Back to Front Page

የፌደራሊስት ሐይሎችና የሀገር አድን ጥሪና መስከረም 25

የፌደራሊስት ሐይሎችና የሀገር አድን ጥሪና መስከረም 25

 

አልማዝ በዳኔ

ፊንፊኔ

መስከረም 2013.

 

ከመስከረም 25 በኃላ የኮ/ አብይ ፓርቲ መንግስታዊ ስልጣኑ እንደሚያበቃ ሁሉም የሚስማማበት ነው። የፌደራሊስት ሐይሎች የሀገር ማዳን ጥሪም / አብይና ፓርቲያቸው ፒፒ በስልጣናቸውን ላይ መቀጠል ከወሰኑ የመገለጫው/ የጥሪው አንዳንድ ይዘቶች እንዳሉ የሚቀጥሉ አይመስለኝም። ለምን? አሁን በፌደራሊስት ሐይሎች ሀገር የማዳን ጥሪ ላይ የቀረቡ ነጠቦች ከመስከረም 25 በሃላ አስራአንዱ ነጠቦች እንዳሉ በፈፁም አይቀጥሉም። ለምን?

 

. ለምን መስከረም 25 ቀን ተመረጠ?

 

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ህገ መንግስት መሰረት አንቀፅ ፶፰/58/ ቁጥር ሁለት የምክርቤቱ የስራ ጊዜ ከመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ እስከ ሰኔ ሠላሳ ነው፣ በመካከሉም ምክርቤቱ በሚወስነው ጊዜ የአንድ ወር ዕረፍት ይኖረዋል። ይላል ቀጥሎም በተመሳሳይ አንቀፅ በቁጥር ሶስት የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት የሚመረጠው ለአምስት ዓመታት ነው፣ የሥራ ዘመኑ ከማብቃቱ ከአንድ ወር በፊት አዲስ ምርጫ ተካሒዶ ይጠናቀቃል። ይላል (ማጥቆሩ የኔ) በመሆኑም / አብይ እንዳደረገወ ይህን ተርጉመህ የስልጣን ዕድሜ ለማራዘም የመሞከር ጥረት ምንም ህጋዊነት የለውም።

 

ሰለሆነም ከሰኞ መስከረም 25 2013. የኮ/ አብይ ፒፒ መንግስታዊ ስልጣን የመቀጠል ዕድል ዝግ ነው። ቀኑ ያለፈ መድሓኒት አይወሰድም። በማራዘም መድሓኒቱ መውሰድ ሓኪም አይመክርም። ክልክል ነው! በቃ መድሓኒቱ ይጣላል። ቀኑ ያለፈበት መድሓኒት እንደቆሻሻና እንደመርዝ ተቆጥሮ ይወገዳል። / አብይና ፒፒ ፓርቲያቸው በውርስ ይዘውት ከነበረው መንግስታዊ ስልጣንም መስከረም 25 ያበቃል። ከዛ በኃላ ስልጣን ይዞ መቆየት ከህገ መንግስት ውጭና ከህዝቡ ምርጫ ውጭ የተያዘ ስልጣን ስለሆነ በምንም መንገድ ተቀባይነት የለውም። ክልክል ነው! ሰለሆነም መወገድ አለበት። ኮኔረሉ በፍቃዱ ቀደም ብሎ ወርጃለሁ ካለ እሰየው ነው። አገር ለማዳን በሚደረገው ጥረት በመሳተፉ ታሪክ ይሰራል። ከዛ ውጭ ከመስከረም 25 ለሰከንድም፣ ለደቂቃም፣ ለሰዓትም፣ ለአንድ ቀንም እንዲያሳልፈ ግን በፍፁም አይችልም። ማሳለፍ የሚችለው በህገ ወጥነትና በጠመንጃ አፈሙዝ ብቻ ነው። ስለዚህ መስከረም 25 ቀን የተመረጠው የኢትዮጵያ ህዝብ በህገ መንግስቱ ባሰፈረው መሰረት ስልጣን የሚያበቃበት ቀን ሰለሆነ ነው። ይህን የህዝብ ድምፅ ተላልፎ ስልጣን ከህዝብ ፍቃድ ውጭ ማስረዘም መሞከር የሰላሙን ጥሪ አለመቀበል ስለሆነ የትግሉን መልክ በእጀጉን የሚቀይር ይሆናል።

Videos From Around The World

 

. የፌደራሊስት ሓይሎች ሀገርን የማዳን ጥሪና መስከረም 25

 

