Back to Front Page

ፈጣሪ ኢትዮጵያና ህዝቦችዋ ይባርክ እና የመደብ ትግል በኢትየጵያ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያና ህዝቦችዋ ይባርክ እና የመደብ ትግል በኢትየጵያ።

ብርሃን ንርአ

20/08/2012ዓ/ም

brhannrae@gmail.com

ማንኛውም እምነት(ሃይማኖት)የሌላውን ሰው ወይም ማሕበረሰብ መብት እስካልነካ ድረስ እምነቱ(ሃይማኖቱ)ለኣማኙ ፍፅማዊ ነው።ክርስትና ለክርስያኑ፤እስልምና ለሙስሊሙ ፍፃማዊ እንከን የለሽ ፍፅም ጉድፍ የማይገኝበት እምነት ነው።ክርስትያኑ ለሙስሊሙ ወይም ሙስሊሙ ለክርስትያኑ ያንተ እምነት ይህንን ስህተት ኣለው ቢለው እንኳን ለክርስትያኑ ወይ ለሙስሊሙ የእምነቱ ስህተት ፍፁም አይታየውም ፍፅማዊ ነው ብሎ በእምነት ተቀብሎታል እና።ይህንን እምነት በጥብቅ ካልያዘክ አንዱን ሃይማኖት በሌላ ሃይማኖት ለመጫን መመኮር የሃይማኖቶች ትርምስ ይፈጠራል።ግዜ ሊረዝም ይችላል እንጂ እምነቱ በነፃ ለማረመድ የሚደረግ ትግል ድል ኣድራጊ ይሆናል።በኢትዮጵያ የታየ ታሪካዊ ክስተትም ይህንን የሚያረጋግጥ ነው።

ኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህቦች የተሰባሰቡባት አገር ናት።የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች አገር ብቻ አይደለችም የብዙ የተላያዩ እምነቶእ(ሐይማኖቶች)አገርም ናት።እውናታው ይህ ሁኖ ሳለ የኢትዮጵያ አመሰራረት ብዙሃነቷን በሚያስተናግድ መልክ ኣልተመሰረተችም። ኢትዮጵያውነት ማለት በቋንቋ አማርኛ የሚችል በባህል የአማራ ባህል ያለው በሃይማኖት ደግሞ ክርስትና ኦርቶዶክስ የሚያምን ነው ኢትዮጵያ ተብሎ የሚጠራው።ክርስትያን ነህ ሙስሊም ብለው ሊጠይቁህ ሲፈልጉ ኣንዳንድ ያገራችን አከባቢዎች አማራነህ ሙስሊም? ብለው ይጠይቁሃል።አማራ መሆን ኢትዮጵያ መሆን ብቻ ሳይሆን ኦርተደኩስ ለመሆንህም ማረጋገጫ ነበር።በኢትዮጵያ ኦርተደኩስ መንግስታዊ ሃይማኖት ነበር እና።

Videos From Around The World

የኢትዮጵያ ህዝቦች ለብሄራዊ መብታቸው ለሃይማኖታዊና ፆታዊ እኩልነት ታግለው ከፍተኛ መስዋእትነት ከፍለው ለድል በቅተዋል።1987ዓ/ም የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች መብት የሚያረጋግጥ ሕገ መንግስት አፅድቀዋል።በ1987ዓ/ም የፀደቀው ህገ መንግስት መንግስትና ሃይማኖት የተለያዩ መሆናቸው፤መንግስታዊ ሃይማኖት ከእንግዲህ በኋላ እንደሌለ፤መንግስት በሃማኖት ውስጥ ጣልቃ አይገባም፤ሃይማኖቶችም በመንግስት ጉዳይ ጣልቃ እንዳይማይገቡ በህገ መንግስት አስፍረዋል።በሌላ ኣነጋገር መንግስት ምድራዊ ስራን ሲሰራ ማለትም ማህበረሰብ ፀረ ድህነት ትግል የማስተባበር፣ህዝቦች በዚች በምንኖርባት ዓለም ፍትህ ኣግኝተው የተሻለ ኑሮ እንዲኖሩ ይሰራል።ሃይማኖቶች ደግሞ ሰማያዊ ስራ ማለትም አማኝ ከሞት በኋላ ፅድቅ እንዴት እንዲሚያገኝ ከሓጥያት እንዴት መራቅ እንዳለበት ይሰራሉ ማለት ነው።ይህ ማለት መንግስትና ሃይማኖቶች በጋራ ጉዳይ በጋራ ኣይሰሩም ማለት አይደለም።መንግስትና የሃይማኖት መሪዎች እንዲሁም መእምናን በጋራ ጉዳይ በጋራ መስራት ተፈለጊም ተገቢም ነው።

