Back to Front Page

6ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አስመልክቶ የህገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ያቀረበውን የህገ-መንግስት ትርጉም የውሳኔ ሐሳብ በተመለከተ የተዘጋጀ የህግ አስተያየት

 

 

 

6ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አስመልክቶ የህገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ያቀረበውን -ንግ ትርጉም የውሳኔ ሐሳብ በተመለከተ የተዘጋጀ የህግ አስተያየት

 

አረጋዊ ካብ ጀርመን

June 09, 2020

 


1.  መነሻ፤

 

6ኛው ጠቅላላ ምርጫ በተመለከተ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ማካሄድ እንደማይቻል ሪፖርቱን ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ማቅረቡ ይታወሳል፡፡ ም/ቤቱም የቦርዱን ሪፖርት በማፅደቅ ቀጣይ ሁኔታዎች ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ የህገ መንግስት ትርጉም ያስፈልጋል በማለት የህገመንግስቱ አንቀፅ 54/1/፣ አንቀፅ 58/3/ እና አንቀፅ 93 ላይ የህገመንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ትርጉም እንዲሰጥበት ጥያቄ ማቅረቡ የሚታወቅ ነው፡፡

 

በሌላ በኩል የፌደራሉ መንግስት አስፈፃሚ አካል ሰብሳቢና የሪፐብሊኩ ጠቅላይ ሚኒስትር 6ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ማካሄድ እንደማይቻል ታሳቢ በማድረግ እና በማመን አራት ህገመንግስታዊ አማራጮች አሉ በሚል ከአገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት አድርገው ከአማራጮቹ የህገ-መንግስት ትርጉም የመስጠት አማራጭ ተገቢ ነው የሚል አቋማቸውን አቅርበዋል፡፡ በማስከተልም የአገሪቱ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ዜጐችና ጉዳዩ ይመለከተኛል የሚሉ አካላት የ6ኛውን ጠቅላላ ምርጫ በተመለከተ የየራሳቸውን አቋም፣ አስተያየትና መግለጫ በተለያየ መልኩ እየገለፁ ይገኛሉ፡፡

 

ስለሆነም የህገመንግሥት አጣሪ ጉባዔ ባቀረበው የህገ መንግሥት ትርጉም የውሳኔ ሐሳብ እና ለትርጉም ጥያቄው መነሻ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ከዚህ የሚከተለው ሃሳብ ቀርቧል፡፡

 

2.  የተዘለለ መሰረታዊ ጉዳይ ስለመኖሩ፤

ከባለፈው ሁለት ዓመት ጀምሮ 6ኛው ጠቅላላ ምርጫ መካሄድ እንደሌለበት በተለያዩ አካላት ሲገለፅ የነበረ ሲሆን በቅርቡ የተከሰተውን ኮቪድ-19 ምክንያት በማድረግ ደግሞ ምርጫውን ማካሄድ አይቻልም በሚል መነሻነት አራት ህገ-መንግስታዊ አማራጮች አሉ ተብለው በፌደራል መንግስቱ ቀርበዋል፡፡ ሆኖም በእርግጥ እነዚህ አማራጮች አማራጭ ሆነው ሊቀርቡ የሚችሉ ናቸው? ከአራቱ ውጪ ሌሎች አማራጮች የሉም ? ከአራቱ አማራጮች የትኛው የበለጠ ተመራጭነት አለው? ለሚሉና ለሌችም ጥያቄዎች ምላሽ ከመሰጠቱ በፊት ምርጫና ዲሞክራሲ ለኢትዮጵያ ምን ማለት ነው? ምርጫ አለማድረግስ ይቻላል? ለሚሉ መሰረታዊ የምርጫ ጉዳዮች ተገቢው ትኩረትና ክብደት እንዳይሰጥ በማድረግ እንዲዘለል ተደርጐ ምርጫ ለማካሄድ ሳይሆን ምርጫ ላለማካሄድ ስለሚኖሩ ህገ-መንግስታዊና ህገ-መንግስታዊ መሰል አማራጮች ላይ ትኩረትና ቀልብ እንዲዞር ተደርጓል፡፡ አገራችን ኢትዮጵያ ከጥንት አፈጣጠሯ ጀምሮ አሁንም ጭምር የአንድ ወጥ ህዝብ አገር ሳትሆን የብዙ ህዝቦች፣ ብሔሮች፣ብሔረሰቦች፣ እምነቶች፣ ባህሎች አገር ናት፡፡ ይህን ብዝሃነቷን የማያከብሩና የማይቀበሉ የፖለቲካ ስርዓቶች አገሪቷን ለከፍተኛ ኪሳራና እልቂት ዳርገዋል፡፡ ስለዚሀም ኢትዮጵያ ህልውናዋና አንድነቷ ተጠብቆና ዳብሮ በዘላቂነት ሊኖር የሚችለው ብዝሃነትን የተቀበለ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ሲሰፍን እና የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ራስን በራስ ማስተዳደር ጨምሮ አጠቃላይ መብቶችን የሚያከብርና ዋስትና የሚሰጥ ህገ-መንግስታዊ ስርዓት ሲኖር እንደሆነ በማመን አሁን ያለው የአገራችን ህገ-መንግስት ከ15 ሚሊዮን በላይ የአገሪቷ ህዝቦች እንዲሳተፉ ተደርጐ ፀድቋል፡፡

Videos From Around The World

 

በመሆኑም ምርጫ ለአገራችን ኢትዮጵያ ልዩ ትርጉም ያለው ፖለቲካዊ ጉዳይ ነው፡፡ ምርጫ የዜጐች መብት ብቻ ሳይሆን የብ/ብ/ህ መብትና የአገሪቷ ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤትነት ብቸኛ ምንጭ ነው፡፡ ለዚህም ነው በሌላው ዓለም ብዙም ባልተለመደ መልኩ የአገራችንን ልዩ ሁኔታ መነሻ በማድረግ ብ/ብ/ህ/ የሚወከሉበት የፌደሬሽን ም/ቤት ተብሎ የሚጠራ ም/ቤት እንዲኖር የተደረገውና የህገ-መንግስት ትርጉምም ለዚህ ም/ቤት እንዲሰጥ የተደረገው፡፡

 

አገራችን ያገኘችው ሰላምና ዲሞክራሲ በአጋጣሚ ወይም በእድለኝነት የመጣ ሳይሆን የትግራይ ህዝብን ጨምሮ ሁሉም የአገሪቷ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች መስዋዕት በመክፈል ያስገኙት ስርዓት ነው፡፡ በህዝብ ምርጫና ፈቃድ ላይ ብቻ ተመስርቶ የሚቋቋም መንግስት እንዲኖር የሚያስችል ስርዓት ለማምጣት አገራችን ውድ ልጆቿ መስዋዕት ሆነዋል፡፡

 