የፌደራሊስት ሓይሎች በሀገር የማዳን ጥሪው የኮ/ አብይ ፓርቲ ፒፒ ከመስከረም 25 በፊት ከአምስት ደቂቃ በፊትም ቢሆን ተቀብሎ ስልጣኑ በማስረከብ፣ የፖለቲካ እስረኛች በመፍታትና ኮማንድ ፖስት በማፍረስ፣ የውጭ የፀጥታ ኣካላት እንዲወጡ ቢያደርግና በቀጥታ የህዝብን ጥያቄ ለማፈን ሲፈፅመው የነበረ ግድያና ጭፍጨፋ አቁሞ ለሰላማዊ ድርድር ቅርቡነቱን በይፋ ለመላው የኢትይጵያ ህዝቦች ከገለፀ ሀገር ለማዳን የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዳደረገ ተቆጥሮ በጥሪው መሰረት የሁሉም ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ተወካዮች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የፌደራልና የክልሎች የተለያዩ ህዝባዊ ማህበራት ተወካዮች የሚሳተፉበት የሰላምና የሀገር ማዳን ኮንፍረንስ ላይ ፒፒ ይካተታል ይላል። በዚህም መሰረት ፒፒም ይሳተፋል ማላት ነው።

 

ይህ ካልሆነ ግን ከመስከረም 25 ቀን አንድ ሰከንድ ካሳለፈ የፒፒና የኮ/ አብይ መንግስታዊ ስልጣን ህገመንግስታዊ ባለመሆኑና ሀገር ለማዳን በሰላማዊ መንገድ ለሚደረገው ጥረት በአደናቃፊነት የሚታይ ሐይል ስለሚሆን የፌደራሊስት ሐይሎች የሰላም ጥሪም ወደ የትግል ጥሪ ይቀየራል። የዚህ ለውጥ ደግሞ የፌደራሊስት ሀገር ለማዳን ከዘረዘራቸው 11 ነጥቦች ጥሪ ውስጥ ከቁጥር አንድ እስከ አራት ያሉት ጥሪዎች ቀናቸው እንዳሳለፉ መድሓኒቶች ተቆጥረው ይወገዳሉ። እንደኔ በምትካቸው አንድ አዲስ ነጥብ መተካት አለበት ባይ ነኝ። ይኸውም በአገር አቀፍ ደረጃና በክልሎች ደረጃ ጠቅላላ አድማ እንዲመታና የኮ/ አብይ መንግስትና ፓርቲው ፒፒ በአስቸካይ ከስልጣን እንዲወርዱ ትግል መጀመር የሚል ነጥብ መካተት አለበት እላለሁ። በመቀጠልም፡-

-        ፖለቲካ እስረኞቻችን በትግል በሐይል እናስፈታቸዋለን።

-        ኮማንድ ፖስቶች በትግላችን ይፈርሳሉ።

-        የውጭ ፀጥታ አካላት በትግላችን ይባረራሉ።

-        ህዝቦች በትግላቸው ከግድያና አፈና ነፃ ይወጣሉ።

-        ገዳዮችና አፋኞች ፒፒዎችን ከስልጣን ወርደው በህግ ይጠይቃሉ።

-        በውዴታ እምቢ ያለቱን በግዴታ ተገደው ይፈፁሙታል።

 

. በሌሎቹ የፌደራሊስቱ ሀገር የማዳን ጥሪ ነጥቦች መጠናከር የሚገባቸው የሉም?

በእርገጥኘነት አሉ። ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ ማህበረሰቦችና መንግስታት ከዚህ ህገ ወጥ መንግስት የሚኖራቸው ግንኙነቶች እንዲያቃርጡ የሚለው መካተት አለበት። ምንም ስምምነቶች ማድረግ እንደሌለባቸውና የምናደርገውን ትግል እንዲደግፉ ጥሪያችን ማጠናከር ያለብን ይመስለኛል።

 

ከፒፒና ከኮ/ አብይ አስተዳደር ውጭ በፌደራልና በክልልሎች ያሉት መንግስታ ቢሮክራሲ አባላት ለዚህ ህገወጥ መንግስት እንዳይተባበርና በተለያዩ መንገዶች ትግሉን እንዲደግፍ ጥሪ ማድረግ ተገቢ ነው እላለሁ። ፌደራሊስቶቹ ይሁኑ ሌሎች ሐይሎች በአስራአንዱ ጥሪዎች ላይ መጠናከርና ግልፅ መሆን የሚገባቸው ነገሮችና የሚጨምርዋቸው ነጥቦች እንደሚኖሩ አምናለሁ።

 

ቸር ይግጠመን።

 

 

Back to Front Page