Back to Front Page

አብይ እጀ ቆራጣ ኢትዮጵያ ሊመርቃት መጣ

 

አለም ወርቂ 06-12-20

 

ድሮ በጎንደር ኣካባቢ ቤተ እስራኤሎች ሰው ይበላሉ፡ ይገድላሉ፡ ቡዳ ናቸው ወዘተ እየተባሉ ብዙ መከራ ይቀበሉ ነበር። ታድያ አንድ ጊዜ ከቤተ እስራኤሎች ወገን ሰው ይሞትና ቤተ እስራኤሎቹ ደግሞ እንዲህ በማለት ይገጥማሉ፥

የእናንተውስ እኛ የኛ ማን ገደለው

እግዚኣብሄር ነው እንጂ የሚያዳልድለው ኣሉ ይባላል።

 

በኢህኣደግ ዘመንና በኋላ ጨቋኙ፡ በዥባዡ ወዘተ ህወሓት ብቻ ነው እየተባለ አሁንም እንደተወገዘ ነው። እውነት እሱ ብቻ ግፍ ፈጻሚ ከነበረ አሁን የሚሞተውና የሚገድለው ወገን በማን እጅ ነው ተብሎ ቢጠየቅ መልሱ ኣሁንም ወያኔ በስተጀርባ ኣለበት ነው በብልጽግና መሪዎች ኣንደበት። በውነቱ በስልጣን ያለው ቡዱን የያልተገረዙ ሰዎች ስብስብ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። በማስመሰልና በመዋሸት ስልጣን ማስቀጠል የሚፈልግና አገርም ቢሆን ሽጦ በስልጣን መቆየት የሚመርጥ ድርጅት ነው የአብይ መንግስት።በስልጣን ላይ መቆየት መፈለግ ሌላ ሁኖ ያገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ ግን ይህንኑ የሚፈቅድ ኣይመስልም።ከመጪው መስከረም ወርበኋላ የሚለይለት ይመስላል።

ሌላው ትናንትና አገር ተበተነች፡ የህዝቡ መብት ተገፏል ብለው ሲያላዝኑ የነበሩ ፖለቲከኞች ዛሬ ስልጣና ጥቅም ሲያገኙ ዝምታን መርጠዋል። በነሱ እይታ ኣሁን ሰው ኣይገደልም፡ የመብት ጥሰት የለም ነው። እነሱ ስለተመቻቸው አገር አማን ብለው ለማሳመን ይሞክራሉ። የኔ ሙግት በዘመነ ኢህኣደግችግር ኣልነበረም ማለቴ ሳይሆን ግን ድሮ ሲያወግዙት የነበረ ፍጻሜ/ተግባር ኣሁንም በከፋ መልኩ የሰብአዊ መብት ጥሰት እየቀጠለ ይገኛል። እና ምነው እንደቀድሞው ደንፊ ጠፋ ያስብላል። መልሱ ቀላል ነው።ብግልጽ ቋንቋ እንኳን ትግሬ/ወያኔን ከስልጣን ኣባረርን እንጂ ሌላ እዳው ገብስ ነው የተባለ ይመስላል። በዚሁ ስሌት የምትቀጥል ሃገር ካለች እናያለን።

Videos From Around The World

የፖለተኮኞቻችን ግብዝነት ለከት የለውም። በምሳሌ እንየው፡

ኣቶ ኣንዳርጋቸው ጽጌ፥

የረጅም ጊዜ የፖለቲካ ሰው ናቸው።አንዴ በኢሳት ሚድያ ቀርበው በኤርትራው መሪ አካባቢ ያላቸው እይታ የተነሳው ጥያቄ ሲመልሱ እንዲህ የሚል እድምታ ያለው መልስ ሰጥተዋል።

 

የኤርትራው መሪ በሙስና የማይታማ፡ ሰንደል ጫማ ለባሽ፡ ልጆቹ እንደማንኛውም ኤርትራዊ ለብሄራዊ ውትድርና ስልጠና ወደ ሳዋ የሚልክና ተራ ኑሮ የሚኖር ኣርገው ሲያቀርቡት ሰምቼ ከልብ ነው ያዘንኩት።

አቶ አንዳርጋቸው በዚሁ ጉዳይ ልክ እንደ ኤሳው ቡክርናቸው በጥቅም ሽጥዋል የሚል እምነት አለኝ።

 

