Back to Front Page

ግብፅ አሸነፈች

ግብፅ አሸነፈች

በኛ  ገንዘብ ... በኛ  መሀንዲሶች
በኛ  አባይ ... በኛ  ሀብት
አዛዥ ፣ ፈላጭ፣ ቆራጭ ...
  ስጡ ፣ ቀንሱ ፣ ጨምሩ ፣ ተቀበሉ
የሚለንን ... አንቀበልም ...
ብሎ  ቆርጦ  የተነሳው

... ውዱን
መሪያችንን ... ያኮራንን  ያስከበረንን..
የ  ጥቁር  አፍሪካ ... አለኝታናን
... ናፈቅን ... እጅጉን
... መለስ  ዜናዊን ... ናፈቅን

ግብፅዬ ...
አንገታችንን  ቀና... ያደረገውን ...
በተንኮል  ወጥምድሽ ... ያልገባውን
እንቅልፍ  የነሳሽን ...
... መሪያችንን ... እጅጉን ናፈቅን

አሁንማ ... ግብጽዬ ... አሸነፍሽን
አስጎበደድሽን ... ላንቺ  ታዛዥና ተገዢ ...መሪ ...

መርጠሽ ሰጠሽን

ግብፅዬ ...
የ  መረጥሽልን  መሪ...
አንቺን  ለማስደሰት ... ባንቺ  የተመረጠው
የመደመር  ፈላስፋው ...
ሶስቱን  ተርባይን ... ላንቺ  ሲል  ቀንሰልን
ሊጠቅመን  ይሆን ... ሊጎዳን
ሊያኮራን  ሳይሆን ... ሊያስጎበድደን

ግብፅዬ ... የምትወጅው  መሪያችን
በትዛሻሽ ...

የ አባዩን ጌታ ... መሀንዲሳችንን

በጠራራ  ፀሀይ .... በአደባባይ ...ቀጨብን
ግብጽዬ .... አሸነፍሽን

... ኢትዮጵያዊ  ነን  በሚሉ ... ተጋሩን  በሚጠሉ
በሆዳቸው  ገብተሽ ...
የጥላቻ  ዘመቻ ... አወረድሽብን
መርጠሽ ... መራርጠሽ ....
ልክ  ቃል  እንደገባሽው ... አተራመስሽን
ግብጽዬ ... አንገት  አስደፋሽን
... አሸነፍሽን
አራት  ኪሎ ... የገቡት  ቅጥረኞችሽ
አባይን  ላይጠሩ ... የማሉልሽ
አንገታችንን ... አስደፉን
ኩራታችንን ... ሰረቁብን

ግብፅዬ ... አሸነፍሽን

ኢዮብ ከጮማ እምኒ

02-02-2020

Back to Front Page