ከብት ባልዋለበት ኩበት ለቀማ
ሙሉጌታ በሪሁን ከሃገረ ካናዳ 7-27-20
ጠ/ሚ አብይ አህመድ ፣ እንደነ ንጉሡ ጥላሁንና ፣ ዳንኤል ክብረትን ፣ የመሳሰሉ አፈቀላጤዎችና ፣ ካሳ ከበደ ፣ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ ፣ ካሳ ጨመዳ ፣ ብርሃኑ ነጋ ፣ የመሳሰሉ የዉስጥ አማካሪዎችን ፣ ይዞ ፌደራላዊትና ዲሞክራሲያዊት ኢትዮዽያን መምራትም ሆነ መገንባት አይችልም ።
ኢትዮዽያ ሃገራችን ወደ ኃላ ከጎተታት ዋነኛው ምክንያት ፣ ከዘመነ አፄ ምሊሊክ እስከ ስው በላው አምባገነኑ የደርግ ዘመን ፣በድምሩ ከ፻(100)ዓመት በላይ የተጠናወታት ፣ የዘመነ መሳፍንትና ፣ የነፍጠኞች የስግብግብነት ፣ የተስፋፊነት ሁሉም የኛ አባዜ ነበር ።
ይቅርታ ይደረግልኝና ፣ ሌባን ሌባ ማለትን እንልመድ ። የትምክህተኞቹ ጎራ በዘረጉት የትየ ለሌ ሚድያ ያለ እረፍት የውሸትና ፣ የቅጥፈት ፕሮፓጋንዳቸውን መመከት የምንችለው ሃቁን ያለ ይሉኝታ መናገር ስንችል ብቻ ነው ። ያለን አማራጭም ይህ ብቻ ነው ።
እንሆ ይህንን አሰከፊ ስርአት በእልህ አስጨራሽ የ፲፯(17) ዓመት የብረት ትግል በጀግናው የወያኔ ጦር መሪነት ላይመለስ አፈር ከድሜ ከቀላቀሉት በኃላ ለካ የእባቦቹ ጭንቅላት አልቀበሩትም ኖሯል ፤ ከ፳፯(27) አመት የሰላም፣ የእድገትና ፣የብሩህ ተስፋ ጉዞ የኃሊት በቅጽበት ማሽቆልቆል ጀምረናል ። የአማራው ልሂቃንና የነፍጠኞቹ ጠበቆች ፣የኢትዮዽያ ታሪክ ፣ ባህል ፣ ቛንቛና ፣ ስልጣኔና ፣ የሃገሪቱ እድገት በአጠቃላይ ከንጉሳቸው ከምሊሊክ ጀምሮ ኢትዮዽያን እንዳሳደጉ ሲመጻደቁ መስማታችን ይገርማል። ለምሳሌ አፄ ምሊሊክ ዘመናዊነትን ወደ ኢትዮዽያ ያስገባ ንጉሥ ነው በማለት ከኔም ጋር የተከራከርኩበት ግዜ አለ ፣ ለመሆኑ አፄ ምሊሊክ ወደ ኢትዮዽያ ካስገባው ስልጣኔ ጥቀሱልን ሲባሉ ፣ ተንደርድረው የምድር ባቡር ፣ቴሌፎን ፣ መኪና ፣ ባህር ዛፍ ይሉና ፣ ሽርሙጥናን ይረሷታል። ጥሩ ባህር ዛፍ ሁላችን እንደምናውቀው የማአድን ጠር የሆነ መጥፎ ተክል ነው ። በአሁኑ ዘመን ከጥቅሙ ጉዳቱ ስለሚያመዝን ኢትዮዽያ በሃገር በቀል ዛፎች እየተዋበች ነው። በተለይ ደግሞ በትግራይ ፨ ነጮች የአውስትራልያ ባህር ዛፎ ሲሰጡን በወቅቱ የጠቀሙን ቢመስለንም ፣ መሬታችን የተዘሩባት ሰብሎች የሚገባውን ምርት እንዳይሰጠን ባህር ዛፍ የመሬት ማአድናችንን ቅርጥፍ አድርጎ ተሻምቶናል ፣ ለሃገራችን እድገት በቀደዱልን ቦይ በመፍሰስ ለኃላ ቀርነታችን የራሳችንን አስተዋፅኦ አድርገናል።