አቶ አንዳርጋቸው! ወደ የኤርትራ መሪ የግል ስብዕና ሳልገባ በየወሩ በሺዎች የሚቆጠሩ የኤርትራ ዜጎች አገራቸው ለቀው የሚወጡት ለሽርሽር ይመስሎዎታል?የህዝቡ ፍልሰት የስርዓቱ አስከፊነት ኣይገልጽም ይላሉ? ለመሆኑ የኤርትራው መሪ በጥሩ ነገር ማለትም በልማት፣ በሰላም ወይም በዲሞክራሲ ታምቶ ያውቃል?ከወጣትነት እድሜዬ ጀምሮ ለህዝብ መብት ታግያለሁ የሚል ሰው እውነት ካልደፈረ አዲሱ ትውልድ እንግዲህ ከቀደምቱ ሰዎች ምን ይማር? ባጭሩኢህኣደግን የወቀሰ/የተቃወመ ሰው የኤርትራው መሪ ሊያወድስ በፍጹም ኣይችልም!። በዚሁ ስሌት እሳቸው ኢህአደግን የሚቃመሙት የነበረው በትግራይ ሰው ለምን ተመራን ከሚል ውጭ ሌላ ትርጉም የለውም። እና እንዲህ ኣይነት ግብዝ ኣቋምና ሸውራራ ኣመለካከት ያላቸው ልሂቃን ናቸው እንግዲህ ኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ አመጣን ብለው የሚኩራሩት፣ በየአደባባዩ የሚደሰኩሩት። እውነት ለመናገር ባገሪቱ ለውጥ ሳይሆን የመጣው ሌላ ኣዲስ የፖለቲካ ኣዙሪት ማለትም አገር የሚንድ፣ ህዝብ የሚለያይና ለከፋ መናቆር መንገድ የሚከፍት ነው ለውጡ ይዞ ብቅ ያለው።ኢህኣደግ እባክህ ናልን የሚባልበት ጊዜ እየመጣ ነው ያስብላል። እዚህ ላይ ግልጽ ለማድረግ ኢህአደግ የተዋጣለት መንግስት ነበር ለማለት አይደለም። ለማለት የተፈለገው ኢህአደግ ከነችግሩ ኣስፈላጊ [necessary evil] ነበር ለማለት ነው።

 

የኢትዮጵያ ፖለቲካ እንደ አጃ ዘር ነው

 

በኛ ኣገር አንድ ብሂል ኣለ። ኣጃ ወቅጠው ቢዘሩት ተመልሶ ወደ ዘሩ ገባ ይባላል። ያው ዙሮ ወደነበረበት መመለሱ የሚገልጽ ነው።ያገራችን ፖለቲካም ከዚሁ የተለየ ኣይደለም። የኛ ፖለቲካ እንደ ሽንፍላ ታጥቦ የማይጠራ፣ሰልጥኖ የማይሰለጥን፥ በቂምና ቁርሾ የተበተበ/ቅይድ ነው። ለዚህ ይመስላል በትግራይ አካባቢ አዲስ አገር የመሆን አጀንዳ ብቅ ያለው። ድሮ ሰምቸው የማላውቅ ስሜት ነው። የኢትዮጵያዊነት መንፈስ ከትግራይ ልጆች ህሊናና ልብ እየሸሸች ነው። ኢትዮጵያ የምትባል ሃገር ለትግራይ ህዝብ ምን ጠመቀች ይላሉ። የትግራይን ህዝብ ለኢትዮጵያ መኖር የከፈለውን ዋጋ እውቅና/ክብር የማትሰጥ ኢትዮጵያ ምናችን ናት ብለው በቁጭት ይናገራሉ። የመሃል አገር መንግስታት ከሚኒልክ ጀምሮ የትግራይን ህዝብ ለኢትዮጵያ የዋለው ውለታ ከከንፈር የዘለለ ቦታ አይሰጡትም የሚል መከራከርያ ነጥብ ያነሳሉ። የማግለል መንፈስ ሁሌ ይታይበታል ብለው ያምናሉ። የአብይ መንግስትም ከነበረው የድሮ ስርአት የተለየ ስሜት የለውም ብለው ያምናሉ። እድምታው ለኢትዮጵያ ደግሞ ደጋግሞ መስዋእት መከፈል ውጤት የለውም። አልበርት አነስታይን እንዳለው- እብደት ማለት አንድ ነገር ደጋግሞ ማድረግና የየተለየ ውጤት መጠበቅ ነው እንዳለው። ሌላ የሚያዋጣን ብንሞክር ይሻላል ነው መልእክታቸው።