ምርጫና አጠቃላይ ዲሞክራሲ የአገራችን አንድነትና ህልውና የሚወሰንበት ነው፡፡ ይህ ጉዳይ ደግሞ ሌላ ምትክ አማራጭ ወይም አቋራጭ መንገድ የለውም ፣ ሊኖረውም አይችልም፡፡ ስለዚህ 6ኛው ጠቅላላ ምርጫና አጠቃላይ የምርጫ ጉዳይ ከዚህ አገራዊ አንድነትና ዘላቂነት አንጻር መታየት የሚገባውና ለምርጫ የሚደረገው ዝግጅትም ይህንን በሚመጥን ደረጃ ሆኖ በመንግስት፣ በምርጫ ቦርድ፣ በፓርቲዎችና በሁሉም ዘንድ መመራትና መፈፀም ነበረበት፡፡ ምርጫ የአገሪቷ ህልውናና አንድነት መሰረታዊ ጉዳይ ነው በሚል መነሻነት የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ፣ የምርጫ ቁሳቁስና ግብዓት ማሟላት፣ ስልጠና እና ሌሎች ዝርዝር የዝግጅት ሂደትና ጉዳዮች ቢካሄዱ ኖሮ 6ኛውን ጠቅላላ ምርጫ በተሟላ ማካሄድ እንደሚቻል ጥረጥር የለውም፡፡

 

የፌደራል መንግስቱና ምርጫ ቦርድ በህገ-መንግስቱ በተሰጠው ክብደት ልክ ለምርጫው ተገቢውን ትኩረትና ዝግጅት አላደረጉም፡፡ የጊዜ ሰሌዳው ዘግይቶ ከመውጣቱም በላይ ከሚመጡ ያልተገመቱ ሁኔታዎችና አደጋዎች አንጻር ለማሻገር በማያስችል መልኩ ወደ ጫፍ በመውሰድ ነሃሴ ወር እንዲሆን መደረጉ በራሱ ለምርጫና ለዲሞክራሲ ሊሰጠው የሚገባውን ህገ-መንግስታዊ ስፍራ ካለመስጠት የመነጨ ለመሆኑ ማሳያ ነው፡፡

 

የኮቪድ-19 ወረርሽኝን የመከላከል እና የመቆጣጠር ስራን እና 6ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ማካሄድ ይቻላል፣ ይገባልም፡፡ አንደኛው ስራ ሌላውን ስራ ሊጐዳ ወይም ሊያስተጓጉል አይችልም፣ የሚችልበት እድል እንኳን ቢኖር ከህዝባችን ጋር በመሆን የምንቆጣጠርባቸው በርካታ አማራጮች አሉ፡፡ በዚህ ረገድ ህዝባችን በሉዓላዊነቱ ላይ የሚመጡ ማናቸውም ነገሮች እንደማያሸንፉት የሚያረጋግጥበት ዳግመኛ ታሪክ እንዳይሰራ ሆኗል፡፡

 

ምርጫ ማካሄድ እና ኮቪድ-19 መከላከልና መቆጣጠር ስራ በአንድ ላይ መከናወን አይችሉም ብሎ ማቅረብ የኢትዮጵያ ብ/ብ/ህ አቅምና አይበገሬነትን አሳንሶ ከመመልከት የሚመነጭ ነው፡፡ እንኳን እነዚህን ሁለት አገራዊ ጉዳዮች በድልና በአሸናፊነት መወጣት ቀርቶ ከዚህ የበለጡ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎችንም መሪና አስተባባሪ ካገኙ የአገራችን ብ/ብ/ህ በብቃት ድል መምታት የሚችሉ ናቸው፡፡ ሆኖም ምርጫን እና ኮቪድ-19 መከላከልና መቆጣጠር ተግባራት ማከናወን ይቻላል የሚል ሃሳብ የሚያነሱ አካላትን እንደ 21ኛው ክፍለ ዘመን የአገራችን አርበኛ አድርጐ ከመቁጠር ይልቅ በተቃራኒው ለህዝብ የማይጨነቁ፣ ያለአግባብ ስልጣን ፈላጊዎች እንደሆኑ ተደርጐ እየቀረበ ይገኛል፡፡ ምርጫ የዜጐችና የብ/ብ/ህ መብትና የስልጣን ባለቤትንት የሚረጋገጥበት ሆኖ ሳለ ነገር ግን ከዚህ ውጪ ምርጫ የፖርቲዎች መብትና ተግባር ብቻ አድርጐ የመቁጠር አዝማሚያም በስፋት ይታያል፡፡ ምርጫ የዜጐችና የአገሪቷ ብ/ብ/ህ መብት በመሆኑ ምርጫን የተመለከቱ ህገ-መንግስታዊ ጉዳዮችና አፈጻጸማቸውን ከመምራትና ከመተግበር ውጪ መንግስት፣ ፓርቲዎችና ሌሎች አካላት ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጥ፣ ማርዘም፣ ማሳጠር፣ ማሻሻል፣ መጨመር፣ መቀነስ ወዘተ ተግባራትን ማከናወን አይችሉም፡፡

3.  አራት አማራጮች ስለተባሉት

 

ምርጫን ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ከሚያስብሉት አንዱ መሰረታዊ ጉዳይ በየተወሰነ ወቅት (Periodical election) የሚካሄድ መሆኑና ከተወሰነው ጊዜ ውጪ የሚካሄድ ከሆነም ጊዜውን ለማሸጋገር የሚያስችል ረት ፡፡ - ናና ሶ እንደሆነ ስለሚያምን ምርጫን ሊካሄድ የማይችልበትን ምቹ ሁኔታና ምክንያት እንዳይኖር አድርጓል፡፡ ይህንን ማድረጉ ምርጫ ምን ያህል ከፍተኛ አገራዊ ጉዳይ እንደሆነ ለመገንዘብ ይቻላል፡፡ ነገር ግን በዚህ መልኩ ከመገንዘብ ከህ- ንደ - ፡፡

 

በሌላ በኩል ምርጫ በወቅቱ አለማካሄድ እንደችግር ተቆጥሮ መፍትሄ መሆን ያለበት ምርጫ በወቅቱ ማድረግ የሚቻልባቸውን አማራጮችና መንገዶች ከህዝብ ጋር በመሆን መፈለግና ተግባራዊ ማድረግ መሆን ሲገባው ረት -ት እንዲፈጠር ጥረት ማድረግ ነው፡፡ ስለሆነም አራት ተብለው የቀረቡት አማራጮች ምርጫን በወቅቱ ላለማካሄድ -ህገመንግስታዊ መስሎ እንዲቀርብ የሚደግፉ አማራጮች ናቸው፡፡

 

ንደ ንድ ፡፡ ነገ -ንደ -19 ሰው ሰራሽ አደጋዎችን በፍጥነት ጉዳት ሳያስከትሉ ወይም በአነስተኛ ጉዳት ለመከላከልና ለመቆጣጠር ነው፡፡ በዚህ ሂደት የሚታገዱት መብቶች የተከሰተውን አደጋ ለመቆጣጠር በሚያስፈልግ መጠን እና ደረጃ እንጂ እነዚህን መብቶች እንዲጐዱ ለማድረግ መሆን የለበትም፡፡ ምርጫንና ወረርሽኙን መከላከልና መቆጣጠር በተሳካ መልኩ ከህ- ንደ ንደ -ት የሌለው ነው፡፡

 