የምድር ባቡር ፤ እርግጥ ነው የጅቡቲ ድሬዳዋ አዲስ አበባ ሃዲድ ተሰርቷል ፣ ግን ጅቡቲን የሚያክል መሬት ሽጠህ ፣ምንም አይነት የውጭ ንግድ ግብይት ሳይኖርህ የአስፋልት መንገድ የሌላትን ሃገር ላይ የባቡር ሃዲድ መመኘት ከበስተ ጀርባው የተገኘው ገንዘብና የጦር መሳርያ ምን አይነት ሃገራዊ ራኢይ ለማሳካት ነበር ? ኢትዮዽያን ለማሳደግ ወይስ በነጮች ድጋፍ ግዛትን ለማስፋፋት ? አንተና/አንቺ የሚታየውንና የሚጨበጠውን ሃቅ ስትክድ/ዱ እኔ/እኛ ያንተን/ቺን ቅራቅምቦ የትርክት ወሬ ማመን አለብን ? የለብንም ። እሾህን በእሾህ አሉ፨ መኪናም ይላሉ ፣ የነፍጠኞቹ ግብዝነት ከዚህ መረዳት ይቻላል ፣ ለመጀመርያ ጊዜ ምሊሊክ መኪና ያየበትና መኪና ላይ የወጣበት ጊዜ ፣ ከኢትዮዽያ ህዝብ ስልጣኔና እድገት ጋር ምን ያገናኘዋል ?
የሚሊሊክ ባለመኪና መሆን ለኢትዮዽያ ህዝብ ምኑ ነው? መልሱ ለናንተ ልተወው ።ዘመናዊ ማረሻ የሌለው ህዝብ ሰለ ዘመናዊ መኪና ብታወራለት አይገባውም ፣ ደግሞም ለህዝቡ ምኑም አይደለም ፤ ስልክ ፣ አጃኢብ ነው አሉ ፡ ስልክ ባቡር መኪና ወደ ኢትዮዽያ የገባበት ዋናው ምክንያት ጣልያን የሶማልያው ፑንትላንድና ኤርትራን በቅኝ ግዛቱ ውስጥ ስለነበሩ ፣ ከፈረንሳይና ከእንግሊዞች በነበራቸው የምስራቅ አፍሪካን ሃገራት ቅርምት ፣አላማቸውን ለማሳካት ምሊሊክን በፍሬ ከርሲኪ ስጦታዎች እየደለሉ ኢትዮዽያን በቁጥጥር ስር ውስጥ ማስገባት ነበር ። ከነዚህ ሁሉ የዘመኑ ቴክኖሎጂ ወይም ስልጣኔ ፣ የተጠቀሙት የገዢው መደብ አባላትና ፣ ጋሻ ጃግሬዎቻቸው እንጂ፣ ሰፊው የኢትዮዽያ ህዝብ ፣ እስከ ዘመነ ህ.ወ.ሓ.ት ፼፱፻፹፫ (1983)ዓ/ምህረት የስልጣኔ ጭላንጭል በመደብ ገዢዎቹና ቤተሰቦቻቸው ቅንጡ ሂወት በማየት ነበር የሚያውቀው።
ለምሳሌ እስከ ደርግ ዘመን ፡ የኢትዮዽያ ህዝብ አማካኝ የእድሜ ዘመን ፵፰ (48)ነበር ፤ በአሁኑ ስአት የአንድ ኢትዮዽያዊ አማካኝ የእድሜ ዘመን ወደ ፷፰(68) ዓመት ከፍ ብሏል። የአማካኝ እድሜ መጨመር ደግሞ የሃገራዊ እድገት ውጤት ነው ። ወሬ ፡ ሃሜት ፡ ምቀኝነት ፡ ክፋት ፡ ተንል ፡የእድገት መለኪያዎች ቢሆኑ ኖሮ ፤ በዚህች አለም ውስጥ የኢትዮዽያን ህዝብ በተለይ ነፍጠኞቹ የሚወዳደር ባልተገኘ ነበር ። ለምሳሌ ምሊሊካውያን ፣ ደርጋውያን ህዝቡን በኃላ ቀር ባህልና ወግ ጠፍንገው አስረው ፡ ለ፻ (100)ዓመት እን ን ሊስሩት ፣ አልመዉት የማያውቁትን ፤ እድገት ወያኔው ህ.ወ.ሓ.ት በ፳፯(27) አመት በሳይንስ ፣ በቴክኖሎጂ ፣ በኢንዳስትሪ ፣ በትምህርት ወ.ዘ.