ኢትዮጵያ ከ1983ዓ/ም በኋላ በተለይ ህገ መንግስት ካፀቀች በኋላ የመጣውን ህዝባዊ መንግስት ለዚህ የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት ተገዢ ሁኖ ለ27 ዓመታትን የሰላም የልማት የዲሞክራሲ ግንባታን በኢትዮጵያ ኣከናውነዋል።ለ27ዓመታትን በሰላም ልማት እና ዲሞክራሲ ጎዳና እንድትጓዝ የመራ ኢህአዴግ በሃይማኖታዊ ስብከት ሳይሆን በመደባዊ ትግል እየመራ ነው ኢትዮጵያ ከዛ በፊት ኣይታው የማታወቀውን እድገት ማስመዝገብ የቻለችው።ያን ግዜ የነበሩ መሪዎች ማለትም ለ27 ዓመታት የልማት፣ሰላምና ዲሞክራሲ መንገድ የመሩ መሪዎች ፈጠሪ ኢትዮጵያና ህዝቦችዋ ይባርክ የሚል ሲናገሩ ለአንድቀንም የተደመጡ ኣይመሰለኝም።በዚህ 27 ዓመታት ይህን አይነት ምርቃ የሚደመጥ የነበረ በሃይማኖት መሪዎች በተላላቅ ኣባቶች እና እናቶች ምርቃት ነው።ለ27ዓመታት የመሩ መሪዎች ደጋግመው የሚናገሩት ነገር ነበረ።ዋነኛ ጠላታችን ድህነት ነው።እናት ሂወት እየሰጠች በወሊድ ምክንያት መሞት የላባትም።የድህነት ተራራ የሚናደው ብእውቀት ጥይት ነው።ያገር ፍቅር ማለት የህዝብ ፍቅር ነው።ይሉ ነበር።ድህነት ለማሸነፍ ፖሊሲና ስትራተጂ ቀርፀው ለተግባራዊ ይረባረቡ ነበር።ፀረ ድህነት ትግል ዋነኛ መሳርያቸው ደግሞ መዳባዊ ትግል ማካሄድ ነበር።በዚህ የመደብ ትግል ኢትዮጵያ ባለ ሁለት ኣሃዝ እድገት ማስመዝገብ ችላ ነበር።በዲፕሎማስም ተሰሚነት ያገኘች ኣገር ነበረች።

ፈጣሪ ኢትዮጵያና ህዝቦችዋ ይባርክየሚል ንግግር በመንግስት ባለስልጣን ደረጃ ከ27ዓመታት በኋላ ለመጀመርያ ግዜ የሰማነው ዶር አብዪ ኣሕመድ የጠቅላይ ሚኒስትርነት ሹመት በፓርላማ ሲሾም በአቀረበው ንግግር ላይ ነው።ያን ግዜ የቀጥታ ስርጭቱን እከተታል ነበር።ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመጠቃለያ ንግግሩ ፈጣሪ ኢትዮጵያና ህዝቦችዋ ይባረክሲል ቀጥታ ወደ ህልናየ የመጣሊኝ የአመሪካኖች የፕረዚዳንታዊ ውድድር የመጣቀላያ ንግግራቸው ፈጣሪ አመሪካን ይባርክ የሚል ነው።

ጠቅላይ ሚኒትር ዓብዪ ኣሕመድ በማንኛውም ንግግሩ ማጠቃለያ ፈጣሪ ኢትዮጵያና ህዝቦቿ ይበርክ ይበል እንጂ በመደመር መፅሓፉ ምረቃ ላይ በመደመር እሳቤ ድህነት ወዳጅም ጠላትም እንዳልሆ በኢፋ ነግሮናል።ፈጣሪ ኢትዮጵያና ህዝቦችዋ እንዲባሪክ ሰርክ የሚናገር ጠቅላይ ሚኒስትር ፀረ ድህነት ትግል እንደማያካሂድ በግልፅ ነግሮናል።ኢትዮጵያና ህዝቦችዋ ድህነት ጠላታችን ነው መፋለም አለብን ብልው ከድህነት ለምውጣት ካልታገሉ ታድያ እንዴት ነው ፈጣሪ የሚባርካቸው? ማንኛውም እምነት ሰርተህ መኖር የግድ ይላል።ክርስትና ብላዕ ብሓፈ ገፅከይላል።እስልምና ስራ ዒባዳ ነው(ስራ ግዴታ ነው)ይላል።ታድያ የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብዪ አሕመድ ድህነት ወዳጅም ጠላትም አይደለም ከየት ተገኘ?

