Back to Front Page

የዓለማችን ሰራተኛው ህዝብ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ሁለት ግዜ እየሞተ ነው።

የዓለማችን ሰራተኛው ህዝብ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ሁለት ግዜ እየሞተ ነው።

ብርሃን ንርአ

17/08/2012ዓ/ም

brhannrae@gmail.com

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በሃገረ ቻይና በውሃን ከተማ ይጀምር እንጂ መላውን ዓለም ያደረሰ ወረርሽኝ ሁኖዋል።በጣት በሚቆጠሩት ወራት ውስጥም ከ2 ሚልዮን በላይ ህዝቦች በቫይረሱ ተይዘዋል 190 ሽህ በላይ ህዝቦች በቫይረሱ ምክንያት ሂወታቸው ተቀጥፈዋል።የቫይረሱ ስርጭት በኤሽያ ይጀምር እንጂ በኣውሮፓ እና አሜሪካ ጥቃቱን እያየለ መጥተዋል።የኤሽያ ሃገራት መንግስት እና ህዝቦች ተኣምር ያስባለ የመከላከል ስራ ሰርተው ስርጭቱ እንዲቀንስ ብሎም እንዲቆም ሲያደርጉት የአውሮፓ እና የአመሪካ መንግስታት ግን በአሳዩት እንዝህላልነት ህዝቦች እንደቅጠል እንዲረግፉ ምክንያት ሁኖዋል።በኣውሮፓ እና በአመሪካ በቫይረሱ የመያዝም ይሁን የመሞት ፍጥነት ሲቀንስ እየታየ ኣይደለም።።በኤሽያ የቫይረሱ ስርጭት ለምን በፍጥነት መቆጣጠር እንደቻሉ እና አውሮፓ እና አመሪካ የቫይረሱ ስርጭት ለምን መቆጣጠር ተሰናቸው የሚል ከቻይና ልምድ የሚንማረው ምርጫ ለማስቀረት ነው እንዴ? በሚል ፀሁፍ መግለፄን ይታወሳል።በዚህ ፅሑፍ ውስጥ ትኩረት የተሰጠው በኮሮና ቫይረስ ሁለት ጊዜ እየሞተ ያለው ማን እንደሆነ በማብራራት የመፍትሄ ሓሳብ ለመግለፅ ነው።

ኮሮና ቫይረስ በተፈጥሮው የሰው ቀለም(ዘር)፣ሓይማኖት፣ድሃ፣ባለሃብት፣ባለስልጣን ወዘተ በማይለይ ሁኔታ የማጥቃት ኣቅም ያለው ቫይረስ ነው።ቫይረሱ ዕድሉ በአገኘበት ሚኒስትሮች፣የሃይማኖት መሪዎች ተዋቂ ሰዎች ሲያዙ እና ሂወታቸው ሲነጠቅ ኣይተናል።ይሁን እና በኮረና ቫይረስ ሁለት ግዜ እየሞተ ያለው ግን ሰራተኛ ህዝብ ነው።ኮሮና ቫይረስ ስርጭቱ ፈጣን ያደረገው ንክኪ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት ግልፅ ኣድርጎታል።የመከላከያ መንገድም ርቀትህ መጠበቅ፣ንክኪ ማስወገድ ስለማይቻል አንድ ነገር ከነካህ በኋላ እጅህ መታጠብ፣በጣም ኣስፈላጊ የሆነ ስራ ከሌለህ በስተቀር ከቤት ኣለመውጣት ወዘተ መሆናቸውን ተብራርተዋል።