ተ የተገኘው ለውጥ ያየሰው ይመስክር ፣ ምክንያቱም የሚታየውን የሚዳሰሰውን ፣ አላየንም ለሚሉት ነፍጠኞችና ትምክህተኞች በድንጋይ ላይ ውኃ እንደማፍሰስ ነው ፤ይህ ደግሞ ስነልቦናዊ ቀውስ የሚፈጥረው ጫና ይመስለኛል ። አንድ በተፈጥሮው የላሸቀ ህሊና ያለው ሰው ፣ በተለይ ለነ ቅጣው ፣ አሸብር ፣ ግዛቸው ፣ ኩራባቸው ፣ ደምመላሽ በሚል ስነልቦና የተገነባ , ስነልቦና ላላቸው ትምክህተኞች ፤ ፍቅር ፣ ሰላም ፣ አንድነት ፣ እኩልነት ፤ብሄር ብሄረሰቦች የሚለው መርህ ፣ ለነሱ ጉንጭ አልፋ ፣ ከመፈክርነት ውጭ የዘለለ ትርጉም የለውም ። ምንም ብትልና ብትሰራ ፣ ከራሱ የአስተሳሰብ ደረጃ ወጥቶ የማሰብና ፣ የማየት ችሎታ ስላሌለው ፣ ከእውነታው ውጪ እራሱ በፈጠረው የተዛባ እኔነት ከሌሎች ወንድም ህዝቦች ጋር እየተላተመ ይኖራል። ለምሳሌ ትምክህተኞችና ነፍጠኞች የአማራው ሊሂቃን በአሁኑ ስአት ከትግራይ ፣ ከቤንሻንጉል ፣ ከኦሮሞ ፣ ህዝቦች ጋር ቀን በቀን ሲላተሙ የሚውሉት ሌላ ምክንያት ኖሮዋቸው ሳይሆን ፣ ወላጆቻቸው ያቦኩትን ቡኮ እንደነበረው ካልቀጠለ ፣ ሁሉም የኛ የሚለው አባዜ ነው ። ከሁሉም በላይ ግን የታሪክ ዝርፊያቸው ወደር የለውም በቀላል ማስረጃ ላቅርብና የኢትዮዽያ ህዝብ ሚዛናዊ ፍርዱን ይስጥበት ። የአባይ ግድብን እንይ ፣ ይህንን የምተርክላቹህ ታሪክ እዚሁ በምኖርበት አከባቢ የተከሰተ እውነተኛ ታሪክን መሰረት በማድረግ ነው ። የግድቡ የመሰረት ድንጋይ በክቡር ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ከተቀመጠበት ፣ ከተበሰረበ ስአት ጀምሮ በዚህ አከባቢ ያለነው ኢትዮዽያውያን ፡ ብሄር ብሄረስቦች ማለትም የኦሮሞ ፣ የትግራይ ፣ የሶማልያ ፣ የሃረሬ በጣት የሚቆጠሩ አማሮች ያለማቛረጥ ለ፭ዓመታት ለግድቡ የቦንድ ሺያጭና የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቶችን አድርገናል ፤ ታድያ እዚህ ካለነው ኢትዮዽያዊያኖች በሙሉ በብዛት አማሮቹ ላቅ ያለ ቁጥር ቢኖራቸውም ግድቡን የሚያዩበት መነፅር በተንሸዋረረው የወያኔ የፖለቲካ ቁማር እንጂ ፣ እንደ ሃገራዊ የኢኮኖሚ እድገትና ፣ የሃገር ልማት ስላልነበረ ፣ ባካሄድናቸው የገንዘብ ማሰባሰብያ ዝግጅት አንድም ቀን አልተሳተፉም ። እኔ በግሌ የማውቃቸው የቅርብ ደኞቼ በግድቡ ዙርያ ስንከራከር ፣ ምክኒያታቸው ከግል የህ.ወ.ሓ.ት ጥላቻ የተነሳ ነበር የሚቃወሙት ፤ ሃገርና የፖለቲካ ድርጅትን ለይቶ የማያይ ኢትዮዽያዊነት ምን ይባላል ? ፍርዱ ህሊና ላለው ፍጡር ልተወው ። ሆነና ነገሩ ፣ ትናንትና የህ.