Back to Front Page

መከላከያ ሰራዊቱ የህዝቦች ተከላካይ ውይሰ አጥቂ ? ክፍል አንድ

መከላከያ ሰራዊቱ የህዝቦች ተከላካይ ውይሰ አጥቂ ?

ክፍል አንድ

 

በእውነቱ ትዝብት (/ጄነራል)

09-08-20

 

አሁን አሁን መከላከያ ሰራዊት የህዘቦች ስበአዊ መብቶች ከጥቃት መከላከል ይቅርና ራሱ በዕለት ተዕለት እያጋጠሙ ያሉት ግጭቶች በሁለት መልኩ ዋና የግጭቱ አካል ሆናል፡፡ መከላከያ በአንድ በኩል ዜጎች ሲገደሉና ከባድ ቀውስ ሲፈጠር አልታዘዝኩም ብሎ ቁሞ እየተመለከተ በሌላ መንገድ ደግሞ ክልሎችና በህግ የተደራጁት የአከባቢ መሰተዳደር በማፍረስ አመራሮች እያሰረና እያሰቃየ በሁሉም የአገሪቱ ክፍል በቀውስ ላይ ቀውስ እየፈጠረ ይገኛል በመሆኑም ሰራዊቱ ህገ መንግሰቱ በሚያዘው መሰረት የዜጎች መብት እያከበረ አይደለም ፡፡

ለመከላከያ ሰራዊት ህገ መንግሰቱንና ህገ መንግስታዊ ስርአቱን መጠበቅ ምን ማለት ነው ?

Videos From Around The World

የኢፊዲሪ መከላከያ ሰራዊት በተወካዮች /ቤት በአዋጅ የተቋቋ ነው፡፡ የተሰጠው ግዳጅ ህገ መንግሰቱን እና ህገ መንግስታዊ ስርአቱን መጠበቅ መሆኑ በተደጋጋሚ ይነገራል:: ቀጥሎም ከአዋጁ የሚመነጩ ግዳጁ ለመፈፀም የሚያግዙ የሰራዊት መተዳደርያ ደንብና በግጭት ጊዜ ተግባራዊ የሚሆን የግዳጅ አፈፃፀም አለው፡፡ በመሆኑም ከህግ አግባብ ውጪ ከማንም የሚሰጡት ትዕዛዞችና ተፅኖዎች ህጉን ተከትሎ መቃወምና ማሰቆም ህጋዊ መብት አለው ቢያንስ ቢያንስ ግልፅ የሆኑትን ህገ መንግታዊ ጥሰት መከላከል አለበት ፡፡

1.   /ብርሁኑ አደም የፈፀሙት የህገ መንግሰት ጥሰት(የፖለቲካ ቁማር)

በዚህ ሁለት አመት ተወካዮች /ቤት የማያውቀው አስቸካይ ጊዜ አዋጅ በሌ/ አብይ የተደራጀው ኮማንድ ፖሰት ምንም የህግ መሰረት ሳይኖረው መከላከያ ሰራዊቱ ከህግ አግባብ ውጪ የአከባቢ መስተዳድር ተክቶ በበላይነት እንዲያስተዳድርና በሜካናይዝድና ተዋጊ ሄሊካፕተር በመታገዘ የተሰማራ በርካታ እግረኛ ሰራዊት ሰብአዊ መብት ጥሰት በመፈፀመ ይገኛል፡፡ የሚገርመው ግን ኮማንድ ፖስት የተደራጀው / አብይ በሚዲያ በሚሰጠው የማስፈራርያ ትዕዛዝና ለጄ/አደምና / ብርሀኑ በቃል በሚሰጥ ትእዛዝ ብቻ ነው፡፡ የሰራዊቱ አመራርም ሆነ ሰራዊቱ በኮማንድ ፖስት አፈፃፀምና የህጋዊነቱ ምንም የተዘጋጀ ሰነድ/መመርያ ውይይትም የለውም ፡፡ መከላከያ ((/ብርሁኑና /አደም) በህግ አውጪ እውቅና ያልተሠጠው ኮማንድ ፖስት ( አስቸካይ ጊዜ አዋጅ) ሰራዊት በማሰማራት ህገ መንግሰቱን ከኮ/ አብይ አብረው እያፈረሱት ይገኛሉ ፡፡ ይህ ማለት አስፈፃሚው አካል // አብይ በህገ መንግሰቱ አንቀፅ 55(8) እና 93 የተጠቀሰው የህዝብ ተወካዮች /ቤት ስልጣን ለራሱ ጠቅልሎ ወስዶታል ስለዚህ የህግ/ህገመንግሰት የበላይነት ሳይሆን የሰዎች የበላያነት(rule of men) ነው እየተገበረ ያለው በመሆኑም ሰራዊቱ የሌ/ አብይ ፍላጎት ለማሳካት ህገወጥና -ህገ መንግሰታዊ ትዕዛዝ እየፈፀመ ይገኛል ፡፡