አገሪቷ ጠቅላይ ሚኒስትር የህዝብ ተወካዮች ም/ቤትን የሚበትንበትን የህገ-መንግስቱ አንቀፅ 60/1/ ዓላማ በግልፅ እንደሰፈረው ምርጫ ማካሄድ እንጂ ምርጫ አለማካሄድ አይደለም፡፡ እንዲያውም ንዑስ አንቀፁ በየአምስት ዓመቱ የሚካሄደው ምርጫ ከዚህ ጊዜ በታች ሊካሄድ የሚችልበትን አማራጭ የሚያስቀምጥ እንጂ ከአምስት ዓመት በላይ ያለምርጫ ለመቆየት የሚያስችል አማራጭን በፍፁምታሳቢ ያደረገ አይደለም፡፡

 

- ሻሻያ -ዜጐ//ራስ-ሻሻያ ፡፡ -ምት ና ነፃነቶችን መንካት የማይቻልና ተገቢ አለመሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ተግባራዊ እንኳን ቢሆን ሊመለስ የማይችል ጉዳት የሚያስከትል ታሪካዊ ስህተት ነው፡፡

4.   ጉዳዩ በህገመንግስት የመተርጐም ስልጣን ሊታይ የማይቻል ስለመሆኑ፤

 

የህገመንግስቱ አንቀፅ 83 ንዑስ አንቀፅ /1/ እና አንቀፅ 84 ንዑስ አንቀፅ /2/ የህገመንግስት ትርጉም ጥያቄ የሚመነጭበትን አግባብ በወሳኝነት አስቀምጠዋል፡፡ ስለዚህም የህገመንግስት ትርጉም ጥያቄ ሲቀርብ ሁለት መሰረታዊ ጉዳዮች ሊኖሩ ይገባል፡፡ የመጀመሪያው ቢያንስ ቢያንስ ሁለት ተከራካሪ ወገኖች መኖር ያለባቸው መሆኑን የሚገልፅ ነው፡፡

 

ሁለተኛው መሰረታዊ ጉዳይ ደግሞ ለህገመንግስቱ ጥያቄ መነሻ ሊሆን የሚገባ ውሳኔ መወሰን አለበት፣ አልያም የወጣ 798/2005 ፅ 3 ስለ ህገ መንግስት ትርጉም መሰረታዊ የሆነውን መርህ ደንግጓል፡፡ በንዑስ አንቀጽ 1 እንደገለፀው የህገመንግስት ትርጉም ጥያቄ ሊመነጭ የሚችለው የወጣ ህግ፣ ልማዳዊ አሰራር ወይም የመንግስት አካል ወይም ባለስልጣን -ቃረ፡፡ 6ተ የቀረበው የትርጉም ጥያቄ የወጣ ህግን መሰረት ያደረገ አይደለም፣ ልማዳዊ አሰራሮችን ተንተርሶ የቀረበም ም፣ ረበ ምን -ት ትርጉም ጥያቄ የቀረበበት ጉዳይ ሁሉ የህገመንግስት ትርጉም የሚሰጥበት ባይሆንም መጀመሪያ የቀረበው ጥያቄ የህገመንግስት ትርጉም ጥያቄ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለው ጭብጥ በቅድሚያ ተመርምሮ ምላሽ ማግኘት አለበት፡፡

 

ስለዚህም ለህገመንግስት ትርጉም ጥያቄ የሚያበቃ መነሻ ከሌለ የሚቀርብ ማንኛውም ጥያቄ ሊስተናገድ የሚችልበት ህገመንግስታዊና ህጋዊ መሰረት የለም፡፡ የአዋጅ ቁጥር 798/2005 አንቀፅ 3 ንዑስ አንቀፅ /2/ ድንጋጌ የንዑስ አንቀፅ /1/ መርህን ተከትሎ የሚዘርዝር ሲሆን በዚህ አግባብም ማንኛውም ህግ፣ ልማዳዊ ረናል //1/3// ፡፡ ነገ / ጣ እንደሆነ ወይም ልማዳዊ አሰራር ካለ ወይም በመንግስት አካል ወይም ባለስልጣን የተወሰነ ውሳኔ ካለ ነው፡፡ ከዚህ /6 ም ጥያቄ መሰረት ያደረገው የህገመንግስት ጥሰት ካለመኖሩም በተጨማሪ መነሻ የሆነ የፀደቀ ህግ፣ አሰራር ልማድ ወይም የተሰጠ ውሳኔ የለም፡፡ ስለዚህም ይህ በሌለበትና ባልተሟላበት የህገመንግስት ትርጉም ጥያቄ ሆኖ ሊቆጠር አይችልም፡፡ በዚህ አግባብ ጉባዔው በርካታ የህገመንግስት ትርጉም ጥያቄዎችን ውድቅ ያደረገበት ልምድ አለ፡፡ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የቀረበው የህገመንግስት ትርጉም ጥያቄ ማመልከቻ፣ ውሳኔ እና ሪፖርት እንደሚልፀው 6ኛውን ጠቅላላ ምርጫ በተቀመጠው ጊዜ ማካሄድ ባለመቻሉ ቀጣይ መፍትሔ ላይ የህገመንግስት ትርጉም ይሰጥበት የሚል ነው፡፡ ማመልከቻው የህገመንግስት ጥሰትን የማይመለከት ከመሆኑም በተጨማሪ ህገመንግስቱ ምርጫ በተያዘለት ጊዜ ማካሄድ ካልተቻለ ስለሚራዘምበት ሁኔታ አለመደንገጉ እንደ ክፍተት ገልፆታል፡፡ ጉዳዩ የህገመንግስት ክፍተት እንኳን ቢሆን የህገመንግስት ክፍተትን በህገመንግስት ትርጉም መሙላት በፍፁም የሚቻል አይደለም፡፡

 

የህገመንግስት ክፍተት የሚኖር ከሆነ በሌላ ግልፅ ስርዓት ምላሽ ማግኘት የሚችል እንጂ ህገመንግስት ትርጉም መሸከም ከሚችለው ተልዕኮ ውጪ ሌላ ከባድ ተልዕኮ መስጠት የሚቻልበት ህገመንግስታዊ መሰረት የለም፡፡ የህገመንግስት ትርጉም ጥያቄና ምላሹ በህገመንግስቱ ማዕቀፍ ውስጥ የሚኖሩ ናቸው፡፡ ለዚህም ነው የህገመንግስት ትርጉም ጥያቄ ሊቀርብ የሚችለው ህገመንግስታዊ ጥሰት ተፈፅሟል በሚል መነሻነት ሊሆን የሚገባው፡፡ ልክ እንደ ጥያቄው ሁሉ የትርጉም ምርመራና ውሳኔውም ከህገመንግስቱ ማዕቀፍ ሳይወጣ በህገመንግስቱ ላይ መወሰን ያለበት ነው፡፡ በመሆኑም የህገመንግስት ትርጉምን ያልተመለከተ ጥያቄን እንደ ህገመንግስታዊ ትርጉም ጥያቄ የሚቆጠር ከሆነ የሚሰጠው የትርጉም ምላሽም ህገመንግስቱን የተመለከተና በህገመንግስቱ ማዕቀፍ ውስጥ ሊሆን አይችልም፡፡

 

 

 

 

 

5.  - በሚመለከት፤

 

