Back to Front Page

ከዚህ በሃላ ሽመልስ አብዲሳ ጋር በአንድ ፖርቲ መቀጠል ማለት ከአማራ ህዝብ ጋር ፊት ለፊት መላተም ማለት ነው፡፡

ከዚህ በሃላ ሽመልስ አብዲሳ ጋር በአንድ ፖርቲ መቀጠል ማለት ከአማራ ህዝብ ጋር ፊት ለፊት መላተም ማለት ነው፡፡

 

 

📩 #Top_Secret_Via_ Inbox 📩

 

" ከዚህ በሃላ ሽመልስ አብዲሳ ጋር በአንድ ፖርቲ መቀጠል ማለት ከአማራ ህዝብ ጋር ፊት ለፊት መላተም ማለት ነው፡፡ ለራሳችንንና ለህዝባችን ክብር ሲባል ከዚህ ቀን ጀምረን ሽመልስ አብዲሳ በፖለቲካዊ ውሳኔ ከብልፅግና እንዲባረር ብቻ ሳይሆን በህግ አግባብ እንዲጠየቅም ማድረግ ካልቻልን አንቅሮ የተፋን የአማራ ህዝብ፤ የቀረችው እንጥፍጣፌ ትእግስት ጨርሶ አርቆ ቆፍሮ እንደሚቀብረን እርግጠኛ ነኝ፡፡ በቆየ የአጎብዳጅነት ባህሪያችን ህዝቡ በማንም ውርጋጥ እንዲሰደብ አድርገነዋል፡፡ እውነት እንነጋገር ከተባለ ከሽመልስ በላይ የአማራ ህዝብ ዋና ጠላቶቹ እኛው ነን፡፡ ስለዚህ በበኩሌ አብይ አሕመድ ወይ ሽመልስን ወይ እኛን መምረጥ አለበት" #አቶ_ላቀ_አያሌው

" ለምን ችግሩ የሽመልስ ብቻ እናደርገዋለን፡፡ አብይ ከጎኑ ተቀምጦ እኮ ነው ሽመልስ እንዲህ የሚያቅራራው፡፡ የሽመልስ ንግግር የፓርቲው ንግግር አድርገን ነው መውሰድ ያለብን፡፡ ተደብቀው የጨረሱት ነገር የፖርቲው ሌሎች አመራሮች እማይቀበሉት ቢሆን ኖሮ ለምን በሰዓቱ እርምት ወስደው ለኛ በጓዳዊ መንፈስ አልነገሩንም፡፡ ከዚህ በፊትም ባሌ ላይ ተመሳሳይ ነገር በከፍተኛ አመራር ሲነገር ሰምተናል፡፡ እራሱ ሽመልስ 'ነፍጠኞችን ሰብረናቸዋል' ብሏል፡፡ የለማ የዴሞግራፊ ቅየራ ልፈፋም የቅርብ ትዝታችን ነው፡፡ ለዚህም ነው ችግሩ የሽመልስ ሳይሆን የድርጅቱ ነው የምለው፡፡ እኛም መገምገም ያለብን ድርጅቱን ነው፡፡ ሰዎቹ እኛን የሚቆጥሩን እንደ ጓድ ነው ወይስ እንደ መጠቀምያ? ግንኙነታችንስ የእኩልነት ነው ወይስ የአለቃና ምንዝር? ሲጀመርስ ኢህአዴግ ሲፈርስና ብልፅግና ሲቋቋም ዘለን የገባነው የግል ስልጣን እንዳናጣ ብለን ነው ወይስ ለህዝባችን ጥቅም አለው ብለን ነው? ሲፈነጩብን ዝም ያልነው ሳይገባን ቀርቶ ነው ወይስ እንደተባለው ማጎብደድ ቋሚ ባህሪያችን ስለሆነ ነው? የአማራ ህዝብ በየቀኑ እያዋረድነው እስከ መቼ የሚታገሰን ይመስላቹሃል? እነዚህን ሳንመልስ ስብሰባው ሽመልስ ላይ ጀምረን ሽመልስ ላይ መጨረስ ራስን ማሞኘት ነው፡፡" #አቶ_አብረሃም

