የአንድ ደቂቃ
አባዜ
ለአንድ ደቂቃ
...
እንተቃቀፍ ... ሰላም
እንዲሰፍን
አገር እንድትለማ
.... አጥብቀን እንለምን
ሀጢአት እየሰራን
... እንጠይቅ ይቅርታን
ገነት እንድንገባ
... እጃችንን ታጥበን
በደም ተጨማልቀን
... በተንኮል ተሞልተን
እንድንበለጽግ
... ሌላውን አድኸይተን
የአባይ ግድብ
ጉዳይን ... ሸፈንፈን አድርገን
ልክ እንዳምናችን
...
የውሸት አቧራ
... ቡን አድርገን በትነን
ፍጹም ሳንሰራ
... ሰላም በሌለበት
...
የሰላም ሚንስቴር
... ለይስሙላ ሾመን
ስንፎክር ውለን
... ስንሰብክ አድረን
በወሬ አባዜ ...
በውሸት ተጠምደን
ጥያቄው ሲበዛ
... ዝምታው ሲሰበር
የለመድነው ጭብጨባ
... ሲከዳን ሲሸሸን
አዳራሹ ባዶ ...
ሲያስከትል ትዝብትን
ፍቅሩ ጩኸቱ ...
የውሀ ሽታ ሲሆን
... ልክ እንደልማዳቸን
...
ለአንድ ደቂቃ
ብ ለን ...
ባለንበት ቆመን
...
እስቲ እንፈቃቀር
... እጅ ለእጅ ተያይዘን
ትህትናን እንላበስ
... እንልመድ ይቅርታን
እንበልጽግ እንደመር
... ሌላውን አክስመን
በወሬ ማጥገቡ
ነው ... አሁን የሚያዋጣን
ብለው መከሩ ...
ካቢኔት ሰብስበው
ለአንድ ደቂቃ
የሚል ... መፈክር አንግበው
ይሄንን ነው ...
የሚሉን
የብልጽግና መሪ
... ከአሁኑ እንውቀው
ወሬና ተንኮል...
ውሸትና ትረካ
ጉራና ልመናው
... ያልጎረበጣቸው ...
የጭፍን ደጋፊ
... በጥቅም ተገዝተው
ሲያመልኩ ሲያወድሱ
... ሁለት አመት ሞላው
የታደልነው ደግሞ
...
በምክንያት የምንነቅፈው
...
በምክንያት የምንደግፈው
ትግርኛ ተናጋሪ
... ፍንፍኔ ያለነው
በቂም በጥላቻ
... ከስራ የተባረርነው
ጡረተኛ ሆነን
... ያለ ጡረታ የቀረነው
መንጋነትን ተጸይፈን
... ብልጽግናን ያወገዝነው
አንገታችንን
ሳንደፋ ... ቀና ብለን የምንሄደው
ምርጫና ፓርቲያችን
... ሁሌም ህወሓት ነው !!!
ቅጥል እርር ይበል
... እኛን የሚጠላን
ምርጫችን ...
ያ ... በአላማ የሰመረው
...
ብልጽግና ፓርቲን
... ሳያቅፍ የተፋው
ለፌደራሊዝም
... በህይወት የከፈለው
ስማቸውን ሲቀየሩ
... በስሙ የጸናው
ሲከሱ ሲወነጅሉት
... ፍርክርክ ያላለው
ተንኮል ሲሸርቡ
... ሁልግዜ የሚያከሽፈው
አገርን ሲያወድሙ
... ክልሉን የሚያለማው
ከህዝቡ ሊለዩት
ሲሉ ...
... በህዝቡ የታቀፈው
...
ሰላምና እድገትን
... በማስመዝገብ ላይ ያለው
የካቲት በአሉን
...
በከበሮ ፣ በጭራ፣
በክራር በእምቢልታ ...ማክበር
ላይ የሚገኘው
ከብልጽግና መሪ
... ለየት የሚያደርገው
ከህዝቡ ተወልዶ
... ለህዝቡ የሞተው
ምርኮኛ ማርኮ
... ቀልቦ የሚለቀው
በጦርነት አውድማ
... በድል የሚቀዳጀው
በ አላማ ጽናቱ
... ሁሌም የሚታወቀው
የጀግኖቹ ጥርቅም
...ህወሓት የኛ ነው !!!
ክብርና ሞገስ
ውድ ህየወታቸውን ለገበሩ
ሰማአታት !!!
ኢዮብ ከጮማ እምኒ
02-19-20