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብዪ አሕመድ ከተመረጠ ወዲህ በኢህአዴግ ዘመን ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ህዝቦች ተፈናቅለዋል።ዜጎች በማንነታቸው ምክንያት በሺዎች የሚቆጠሩ ተገድለዋል።ታዋቂ ሰዎች በኣደባባይ ተገድለዋል።በአደባባይ ከተገደሉት ውስጥ የተወሰኑ ስማቸው ለመጥቀስ ያህል ኢንጅነር ስመኝ በቀለ፣ጠቅላይ ኢተማጆር ሹም ሰዓረ መኮነን፣የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳደር ዶር አምባቸው ከብዙ በጥቂቱ ናቸው።ከዚህ በተጨማሪ በዐብዪ ዘመን ብዛት ያለቸው አብያተ ክርስትያናትና መስጊዶች ተቃጥለዋል።ዐብዪ አሕመድ በደርግ ዘመን የነበሩ ጳጳስና የአሁኑ ጳጳስ አስታረቅኩ ብሎ ውስጥ ለውስጥ በቅራኔ እንዲጠመዱ እድርገዋል።ይህ አልበቃ ብሎ ኦርተዶኩስ ሃይማኖት በሁለት እንዲከፈል በዐብዪ አሕመድ ባለስልጣናት የሚመራ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው።ተሃድሶ ኦርተዶክስ የሚባል እንደአዲስ ተነስቶ ነባርዋ ኦርቶዶክስ ላይ ችግር እየፈጠረ እንዳለ ይነገራል።ኦርቶዶክስና ፕሮቲስታንት ኦርቶዶክስ እና ሙስሊም በመንግስት በጥንቃቄ በተመራ መንገድ ቅራኔዎቹን እንዲካረሩ እየተደረገ መሆኑን ከሚታዩ የመንግስት እንቅስቃሴዎች መረዳት ይቻላለል።ለሁለት ዓመት ሙሉ አንዱን ክልል ከሌላው ክልል የሚያገናኝ መንገድ ተዘግተዋል።ከዚህ በተጨማሪ የኢትዮጵያ ሶማሊና የደቡብ ህዝቦች በዓብዪ ትእዛዝ እንዲፈርሱ እና በኮማንድ ፖስት እንዲተዳደሩ የተደረገበት ዘመን በዓብዪ ዘመን ነው።የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ቁልቁል ወርደዋል።የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ተሰሚነት ተነጥቃለች።አባይ በራሳችን አቅም መገንባት ጀምረን ከ70% በላይ ግንባታው ተጠናቅቀዋል።ግን በውሃ ሙሌት ላይ አመሪካ እንድታደረድርና እጅዋ በኢትዮጵያ እንድታስገባ ከዐብዪ ፍቃድ አግኝታለች።ዓለም አቀፍ ወረርሽን የሆነውን ኮሮና ቫይረስ በተቀሰቀሰበት ወቅት በአብዪ የተሸሙ ጤና ምኒስትርና የቴክኖሎጂ ሚኒስተር ድንገት ተነስተው ኢትዮጵያ ኮሮና ቫይረስ ማከም የሚያስችል መድሃኒት ሰራች ብለው በሚድያ በማስነገር ህዝቡ የመከላከል ስራው አጥብቆ እንዳይዝ አድርገዋል።ይህም እንደ አመሪካው ፕረዚዳንት ዶናል ትራምፕ እንዝህለልነት ታይቶባቸዋል።ይህ ሁሉ ችግር በዐብዪ መሪነት ተፈጥሮ እያለ እንዴት ነው ፈጣሪ ኢትዮጵዩ እና ህዝቦችዋ የሚባርከው?አንድ አማኝ የዐብዪ ኢትዮጵያ እና ህዝቦችዋ ይበርክ ማለቱ የአዞ እምባ መሆኑን ይረዳዋል እና ፈጣሪ ርህሩህ ነህ እና የዐብዪ ተግባር ትተህ ምህረት ስጠን ብሎ እንደሚፀሊ ምንም የሚያጠራጥር ነገር የለውም።በፖለቲካ ተኝታኞች እምነትም ኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስተር ዐብዪ አሕመድ በሚመራው የመደመር መንገድ በመጓዝዋ ምክንያት ወደ መበታተን አፋፍላይ መድረስዋን ይስማማሉ።