Videos From Around The World

የቫይረሱ ስርጭት ለመግታት የተቀመጡ መፍትሄዎች ለመተግበር ለሰራተኛው ህዝብ ለብቻው ከተተወ አይነኬ መሆነቸው በተግባር ታይተዋል።የኤሽያ ሃገራት ቫይረሱ ለመከላከል የግለሰብ ጉዳይ ብቻ ኣይደለም የመንግስት ሚና ወሳኝ ነው በሚል እምነት ከሆስፒታል ግንባታ ጀምሮ ማስክ ጓንት ምግብ ለዜጎች በነፃ ማቅረብ ወዘተ የዘለቀ እንቅስቃሴ በማካሄዳቸው ሰራተኛ ህዝባቸው ለመታደግ ችለዋል።በአውሮፓ እና አመሪካ መንግስታት ቫይረሱ በቻይና ከታየበት ቀን ጀምሮ ቀልድ ነው የጀመሩት።የታላቋ አመሪካ ፕረዚደንት የቻይና ቫይረስ ነው።ቀላል ጉንፋን ነው። በማለት ነው የአገሪቱ ሰረተኛ ህዝብ እንደቅጠል እንዲረግፍ እያደረገ ያለውን ኮሮና ቫይረስን አሳንሰው ያዩት።ችላ ባሉት መንግስታት የሚመራ ህዝብ በኮሮና ቫይረስ እንደቅጠል እየረገፈ ነው።በአውሮፓ እና አመሪካ እንደቅጠል እየረገፈ ያለው ሰራተኛ ህዝብ ነው።ቫይረሱ ዓለም አንቀጥቅጥ ጥቃቱ ሲዘንዝር ቤታችሁ ቆዩ የሚል ሓሳብ ቀረበ።ሓኪሞችም ህዝቡ ቤቱ በመቆየት እነሱን እንድያግዝ አጥብቀው ተማፀኑ።ይሁንና ከሰራተኛው ህዝብ የተነሳው ጥያቄ ግን መልስ አላገኘም።የሰረተኛው ህዝብ ጥያቄ እኛ ጎደና አደር ቤት የለለን ዜጎችስ የትነው የምንቆየው?ተከራይተንም የግላችን ቤት ኑሮንም ቤታችን ከተቀመጥን ምንነው የምንበላው?ወዘተ ጥያቄዎች አቅርበዋል።ከሰረታኛው ህዝብ የቀረበ ጥያቄ የነፃ ገባያ ኣክራሪነት የሚከተሉ መንግስታት መልስ አልሰጡትም ።ሁኔታው እየተባባሰ ሄዶ ከ2 ሚልዮን ህዝብ በቫይረሱ ሲያዝ ከ190 ሽህ በላይ ህዝብ ሓኪሞችን ጨምሮ በቫይረሱ ሂወታቸው ተቀጠፈ።በቫይረሱ የተያዙትም የሞቱትም የአመሪካ እና የአውሮፓ ህዝቦች ከፍተኛውን ቁጥር ይይዛሉ።ታሪክ ራሱን ደገመ።በዕለተ ሜይደይ በአክራሪ የርእሰማል ሓይሎች(capitalist)በአደባባይ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰረተኞች የተጨፈጨፉበት ታሪክ የ21ኛው ክፍለዘመን የነፃ ገበያ ኣክራሪ ሓየሎች በፈፀሙት ስህተት በስውሩ በኮሮና ቫይረስ በዓስር ሺዎች የሚቆጠር ሰረተኛ ህዝብ እንድያልቅ እየፈረዱበት ነው።ይህ ኢልቂት እንዲቀጥል በመፍቀድ አመሪካ ለዓለም ጤና ድርጅት(WHO)እየሰጠችው የነበረ ድጎማ ለማቋረጥ መወሰንዎ ጉዳይ ግልፅ አድርጎታል።

የዓለም ሰራተኛ ህዝብ ግን አንዴ ብቻ ኣይደለም በኮሮና ቫይረስ እየሞተ ያለው።አንደኛው በኮሮና ቫይረስ በመያዙ ሚክንያት ሲሞት ሁለተኛው ደግሞ ኮሮና ቫይረስ በፈጠረው ኢኮኖምያዊ ቀውስ ምክንያት በስራ አጥነት እና ኑሮ ውድነት ነው እየሞተ ያለው።የአውሮፓ እና የአሜሪካ የነፃ ገበያ ኣክራሪ ሓይሎች የሰራተኛው ህዝብ ስራኣጥነት እና ኑሮ ውድነት ለመፍታት ጥረት ሲያደርጉ እየታዩ አይደለም።በዚህ ምክንያት ይመስላል እየበላን እንሙት ከረሃብ ይሀይስ ኵናት እንደሚለው ያገሬ ሰው እየታመም እየሞተም ቢሆን ስራ እንዲፈጠረልት በሰላማዊ ሰልፍ ሓሳቡ እየገለፀ ያለው።

