍቀድ ለፍርድ ቤቱ አሳስቦት ይህ ያደረገው፡፡ ከመጋረጃ በስተጀርባ ምስክርነት መፍቀድ -ህገ መንግስታዊ፣ ፍትህ ስርአቱ መቀመቅ ውስጥ የሚከት፣ ሰብአዊ መብት ረገጣና የፍትህ ስርአቱ የፖለቲካ መሳርያ እንዲሆን የሚያደርግ የፍርድ ቤቶች ሽባነት ያሳየ ታሪካዊ ጥቁር ነጥብ፡፡

4.  እየየ ማለትም ሲደላ!

ልሂቃኑ ሳያውቁ በሰህተት ወይም አውቀው በድፍረት ከመጋረጃ በስተጀርባ ምስክርነት ለፍትህ በቂ እንደሆነ መርህ በመጣስ ተልእኮ ፈጻሚነታቸው በተግባር አረጋግጧል፡፡ ለሌባው ትልቁ ጉልበቱ ገዢው ነው ይል የለ የአገሬ ሰው፡፡ በፍርድ ቤቱ ትንታኔ መሰረት የምስክሮች ጥበቃ አዋጅ መሰረት ማድረጉ ነግሮናል፡፡ ይህ የፍርድ ቤቱ ሽባነት በተግባር ያሳየ ነው፡፡ ለምስክሮች ጥበቃ ማድረግ ያለበት እኮ መንግስት ነው፡፡ እንዴት ተደርጎ ማረምያ ቤት ያለ ተጠርጣሪ መንግስት ኃላፊነቱ ባለ መወጣቱ እንዲ ቀጣበት ይደረጋል፡፡ ለህግ የበላይነት ገና መታገል ያለብን ጊዜ ላይ ነን፡፡ አሁን የሚታየው መንግስታዊ የተጠና ውሸትን ስርቆትንና ዋልጌነትን የሚያበረታታ፣ ኢፍትሀዊነት፡ ለሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች በእኩል ማዳረስ አስፈላጊ ሆኖ ስለተገኘ የፍትህ ስርአቱ ለብሄር ማቻቻል ተብሎ 'ከዛም ብሄር አስራናል እኮ!' በማለት ዋልጌነት ለመሸፈን የእስር ዘመቻ ነው። እንጂ መንግስት የአገርና የህዝብን ሰላምና ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊነት ክዶ ለአገራችንና ለዓለም ህዝብ ሰላምና ደህንነት ከፍተኛ ስጋት የሆነው ሽብር፣ ሙስናና የኣገር ክህደት እንዳያጋልጡ ሉአላዊነትና የህዝብ ደህንነት ሲጠብቁ የነበሩ ሰዎች ስቃይ ከህሊና ስቃይ በላይ ነው፡፡ ኣይ እማማ ኢትጵያ! እየየ ማለትም ሲደላ! `I am concerned for the security of our great Nation; not so much because of any threat from without, but because of the insidious forces working from within.` Douglas MacArthur

 

አባሪ


ተከሳሾችና የስራ ድርሻ                                                            

1.    ጌታቸው አሰፋ  ሁለት ክስ 407/ 881             ዋና ዳይሬክተር

2.    ያሬድ ዘሪሁን 3 ክስ 407/881/881               //ዳይሬክተር

3.    መዓሾ ኪዳኔ 2 ክስ 407/881                    ዳይሬክተር

4.    አማኑኤል ኪሮስ 2 ክስ 407/881                 ዳይሬክተር

5.    ደርበው ደመላሽ 2 ክስ 407/881                 ዳይሬክተር

6.    ተስፋዬ ኡርጌክስ 407/881/881             መምሪያ ሀላፊ 

7.    ተስፋዪ /ፃዲቅ 2 ክስ 407/881                 መምሪያ ሀላፊ

8.    ጎሃፅባህ /ህይወት 2 ክስ 407/881               ዋና ሀላፊ

9.    አፅበሃ ግደይ 2 ክስ 407/881                    መምሪያ ሀላፊ

10. ቢንያም ማሙሸት 2 ክስ 407/881               መምሪያ ሀላፊ

11. አሰፋ በላይ 2 ክስ 407/881                     መምሪያ ሀላፊ

12. ሺሻይ ልኡል 2 ክስ 407/881                   ዋና ክፍል ሀላፊ

13. ሸዊት በላይ 2 ክስ 407/881                    ምክትል መምሪያ ሀላፊ

14. ዮሐንስ )/እግዚኣብሄር) ውበት 2 ክስ 407/881    ዋና ክፍል ሀላፊ

15. ነጋ ካሴ 2 ክስ 407/881                       የክፍል ሀላፊ

16. ተመስገን በርሄ 2 ክስ 407/881

17. አዲሱ በዳሳ 2 ክስ 407/881                   /መምርያ ሀላፊ

18. ሳሙኤል ጋዲሳ 1 ክስ 407                    ዴስክ ሀላፊ

19. አህመድ ገዳ 2 ክስ 407/881                  ምክትል ሀላፊ

20. እዮብ ተወልደ 1 ክስ 407                     /ቤት ሀላፊ

21. ሰይፈ በላይ 1 ክስ 407                       ክፍል ሀላፊ

22. ተሾሜ ሀይሌ 2 ክስ 407/881

23. አሸናፊ ተስፋሁን 2 ክስ 407/881              ዋና ክፍል ሀላፊ

24. ደርሶ አየነው 2 ክስ 407/881                  ክፍል ሀላፊ

25. ሓዱሽ ካሳ 2 ክስ 407/881                    //ሃላፊ

26. ማርክስ ፀሃዬ 2 ክስ 407/881                 ምክትል ክፍል ሃላፊ

 ክስ

·       የወንጀል ህግ አንቀፅ 407 (1) እና ሐ፥ ስልጣን ያለአግባብ መገልገል

·       881/2007 አንቀፅ 9 (1/ እና 9/3) ስልጣንን አለአግባብ መገልገል 


 

Back to Front Page