2.   ለሰራዊቱ - ህገ መንግስታዊ የሆነ ፖቲካዊ ውይይት ማወያየትት

በኮረና በሽታ ምክንያተ ያለ ገደብ ስልጣኑ ያራዘመበት መንገድ በህገ መንግሰቱ የተሰጡት የሶስቱ የመንግሰት አካላት በራሱ ስልጣን ጠቅልሎ በመያዝና በህገ መንገስቱ የተሰጣቸው ስልጣን ጣለቃ በመግባት ንጉስ ነኝ በግድ ተቀበሉኝ እያለ መከላከያ ሰራዊቱ በአገሪቱ ትርምስ እየፈጠረ ይገኛል፡፡ ውሳኔውም ወደ ሰራዊቱ በማወያየት ፌደሬሽን ያልተገደበ ጊዜ ስልጣን አራዝሞልኛል ስለዚህ ይህን ውሰኔ የሚቃወም ማንኛውም አካል በኃይል መጨፍለቅ አለባችህ ብሎ ለሰራዊቱ ትዕዛዝ ሰጥታል ፡፡

ሆኖም /ኮሎኔል አብይ አዲስ ያልተጠበቅ አለማዊ ክስt ሲፈጠርና 5 አመት ስልጣን ጊዜ ሲያልቅ የኢፈዲሪ ህገ መንግሰት በሚፈቅደው መሰረት ከፖለቲካ ፓርቲዎች ዲሞክራሲዊና አሳታፊ በሆነ ሁኔታ ከመፍታት ይልቅ መከላከያ ሰራዊቱን ተማምኖ አሻፈረኝ ብሎ ቀጥላል ፡፡ አሁን ደግሞ የትግራይ ምርጫ ፌደሬሽን /ቤት ህገ ወጥ ብሎልኛል ስለሆነም ቶሎ ተዘጋጁ ወደ ጠርነት ብሎ ሰራዊት ያወያያል ፡፡ ሰራዊቱ እዚህ ማወቅ ያለበት ጉዳይ / አብይ ህገ መንግሰቱ በግላጭ እየጣሰ ሰራዊቱ በህገ መንገሰስት ጠባቂነት ሰበብ -ህገመንግስታዊ ትዕዛዞች በማዘዝ ለፖቲካ አለማው እየተጠቀመበት መሆኑ በጥልቅ መገንዘብ አለበት፡፡ ከዚህ በፊትም ሰራዊቱ የማይመለከተው ጉዳይ የውህድ ፓርቲ አካሄድ ህጋዊ ነው ብሎ ያወያየው /ብርሀኑ ጁላ ማወያየቱ በሰራዊት ከፍተኛ ውሞ አድርጋል፡፡

 

