Back to Front Page

ይተዉት ቆሻሻውን

ይተዉት ቆሻሻውን

ይተዉት  ቆሻሻውን ...
ህይወት  የሌለው ... የማይናገረውን
መች  ሆነ ... ቆሻሻው
ነፍስ  የሌለው ... የማይናገረው
መች  ሆነ ... ጠላታችን
ቆሻሻው ... ህይወተ  አልባው
መች  አልን .. ጥረጉልን ...
ቆሻሻው  ነው ... ጠላታችን
መች  አልን ...
ቆሻሻው  አስቸገረን
አቅም  አጣን ... ድረሱልን
ጥርግ  ጥርግ ...
ኮስተር  ኮስተር ... ያድርጉልን

ቆሻሻ ... ህይወት  የሌለውን
አቅመ  አልባ ... አብሮ  አደግን
የሰፈራችን ... የማንፈራውን ...
የምናቀው ... የሚያቀንን....

መች  ሆነ ... ጠላታችን ...
የሚጠርጉት  ቆሻሻ ...
የማይላወስ ... ነፍስ  የሌለው
የማንፈራው ... የማይተኩሰው
... አልገደለም ... አላየንም
ነፍስ  ያለውን ... አያባርርም
የሰው  ፍጡርን ...
አይቀጥፍም ... አያቃጥልም
... እየለይም  ዘርን ...  አያዳላም

ይተዉት ...  ቆሻሻውን ....
ቆሻሻ  ከጠሉ ... ከተጸየፉ ...
ምናለ ...ቢጠርጉ...
የግራዎትን ... የቀኞትን
... በፊትና... በኋላዎ  ያሉትን
ከሀዲ ... አጨብጫቢዎችን
በመሀል ...የተሰገሰጉትን
ይጥረጉ ... ይልቅስ ...
የሚተነፍሰውን ...
ቆሻሻ  ህይወት ...  የተላበሰውን
ቆሻሻውን ...
አገር  የሚሽጥ ...  ቅጥረኛውን
ይተዉት ...
ቆሻሻ ... የማይተነፍሰውን
በየመንደሩ ... የተከማቸውን

ካልቻለ ... የርሶ  መጥረጊያ
የማይለየው ...
... ነፍስ ያላው ...  ከሌለውን
መጥረጊያዎ ... ይመርመር
ጠረጊውም ... ይጠርጠር
ይለወጥ ... ይቀየር

 

ኢዮብ ከ ጮማ እምኒ

03-07-20

 

Videos From Around The World

Back to Front Page