Back to Front Page

"ማንም ወፈፌ እየተነሳ ህወሓት ላይ የሆነ ነገር ባለቁጥር መልስ ልስጥ ካልክ ስራ የምትሰራበት ጊዜም ኣይኖርም።"

             

 

"ማንም ወፈፌ እየተነሳ ህወሓት ላይ የሆነ ነገር ባለቁጥር መልስ ልስጥ ካልክ ስራ የምትሰራበት ጊዜም ኣይኖርም።"


አቶ ጌታቸው ረዳ  04-09-20

 

ማንም ወፈፊ እየተነሳ ህወሓት ላይ የሆነ ነገር ባለቁጥር መልስ ልስጥ ካልክ ስራ የምትሰራበት ጊዜ ኣይኖርም። ለዛ ነው መልስ ያልሰጠነው ።dw-tv-getachew-reda-2020.jpg

አሁን ትንንሽ ፓለቲካ የምትጫወትበት አይደለም ፣ አለም እንደ አለም ያለው ጊዜ፣ ሃብት፣ አስተባብሮ ሊመክተው የሚገባ አለምን እያስጨነቀ ያለ ችግር አለ፣ ይሄ ችግር የኢትዮጵያ የትግራይም ችግር ነው ።

የኮሮናቫይረስ ከመከላከል አንፃር ትግራይ ክልል በሚቻል አደጋ ላይ እንዳይወድቅ መስራት አለብን ብለን እየተንቀሳቀስን ነው ። ያለንን አቅም አስተባብረን ልንመክተው የሚገባ ትልቅ ወረርሽኝ ባለበት ሰዓት ለነዚህ ጉዳዮች መልስ ለመስጠት መሞከር ይህንን ሀላፊነት ዘንግቶ በእንደዚህ አይነት የወፈፊ ስራ ላይ የተጠመደ ወገን ሀላፊነት የጎደለው አካሄድ ነው የሚሆነው ከዛ አንፃር መልስ ለመስጠት አስፈላጊ ሆኑ አላገኘኑውም ።

 

ብልፅግና የተባለ ስብስብ በየወቅቱ የሚያሰበሰባቸው ወፈፊዎች አሉ እነሱ የሚሰጥዋቸው መግለጫዎች ተከትለህ ልንጎድ ካልክ መጥፋት ነው የሚሆነው ግን ደግሞ ዝም ማለት የተሳሳተ ግንዛቤ በኣንዳንድ ወገኖች ሊፈጥር ሰለሚችል ፣ በተወሰነ መልኩ ምላሽ መስጠት ጥሩ ነው ።

 

ኢትዮጵያ ውስጥ ትልቅ እና ትንሽ የሚባል ህዝብ የለም። እኔ የነበርኩበት ኢህኣዴግ የሚያምነው ኢትዮጵያ ውስጥ ትልቅ እና ትንሽ የሚባል ህዝብ የለም ። ለእኩልነት ነው የታገለው ። ኢህአዴግ የታገላለቸው አላማዎች ዋነኛ ትኩረት የሚያደርጉት የህዝቦች እኩልነት ላይ ነው ። ቁጥራቸው 5 መቶ ሊሆን ይችላል፣ 5 መቶ ሺህ ሊሆን ይችላል 50 ሚሊየን ሊሆን ይችላል ። ስለ ህዝቦች እኩልነት የምናወራ ከሆነ የመጀመርያ ጉዳዮቻችን ህዝቦች መብቶቻቸው ተከብሮ ፣ ፍላጎቶቻቸው እንዲማላ ለማድረግ የሚያስችል የፓለቲካ ስርዓት ተገንብቷል ወይ አልተገነበም የሚለው ነገር ነው የሚሆነው ።

 

ሰውየው ያሉቱን ሰምቼሎህ ቅድም ካልኳቸው ወፈፊዎች አንዱ ናቸው ብየ ነው የማምነው ። ርእስ የመፍጠር ፍላጎት አለ በዚህ ብልፅግና በሚባለው ስብስብ ውስጥ አገር ከማስተዳደር ይልቅ ለጫጫታ የሚሆኑ ርእሶች በየደቂቃው እየሰጡ የህዝብን ትኩረት ወደ የማይረቡ ጉዳዮች የማስቀየስ የተደራጀ እንቅስቃሴ እንዳለ ምንም የሚያጠራጥር ነገር የለውም ። ስለዚህ የዛ አስፈፃሚ ሰው ናቸው ማለት ነው ።

ኣንድ አገር ውስጥ ትልቅ ህዝብ ትንሽ ህዝብ ብሎ ለነፈረጅ መሞከር ሀላፊነት የጎደለው አስተሳሰብ የመጨረሻው መገለጫ ነው ።

 

ኦሮምያ ውስጥ ከ20 የማያንሱ ፓለቲካ ፓርቲዎች አሉ ፤ ኦነግ ፣ ኦፌኮ ያላቸው ተቀባይነት ያክል ቢያንስ በወፍ በረር በማውቀው ደረጃ ብልፅግና ያለው ኣይመስለኝም ።


ሰውየው የሚናገሩለት ብልፅግና የኦሮሞ ህዝብ በቁጥሩ እወክላሎህ የሚልበት መብት ከየት እንዳመጣው እግዛብሄር ብቻ ነው የሚያውቀው ፣ፓርላማ ላይ በህዝብ ቁጥርህ ነው የምትወከለው ፓርቲዎች ግን ሀሳባት ነው ይዘው የሚመጡት አክሲዮን ማህበራት አይደሉም ፣ የአክሲዮን ማህበር ነው ባዋጣሀው ልክ ልምረጥ የምትለው ።

 