ወ.ሓ.ት የፖለቲካ መሳርያ ሲባል የነበረው የህዳሴ ግድብ ፤ ከምኔው ግድባችን መባል ተጀመረ ? ትንሽ ሃፍረት የሚባል ያልፈጠረባቸው ጉዶችን ማየት ቻልን ፤ እንሆ ከብት ባልዋለበት ኩበት ለቀማ ማለት ይሄ ነው ። ታድያ የፈለከውን/የፈለግሽውን ብትቛምጥ/ብትቛምጪ ፣ ታሪክ ለሰሪዉ እንጂ ለቀላዋጭ አይሰጥም ።
እነ ፕሮፌሰር አለማርያም ፣ ታማኝ በየነ ፣ ኢሳቶችና ፣ ትምክህተኛው የአማራ ዳያስፖራ ፣ ዛሬ ደርሶ ፣ የመፈክር ጋጋታ ፣ ጭብጥ ማስረጃ የሌለው ውንጀላ ፣ የአቅመ ቢሶች ፀባይና ተግባር ነው ። ለምሳሌ ደርግ ያለምንም ደም ኢትዮዽያ ትቅደም ፣ ብሎ መጥቶ በ፪ዓመት ውስጥ ሃገሪቷን በወጣቱ ደም አጠባት ፣አብይ አህመድም ሳናጣራ አናስርም ፣ብሎ ስልጣን ላይ ወጥቶ ፣ በአሁኑ ስአት እሱን የተቃወመ ሁሉ እስር ቤት ታጉሯል ። እኔምለው የአማራ ልሂቃን ብአዴኖች ለ፳፯(27)ዓመት ተላላኪዎች ነበርን አሉን ፣ አሁንስ እግር ላሾች ፣ ወይሰ ምን ሆኑ ? ለማንኛውም መፈክሩ ማንም ይበለው ፣ እንደ ጀመርነው እንጨርሰዋለን ፤ ይህ የክቡር ጠ/ም መለስ ዜናዊ የአመራር ፣ የፖለቲካ ብልጠትና ፣ የትግራይ ህዝብ የትግል ውጤት ፣ ከመሆኑም ባሻግር የድፍን የኢትዮዽያ ህዝብ የእጅ አሻራ ያረፈበት የማንነት መገለጫችን ስለሆነ ፣ እንደ ጀመርነው እንጨርሰዋለን ። እልል ግድባችን ውኃ መያዝ ጀመረ ተብሎ ዳንኪራ መመታቱ ለነዛ ከጅምሩ እስከ ዛሬዋ እለት በጉልበታቸው ፣ በፋይናንሳዊ ድጋፍ ላበረከቱት ፣ እንጂ ለሃፍረተ ቢሶቹ አይመለከትም ፤ እልልታና ሽለላ ከማስቀደም እስኪ በእጃቹህ ቦንዱን ያዙ ፣ ኪሳችሁን ዳበስ አድርጋቹህ ቦንዱን ግዙ መጀመርያ ፤ ወኃ መያዙ ይህን ያክል ያሰጨፈራቸው ፣ ግድቡ ውኃ ላይሞላ ነውዴ የተገነባው ? ሌላው ይህንን ፅሁፍ ለመፃፍ ያስገደደኝ ፣ በዛሬው እለት የአማራ ሀሁ ሚዲያ የመጀመርያው የአባይ ግድብ የውኃ ፕሮጀክት የመሰረት ድንጋይ በቀዳማዊ ሃይለ ስላሴ ሲቀመጥ ብሎ ዜና አቀረበ ፣ ከብት ባልዋለበት ኩበት ለቀማ ያልኩትም ለዚህ ነው ፣ የሚያሳዩት ስእል ደግሞ ሃይለስላሴና እንጅነር ስመኘውን ነበር ገረመኝ ሳላውቅ ፣ የጠ/ም መለስ ሰም ፣ ሃይለ ስላሴ ሆነዴ ? ብዬ እራሴን ጠየኩኝ ። እዉነትም የህሊና ችግር ,የሰነልቦና ቀውስ እንዳለ ገባኝ ፣ ግን እራሴን ደግሞ ጠየኩኝ አንድ ድፍን ማህበረ ሰብ መሳሳት ይችላልን ? ለሚለዉ ጥያቄ ፣ በርግጥ እንዳለ ድፍን ማህበረሰብ ባይሳሳትም ፣ አንድን ነገር ሃቅ ነው ? ወይስ ውሽት ? በማለት ነገርን መዝኖ ፍርድ መስጠት ፀጋ ቢሆንም ፣ አለመቃወም መስማማትን ይወክላል ።