3.   በግጭት ጊዜ የሚተገብረወ የኢፈዲሪ መከላከያ ሰራዊት የግዳጅ አፈፃፀም ደንብ መሻር

2009/2010 . ከነውጥ/ለውጥ በፊት የነበረው አስቸካይ ጊዜ አዋጅ ሰራዊቱ በግጭት ጊዜ ዝርዝር የግዳጅ አፈፃፀም በኃይል አጠቃቀም ሊወሰድ የሚገባው ከፍተኛ ጥንቃቄ፤ የአመራር ክትትልና ተጠያቂነት በተመለከተ አዋጁንና ሌሎች ህጎች መሰረት ያደረገ ሰነድ ተዘጋጅቶ እሰከ ታች ተወያይታል፡፡ በዚህ መልኩ ተጠያቂ የሆኑ ሰራዊት አመራርና አባለት በመኖሩ ከነበረው ሁኔታ አንፀር በህብረተሰብ የደረሰው ጉዳት በእጅጉ መቀነስ ተችሎ ነበር ፡፡

በዚህ ሁለት አመት ያለው ህገ ውጥ ኮማንድ ፖስት ግን ለኢፊዲሪ መከላከያ ሰራዊት ግዳጅ እንዴት እንደሚፈፅም ትእዛዙ የተሰጠው በሚደያ በደርግ ወታደር በብ/ ካሰየ ጨመዳ በሚከተለው መልኩ ነው፡፡ በየመንደሩ ዱላ ይዞ ውር ውር የሚል /የሚንቀሳቀስ ሰው ቁም ብለው እምቢ ካለ በጥይት በለው ይህ ደርጋዊ ትዕዛዝ አጋጣሚ ሳይሆን የተናገረው ላለፉት ሁለት አመታት ጀምሮ በሌ/ አብይ ትዕዛዝ የደርግ ሙርኮኛው ጄነራል ለመከላከያ ልዩ ልዩ ክፍሎችና አየር ኃይል አመራሮች ማንኛውም አመፅ በኃይል ማጥፋት/መቆጣጠር በሚል ርዕስ ስልጠና ልምድ ሰጥታል ( አሁንም እየሠጠ ነው )፡፡ ለጠ/ኢታማዦር ሹምና ምክትሉ ደግሞ በሌ/ አብይ የተመደበ መደበኛ የደርጋዊ ፍልሰፍና አማካሪ ነው፡፡ በተጨማሪም በመከላከያ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ቀርቦ የደርግ አምባገነናዊ አካሄድ/ልምድ በሰራዊቱ ለማስረፅ እንዲችል በሌ/ አብይ ትእዛዝ እድል ተስጥቶታል ስለሆነም የሙርኮኛው ድርጊት የተቀነባበረና የተቀናጀ ነው

4.   ኢትዮጵያ ያፀደቀችው አለም አቀፍ የጦርነት/ግጭት ህግ በሚደያ ተሸራል

የሙርኩኛው ካሳየ ጨመዳ ተኩሰህ ግደል የሚል በሚድያ የሰጠው ትዕዛዝ ኢትዮጵያ ያፀደቀችው አለም አቀፍ የጦርነት/ግጭትና የኢፊዲሪ ግዳጅ አፈፃፀም ደንብ በተግባር ሸራል፡፡ በመሆኑም በኢፈዲሪ የወንጀል ህግ ሙርከኛው ወታደር፤ ሚዲያውና የመከላከያ አመራሮች ተጠያቂ ናቸው ምክንያቱም ሰልፍ የወጣ ሲቪል ማህበረሰብ ቁም በለው እንቢ ካለ ተኩሰህ ግደለው በማለት ለመከላከያ ሰራዊቱ በመንግሰት ሚዲያ በመቀስቀስ በኦሮሚያና በወላይታ የተነሱ ተቃውሞዎች ሰራዊቱ እጅግ ተመጣጣኝ ያልሆነ የተቀናጀና ማዊ የሆነ የጅምላ ጭፍጨፋ ፈፅማል ፡፡ የአንድ አገር ሰራዊት ልክ ከጣለት ኃይል ጋር እንደሚዋጋ በሲቨል ህዝብ ላይ እንዲህ አይነት ጭፍጨፋ ሲፈፅም ፀሃፊዎች የቀውሶች ሁሉ ቀውስ ( master of crisis) በማለት ይገልፁታል፡፡ የአለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴም ድርጊቱ ማውገዝ አለበት፡፡