የህገ መንግስት ትርጉም የሚሰጠው የህገመንግስት ክርክርና ጥያቄን መነሻ በማድረግ እንደሆነ የህገ-መንግስት አንቀፅ 24/2/ እና የአዋጅ ቁጥር 798/2005 አንቀፅ 3/1/ ድንጋጌ በግልፅ ያስቀመጠ ከመሆኑም በላይ የጉባዔው የአሰራር ልምድም ይህንኑ ሙሉ በሙሉ የሚያንፀባርቅ ነው፡፡ በቀረበው ጉዳይ ላይ ብቻ መሰረት በማድረግ ብያኔ እና ውሳኔ መሰጠት መርህ የዳኝነትና የከፊል ዳኝነት አካላት ሁለንተናዊ የአሰራር መርህ ነው፡፡ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት በጉዳዩ ላይ ከተወያየ በኃላ ዝርዝር ምርመራ ተደርጐ የውሳኔ ሃሳብ እንዲመጣለት በልምድ እና በአሰራር እንደሚያደርገው ለቋሚ ኮሚቴው ማለትም ለህ/ፍ/ዲ/ጉ/ቋሚ ኮሚቴ እንዲመራ ወሰኗል፡፡ ቋሚ ኮሚቴው ምርመራ አድርጐ ለም/ቤቱ አምስት ገፅ ያሉት ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ ያቀረበ ሲሆን በውሳኔ ሃሳቡ ገፅ 4 እና 5 መሆን ስለሚገባው ሁኔታ የህገመንግስት ትርጉም ጥያቄ በሚል አቅርቧል፡፡ በዚህ መሰረትም ቋሚ ኮሚቴው የህገመንግስቱ አንቀፅ 54/1/ አንቀፅ 58/3/ እና አንቀፅ 93 ላይ የህገ-መንግስት ትርጉም እንዲሰጥባቸው ያቀረበው የውሳኔ ሃሳብ በም/ቤቱ አብላጫ ድምፅ ተቀባይነት አግኝቶ ለጉባዔው እንዲቀርብለት ተደርጓል፡፡

 

እነዚህ የህገ-መንግስት ትርጉም የተጠየቀባቸው አንቀፅ 54/1/ እና 58/3/ ድንጋጌዎች በግልፅ የሚመለከቱት ስለ ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ምርጫና የስራ ዘመን ነው፡፡ ነገር ግን ጉባዔው ከተሰጠው የትርጉም ጥያቄ በማለፍ ጠቃሚና አስፈላጊነት ያለው ተያያዥ ጉዳይ ነው የሚል የራሱን ብይን በመስጠት ስለ ክልል ም/ቤቶች እና ስለ ክልል መንግስታት አስፈጻሚ አካላት የስልጣን ዘመን መራዘምን የሚመለከት የህገ-መንግስት ትርጉም የውሳኔ ሃሳብ በገፅ 21 እና 22 አቅርቧል፡፡ ለዚህ ጉባዔው መነሻ ያደረገው የምርጫ ቦርድ ዝግጅት ለፌደራልም ለክልል ም/ቤቶችም ምርጫ መሆኑን፣ ወረርሽኙ አገራዊ ስርጭት ያለው መሆኑን እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ነው፡፡ ነገር ግን እነዚህ ሦስት መነሻዎች ለህገ-መንግስት ትርጉም ጥያቄው መነሻ እንጅ ራሳቸውን ችለው እንደ ህገ-መንግስት ትርጉም ጥያቄ አልቀረቡም፣ ሊቀርቡም የሚችሉ አይደሉም፡፡ ምክንያቱም የህገ-መንግስት ትርጉም ጥያቄ የወጣ ህግን ወይም ውሳኔን ተለይቶ ከሚታወቅ የህገ-መንግስት ድንጋጌ ጋር ይቃረናል በሚል የሚቀርብ ጥያቄ እንጂ የህገ-መንግስት ትርጉም ጥያቄ ባልቀረበበት እና ፈፅሞ በሌለበት ጉዳይ ላይ ብይን እና ውሳኔ ሊሰጥ አይችልም፡፡

 

በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት በፀደቀው የቋሚ ኮሚቴው የውሳኔ ሀሳብ የትርጉም ጥያቄ እንዲቀርብባቸው የተወሰኑት አንቀፅ 54/1/ እና 58/3/ የሚመለከቱት የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የስልጣን ዘመን አምስት ዓመት መሆኑን ነው፡፡ ነገር ግን የክልል ምክር ቤቶች የስልጣን ዘመን አምስት ዓመት መሆን አለመሆን የተደነገገው በፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ህገ-መንግስቱ ሳይሆን በየራሳቸው ህገመንግስት ነው፡፡ ይህ በየራሳቸው መንግስታት የተደነገገ እና በፌደራል መንግስቱ መከበር እንደሚገባው በኢፌዲሪ ህገ-መንግስት አንቀፅ 50/8/ የተደነገገው በጉባዔው ተገቢው ክብደትና ክብር ሳይሰጠው እንዲጣስ ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡

 

የክልሎች ከፍተኛ የስልጣን አካል የክልል ም/ቤቶች እንደሆኑ እና ተጠሪነታቸውና ለወከሏቸው የክልል ህዝቦች መሆኑ በህገ-መንግስቱ አንቀፅ 50/3/ ተደንግጓል፡፡ በተያያዘም ለክልሎች የኢፌዲሪ ህገ-መንግስት በአንቀፅ 52/2//ሀ/ ስልጣንና ተግባራቸውን በተመለከተ ካስቀመጣቸው ድንጋጌዎች አንዱ መሰረታዊ ጉዳይ፤ ክልሎች ራስን በራስ ማስተዳደር ዓላማ ያደረገ መስተዳደራዊ ስርዓት ማዋቀር እና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መገንባት ነው፡፡ በግልፅ ለፌደራልና ለክልል በጋራ ያልተሰጠ ወይም ለፌደራሉ መንግስት ተለይቶ በግልፅ ያልተሰጠ ስልጣን የክልሎች ስልጣን በመሆኑ ለክልሎች ስለ ራስን በራስ ማስተዳደር፣ ክልላዊ የውስጥ አወቃቀር እና የመሳሰሉትን ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር ጉዳዮች በየህገ-መንግስታቸውና የበታች ህጐቻቸው በመደንገግ ራሳቸውን በራሳቸው የሚያስተዳድሩበት ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር በተጣጣመ መልኩ በመዘርጋት ተጠቃሚ እየሆኑ ይገኛል፡፡

 

የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች የስልጣን ባለቤትነት በማዕከላዊ መንግስት በመወከልና በክልላቸው ራሳቸውንና በራሳቸው በማስተዳደር የሚገለፅ ትልቅ የአገሪቷ የድህረ 1983 ዲሞክራሲያዊ መፍትሄና እምርታ ነው፡፡ ሆኖም ይህን ዲሞክራሲያዊ የብሔር ብሔረሠቦችና ህዝቦች መብት አደጋ ላይ በሚጥል መልኩ እና በቀጣይ አገራዊ አንድነት ላይም መሰረታዊ ስጋት የሚፈጥር የህገ-መንግስት ትርጉም የውሳኔ ሃሳብ መቅረቡ ህገ-መንግስታዊ ካለመሆኑም በላይ ከባድ ታሪካዊ ስህተት ነው፡፡

