Back to Front Page

አንድ ለበረከት (ጎንደሬዉ በረክት አገሩን ይወዳል? መጠርጠሩስ!)

አንድ ለበረከት (ጎንደሬዉ በረክት አገሩን ይወዳል? መጠርጠሩስ!)

 

ሰሎሞን አዲስ የካቲት 2012 ዓም

 

ይህን መጣጥፍ ለመጫር ያነሳሳኝ፡ ተፈሪ መኮንን የተባሉ ጠሃፊ፡ በረከት አገሩን ይወዳል በሚል ርዕስ የተየቡት ጽሁፍ ነዉ። ይህን ጽሁፍ በመጻፋቸዉ አድናቆቴን በጣም እቸራቸዋለሁ። ለምን ቢሉ? ያንድ ሰዉ የቁርጥ ቀን ወዳጅነት፡ ያ ሰዉ የወደቀ ግንድ ምሳር ይበዛበታል እንደሚባለዉ፡ ቀብራራዉ ጎንደሪ፣ በረከት ስሞዖን፣ መንበረ ስልጣኑ ላይ በነበረት፣ እጁ በጨበጠ እግሩ በረገጠ፣ ይሰጥ በነበረብት ዘመን የተጻፈ ሳይሆን፡ በእስር፣ ወህኒ በወረደበትና ወዳጆቹና አሽቃባጮቹ፣ በሸሹበት ወቅት፡ ለፍትህና ለዕዉነት የቆሙ ሰዎች፡ አድርባይነት፣ ተረኝነት፣ ጎጠኝነት፣ ከደመቀዉ ዘፋኝነት፣ አልያም ያላዋቂ ሳሚነት በገነነበት ዘመን፡ የተጻፈ በመሆኑ ነዉ። የህ ጽሁፍ፡ ባጭሩ፡ በህወህት፟_ ኢህ አዲግ ዘመን ያልተጻፈ በመሆኑ ነዉ። በረከት የሃቀኛ ኢትይጵያዉያንን፣ የህሊና ፍርድ በሚሽበት ወቅት የተጣፈ በመሆኙ ነዉ። እኔም፟፡ የተሰማኝን እንደሚከተለዉ ልሞነጫጭር፡ ከይቅርታ ጋር።

Videos From Around The World

የበረከት ስሪት ማርክሲዚም ሌኒኒዝም ነዉ። ለዚህም ማስረጃዉ፡ ለብሄሮች እኩልነት ሲል ከወንድሙ ገዳዮች፣ ከውያነ ጋር፡ ለታክቲክም የሁን ለስትራቴጂ ሲል፡ ከህወሃት ጋር ግ ንባር ፈጥሮ፡ ለኢትዮጵያ ምንዱባን የተሻለ ቀን ለማምጣት ማሰቡና መሞከሩ ነዉ። ያ ባይሆንማ ኖሮ፡ ተወልዶ ካደገበት ጎንደር ይልቅ፡ ያብትና የናቱን አገር፣ የትዉልድ መንድር መርጦ፣ ኤርትሪያዊ ሆኖ፡ ብዙዎቹ ኤርትራዉያን ወንድሞቻችንና ጎረቤቶቻችን እንዳደረጉትና፡ እንደሆኑት ኤርትራዊ ሆኖ፣ ጀብሃን ወይንም ሻቢያን መጎዳኘት ይችል ነበር። በረከት ስምዖን። ነገር ግ ን፡ የኢትዮጵያ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄን (ኢፒዲም)ን በመመስረት፡ ከህወሃት ጋር ግ ንባር ፈጥሮ፣ በኋላም ስሙን ወደ አማራ ብሄራዊ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (አብዲን) ስሙን በመቀየር፡ እራሱን ዝቅ እድርጎ፡ ከህወሃት፡ እኩል እድርጎ፡ ትግሉን ቀጠለ። እያሌ ኢትዮጵያዉያን፡ የበረክትን፣ ያዲሱ ለገሰንና ተፈራ ዋልዋን ወዘተ ድርጅት እንደ አድርባይና የህወሃት ተላላኪ ያዩታል። በትወሰነ ደረጃ ይህ አባባል ትክክል ቢሆንም፡ የበረከትን ማርክሳዊና ለኒናዊ አመለካከት ከቦታዉ ዝቅ እያደርገዉም። ለምን ቢሉ ይህ አቋም፟ የኢፒዲምን (የአባቱን) ከዛም አልፎ ተርፎ የአያቱን የኢህ አ ፓቲን፡ በኢትዮጵያ የብሄር ጥያቂን በተመለከተ የነበረዉን አቅዏም (ከዋለልኝን ህልምና ምኞት) የተለየ እልነበረምና። ይህ የትግል አቅጣጫና ህልም ልክ ነበር አልነበረም የሚለዉ ጥያቄ እንደጠጠበቀ ሆኖ።