Videos From Around The World

ፓርቲዎች ሀሳብ ይዘው ነው የሚመጡት የሚወክሉት ህዝብ የለም ፣የኦሮሞ ህዝብን የማይወክሎ ሰዎች የኦሮሞ ፓርቲ ነን ስላሉ ብቻ በዛ ቁጥር ኦሮሞን እወክላሎህ ብለው ሊሞጉቱ ኣይችሉም ። ኦሮሞን እወክላሎህ የሚል ፓርቲ ኦሮምያ ውስጥ ድምፅ ቢያጣ የሀገራዊ ስብስቡ አካል ቢሆን ድምፁ እኩል ነው የሚሆነው ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር ፣ይህንን ነው ኢህአዴግ ይከተለው የነበረው አሰራር ።

 

አክስዮን ማህበራት አልነበሩም ግን በአጋጣሚ እነ አወሉ ያሉበት አስተሳሰብ ፓርቲዎች እንደ አክስዮን ማህበር የሚቆጠር አስተሳሰብ ነው በበዙ መልኩ ፣ ከምታገኘው ጥቅም አንፃር ነው የሚሰበከው ፣ከምትነዳው መኪና አንፃር ነው የሚሰበከው ፣ ከሚቆረጥልህ አበል ጋር ነው የሚያያዘው ፣ ድርሻችን የሚባል ነገር ሲመጣ የመብላት ሎጂክ ላይ የተመሰረተ ነገር አለው ።

 

የፓለቲካ ፓርቲ ሀሳብ ማፍለቅያና ሀገርን ለማስተዳደር የተሻለ ሀሳብ የምታቀርብበት መድረክ ሳይሆን የተሰበሰበን ሃብት እንደ ግሪሳ የምትከፋፈልበት መድረክ አድርጎ መቆጠር አደገኛ አዝማሚያ ስለነበር ነው ፣ያ አዝማሚያ ነው ብልፅግና ይዞ እየተንቀሳቀሰ ያለው ፣ በየመድረኩ ይህንን ቋንቋ ነው ሲደግሙ የምትሰማው ።

 

ለድርሻችን ለቁጥራችን የሚባለው ነገር ስለ ኦሮሞ ህዝብ አይደለም እየተወራ ያለው ፣የኦሮሞን ህዝብ እወክላሎህ የሚልህ ሰውየ አሁን ባለበት ስልጣን ከመምጣቱ በፊት የኦሮሞ ህዝብ ሲቀጠቀጥ ሲበላ ፣ በራሱ ልጆች ሲበዘበዝ ከበይዎቹ ውስጥ የነበረ ሰው ነው ። መሬት ሲዘረፍ መሬት ዘራፊ የነበረ ሰው ነው።

 

አቶ አወሉ እወክለዋሎህ የሚሉት አቶ አብይ እመራዋሎህ የሚሉት ብልፅግና የሲዳማ ህዝብ ቁጥሩ ምንመ ይሁን ምን 98/99 በመቶ ድምፅ ሰጥቶ ራሴን በራሴ እንደ ክልል አስተዳድራሎህ ብሎ የወሰነው ወሳኔ ተግባራዊ ከማድረግ ይልቅ ፣ ትግራይ ኣራት ዩኒቨርስቲ ኣለው ሲዳማ ግን ለቁጥሩ የሚበቃ ዩኒቨርስቲ የለውም ወደ የሚል ክርክር ነው እየገቡ ያሉት ።

 

የመዝረፍ አስተሳሰብ ውስጥ ስትገባ ሁልጊዜ እንደ አክስዮን ማህበርን ነው ፓርቲም መብግስትም የምታስበው።

 

ብልፅግና ህወሓት ላይ እየየ የሚለው ሀገር ማስተዳደር ስለማይችል፣ ራእይም የለውም ፣ፍላጎትም የለውም ። መንግስት ፀሎት ማደራጀት አይደለም ስራው ።

 

የአስፋልት ጥያቄ የምታነሳው ፣እነ አወሉ መሬት ዘረፋ ላይ በተሰማሩበት ወቅት ፣እነ አቶ አወሉ የኦሮሞን ወጣት ስራ እጥ አድርገው ኪሳቸው ለሞምላት በሚንደፋደፉበት ወቅት ፣ትግራይ ውስጥ በፌደራል ቀመር በተሰሩ የልማት እንቅስቃሴዎች የተሻለ ስራ መስራት ሰለተቻለ የተሻለ አስፋልት ሊኖር ይችላል ።

አምስት ወጣቶች ከዩኒቨርስቲ ወጥተው የትግራይ ህዝብ ከጭቆና ማላቀቅ አለብን ብለው ሲወጡ የትግራይ ህዝብ ቁጥር ግምት ውስጥ አስገብተው ኣልነበረም። ለሀሳባቸው ትልቅነት የሰጡትን ዋጋ ያ የሀሳብ ትልቅነት ህዝብን ከሳመነ ሊፈጥረው የሚችለው ታኣምር አምነው ብቻ መንቀሳቀሳቸው የፈጠረው ለውጥ ነው። መጨረሻ ላይ አሁን እየዞሩ ብልፅግና የሚባለው ፓርቲ መሪዎች እየዞሩ የሚመርቅዋቸው ፕሮጀክቶች ለመስራት ያስቻሉን ለውጥ ያመጣን የነዛ 7 ስምንት ግለ ሰዎች ህልም የማየት ድፍረት ።

አሁን ትግራይ ችግርዋ መንግስት መንግስት የሚሸት ነገር ያለባት አከባቢ ሆና መቅረትዋ እንደ ጥፋት እየተቆጠረ ያለው ።

 

Back to Front Page