 

 

6.  በቀጣይ ምርጫ የሚካሄደው በዓለም አቀፍና በአህጉር አቀፍ ድርጅቶች በሚወጡ መረጃዎች መሰረት የጤና ሚኒስቴር፣ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና የሳይንስ ማህበረሰብ አካላት ወረርሽኙ የህዝብ ጤና ስጋት አለመሆኑን አረጋግጠው እና / 9 12 ት ባለው -በሚመለከት፤

ጉባዔው በመጨረሻው የህገ-መንግስት ትርጉም የውሳኔ ሃሳቡ ላይ ስለ ቀጣይ ምርጫ መካሄድ በተመለከተ ህገ- መንግስቱን በሚጥስ፣ በብዙ ቅድመ ሁኔታ ላይ የተመሰረተ እና የብሔር ብሔረሠቦችና ህዝቦች ሉዓላዊነትን ለውጭ አካላት እና በሁኔታው ላይ ገለልተኛ ሊሆኑ ለማይችሉ ተቋማት ውሳኔ አሳልፎ የሚሰጥ ነው፡፡

ዓለም አቀፍ እና አህጉር አቀፍ የጤና ድርጅቶች የሚለው የጉባዔው አገላለፅ የትኞቹን ድርጅቶች እንደሚመለከት በግልፅ በስም ጠቅሶ አላመለከተም፣ በመሆኑም በጤና እና በተለያዩ በሽታዎች ላይ የሚሰሩ ዓለም አቀፍና አህጉራዊ የጤና ድርጅቶች በርካታ ሲሆኑ የዓለም ጤና ድርጅት ግን አንዱና የተባበሩት መንግስት ድርጅት አካል ነው፡፡ ስለዚህ እንደ ጉባዔው ውሳኔ ሃሳብ ከሆነ የጤና ሚኒስቴር፣ የህበረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ፣ የሳይንስ ማህበረሰብ አካላት እና የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ውሳኔ መወሰን የሚችሉት የእነዚህን የዓለም አቀፍና የአህጉር አቀፍ የጤና ድርጅቶች መረጃና አስተያየት መነሻ በማድረግ እንጂ በራሳቸው ተመስርተው መወሰን የሚችሉበት እድል የለም፡፡ በተመሳሳይም ሁለቱ የአገር ውስጥ የፌደራሉ መንግስት የጤና ዘርፍ ተቋማት እና በብዙ ቁጥር የተገለፁትና ማንን ያካትት አያካትት የማይታወቁ የሳይንስ ማህበረሰብ አካላት ማረጋገጫና ውሳኔ ያለ ልዩነት በአንድ አቋም ካልሰጡ በስተቀር የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት በራሱ ተነስቶ ውሳኔ ማሳለፍ የሚችልበት አካሄድ በጉባዔው የውሳኔ ሀሳብ መሰረት አልተሰጠውም፡፡

 

በቀጣይ የምርጫ መካሄድ የውሳኔ ሂደት ሙሉ በሙሉ የጉባዔው የውሳኔ ሃሳብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች፣ ክልሎች፣ ፓርቲዎች እና የሚመለከታቸው አካላት ምንም ዓይነት ሚና እንዳይኖራቸው አድርጓል፡፡ በአጠቃላይ የቀጣይ ምርጫን በተመለከተ ጉባዔው ያቀረበው የትርጉም የውሳኔ ሃሳብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች የስልጣን ባለቤትነትን የሚነጥቅ እና ፀረ-ዲሞክራሲያዊ አገዛዝ እንዲሰፍን በር የሚከፍት የውሳኔ ሃሳብ ነው፡፡

 

7.   የይዘት ተቃርኖ ነጥቦች፤

 

1.   ጉባኤው የምርጫውን መራዘም በሚመለከት የቀረበለት ጥያቄ የለም። ስለዚህ በፓራግራፍ 29 ምርጫ ማካሄጃ ጊዜ ሊራዘም ይገባል ሲል የደረሰበት መደምደሚያ ያልተገባ ነው። ምርጫ ቦርድና ፓርላማው በራሳቸው መንገድና ምክንያት ምርጫውን አራዝመዋል እንጂ ምርጫውን ማራዘም እንችላለን ወይ ብለው አልጠየቁም። ባልተጠየቀበት ነጥብ ላይ የህገ መንግስት ትርጉም ለመስጠት መጨነቁ ምን ያህል ከመንገዱ ወጥቶ አንዱን ወገን ለማስደስት እንደፈለገ አመላካች ነው።

2.   ጉባኤው በኮቪድ 19 ና በአስቸዃይ ጊዜ አዋጅ ምክንያት ቀጣይ ምርጫ ማካሄድ እንዳልተቻለ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተረጋግጣል ሲል በፓራግራፍ 28 ደምድሟል። ሆኖም ጉባኤው ይህ ስለመሆኑ በራሱ መንገድ ማረጋገጥ ይገባው ነበር። ኮቪድ 19 እንዴት ምርጫውን እንደሚያስተጓጉል አንዲት ነገር እንኳን አልገለፀም። ስለዚህ ለህገ መንግስት ትርጉም መሰረት የሆነው ፍሬ ነገር ስለመኖሩ የገለፀው የለም። ባልተረጋገጠ ፍሬ ነገር ደግሞ ህግ ተፈፃሚ አይሆንም።

3.   የቀረበው የውሳኔ ሀሳብ የህገ መንግስቱን ዓላማዎች፥ እምነቶች መርሆዎችና ግልፅ ድንጋጌዎች የሚጥስና ለፌደሬሽኑ መፍረስ ድንጋይ የሚያቀብል ነው።

4.   ጉባኤው የምክር ቤቱ የስራ ዘመን በአዲስ ምርጫ መካሄድ ሁኔታ ላይ የተመሰረት እንጂ ብቻውን የቆመ ድንጋጌ ባለመሆኑ የምክር ቤቱ የስራ ዘመን የምርጫ ጊዜውን ተከትሎ የሚሄድ ነው ሲል ገልፀል። ይህ ሁኔታ ጉባኤው ስለምርጫም ሆነ ስለምክር ቤቱ እንዲሁም ስለህገመንግስቱ በቂ ግንዛቤ እንደሌለው የሚያመለከት ነው። ምርጫ እስካልተከናወነ ድረስ የስራ ዘመን ቀጣይ ነው የሚል መደምደሚያ ከጉባኤው መስማት የሚያሳፍር ነው።

5.   ምርጫ በህገ መንግስቱ የሰፈሩትን መለኪያዎች ማሟላት እንዳለበት ግልፅ ነው። ሆኖም እንከን የለሽ ምርጫ ካልተከናወነ ምርጫ እንደተደረገ ይቆጠራል የሚል እንደምታ ያለው የጉባኤው መደምደምያ ግን በዓለም የመጀመሪያ መሆን አለበት። በአንድ አገር ያሉ ተጨባጭ ሁኔታዎች ምርጫ ላይ ተፅእኖ እንደሚያሳርፉ እሙን ነው። ኮቪድ 19ም ተፅእኖ እንደሚኖረው ይታመናል። ሆኖም ይህ ተፅእኖ ጭራሽ ምርጫውን ዋጋ እንዳይኖረው የሚያደርግ ነው የሚል እንደምታ ጉባኤው ከየት እንዳመጣው ግን ግልፅ አይደለም።