እኔ የትግራዋይን ጥቅም ፣ ደህንነት መከላከል ትክክለኛ ውሳኔ ነው ብዬ ስላመንኩኝ ፣ የህዝቤን ጥቅም ሰላም ደህንነትን ፣ የሚጋፋ የሚፃረርን ሃይል እየታገልኩኝ ነዉ ። ነፍጠኞችን ትምክህተኞችን የታሪክ ሌቦችን እጋፈጣለሁኝ ፣ እስከ መስዋእትነትም ለመክፈል ዝግጁ ነኝ ፣ ምክንያቱም ትግራዋይነት የተከበረ ማንነት ነው ፤ ስለተመኘከው የምታገኘው ማንነት አይደለም። ሰው እንዴት ከትናንትና ስህተቱ መማር ያቅተዋል ? ሰው እንዴት የሚያየውን ማመን ይከብደዋል ? ሰው እንዴት ሌሎች ይታዘቡኛል አይልም ? ይገርማል የሽዋዎቹ የምሊሊክ ደቀመዛምርት ፣ ስልጣኔ በኢትዮዽያ ውስጥ ከነበረ ፣ እንዴት ሃገራችን ኢትዮዽያ በርሃብና በበሽታ ከመቶ አመት በላይ ህዝቦቿ ተሰቃዩ ? እኔ ሃገሬን ሳውቃት የአንድ ዩኒቨርሲቲና የሁለት ኮለጆች በለቤት ብቻ ነበረች ። እነሱም ቀ.ሃ.ስ ፣ ሃሮማያ ኮለጅና የባህርዳር ኮለጅ ብቻ ነበሩ። በ፳፯(27) ዓመት ውስጥ ግን ከ፵ (40)ዩኒቨርሲቲና ኮለጆች የገነባን ስርአት በምን መለኪያ የጨለማ ዘመን ሆነ ? ሌባ ላመሉ ዳቦ ይልሳል አሉ ። ዩኒቨርሲቲዎቹ ጥራት ያለው ትምህርት አይሰጡም ሲሉ የሰማሁኝ መሰለኝ ፣ ማንም ደደብ ኮርጆ ገብቶ በመጀመርያው አመት ከተባረረ የማን ድክመት ነው ? ይህ አካሄድ ሃገሪቷ ወዴት ይወስዳት ይሆን ? ብዬ እራሴን ስጠይቅ እያንዳንዱ ኢትዮዽያዊ ህሊናውን ከፍቶ ምን እየተደረገ እንዳለ ማየት ተገቢ ነው ብዬ አምናለሁኝ ። ይህች ሃገር በርግጠኝነት ለመናገር ፣ የምሁራን ድሃ መሆኗ ፣ የወላድ መካን መሆኗ አሉ ባይባልም ፣ ህዝቧ አይእምሮው ካላሰራው ወደኃሊት ከመቶ ሃምሳ አመት በፊት ወደነበረችበት የዘመነ መሳፍንት ኢራ ወይም ዘመን ከመመለስ የሚያግዳት ነገር አይታየኝም ። ሰው እንዴት ከአለም እድገት አይማርም ? ጃፖን ከ፹(80)ዓመት በፊት ከኛ ያነሰ ህዝብና እድገት ነበራት ፤ ቻይና ከ፶(50)ዓመት በፊት የማኒፋክቸር እድገት ስላልነበራት ቸርማን ማኦ ሱቲንግ ትኩረታቸው በእርሻው ክፍለ ኢኮኖሚ ነበር ፣ ደቡብ ኮርያ ከ፶(50)ዓመት በፊት አይደለም የኢኮኖሚ እድገት ፣ የመኖር ዋስትናዋ መከላከል በማትችልበት ደረጃ ስለነበረች ፣ ነው በጀነራል አማን ሜካኤል ዓንዶም መሪነት የኢትዮዽያ ድጋፍ የተደረገላት ፣ እነዚህ ከላይ የጠቀስኴቸው ሃገራት በአሁኑ ጊዜ በአለም አሉ ከሚባሉ ሃብታም አገሮች ውስጥ ናቸው ። ታድያ ለምን እኛ ወደ ዘቀጥንበት ዝቅጠትት ተዳረግን ? ለምን ?