ቶሎ መፍትሄ ካልተበጀለት ለወደፊቱ ይህን ሃሳብ የሚያራምዱ በህዝቡ ተቀባይነታቸው እየጎላ እንደሜሄድ ግልጽ ነው።

 

አዲስ መንግስት ሲመጣ ማወደስ ሲቆይ ደግሞ መውቀስ ባህላችን ነው። ኢትዮጵያውያን ነገሮችን በትክክል የመመዘን ችግር አለብን። ሌላው ምሁሩ የሚያነሳው ስለ ዲሞክራሲ ጥያቄና ሌላው ተዛማጅ ጉዳዮች ካገሪቱ ተጨባጭ ጋር ይሄዳል ማለት አስቸጋሪ ነው። ዲሞክራሲ ደሞክራሲ የሚለው ጋጋታ በሁሉም ፖለቲከኛ ሲነሳ ይሰማል። በምእራቡ አለም ስለተነገረለት ለኛ ይጠቅማል? እኛ የራሳችን ታሪክና ባህል ያለን ህዝብ ነን። ላገራችን የሚበጀን ደግሞ እኛነታችን ግምት ውስጥ ያስገባ ስርዓተ መንግስት መገንባት እንጂ ሌላ ሊሆን አይችልም።

ግብዝ ምሁራን አብይን ሳያዩት አንዱ ሙሴ ነው ሌላው ኣምላክ ነው የላከው ሲሉ ሰምተናል። እውነታው ግን

የብልጽግና ሰዎች ትናትና ኣሳሪዎችና ገራፊዎች እንዲሁም ዘራፊዎች ነበሩ። ዛሬም የትናትናው ነውራቸው እንደጌጥ በመቁጠርኣጠናክረው ቀጥለውበታል።

 

እኛ በምድረ ኣፍሪቃ ምድር የምንገኝ ማህበረሰብ ነን። ባመት ልብስ የማይቀይርና በቀን የእለት ጉርስ የማያገኝ ህዝብ ያለን ኣገር ነን። ይህንን የተገንዘበና የገባው ብቻ ነው ኢትዮጵያ መምራት የሚችለው። ኢህኣደግ ከነጉድለቱ ይህንኑ የተገነዘበ ነበር። ባገሪቱም ተጨባጭ ለውጥ ኣምጥተዋል። ይህ እውነታ በስልጣን ፈላጊዎች ጩኸት ፍጹም ሊቀበር አይችልም።ይህ ማለት ኢህአደግን የመውደድ/የመደገፍ ኣይደለምነገሩ። እውነት ስለሆነ ነው ይህንኑ ያልኩት። ካለው ያገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ ሳየው ከነሱ የተሻለ ድርጅት ኣላይም ነው። የዲሞክራሲ ጩኸት ለድሃው ምኑ ነው? መሰረታዊ ፍላጎት ባልተማላበት ኣገር ባዲስ ኣበባ ህዝብ ብቻ ኢትዮጵያን የምናስባት ከሆነ ስህተት ነው። ወረቀት ስለተጻፈ ስለተነገረ ለገበሬው ምኑ ነው? ምርጥ ዘርና ማዳበርያ ላገሬው ገብሬ መሰረታዊ ችግሩን ይቀርፍለታል።

 

የትግራይ ህዝብና ህወሓት

ባገራችን ባህል የተሻለ ሰርቶ ማሳየት ሳይሆን የሰራውንና የተሰራውን ማብጠልጠል ሚዛኑ የደፋ ነው። የኢትዮጵያ ልሂቃን የተሻለ ነገር ያበረከቱ/ የፈጠሩ ይመስል የትግራይን ህዝብና ድርጅቱ መኮነን ስራዬ ብለው ከያዙት ውለው አድረዋል። ተወደደም ተጠላም በኢትዮጵያ ምድር ያሰበውን በመስዋእትነት ያረጋገጠ ቢኖር ህወሓት ብቻ ነው። ስልጣን ላይ እያለም አገሪቱ ለዘመናት ለብሳው የነበረ የድህነት ብቱቶ በማውለቅ የልማትና የፈጣን እድገት ተምሳሌት እንድትሆንና ባለም ፊት ክብር እንድታገኝ አርግዋታል ወያኔ።

 