6.   ጉባኤው በፓራግራፍ 39 አስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ በምርጫ ሂደት እና አፈፃፀም ላይ ባደረሰው ተፅእኖ የዜጎች የመምረጥና የመመረጥ መብት ተግባራዊ እንዳይደረግ አድርጓል የሚለው አስተያየት ትክክል አይደለም።

7.   በፓራግራፍ 47 አስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅና ምርጫ በሚገጣጠሙበት ወቅት የመንግስት ስልጣን የስራ ዘመን ተፈፃሚ አይሆንም የሚለው የህገ መንግስት ትርጉም ሳይሆን የማሻሻያ ሀሳብ ነው። ሕገ መንግስቱ እንዲህ ዓይነት ትርጉም በጭራሽ አይሰጥም።

8.   አሁን ያለው መንግስት ሙሉ ስልጣኑን ይዞ እንዲቀጥል የሚለው የውሳኔ ሀሳቡ ይዘት (ፓራግራፍ 53) የህገ መንግስቱን አንቀፅ 60 በግልፅ የሚጥስ ነው። ህገ መንግስቱ የማያውቀው የስልጣን ችሮታ ነው።

9.   በቀረበው ሀሳብ የኮቪድን ሁኔታ በማስመልከት ውሳኔ የሚሰጠው ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ነው። ስለዚህ በውጤት አንፃር ቀጣዩን የምርጫ ጊዜ የሚወስነው ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ነው (ፓራግራፍ 63)። ስለዚህ ቀጣይ ምርጫ መች ይካሄድ የሚለውን የሚወስነው አሁን በችሮታ ስልጣን የተቸረው መንግስት ነው።

10. የክልሎች ጉዳይ በሚመለከት ለጉባኤው የቀረበ ጉዳይ የለም። ስለዚህ በዚህ ጉዳይ ላይ ጉባኤው ያለው ነገር ግምት ውስጥም ሊገባ አይገባም።

 

8.  ስነስርዓት ነክ ነጥቦች፤

1.   ጉባኤ በጉዳዩ ላይ ስልጣን አለኝ ያለው በቂ ባልሆነ ምክንያት ነው። ጉባኤው ጉዳዩን ስልጣን የለውም። ስልጣን በሌለው ጉዳይ አስተያየት መስጠትም አልነበረበትም። ስልጣን አለኝ የሚለው ድምዳሜ ላይ የደረሰው በእንግሊዘኛና በአማርኛው የህገ መንግስቱ አንቀፆች መካከል አለ ያለውን ምክንያት በመግለፅ ነው። በእንደዚህ ባለ ትልቅ ጉዳይ የእንደዚህ ዓይነት ቧልት የተሞላበት ኣካሄድ መምረጡ አሳዛኝ ነው። ይህ ነጥብ በሌሎች አገሮች ቢሆን ሰፋፊ ውሳኔዎች የሚሰጡበት ነው።

2.   ስልጣን ያለው መሆን አለመሆኑን ለመወሰን የባለሙያ አስተያየት ለመስማት አልፈለገም። ባለሞያ ጠራሁ ያለው በሌሎች ጉይዮች ነው። የስልጣን ጉዳይ ዋናው የስነስነስርዓት ጉዳይ ሆኖ ሳለ በጓዳ እንዲወሰን የተፈልገበት ምክንያት ግልፅ ኣይደለም።

3.   ባለጉዳዮችን የመረጠበት ሂደት የጉዳዩ ገለልተኛ አካሄድ የተፈታተነ ነው። ባለሙያ የተጠራው በአጭር ጊዜ ውስጥ ከመሆኑም በላይ አስተያየት ከላኩት ሰዎች እንዲቀርቡ የተደረጉት በምን መስፈርት እንደሆነ ግልፅ አይደለም። ሁሉም ሞያተኞች አንድ ዓይነት ሀሳብ የነበራቸው መሆኑ ሲታይ፥ የተለየ ሀሳብ የነበራቸው ሞያተኞች እንዳይቀርቡ መደረጉ ሲታይ ጉባኤ ጉዳዩን ገለልተኛ በሆነ ስርዓት እንዳልያዘው ያሳያል።

4.   አንዳንዶቹ አስተያየት የሰጡት ሞያተኞች ቀደም ሲል በመንግስት/ ምርጫ ቦርድ አማካሪነት የሰሩ ናቸው። ይህም የሞያ ግብአቱ ምን ያህል ውጤት ላይ ያተኮረ እንደሆነና ለመሰረታዊ የሞያ ተጠያቂነት ደንታ እንዳልነበራቸው አማላካች ነው።

5.   ከሁሉ የሚገርመው የጠበቆች ማህበር በአገር አቀፍም ሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና የተሰጠውን ስርዓት በመተላለፍ ወገንተኛ ምስክርነት እንዲሰጥ መደረጉ ነው። የዚህ ተቋም አስተያየት የሁሉም አባላቱን አስተያየት እንደማይወክል ይታወቃል። ይህ መሆኑ እየታወቀ የቀረቡት ኣባላት ሁሉንም የሚወክል ምስክርነት አቅርበዋል። ይህ ጭራሽ ግምት ውስጥ መግባት ያልነበረበት አስተያየት ነው። የጥብቅና ተቋሙም ለዚህ ድርጊቱ ተጠያቂ ሊሆን ይገባል።

6.   ያም ሆኖ ተሰማ የተባለው አስተያየት አንዱም ቢሆን በተሰጠው የውሳነው ሀሳብ አልተንፀባራቀም። ያ ሁሉ የንመግስትና የህዝብ ሀብት የወጣበት አስተያየት የጉባኤውን ውሳኔ በምን ዓይነት ሁኔት ተፅእኖ እንዳደረገ ማወቅ የሚቻልበት መንገድ የለም፡፡ ሰለዚህ ጉባኤው እንዲሁ ለሚድያ ፍጆታ ያክል ባለሙያተኞች ጠራሁ አለ እንድጂ የቀረበውን አስተያየት ለውሳኔው ግብኣት አላደረገውም። ስለዚህ ህገ መንግስቱ የተተረጎመው በአባላቱ የግል ፍላጎት ላይ ተመስርቶ እንጂ የሞያ ዕውቀት ላይ ተመስርቶ አይደለም።

9.    የጥሰቶቹ እንደምታ፤

 