የኤሽያና ደቡብ ኮርያ ልማታዊ መንግስታት ሰረተኛ ህዝባቸው ሁለት ግዜ እንዳይሞትባቸው ሰፊ ጥረት ኣድረገዋል።መጀመርያ በኮሮና ቫይረስ እንዳይያዝ እና ከተያዘም በአፈጣኝ በመለየት ህክምና የሚያገኝበትን ሁኔታ ፈጠሩ። ይህ የመከላከሉ ስራም ይሁን የህክምና ስራ በኣብዛኛው ልማታዊ መንግስታት በነፃ የሰጡት አገልግሎት ነበር።እንዲህ የተገደዱበት ምክንያትም ለህዝብ ያለቸው ውግንና ነው።ልማታዊ ዲሞክራስያዊ አስተሳሰብ ግራዘመም ነው አማራጭ ሊሆን አይችልም የሚሉ የነበሩ የነፃ ገበያ ኣክራሪዎች አገራቸው ከኮሮና ቫይረስ መታደግ ሲያቅታቸው፤ልማታዊ ዲሞክራስያውያን የኤሽያ መንግስታት ግን በተኣምራዊ ቅፅበት የቫረሱን ስርጭት መግታት ብቻ ኣይደለም በቀጥታ ወደ ልማታዊ ዲሞክራስያዊ ስራቸው በፍጥነት ገብተዋል።ቻይና የቫይረሱ መነሻ የነበረች ውሃን ከተማ ወደ ኢኮኖምያዊ እንቅስቃሴ እንድትገባ ስታደርግ ደቡብ ኮርያ ዓለም ዓጀብ ያሰኘ ዲሞክርስያዊ ምርጫ አካሂዳለች።በዚህ ምክንያት ይመስላል የዓለማችን ሰራተኛው ህዝብ በነፃ ገበያ አክራሪ መንግስታት ሁለት ግዜ ከሞሞት ወደ ልማታዊ ዲሞክራስያዊ መስመር(ግራዘመሙ)ወይም ለጭቁን ህዝብ የወገነ መስመር የነበሩትን ጉድለቶች በማስተካከል ለመከተልና ተግባራዊ ለማድረግ ለመንቀሳቀስ እየወሰነ ያለው።የዓለማችን ፖለቲከኞች ፖለቲካዊ ድርጅቶች ዓለማችን ወደ አጠቃላይ ቀውስ ከመግባትዋ በፊት ሰራተኛው ህዝብ ምስቅልቅሉ ከመውጣቱ በፊት ፈጥነው የልማታዊ ዲሞክራስያዊ መስመር በመፈተሽ ጉድለቶች ካሉትም ማስተካከያ በማድረግ ወደተጨባጭ ለውጥ እንዲገባ በማድረግ ሰራተኛው ህዝባቸው መታደግ ይገባቸዋል።ዓለም ከአክራሪ ነፃ ገበያ መር ምህዋር ወደ ልማታዊ ዲሞክራስያዊ መር ምህዋል ለመግባት እየተንደረደረች ነውእና።

የአገራችን ፖለቲካ መሪዎችም ከዓለም ልምድ በመቅሰም የ27 ዓመታት የኢትዮጵያ የሰላም ፣ልማት እና ዲሞክራሲ ጉዞ ለማስቀጠል የሚያስችል እርምጃ የሚወስዱበት ወሳኝ ግዜ መሆናቸው ተገንዝበው አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ ይጠበቅባችሃል።