መልስ የሌለው ጥያቄ ፣ የኛ ሙሁሮች ምን ትላላቹህ ? ማውራት የእድገት መለኪያ አይደለም እንጂ , ቢሆን ኖሮ ፣ ከአለም ወደር የማይገኝልን የወሬ ቛቶች በመሆን እንሸለምን ነበር ። ስማችንም እንደነ ቻይና አሜሪካ ጃፓን የአለም የወሬ ቜቶቹ ኢትዮዽያዊያን እንባል ነበር ፣የድንቁርናችን ጥልቀቱ ደግሞ ፣ ዛሬም በዘመነ ፯ኛው ንጉስ አብይ አህመድ ከቅርብ ስህተታችን ከደርግና ከኢህአዴግ አለመማራችን ነው ። ወያኔው ህ.ወ.ሃ.ት ፡ ጦርነት ብቻ ሳይሆን ፣ ፖለቲካን ፣ ኢኮኖሚን ፣ዲፕሎማሲን የሃገር ልእላዊነትን ጨምሮ ሰላምና ደህንነት ፣ ለ፳፯ (27)ዓመት በተግባር ያስመሰከረ ብቃት ያለው ፣ በአፍሪካ ረዘም ያለ ልምድና እድሜ ያለው የፖለቲካ ድርጅት ነው ። ወደድክም ጠላህም ይህንን እውነታ መቀየር አትችልም ምክንያቱም የአንድ ፖለቲካዊ ድርጅትም ሆነ መንግስት ፣ ጥንካሬ የሚለካው ባለው ህዝባዊነት ነው ። የመሽረፈት፣ኢሳያስ አፈወርቂና ፣ የህወሓት ልዩነትም እዚህ ላይ ነው ። የትግራይ ህዝብ እስከነ ስህተቷ ህ.ወ.ሓ.ትን ዳግም በደሙ ይጠብቃታል, እንጠብቃታለን ። ይህ ማለት ግን ፍፁም የሆነ ምንም እንከን የሌለው የፖለቲካ ደርጅት ነው ማለት አይደለም ፣ የሚስራ አይእምሮ ይሳሳታል ፣ በብስል ማሃል ጥሬ እንደሚገኝ ሁሉ ፣ በህ.ወ.ሓ.ት አመራር ውስጥም ሌቦች ፣ ክሃዲዎች ፣ የድርጅቱ አላማ ወደ ግል ጥቅማቸው የቀየሩ የሉም ማለት ግን አይደለም ፣ የህ.ወ.ሓ.ት አመራሮችና ድርጅቹ በሚከተለው የዲሞክራሲ መርህ መሰረት ስልጣናቸው ያለምንም ጦርነት, በሰላም አስረክበው ሲያበቁ ፣ የወሬ ጀግኖቹ ፡ ጭራሽ አፋቸው ለከት ባጣ መልኩ ወደ ውንጀላ ገቡ ። ላለፈው ፳፯(27) ዓመት ለተፈጠረው የመብት ጥሰትና ግፍ ፣ የህ.ወ.ሓ.ት አመራር ተጠያቂ አድርገዉት እርፍ አሉ። ተጠያቂነት ከሆነ እየለዩ የሚባል ነገር የለም ፣ አባዱላ ገመዳ የታወቀ ሙሰኛና ፣ በሃገር ሃብት በተለይ የኦሮሚያ መሬት ፣ እንደ ግል ንብረቱ ቸብችቦ የጨረሰ ሙሰኛ ነው። ሽፈራው ሽጉጤ የአዋሳ ሃብትና ፣ ፎቆችን የተቆጣጠረ ሙሰኛ ነው ። ሃይለማርያም ደሳለኝ የደቡብ ክልል አስተዳደር እያለ በብዙ ወንጀሎች ይታማል ፣ ደመቀ መኮንንና ገዱ አንዳርጋቸው ፣ ከሙስናቸው ባሻገር በቅማንትና ፣ በአገው ማህበረሰብ ፣ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተጠያቂዎች ናቸው ። ታድያ ማንላይ ቆመሽ፣ ማንን ታሚ ? ነው ነገሩ ሚዛናዊነት ለሌለዉ አስተሳሰብ ምንጩ ምንድነው ? ብለን ብንጠይቅ መልሱ ያው የተለመደው የበታችነትና ፣ ቅናት ነው፣ የሚል እምነት ነው ያለኝ ፣እንጂማ ሰው ስትወነጅል ማስረጃ የሚባል ህጋዊ ጭብጥ ማቅረብ ያስፈልጋል ።