1.  ስድስተኛው አገራዊና ክልላዊ ምርጫ ማካሄድ ይቻላል ወይስ አይቻልም የሚለው ጉዳይ የፖለቲካ ሃይሎች የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች የኢትዮጵያ ክልሎች ፌደሬሽኑና የሌሎች ህገ መንግስቱን ለመጠበቅ የተቁቁሙ አካላት ምርጫ ለማሰቀረት የሚያሰችል በቂ ምክንያት መኖሩን ሊወያዩበትና ሊስማሙበት ይገባ ነበር፡፡ ኮቪድ 19 ከሚያመጣው አደጋ ይልቅ ምርጫ በማሰቀረት የሚመጣ አደጋ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል፡፡ ይህ በውድ መስዋእትነት እውን የሆነው ህገ መንግስት የኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሄረሰብና ህዝቦች የሉአላዊ ስልጣን ባለቤት መሆናቸው፣ ያለ ህዝብ ፈቃድና ውክልና ማንም ሰው ስልጣን መያዝ እንደማይችል፣ ዜጐች በቀጥታና በወኪሎቻቸው አማካኝነት በሚያደርጉት ተሳትፎ ሉአላዊ ህግ የማውጣትና አገር የማስተዳደር ስልጣናቸው የመጠቀም መብት፣ ከአንድ ህዝብ ፈቃድና ስምምነት ውጪ ህዝብን ለማስተዳደርና ከፍተኛ የሆነ ውድመት እንዲደርስ የብሄር ብሄረሰብና የህዝቦች መብት ለመግፈፍና ለመንጠቅ ህገመንግስታዊ ከሆነ መንገድ ውጪ ስልጣን ለመያዝ (በስልጣን መቆየትን ጨምሮ) እየተሰራ ነው፤

2.  ምርጫን ማካሄዴ ግዳታ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ምርጫን አላካሂድም ማለት እንደ ስልጣንን በሃይልመያዣ የሚያስቆጥር ነው፡፡ ስልጣን ያለ አግባብ ለመያዝ ወይም በስልጣን ላይ ለመቆየት ማንኛዉም የህግ ማሻሻያወይም የህገመንግስት ትርጉም ወይም ማንኛዉም የህግ ለዉጥ ዲሞክራሲያዊ የመንግስት ስልጣን ሽግግር የሚጣረስ ተግባር ነው፡፡ በህገ መንግስቱ ምርጫ ብቸኛ የመንግስት ስልጣን መያዣ ሆኖ ሳለ፤ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚመረጠው ለአምስት አመታት ብቻመሆኑን እየታወቀ፤ የፌደሬሽን ምክር ቤትም እንዲሁ የአምስት ዓመት የስራ ዘመን እንደሆነ በግልፅ ሁኔታና በማያሻማ መልኩ እየታወቀ ይህ መርህ ገደል የሚከት ውሳኔ ቀርቧል ፡፡ በመሰረቱ የሕገ መንግስት ትርጉም በመስጠት ምርጫን ማስቀረትና ስልጣን ማራዘም የትርጉም ጉዳይ አይደለም፡፡ የሕገ መንግስት ትርጉም የሚያስፈልገው ለትርጉም የተጋለጠ ድንጋጌ ሲኖርና ለመረዳት የምከብድ ድንጋጌ ሲያጋጥም ነው፡፡ ሕገ መንግስቱ መሰረት በማድረግ በሁለትና ከዚያ በላይ በሆኑ አካላት የሕገ መንግስት ትርጉም ክርክር ሲነሳ ነው፡፡ አንቀፅ 54 1 በሚመለከት የህገ መንግስት ትርጉም እንድሰጥበት የቀረበው ጥያቄ በሚመለከት ድንጋጌው ምርጫ በየአምስት አመቱ እንድካሄድ የተቀመጠ ህገ መንግስታዊ ግዴታና የህዝቦች መብት እንጂ ምንም ለትርጉም የተጋለጠ ነገር የለውም፡፡ አምስት ዓመት የሚል ቁጥር በመተርጎም ሰበብ ከዚህ በላይ ማድረግ አዲስ የህገ መንግስት ድንጋጌ ማውጣት እንጂ ትርጉም መስጠት አይደለም፡፡ አዲስ ሕግ ማውጣትና የተፃፈውን መተርጎምና የተለያዩ ናቸው፡፡ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በትርጉም ሰበብ ህገ መንግስቱን የማሻሻል ስልጣን የለውም፡፡

3.  የፌደራላዊ ስርዓቱ ቱሩፋት የሆነው የራስና የጋራ-አስተዳደርን ያጣመረ፣ በቃል-ኪዳን የሚመሰረትና የሚመራ አጋርነት ፈርሷል፡፡ በፌደራል መንግስታና በክልሎች የነበረው አጋርነት፣ በመካከላቸው የነበረው ህገመንግስታዊ የስልጣን ክፍፍልና ዝምድና ተጥሷል፡፡ አንዱ የሌላውን ቅንነትና አብሮ የመኖር እሳቤን በማመን ላይ የተመሰረተ፤ አንዱ የሌላውን ልዩታሪክ፣ ባህል፣ ቋንቋ፣ ሃይማኖት በማክበርና በእኩልነት በመጠበቅ ላይ የተመሰረተ ስርዓት ተጨፍልቋል፡፡

4.  በህገ መንግስቱ በአንቀፅ 8 (3) እና 39 (3) የኢፌዲሪ ህገ መንግስት መሰረት ህዝቦች ህገ መንግስቱ ባስቀመጠዉ የመሳተፍ መብት ተጠቅመዉ ያሻቸዉን መንግስት የመምረጥ መብት አላቸው፡፡ ይህ መብት በህገ መንግስቱ በአንቀፅ 93 መሰረት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅም ቢሆን ያልተገደበ ነው፡፡ በህገመንግስቱ አንቀፅ 93 (4) (ሐ) በግልፅ እንደተቀመጠው ራስን በራስ የማስተዳደር መብት (አንቀፅ 39 (1 2)) እናየፌደራሉሞክራሲያዊ ሪፖብሊካዊ ስርዓት (አንቀፅ1) በአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታም ቢሆን የማይገደቡ እንደሆኑ ተምልክቷል፡፡ ዲሞክራሲ ያለ ህዝቦች ሉአላዊ ስልጣን፣ የህገ መንግስት የበላይነት፣ ራስን በራስ የማስተዳደር መብትና ምርጫ የማይታሰብ ሆኖ እያለ አንቀፅ 54 (1) እና 58 (3) አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጆ በትርጉም ምክንያት ለመገደብና የመንግስት ስልጣን ለማራዘም የህዝቦች መንግስታቸውን የመምረጥ፣ የመቀየርና የመተካት የማይነካ መብታቸው መገደብ ብቻ የሚጋፋ ሳይሆን የፌደራሉሞክራሲያዊ ሪፖብሊካዊ ስርዓት (አንቀፅ1) ባህሪና በአንቀፅ39 የተቀመጠው ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ጭምር የሚቃረን ነው፡፡