በአገራችን ኢትዮጵያም የስልጣን ዝፋኑን የተቆጣጠረው የነውጥ ሓይል የምዕራቡ አስተሳሰብ እንደማያዋጣው ቆም ብሎ ማሰብ ይጠበቅበታል።የምዕራቡ ኣክራሪ የነፃ ገበያ አስተሳሰብ በኮሮና ቫይረስ ተፈትኖ መውደቁ እየታየ ነውእና።ከዚህ በመቀጠልም ዘርፎ የወሰደውን የህዝብ ስልጣን ያለምን መንገራገጭ በሰላማዊ አገባብ ማስረከብ ይጠበቅበታል።ይህንን አክራሪ የነፃ ገበያ ኣስተሳሰብ በኢትዮጵያ ለማስቀጠል ካሰበ ግን የኢትዮጵያ ሰረተኛ ህዝብ የሚያካሂደውን ትግል ከዓለማቀፉ ትግል ተዳምሮው ጠራርጎ እንደሚጥለው ሳይታለም የተፈታ ነው።

በኢትዮጵያ ውስጥ ከፈዴራልም ከሌሎች ክልሎችም በተለየ ኣቅጣጫ ሰረተኛው ህዝብ ለመታደግ እየሰራች ያለች ክልል ትግራይ ናት።በህወሓት የሚመራው የትግራይ ክልል መንግስት ህገ-መንግስት በሚፈቅድለት መንገድ መጋቢት 17/2012ዓ/ም ኮሮና ቫይረስ ለመከላክል የሚያስችል አስቸኳይ ግዜ ኣዋጅ አዋጀ።ህዝቡም በነበሩት ጠንካራ ኣደረጃጀቱ ታግዞ ተግባሪዊ ኣደረገ።ይህ በትግራይ ካቢኔ የወጣ ኣዋጅ ዲሞክራስያዊ ስርዓቱ በሚጠይቀው መንገድ የክልሉ ምክርቤት ተሰብስቦ ማፅደቅ ነበረበት።ቫይሮሱ ፈጥኖ ከሚተላልፈበት መንገድ ደግሞ ስብሰባ(ርቀትህን ኣለመጠበቅ)ነው።ለዚህም በህወሓት የሚመራው የትግራይ ክልል መንግስት መፍትሄ አበጀ።በ8 ማእከላት ፕላዝማ አዘጋጀ።የምክርቤቱ ኣባላት ወደ አቅራብያቸው የሚገኙ ማእከላት ቀረቡ።የምክሪቤቱ መደበኛ ስብሰባ በፕላዝማ ተካሄደ።አስቸኳይ አዋጅም ፀደቀ።የትግራይ ሰራተኛው ህዝብ በኢኮኖሚ እንዳይጎዳ ጥንቃቄ በተሞለበት ገደቦቹ መላላት ጀምረዋል።ከገጠር ገጠር፣ከገጠር ቀበሌ ወደ ወረዳው ማእከል መንቀሳቀስ ተፈቅደዋል።ክረምት እየገባ ነው።ኣርሶአደሩ ማምረት አለበት።ምርታማነት ለመጨመር ደግሞ የአመራርና የባለሞያዎች ድጋፍ ማግኘት ኣለበት።ለእርሻ የሚያገላገሉ ግብኣቶች መቅረብ ኣለባቸው።እነዚህ ጉዳዮች በጥንቃቄ እንደሚከወኑ የትግራይ ምክትል ርእሰመስተዳደር ገልፀዋል።ትግራይ ትንሽዋ ቻይና እየተባለች የምትጠራበት ምክንያት ይህ ይሆን?

በመጨረሻ ሜይደይ(የሰራተኞች ቀን)ለማክበር የቀሩት ቀናት በጣት የሚቆጠሩ ናቸው።የዘንድሮ የሰራተኞች ቀን (ሜይደይ)ሲከበር በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ሁለት ግዜ እየሞተ ያለውን የዓለማችን ሰራተኛው ህዝብ በማሰብ እና ለትግል በመነሳሳት መሆን አለበት።

ሰራተኛው ህዝብ ከሮና ቫይረስ ለመታደግ እንስራ!

የዓለም ሰራታኞች ተባበሩ!

 

Back to Front Page