ሌባ ሌባ ነው ፤ ወንጀለኛም ወንጀለኛ ነው ፣ ትናንትና ክልሉን ሲመዘብር ፣ሲበድል የነበረን ተላላኪ ፣ የለውጥ ኃይል ብለህ ፣ ስለ ሃገር ሲል በርሃብ ፣ በመከራ ለ፲፯ (17)ዓመት ወጣትነታቸውን ሰውተው ፳፯(27)ዓመት ከደህነት ፣ ወደ ሁለት ድጅት የኢኮኖሚ እድገት ቀይረው አገርን ፣ በሰላም ላስረከቡ ጀግኖች ፣ ውንጀላ የጤናም አይደለም። ለዚህም ነው ፈልገን ሳይሆን ተገደን እራሳችንን ወደ መከላከል የገባነው ።
ለምሳሌ ንጉስ ሃይለ ስላሴ የወሎ ህዝብ በርሃብ አለንጋ እየተገረፈ እንደ ጉድ ሲረግፍ ፣ እሳቸው ግን የውሻቸው ልደት በኬክ ያከብሩ ነበር ።
የኢትዮዽያ ህዝብ በበሽታና ፣ በድንቁርና ተሸብቦ ፣ በርሃብ አለንጋ ሲረግፍ ሲቸገርና ፣ እሳቸው ግን ፲፫ (13)ሚልዮን ዶላር በሰዊዝ ባንክ አስቀምጠው የሃገሪቷን እድገት ጎድተውታል። መጨረሻቸውም ሳይበሉት ደርግ አሰናበታቸው ። መንግስቱ ሃይለማርያም የሃገሪቷን ሃብት እንዳለ ለወታደራዊ አቅም ግንባታ አዉሎ ለ፲፯ ዓመት በደም ካጨማለቃት በኃላ ፣ መጨረሻው የሃገሪቷን ልዓለዋይነት በታትኖ በ፴፬(34)ሚልዮን ዶላር ቤተእስራኤሎችን ፣ በካሳ ከበደ አማካኝነት ሸጦ ፣ እንሆ ዙምባቤ በናጠጠ የእርሻ ኢንቨስትመንት ኑሮውን ይኖራል ።
ፅንፈኞቹ የህ.ወ.ሓ.ት አመራር ሃገሪቷን ዘርፈው ሄዱ ይላሉ ፣ ጥሩ የተዘረፈው ነገር ምንድነው ? ዘረፉም እንበል ፣ ከሃገር ውጭ ግን አለማሸሻቸውን ሃገራቸውን ጠቀሙ እንጂ ሃገርን ዘርፈው አለመሸሻቸው ሊያስመሰግናቸው ይገባል ፣ ለምሳሌ አዲስ አበባ፣ አዋሳ ፣ አዳማ ፣ ባህርዳር ፣ መቐለ እድገታቸው የወያኔዎቹ የአመራር ብቃት ነው ።ኢንዱስትሪ ፖርኮቹ , ዊንድ ተርባይኖቹ, ባቡሩ ,የመንገድ እድገቱ ፣ የወያኔዎቹ የአመራር ብቃት ነው ። የነ ንጉሱ ጥላሁንና ፣ የነ ደመቀ መኮንን ፣ ሆድ አደርነት ውጤትማነት ፣ ይኄው ሁለት አመት ከጥፋት ውጭ የተሰራ አዲስ ነገር አላየንም ። ካለም በአይናችን እንየው አሳዩን ፣ ንገሩኝ ። ሃሳቤን ለማጠቃለል ያህል ነፍጠኞችና ፣ ትምክህተኞች ረጋ ብላቹህ አስቡ ፨ እድሜ ላዛ ወርልድ ክላስ ፨ ምጡቅ የአእምሮ ባለቤት ጠም መለስ ዜናዊ ይሁንና ፣ ኢትዮዽያ ወደ ኃላ ላትመለስ ፣ በፌደራል ስርአት ውስጥ ገብታለች ። የኢትዮዽያ መለያ ሰንደቃላማም አረን ዴ ፣ ቢጫ ፣ ቀይ ፣ በማሃሉ ኮከብ ሆኗል ። አከተመ ። ልሙጡን ባንዲራ ስትፈልጉ የአማራ ክልል መለያ አድርጉት ፤ ስትፈልጉ አቃጥሉት ፤ የኢትዮዽያ ብሄር ብሄረሰቦችና ፣ ህዝቦች ወኪል ግን ከቶውንም አይሆንም ። የኢትዮዽያ ፖለቲካም ፣ ጥርት ወዳለ ሁለት ጎራ መጥቷል ፣ ይሄም አሃዳውያን ፣ ጠቅላዮች ሁሉም የኛ ና ፤ የፌደራል ሃይሎች አንድነታችን ፣ እስከነ ልዩነታችን ፣ ወደሚል መስመር ጠርቷል ፤ በዚህኛው መስመር ደግሞ የኦሮሞ ፣ የትግራይ ፣ የሶማሌ ፣ የቤንሻንጉል ፣ የሲዳማ የአፋር ፣ የጋምቤላ ህዝቦች ሲሰለፉ ፤ በአሃዳዊው ጎራ ደግሞ ፣ የአማራና የከዚህና ፡ ከዚያ ስብስብ ፣ የጥቅም ተጋሪዎች ጥምረት ሆኗል ። ልዩነቱ የህዝባዊነትና ፤ የውጭ ሃይሎች የረብጣ ገንዘብ ድጋፍ ላይ የተመሰረተ የሃገር ክህደት ብቻ ነው ።
ስለዚህ ፣ የዚህ ሃገር ጠንቅ ፡ ማን እንደሆነ በግልፅ ለይቶለታል ፤ በርግጥ ላለፋት ረጅም አመታት በተለይ ደግሞ ላለፉት፳፯ አመታት ሚዲያውን በመቆጣጠር የቻላችሁትን ያክል ህዝቡን አደናግራችሁት ነበር ። ውሸት ሲደጋገም እውነት ይሆናል የሚለውን የአውሮፓውያን ለጊዜውም ቢሆን ሰርቶላቹህ ነበር ፤ ከአሁን በኃላ ግን ስትፈልጉ በሃይማኖት ፣ ስትፈልጉ በፖለቲካ ፣ስትፈልጉ በዘር ፣ ስትፈልጉ በድምበር ፣ እሳት እየለኮሳቹህ ወደ ሌላ ሰወስተኛ ወገን የማላከክ አባዜአቹህ ተነቅቶበታል ። ከአሁን በኃላ ሁልሽም ራስሽን መጠበቅና መከላከል እንጂ በስመ ኢትዮዽያ እሳት ላይ የሚማገድልህ የለም። ኢትዮዽያ እንደ በጀት ቀመሯ ብዙውን ተጠቃሚው ብዙውን መሰዋእትነት ከፍለህ ተከላከልላት። እኛ እየሞትን እናንተን የምናነግስበት ዘመን ላይመለስ ከሃይለስላሴ ና ከደርግ ጋር ቀብረነዋል ። እራሳችንን ለመከላከል ግን ፣ የሻብያም ሆነ የአረብ ድጋፍ አያስፈልገንም ። አለቀ ደቀቀ የትግሯይ ህዝብ በአንድ እጁ ዶማ ፣ በሌው ክላሽኑን ይዞ ፤ ወኪሎቹን ለመምረጥ ዝግጅት ላይ ስለሆንን ፤ ከቻላቹህ ወንድማዊ ሞሯላዊ ድጋፋቹህ አድርጉ ካልቻላቹህ እድላችሁን እየረገማቹህ እዛው በፀበላቹህ ። ሳንውድ በግድ ተገፍተን ለምንገባበት የትንኮሳ ተግባር ውዱ ተጋዳላይ ስየ አብርሃ እንዳለው ጦርነት የትም ሊጀመር ይችላል ማብቂያው ግን አይታወቅም ። ሌላው የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለችም የምትለዋን ተረትና ምሳሌ ብናጤናት መልካም ነው እላለሁኝ ። እንግዲህ ለዛሬ እዚህ ላይ ልግታና አስተያየት ሃሳብ ካላቹህ በኢሜሌ ታገኙኛላቹህ ። የኔ እምነት ከልደፈረሰ አይጠራም ብቻ ሳይሆን እንደ ማልካም ኤክስ እሳትን በእሳት ወይም ደግሞ እንደ አበሾች አባባል ሴትን በሴት ነው እምነቴ አመሰግናለሁኝ ።
|