5.   ህገ መንግሰቱ በመፃረር ሶስቱ የመንግሰት አካለት በሌ/ አብይ ስር መውደቃቸው

ከህግ አንፃር ሰራዊቱ ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን ይጠብቃል ማለት ለግለሰብ/ቡደን ሳይሆን በህገ መንገስቱ መሰረት የተደራጁት ህግ አው ፍትህና አስፈፃሚ አካላት በተሰጣቸው ስልጣን ልክ እኩል ተገዢ መሆን ነው፡፡ በዚህ መሰረትም መከለካያ እንደ በህገ መንግሰት በተሰጣቻው ስልጣን ልአላዊ የሆኑት ፈደራልና ክልል መንግሰታት ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ አለመግባት ወይም ስልጣናቸው አለመጋፋት ማለት ነው፡፡ ይህ መሰረታዊ የህገ መንግሰት መርህ ያስፈለገበት ምክንያት ሶስቱ የመንግሰት አካላት የእርስ በርስ ቁጥጥር እንዲኖር ነው ( በህገ መንግሰቱ አንቀፅ 50 የስልጣን አካላት አወቃቀር )፡፡ በአገር ደረጃ ሶስቱ የመንግሰት አካላት ተጨፍልቀው በሌ/ አብይ ስር ሆናል ይህም ያልተገደበ ጊዜ ስልጣን ከማራዘም ጀምሮ ከም/ቤት ውጪ በራሱ ጊዜ ካቢኔ ማደራጀት ወዘተ ያጠቃልላል፡፡ ከመከላከያ አንፃር ጥሰቱ እንደሚከተለው ቀርባል፡፡

6.   በህዝብ ተወካዮች /ቤት ያልተሾመ ሰው መከላከያ / መሾም

በቅርቡ ደግሞ በህገ መንግሰቱ አንቀፅ 55(13) መሰረት በህዝብ ተወካዮች /ቤት ያልተሾመ ሰው / አብይ መከላከያ / ብሎ መድባል ስራም ጀምራል፡፡ ይህ ማለት እየተመራ ያለው በግለሰብ ይሁንታ እንጂ በህዝብ ይሁንታ አይደለም ማለት ነው፡፡ ለመከላከያ እንደ ሶስቱም የመንግሰት አካለት ( ህግ አውጪ፤ ፍትህ አካልና አስፈፃሚ) በህገ መንግሰቱ የተሰጣቸው ስልጣን ማከበርና ማስከበር ግዴታው ቢሆንም ሁለቱ ኢታማዦር ሹሞቹ ህጋዊ ያልሆነ ሰው በቀይ ምንጣፍ ተቀብለውታል ፡፡ ህገ መንግሰት ካሰቀመጠው ውጪ ሁሉም ስልጣን በአንድ ግለሰብ /ንጉስ ስር ሲወድቅ መከላከያ ማሰቆም ነበረበት ምክንያቱም ድርጊት -ህገመንግሰታዊ በመሆኑ አለበለዝያ የህገ መንግሰት ጠበቂ ነኝ እያለ መከላከያ ራሱን ከህገ ወጥ ውሳኔና ትዕዛዝ መከላከል ያልቻለ በየጊዜው ቃለ ማህላ ማድርግ ትርጉም የለውም ፡፡ የሚገርመው ግን ህገ መንግሰቱን ጠብቀው በህዝብ ተወካዮች /ቤት ፊት ቃለ ማህላ ፈፅመው የተሾሙት ኦቦ ለማ መገርሳ ስራቸው በአግባቡ እንዳይፈፅሙ ተደርገው ነበር፡፡

7.   ሁሉም አይነት ተቃውሞ ከፍተኛ ኃይል በማደራጀት በኃይል መጨፍለቅ ዲሞክራሲያዊ ምህዳሩን ማጥፋት ( ደርጋውያን ምከር)