ግን ዐብዪ አሕመድ የመንግስት ስራውን ትቶ ለምን ወደ ሃይማኖት ተጠጋ የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል።ያገሬ ሰው የጨነቀው ሙሁር ወደ እዝጋቢሄር ይጠጋል ይላል።መምህር ሳይንስ ለማስተማር ነው የሚቀጠረው።አንዳንድ መምህር(ጥቂቶቹ)ሳይንሱን ሳይጨብጠው ይቀርና ተማሪዎች በዚህም በዛም ወጥረው በጥያቄ ስያዋክቡት ይህ እዝጋብሄር ነው የሚያውቀው ብሎ ስለሚመልስ ነው የጨነቀው ምሁር ወደ እዝጋብሄር ይጠጋል የተባለው።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብዪ አሕመድም ወደ ሃይማኖት የመጠጋቱ ሚስጥር በሃይማኖት ላይ ፅኑ እምነት ስላለው ሳይሆን ፖለቲካዊ መሪ መሆን ስለኣቃተው ነው።ጠቅላይ ሚኒስር ዐብዪ አሕመድ የምዕራብና የዓረብ መንግስታት ከሚያዙት ውጭ የፖሊሲ አማራጭ የለውም።ችሎታ ኣድርጎ የቆጠረው በምላስ አታልለህ ማለፍ ነው።ይህ በምላስ ማታለልም ብዙ ርቀት ሊወስድ አይችልም።

ኢትዮጵያ መምራት የሚችለው የአርሶአደሩ፣የአርብቶአደሩ፣የሰራተኛው፣የከተማ ነዋሪ፣ የልማታዊ ባለሃብቱ ጥያቄዎች አድምጦ መልስ መስጠት የሚችል መሪ ነው።ይህንን ማድረግ ያልቻሉ ከዘመነ ሚኒሊክ እስካ ሃፀይ ሀይለ ስላሰ ያሉ መሪዎች በሃይማኖት ካባ ውስጥ ተወሽቀው ነው ህዝቡን የሚጨቁኑት የሚመዝብሩት የነበሩት።በአንፃሩ ደርግ ደግሞ የእምነት ነፃነት ለሁለም አማኞች በመግፈፍ ስልጣኑ ለማረዘም ሙኮራ ኣድርገዋል።ኑጉስ ሓይለስላሰ በመፅሃፍ ቅዱስ ውስጥ ስማቸው ገብቶ ይቀድስላቸው እንደነበረ የቅርብ ግዜ ትዝታ ነው።ገበሬው አፀይ ሃይለስላሰ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዳይከፋው ውሃ በሞላ ቤርሚል ውስጥ ሁኖው ነው እየፀለዩ የሚያድሩት ይል ነበር።ንጉሱ ግን በትግራይና በወሎ ድርቅ ግዜ እንግሊዝ አገር በተሰራ ኬክ ልዳተቸው ያከብሩ ነበር።የዐብዪ ፈጣሪ ኢትዮጵያና ህዝቦችዋ ይባርክ ከሃይለስለሰ ፀሎት በምን ነው የሚለየው?

ዐብዪ በስመ ፈጣሪ ኢትዮጵያና ህዝቦችዋ ይባርክ ከመዳባዊ ትግል ለማምለጥ ነው እየመኮረ ያለው።ዐብዪ በሃይማኖት ሰበብ በዚች ዓለም ህዝቡ ኑሮውን ለመሻሻል የሚያደርገው ትግል መምራት አቅቶት ነው ወደ ሃይማኖት እየተጠጋ ያለው።ሃይማኖች ሽፋን አድርገው የስልጣናቸው ዕድሜ ለማራዘም የሚሰሩ ሁሉ ፀረ ህዝብ እንደሆኑ ህሉ የዐብዪ አሕመድ መንግስትም ፀረ ህዝብ ነው።

የኢትዮጵያ ህዝቦች ይህንን የዐብዪ አሕመድ ተግባር እና ወደ ሃማኖት ጠጋጠጋ ማለት ፀረ ህዝብ ተግባሩ ለመሸፈን መሆኑን ተገንዝበው መደባዊ ጥቅማቸው ለማረጋገጥ ለትግል በመነሳሳት የዐብዪ መንግስት አሽቀንጥረው መጣልን ይጠብቅባችዋል።

የሃይማኖት መሪ ወደ ቤተእምነት፤የፖለቲካ መሪ ወደ ፀረ ድህነት ትግል ይሰማሩ!

Back to Front Page