እናም ወዲ ስምዖን፣ ወንድሙ ከሞተለትና፣ እያሌ የኢህአፓ ጉዋዶች ከተሰዉበት፣ ይብሄር እኩልነት ትግል፡ አቁዋም ዝንፍ አይልም፣ እላለም፣ ብሎም አያዉቅም። በበረክት አይን፣ የህወሃት ትግል፡ የብሄር ጥያቄ ነዉ። ነገር ግን ይህ የህወሃትመንገድ፡ የመገንጠልን ጥያቄ ያዘለ ከመሆን አልፎ ተርፎ፡ የግዛት ተስፋፊነትና፣ ሂሳብ የማወራርድ የመሰለ አጀንዳ ያዘለ በሚመስል መልኩ፡ አማራዉን በጠላትነት ከመፈርጅ እልፎ፡ ዛሪ፣ ዛሪ እንደተገለጸ፡ አማራዉን በጠላትነት ከመፈረጅ እልፎ፡ ፍጹም ለማዳከም፣ እልፎ ተርፎም ለማጥፋት የታቀደ በሚመስል መልኩ የተከናወነ በመሆኑ፡ በረክትንና የትግል ጉዋዶቹን፣ እንወክልሃለን በሚሉት ህዝብ ዘንድ፣ ቅቡልነትንና ተአማኒነትን፡ እንዲያጡ እድርጉዋቸዋል።ይህ ኝ የነበረክትና፡ ከዚያም እልፎ ተርፎ፡ የኢህ አፓን፡ በብሄር_ ብሂረሰቦች ላይ ያላቸዉን አቁዋም ሲህተት እአይደርገዉም። እሁንም፣ ዲሞክራሲ በተትረፈረፈት፣ በዶክተር አቢይ የስልጣን ዘመን፣ ባንጻራዊ አገላለጽ (relatively speaking) ትልቁና እንገብጋቢዉ ጥያቄ፡ የብሄርና ብሄረሰቦች የእኩልነት ጥያቄ ሆኖ መዝለቁ (መቀጠሉ) ነዉ። ስለዚህ ወንድሜ በረከት፡ ለህወሃት ስሱ ልብ ቢኖረዉ፡ የአቋሙን ጥንካሪና፡ ለትግራይ ህዝብ መስዋእትናት ያለዉን እድናቆትና አክብሮት፡ ከማሳየት ዉጭ ሌላ ነገር የሌዉ መሆኑን ነዉ።

በመጨሻም፡ በረክት አማራ ህዝብ፡ የተጋረጠበትን አደጋ፡ የስልጣን ዘመኑ ማብቂያ አካባቢ የትናገረዉን፣ ይቅርታ የተነበየዉን ሃቅ፡ በመናገር ጽሁፊን ልድምድም። በረክት ወደ እስር ቤት፡ ከመወርወሩ በፊት ስላማራዉ የሚከተለዉን ተናግሮ ነበር፡ አማራዉን ከምዕራብ በሱዳን፣ ከደቡብ ከኦሮሞ፣ ከሰሜን ከትግራ፣ ከምዕራብ ከአፋር ጋር አጣልተዉ ሊያስጨፈጭፉት (ሊያጣሉት) ነዉ ብለዉ ነበር። ይህ ማስጠንቀቂያ በሙዋቹ ጀኔራል እሳምነዉ ጽጌም በተደጋጋሚ ተነግሮ ነበር። እናም፡ አቶ በረከት ስማዖን፟፣ ትናንትም፡ ዛሬም፣ ነገም፣ ወድፊትም፣ የኢትዮጵያን ኡዳይ፡ ባጠቃላይ፣ ያማራ ህዝብ የተጋረጥበትን እደጋ፡ በትለይ፡ ነቅሶ የሚያዉቅ፡ ማርክሲስት ነበር። ማርክሲዝም እንዳሮጌ ቁና ተወርዉሮ በተጣለበት ዘመን። ሃጢያቱም ይህ ነዉ። በሌብነትማ፣ ሀገርን በመዝረፍማ፣ ከሱ የበለጠ የዘረፉ፡ ነገር ግ ን፡ ዛሬም ተንደላቀዉ የሚኖሩ፡ እያሌዎች፟፡ በነጻነት የሚኖሩ እሉ፟። ዘብጥያ ከመወርወር ያዳናቸዉ፣ ያተረፋቸዉ፣ ከዘመነኛዉ ጋር መጓዛቸዉ፣ በዶክተር እብይ ፍልስፍና፣ መደመራቸዉ ነዉ። የበረክት ሃጢያት፣ ጎንደሬዉ እንድሚለዉ አለዉ አለዉና በማተቡ ጠና በመሆኑ ነዉ። እናም መደመር፡ ባቃማቸዉ፣ የተሳሳቱ ቢሆንም፣ በይቅርታ ሂሳብ የሚደመሩትንም ማካተት ያለበት ይምስለኛል። ቸር ይግጠመን።

 

Back to Front Page