በመሰረቱ ይህ አስተሳሰብና ድርጊት ህገ መንግሰቱን የሚፃረረ ነው፡፡ የሰራዊቱ ፍላጎትም/እንደ / ህዘብ ዲሞክራሲያዊ ምህዳሩ እንዲሰፋ ከማንም ሳይወግን ህገ መንግሰቱና ከህዝቡ በመቆም የህግ የበላይነት የሰፈነባት ዲሞክራሲያዊት አገር ማየት ነው፡፡ አሁን ግን መከላከያ እየሰራ ያለው ዲሞክራሲያዊ ምህዳሩ ማጥበብና አምባገነንነት መሳርያ መሆን ነው፡፡ የዚህ ማሳያም ከላይ ከተገለፁት በተጨማሪም የሚከተሉት ማየት በቂ ነው ፡፡

በዚህ ዓመት 2012 በጥቅምት/ህዳር ወር በአንድ ጊዜ አንድ ክፍለ ጦር ኮማንዶ አስልጥናል፡፡ ይህ አዲስ ቅልብ ጦር ነው እንግዲህ ኦሮሞ ህዝብና የወላይታ ህዝብ የፈጀው የኤርትራ ነብሰ ጉዳይ ኮማንዶ እንደተጠበቀ ሆኖ ፡፡ የሚገርመው ግን በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት እንካን በአንድ ጊዜ ይህን ያህል ቁጥር አልሰልጠነም ፡፡ አሁን ህዝባዊ አመፅ/ተቃውሞ/ጥያቄ ለማፈን ከመከላከያ አደረጃጀት ውጪ በልዩ ሁኔታ በሌ/ኮሌኖሉ የሚታዘዝ ሪፐብሊካን ጋርድ ቅልብና ነብሰ ገዳይ ቡዳን አደራጅቶ ፀረ ህዝብ ተግባር ፐእየፈፀመ ይገኛል ፡፡

አሁንደግሞ እስከ ጥር/የካቲት 2013 . ድረስ በሁለት ዙር 80ሺህ ተጨማሪ ሰራዊት በማሰልጠን ልክ እንደ / መንግሰቱ በሰራዊት ብዛት በህዝቡ የሚነሱ ማንኛውም የመብት ጥያቄ፤ የህዝብ ተቃውሞ፤ጥያቄና አመፅ ልክ እንደ ሲዳማ፤ ወላይታ አወዳይ፤ አሩሲ፤ ወለጋ ፤ጉጂና ኮሽ ያለበት አከባቢዎች ሁሉ ጭፍጨፋ ለመፈፀም ከፍተኛ ዝግጅት እየተደረገ ነው ፡፡ በተጨማሪም ሁኔታወ አይቶ ትግራይ ጦርነት መክፈት ነው፡፡ (ሰራዊቱ ምልመላም ከተወሰነ አከባቢዎች ብቻ በማተኮር ሌላ አደገኛ አላማ ጭምር ያለው ነው ፡፡

በተጨማሪም / አብይ ግንቦት/ሰኔ ወር 2012 ጄነራሎች ቤተ መንግሰት ሰብሰቦ ማንኛውም ትዕዛዝ ትፈፅማላቹህ ማለቱ ይታወሳል ፡፡ አሁን በቅርቡ ደግሞ በሚሰጥር ጥቂት ክፍተኛ ጄነራሎች ብቻ ሰብሰቦ የብልፅግና ህልም የሚሳካው በሰራዊቱ ጥንካሬ ብቻ ነው ፡፡ የብልፅግና ራዒና የመደመር ፍልሰፍና በካድሬውና በህዘቡ ላይ ከፍተኛ ውሞ እየደረሰበት በመሆኑ መከላከያ ሰራዊቱና የክልል ልዩ ሀይሎች የመደመር ፍልሰፍና/ብልፅግና የሚቃወም አከባቢ/ህዘብ ልክ እንደ ወላይታ ተቃውሞ በአጭር ጊዜ መጨፍለቅ 2013 . ዋና ዕቅድ እንዲሆን ትዕዛዝ ስጥታል ፡፡

/ አብይ የክልል ልዩ ኃይል በየክልሉ ፖለቲካ የተጠለፈ /የተሰለበ በመሆኑ በእጅጉ የምንተማመንበት ኃይል መከለከያ ኃይል ሲሆን በተለየ ደግሞ ሪፐፕሊካን ጋርድ(አብይ ጋርድ) ነው በማለት ለታመኝ ከፍተኛ ጄነራሎች አስገንዘባል ፡፡ ለመሆኑ የመከላከያ ሰራዊትስ በክልል/ በአገሪቱ ፖለቲካ ተፅኖ ስር አይወድቁም ያለው ማን ነው ? የመከላከያ ሰራዊት ብሄር የለውም በማለትም ማምታትስ ምን ያህል ይዛልቃል ? ብሄር የለውም የሚሉት አነጋገር ምን ማለት መሆኑ ማየቱ ጠቃሚ ነው ፡፡ ሰራዊቱ ለብሄሩ ለኃይማኖቱ ለአከባቢውና ለማንም ሳይወግን ለኢትዮጵያ ህዘቦች በእኩል መቆም ማለት ነው እንጂ ሰራዊት ብሄር የለወም በሚል ሽፋን ብሄር ብሄር ብሄረሰብ ጭፍጭፍ ማለት አይደለም ፡፡ በተጨማሪም መታወቅ ያለበት ሰራዊቱ ማንነት የለውም ማለት አይደለም የቤተሰቡ የአከባቢዊና የአገሩ ዜጎች ሞትና ሶቆቃ የማይሰማው በድን ማለትም አይደለም ፡፡

8.   ሰራዊቱ ዕለት ተዕለት እንቅስቃሴው ከህዝብ እንዲጋጭ ማድረግ

የሰራዊት የህገ መንግሰት ጠባቂ ነው ማለት ትርጉሙ ከኢፈዲሪ ህገ መንግሰት ውጪ የሚከናወኑ ህገ ወጥ ተግባራት ማሰቆም ህገ ወጥ ትዕዛዝ አለመቀበል፤ በዜጎች ሰብአዊ መብት ጥሰት አለመሳተፍና ለጊዛዊ ፖለቲካ ጥቅም የአንድ ፓርቲ መሳርያ አለመሆን ማለት ነው ፡፡

በፖለቲካ መፍተሄ ወይም በስጥቶ መቀበል ድርደር በቀላሉ መፈታት የሚገባው ሁሉ ሰራዊቱ ከህዝብ እያጋጩ ቁብልነቱ/legitimacy/ እያሳጡት ይገኛሉ፡፡ በዚህ ሁኔታም ሰራዊቱ የአገር መከታ መሆኑ ቀርቶ መፈረካከሱ/ደካማ መሆኑ አይቅርም፡፡ ከንግስ /ስላሴ ጀምሮ የተገነባወ ጦር ሰራዊት የፈረሰው ሁለት ጊዜ አስከ አፍንጫው ታጥቆ (19 54.ምና 1969ዓም) ወደ / የመጣው የሶማለያ ወራሪ ጦር አሸንፎት አይደለም ፡፡ የቀድሞ ስራዊቱ የፈረሰው ንጉሱና ደርግ በወቅቱ በአገር ቤት የነበሩት ፖለቲካዊ ችግሮች/ልይነቶች በወታደራዊ ኃይል ለመፍታት ሙከራ በማድረጋቸው ነው አሁንም / አብይ አገሪቱ የገነባችው ሰራዊት ክህዘቡ ጋር በየቦታው እያላተመ ሁሉም ፖለቲካዊ ችግሮች በሰራዊት በመጨፍለቅ በስልጣን ለመቆየት አምበገነናዊ ጉዞ ጀምራል ፡፡

 