5.  በመሰረቱ ፌደራላዊ ስርአቱ የብሄር ብሄረሰቦችና ህዘቦች፣ የራስ ዕድል በራስ የመወሰን መብት የማይገደብ መሆንና በፌደራልና ክልል ሚዛናዊ ውክልና የማግኘት መብት (አነቀፅ39)፣ የፌደራል መንግስት በክልሎች የተዋቀረ መሆን (አንቀፅ 46) የብሄር ብሄረሰቦችና ህዘቦች በክልሎች የሚገኙ እንጂ የፌደራል መንግስቱ ፈቃድ የሚመሰረቱ አለመሆናቸው (አንቀፅ 46)፣ የፌደራል መንግሰት አባላት የሆኑት ክልሎች እኩል መብትና ስልጣን ያላቸው መሆኑ (አንቀፅ 47(4))፣ ክልሎች የራሳው የህግ አውጪ፣ ህግ አሰፈፃሚና ህግ ተርጓሚ ስልጣን ያላቸው፣ የክልል ከፍተኛ የስልጣን አካል የክልሉ ምክርቤት መሆኑና ተጠሪነቱም ለወከለው የክልሉ ህዝብ መሆኑ፣ በክልሉ ህዘብ ጉዳዮች ስልጣን ያለው የክልሉ ምክር ቤትመሆኑ፣ (አንቀፅ 50 (2፣3-8)) በህገ መንግስቱ ያልተወሰኑ ጉዳዮች በግልፅ ያልተሰጡ ስልጣናትን ጨምሮ የክልል ሰልጣን መሆናቸው፣ (አንቀፅ 52(1)፣ የፌደሬሽን ምክር ቤት አባላት የህገመንግሰቱ የበላይ ጠባቂና በክልል ምክር ቤቶች ወይም በቀጥታ በህዝቡ የሚመረጡ፣ የህዝቦች እኩልነትና በህዝቦች መፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ አንድነት ስር እንዲሰድና እንዲዳብር፣ ህገመንግሰታዊ ስርአቱ አደጋ ላይ እንዳይወድቅ (አንቀፅ 62 (1፣4))፣) ለፌደሬሽን ምክርቤት የተሰጠው ስልጣን ጭምር አደጋ ላይ ወድቋል፡፡

6.  የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀፅ 7 (1) በየአምስት አመቱ ምርጫ የማካሄድ ግዴታ አለበት፡፡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በህገ መንግስቱ አንቀፅ 55 መሰረት ምርጫ እንዲካሄድ ማመቻቸት ግዴታው ነው፡፡ በመሰረቱ ማናቸውም የመንግስት አካል ከህገ መንግስት ስርዓት ውጪ የራሱ ስልጣን በራሱ የማራዘም መብት የለውም፡፡

10.  ማጠቃለያ፤

 

የኢፌዲሪ ሕገ መንግስት በብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦቿ ብዝሃነት ላይ የተዋቀረችውና የቆመችው ሀገር፣ ብዝሃነት መለያዋ፣ የጥንካሬዋና የአንድነቷ ምንጭ እንዲሆን አስችሏል፡፡ እውነተኛ ህብረ-ብሄራዊ ፌደራል ሰርዓት ለመገንባት ከነ አፈፃፀም ችግሮችም ቢሆን መሰረት የጣለ፣ ፈጣንና ፍትሃዊ ልማት ለማስመዝገብ ያስቻለ፣ የአገራችንና ህዝባችን ሉአላዊነት ያስከበረ የኢትዮጵያ ትንሳኤ የመሰረት ማዕዝን ነው፡፡ እንደዛሬ በአሃዳዊነት ሳይፈተኑ የኢትዮጵያ ህዝቦች በሃገራቸው መፃኢ ዕድል ላይ ብሩህ ተስፋ ሰንቀው እንደ አንድ ማህበረሰብ እንዲነሳሱ የሚያደርጋቸውን ዓላማ በህገ መንግስታቸው አስቀምጧል፡፡ ዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ፣ ዋስትና ያለው ዴሞክራሲ ማስፈን፣ ፈጣን ኢኮኖሚያዊና ማሕበራዊ ዕድገት ማረጋገጥ የሚሉት ወርቃማ ምሰሶዎች ላይ የተመሰረተ አገር ግንባታ ማዕከል ያደረገ ነው፡፡

 

የፌደሬሽን ም/ቤት እንደ ብ/ብ/ህ ተወካይ ም/ቤትነቱ ምርጫን በተመለከተ ሊኖር የሚገባው የአገሪቱ ብ/ብ/ህ ራስ በራስ የማስተዳደር ስልጣን እና ዘላቂ አንድነታቸው የሚከበርበትን ህገመንግስታዊ አካሄድ ነው፡፡ ምርጫ የአገሪቷ ብ/ብ/ህ ባደረጉት ረጅም ትግል ያረጋገጡት የፖለቲካ መብት ሆኖ ሳለ እና የአገሪቷ አንድነትም የቆመበት አንዱ መሰረት ሆኖ እያለ ኮቪድ-19 ወረርሽኝን መከላከልና መቆጣጠር እንዲሁም 6ኛውን ጠቅላላ ምርጫ በተሳካ ህዝባዊ ርብርብ ማከናወን እየተቻለ እና እየተገባ አጋጣሚውን ህገመንግስቱን በተቃረነ መልኩ መጠቀም ትልቅ ታሪካዊ ስህተት ሆኖ የሚኖር ነው፡፡

 

ጉባዔው የህገመንግስት ትርጉም ይሰጥበት በማለት ያቀረበው የውሳኔ ሃሳብ በአንድ በኩል የህገመንግስት ትርጉም ጥያቄ ሆኖ ሊቀርብ በማይገባው ጉዳይ ላይ የተመሰረተና ጉባዔውም ሆነ ም/ቤቱ ከተሰጣቸው ስልጣን ውጪ የሆነ ጉዳይ ነው፡፡ በሌላ በኩል ትርጉሙ የብ/ብ/ህ የሉዓላዊ የስልጣን ባለቤትነትና ራስን በራስ ማስተዳደርን የሚቃረን እና ህገመንግስቱን የሚፃረር ነው፡፡

 

መንግስት ለሰላም፣ ለሰብዓዊ መብት መከበርና ለዲሞክራሲ መስፈን ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር እንዲያሳይ ምርጫ እንዲካሄድ ለጠየቀ ህዝብ የጦርነት ነጋሪት ተጎስሟል። መንግስት በሀይል እርምጃ የገደላቸው፣ ያስገደላቸውና ያሰራቸው ዜጎች በርካቶች ናቸው፡፡ ከህግ ውጭ እየወሰደ ያለውን የሀይል እርምጃና የመብት ጥሰት ህጋዊ ለማድረግ፤ ያስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ በማወጅና ኮማንድ ፖስት በማቋቋም በሕግ እውቅና የተሰጣቸውን እና የተረጋገጡትን የዜጎች ሰብአዊና ዴሞክራሲየዊ መብቶች አግዷል፡፡ በሽዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን በእስር ቤት አጉሮና፤ የሚፈልገውን ገድሎ ህዝቡን በፍርሀት ካሸማቀቀ በኋላ፤ ለይስሙላ በህገ መንግሰት ትርጉም ስም ፌዴሬሽኑን ለማፍረስ እየሰራ ይገኛል፡፡ የመላ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቃልኪዳን የሆነዉን ሕገ-መንግስት እንደ ፌደሬሽን ምክር ቤት አባልነት በአንቀፅ 13 (1) መሰረት ባለቸው ህገ መንግስቱ የማስፈፀም፣ የማክበርና የማስከበር ልዩ ግዴታና በአንቀፅ 9 (2) መሰረት ባላቸው ለህገመንግስቱ ተገዢ የመሆን ዜግነታዊ ግዴታ በኢህገመንግስታዊ ተግባራት ላለ መሰታፍ መወሰን ታሪካዊ ሃላፊነት የመወጣት ጉዳይ ነው፡፡

 

Back to Front Page