|
የበቀለ ልጅ....!
ያሬድ ሕሉፍ 04-22-20
ዘመድ የለ ፈጥኖ ደራሽ የሚያበረታታ የሚል ኣይዞሽ በተዘጋ ቤት ፍርስራሽ ውሀ የለ ሚበላ ቁራሽ መኖር ግድ ሆኖ ሥጋ ለባሽ: ቀን እስኪያፍ እስኪመሻሸ: ባለኣደራ ኣትክልት: ማሙሽ ባፈራ እንዴት ደስ ባለኝ : ደም መላሽ::
ይሄው ለዓመታት ስመኝ ሳይታክተኝ ሳይደክመኝ ምን እለ ቢያድለኝ ለተከፍው ልቤ! ማፅናኛ ደብዳቤ: ጌታ ልጅ ቢስጠኝ: ከሚታመን ጏድ ከሚወደኝ ኣለሁ ባይ ሲከፋኝ: ደስታዬም ተካፍይ : ልጅ ካለም ተንከባካይ:: በዓለም ከዚህ በላይ ምን ኣለ ሌላ ንዋይ::
ታድያ ስኖር ስንገላታ ስወጣ ስወርድ በርካታ ካሳስብኝ ሁኔታ:
መለስ ብሎ ጌታ! ተስፋ እንዳልቆርጥ እንድበረታ: ስመፕው ውሎ ያደረ: ለገሠ: ባለውለታ ባል: ወረወረ: መህፀኔም ቆጠቆጠ መሀን ሁኖ ኣልቀረ: የበቀለ ልጅም: ስመፕው ተባለ:: አድጎም ከተማረ ለተጠማው ሁሉ: ኣንጀቱ ላረረ አጥቶት ለነበረ እጅ ስነዘረ: ውሀ : ምግብ ላቀብል ኣለ ጉልበት እስከቻለ::
መሳቅ ኣይሉት ገደብ የለሽ ሳቀ ፍፁም በደስታ ልቤ ፈነደቀ: ፍትሕ መሬት ላይ ፀደቀ::
በዚያው ልክም ምቀኛ ፈለቀ ከወሀ ጥም ድሀን ላላቀቀ ወነጄለው ጉሮሮው እንዳደረቀ: እርር ድብን ብሎም በንዴት ደቀቀ:
ግራ ቅኝም ተቻኮለ ልጄን ሊያጠፋ ምን ግዜ ኸጀለ::
ታድያ በጠማማ አእምሮ ኣምባጏሮ ጭሮ ንፁሃን ገደለ ልጄንም ጨምሮ:: ላያልቅ የኔ እሮሮ!
ወይ ዘንድሮ! መቼ ያልቃል ተነግሮ ቀማኛ ካልተመቸው ኑሮ አቅመ ቢሱን ስባብሮ ልበ ቁኑን አጭበርብሮ ሁሉ እንዲጠፋ ተበነቃቅሮ ይራራጥ ጀመረ በአስተክሮ: የአህያዋን ምሳሌ ተክትሎ: "እኔ ከሞትኩኝ በኃላ ስርዶ አይብቀል እንኻን የሚበላ"::
|