በመሆኑም ስራዊቱ ለህገ መንግሰቱ ብቻ ተገዢ ከሆነ / አብይ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ይደራደራል፤ ያጎራቸው ፖለቲካ እሱሮኞች ይፈታል፤ ሰራዊት ተጠቅሞ የሚፈፅመው ጭፍጨፋ ያቆማል/ይቀንሳል፤ ሳይወድ ህገ መንገስት ማክበር ይጀምራል ይህ መሆን ካልቻለ ኢትዮጵያ ትፈርሳለች ሳይሆን እንደ አሮጌ ሸክላ ትፈራካከሳለች በመሆኑም እያንዳንዱ ወታደር በየደረጃው አገር ከማፈረስ ሊታደግ ይገባል ምክንያቱም ወደ እብሪት፤ አምባገነንነትና ግትርነት እየተቀየረ ያለው ቡዱን ሰራዊቱ ተጠቅሞ ነው፡፡ ሁሉም ልይነት በጉልበት ለመፍታት እየተጠቀመበት ያለው ዜዴና ውጤቱ ማየት በቂ ነው፡፡

እዚህ መታወቅ ያለበት / አብይ ሰራዊቱ የፖለቲካ መሳርያ በተጠቀመበት ቁጥር የሰራዊቱ ግዳጅ ህገ መንግሰታዊ ሳይሆን ፖቲካዊ ይሆናል ይህ ደግሞ በአገሪቱ ፖለቲካ /በክልል ፖለቲካ/ ብሄሩ/ብሄረሰቡ ፖለቲካ አስተሳሰብ ይገዛል ፡፡ በታሪክ የሚታወቀው በውሰጥ ግጭት የተጠመደ ሰራዊት በአገሩ ላይ ተስፋ ይቆርጣል ይከዳል፤ በቁርጠኝነት ለመስዋእትነት ዝግጁ አይሆንም በመጨረሻ ሰራዊቱ በሰፈር ሚሊሻ/ታጣቂ በቀላሉ የሚሸነፍ ኃይል ይሆናል የአገሪቱ እጣ ፈንታም ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት አያዳግትም

ማጠቀለያ

አሁን ታድያ መከላከያ -ህገመንግሰታዊ በሆነ መልኩ ሚነስተር ሲመደብለት ህገ ወጥ ኮማንድ ፖሰት ሲደራጅለት፤ ከህግ አግባብ ወጪ ሰራዊቱ ለሲቪሉ ማህበረሰብ ተኩሰህ ግደል ተብሎ በሚዲያ ሲሰበክ፤ ክልሎችና አከባቢ የህዝብ /ቤቶች በሰራዊት ጣልቃ ገብነት ሲፈርሱ / አብይ ማንኛውም(ህገ ወጥና ህጋዊ መንገድ ) የተሰጠህ ትዕዛዝ ትፈፅማለህ ብሎ በሚድያ ሽብር ሲለቅ፤ ምርጫ ይደረግ/እናድርግ ያሉና መንግሰት ሁሉን አቀፍ ምክክር እንዲያደርግ የጠየቁ ፓርቲዎች ማሰርና ሆን ብሎ ኮሮና እንዲያዙ ማድረግ በመጨረሻም እብደቱ ለይቶለት ጦር በማዝመት እጨፈጭፋሎህ ያለ ፀረ ህዘብ ኃይል የኢፈዲሪ መከላከያ ሰራዊት በህገ መንግሰት አምላክ ማለት ያቃተው ለምንድ ነው ? ስለሆነም የመከላከያ ከፍተኛ ጄነራሎች ህዝብን ለመጨፍጨፍና ህገ መንገስቱን ለማፍረስ ተደምራል ስለሆነም ሰራዊቱ ከህዝብና ጎን በመቆም ከህገ መንግሰትና ፈደራል ስርአቱ ጋር መደመር አለብት፡፡ ፡፡

መከላከያ ነክ ጉዳይ በሌላ ፅሁፍ እስክንገናኝ ቸር ሰንብቱ

 

Back to Front Page