Videos From Around The World

ከባድ ዝምታ፥ አንገት ደፍቶ ማቀርቀር፥ ማንም የማንም ዓይን ቀና ብሎ ለማየት የማይቻልበት የውርዴት ስብሰባ

ንጉሱ ጥላሁን ቀጠለ

" ይገምገም በተባለው በግሌ እስማማለሁ፡፡ እንደሚመስለኝ ግን በጣም ጥንቃቄ ማድረግ አለብን፡፡ አጠገባችን ያለው ህወሃት ሊወረን ዝግጁቱ ጨርሷል፡፡ በተጨማሪ ደግሞ ብዙ የአማራ ህዝብ በኦሮምያ ውስጥ ይኖራል፡፡ ለዚህም ነው ከኦሮሞ አመራር ጋር ላለመጣላት መጠንቀቅ ያለብን፡፡ በዚህ ሰዓት የፌደራል መንግስት ካለኛ ድጋፍ አንዲት ቀንም ማደር አይችልም፡፡ እኛም ካለ ፌዴራል መንግስ ምንም መሄጃ የለንም፡፡ እውነቱን እንቀበል፡፡ አብይም ይህን ያውቃል፡፡ እንደሚመስለኝ እኛ አብይን 'ሽመልስ ይቅርታ ጠይቆ ከስልጣኑ ይውረድልን' ብለን ብንጠይቀው ለመመለስ አይቸገርም፡፡ በተጨማሪም ለአማርኛ ቋንቋ የሆነ ለየት ያለ ፈንድ እንዲበጅትና የአዲስ አበባ ጉዳይም እኛ ዋና ተዋናይ እምንሆንበት ሁኔታ እንዲያመቻች እኔና አቶ ተመስገን አብይን ማግባባት እንችላለን፡፡ ድርጅቱን ገምግመን የት እንደርሳለን። ገምግመን ለውስጥ ጥቅም መያዝ አንድ ነገር ነው፡፡ አሁን ግን ይፋ የምናደርገው እውነተኛ ገምጋም አይኑር ባይ ነኝ፡፡ ምክንያቱም አቶ አብርሃም የጠየቃቸው ጥያቄዎች ብንመልስ መልሱ ግልፅ ስለሆነ፡፡ ስለዚህ ለግዜው ብልጥ መሆን አለብን ባይ ነኝ፡፡ የህዝባችን የተሰበረው ወገብ በቂ የ PR ስራ ሰርተን እንጠግነዋለን፡፡ የምንፈልገው ነገር 1. 2. 3. ብለን በአብይ በኩል ማስፈፀም ስለምንችል በስሜት ወደ ግጭት አንግባ ባይ ነኝ፡፡ የሚደላደል ነገር እስኪደላደል አካሄዳችን የእርቅ ቢመስል መልካም ነው ባይ ነኝ ::" ብሎ #ንጉሱ_ጥላሁን ንግግሩን ጨረሰ፡፡

ቀጥሎ እድል ያገኘው አቶ #ላቀ_አያሌው ነው

" የምን እርቅ ነው? የምን መለሳለስ ነው? ባህርዳር ድረስ ሂደን ምን እንዳደረግናቸው እናውቃለን ነው እኮ የተባልነው፡፡ እኔ እኮ ግድያውን በአይኔ በብረቱ ያየሁ ሰው ነኝ፡፡ ግማሹን አግባብተን ግማሹን ግራ አጋብተን ነው የኛ ባርያና አሽከር ያደረግናቸው የተባልነው፡፡ አማራንና አማርኛን ላይነሳ ገድለነዋል፡፡ ብልፅግና የመሰረትነው እራሳችንን ከስልጣን እንዳንወርድ ለማድረግ ነው እኮ ነው የተባለው፡፡ ይህ ምን ማለት ነው? የአማራ ክልል አመራር ከተላላኪነትም በላይ የራሱን ህዝብ እያታለለ ቋንቋውን የሚያስገድል፥ ህዝቡን የሚያስጠቃ የባዕድ ፓርቲ የሚያገለግል፥ ዘላለሙ የሌሎች መሳርያ ነው ማለት እኮ ነው፡፡ ትክክለኛ አካሄዱ አብርሃም ያስቀመጠው ነው፡፡ በዝርዝር ገምግመን መቀጠል ካለብን በነፃነትና በእኩልነት አብረን እንቀጥላለን፤ ግምገማችን መቀጠል የለብንም የሚያስብል ከሆነ ደግሞ በግልፅ እንወስናለን፡፡ እርቅ፥ ግዝያዊ ጥቅም የሚባሉ ነገሮች የፍርሃት ምልክቶች ናቸው፡፡ ሲጀመር በአብይ በኩል ፍላጎታችን ማሳካት እንችላለን ማለት 'እኛ የሞትን ነን፥ በራሳችን አቅም ምንም ማድረግ አንችልም፥ ተለጣፊ ነን' ማለት ነው፡፡ ስለዚህ መቅደም ያለበት ግንኙነታችን በድርጅት ደረጃ፥ ቀጥሎም በአመራር ደረጃ ገምግመን ያለንበት ሁኔታ ማስቀመጥ ነው ያለብን" ብሎ ላቀ አያሌው አብርሃም የሰጠውን እርምት ተቀብሎ ንግግሩን በቁጨሸት ዘጋ፡፡

#ማጠቃለያ

ውይይቱ ሲጨመቅ በሚከተሉት ርእሶች ላይ ነው ያጠነጠነው፡፡ እየተሰደብንም ቢሆን፥ እንደ ተላላኪ እየተቆጠርንም ቢሆን ለግዜው ህዝባዊ ድጋፍ፥ ድርጅታዊ አቅምና መሸሸግያ ስለሌለን የሽመልስን ነገር በእርቅና በይቅርታ እንለፈው የሚለው የነ ንጉሱ ጥላሁን፥ ደመቀ መኮነንና አቶ ተመስገን ጥሩነህ ጎራ በአንድ ወገን ሲሆን፤ እየተደረገ ያለው ነገር በእርቅ፥ በይቅርታ እንለፈው ማለት ተምበርካኪነት ነው፤ ማድረግ ያለብን ዝርዝር ግምገማ አድርገን እራሳችንን ከተለጣፊነት ማዳን አለብን የሚለው የነ አብርሃም፥ ተፈራ ወንድማገኝና የነ ላቀ ቡድን ነው፡፡ አሸናፊው ጎራ ግዜ እስኪነግረን እንታገስ በልልኝ"

የጉድ አገር!

 

 

Source = https://www.facebook.com/nahusenayb/posts/3782182398464973


Back to Front Page