አሁን ወያኔ ወደ ስልጣን መመለስ የለበትም የሚሉ ሞኞች ብዙ ናቸው። ድሮስ ፈቅዶ ለወያኔ ስልጣን የባረከለት ጳጳስ/ቄስ አለ እንዴ? ህወሕት ለ27 አመታት ስልጣን ላይ የቆየውም በጥንካሬው እንጂ ማንም ስለወደደው አይደለም። ለወደፊትም ወደስልጣን የሚመለስ ከሆነ ማንም በወርቅ ሳህን የሚያቀርብለት ሳይሆን በችሎታው ነው። በዚህች ምድር የማድረግ ችሎታ ካለህ እንኳንስ ወደ ስልጣን መምጣት ይቅርና ወደ ጨረቃም ለመሄድም ተችለዋል። ምስጢሩ ያለውበመቻል ወይም በአለመቻል ጉዳይ ነው። አበቃ! ሃያላን መንግስታት የፈለጉትን የሚፈጽሙት እኮ አቅምና ችሎታ ስላላቸው ነው እንጂ ሌላ ምስጢር የለውም።

 

ብዙ የመሃል ኣገር ሰዎች ለምንድነው የትግራይ ህዝብ ወያኔን ለመጣል ለምን ብዙ ሲታገል ኣይታይም ብለው ይከሱታል። ያልገባቸው ግን ማንን ለማምጣት ነው ህዝቡ ልጆቹን የሚያባርረው ነው? ብልጽግና ወይስ ግንቦት 7? የመጡት መሪዎችዋ በሁለት ካራ የሚበሉ ሁነው ተገኙ።አገርም ቢሆን ኣጥፍተው መኖር የሚፈልጉ አጋስስ ናቸው ያሁኑ የቤተመንግስት ሰዎች።ይባስ ብለውም ኢሳያስን የሚያወድሱ ግን ለውጥና ሃብት ባገሪቱ ያመጣው ህወሕት ደግሞ እንደ ጭራቅ የሚቆጥሩ ናቸው እንግዲህ ያገሪቱ መሪዎች። እና የትግራይ ህዝብ የተሻለ ድርጅትና መሪ ባገሪቱ እስካልመጣ ድረስ በስሜት ይደግፈናል ብለው የሚያስቡ ካሉ ህዝቡን አለማወቅ ነው። ይህ ማለት ግንህወሕት የሚሰራው የማይደገፍ ከሆነ ዝም ይላል ማለት እንዳልሆነ መረዳት አለብን። የትግራይ ድጋፍ የሚፈልግ ድርጅት ካለ ከሌሎች ድርጅቶች ተሽሎ መገኘት ኣለበት። የትግራይን ህዝብ ልብ ማግኘት የሚቻለው በተጠቀሰው መንገድ ብቻ ነው።

 

በመጨረሻም በእጥፍ ወያኔ ይሻላል! የትግራይ ህዝብም ከልጆቹ ጐን መቆሙ ኣልተሳሳተም እላለሁ። ሌላው መታወቅ ያለበት ግን የትግራይ ህዝብ ማተብ እንጂ ዘር ኣይገዛውም ኣሁንም ወደፊትም። የተሻለ ከመጣ እሱን ሁላችን እንደምንደግፍ መታወቅ ኣለበት።

 

አብይ የትግራይ ህዝብ ቀንደኛ ጠላት ነው

 

በማያሻማ ሁኔታ ኣብይ እኮ የትግራይ ህዝብ ጠላት መሆኑን በስራው አሳይቶናል፣ በቃሉም ነግሮናል።

አደገኛ የትግራዋይ ጠላት መሆኑን ማንም የትግራይ ተወላጅ መጠራጠር የለበትም!!!

መገለጫው ምንድነው ብለው ለሚጠይቁ መልሱ የሚከተለው ነው።

 

1.  27 አመት ጨለማ ነበር ማለትኮ የተሰራው መልካም ነገርም ቢኖር የትግራይ ሰዎች ስለሰሩት እርኩስ ነው ለማለት ነው።

2.  ብ27ቱ አመታት ግፍ ፈጻሚዎች የትግራይ ልጆች ብቻ ነበሩ ብሎ በሚድያ አውታሮች የውሸት ትርክት ማስተጋባት ማለት ሌላው ወገን በትግራዋይ ላይ እንዲነሳና የዘር ጦርነት እንዲነሳ የሚችለው ሁሉ አርጓል።

 

የተናገረውና የሰራው በጥቅሉ ስናየው የትግራይ ህዝብ ኣኩሪ ገድልና ለኢትዮጵያ ህዝብ የዋለው ውለታና ደማቅ ታሪኩ አጥፍቶ ሁለተኛ እንዳይነሳ ማድረግ ነው ዋና አላማው።

 

ባጭሩ ታሪክህና እሴትህ እንዲሁም የከፈልከው መስዋእት እርኩስ ነው የሚልህ መሪ እንዴት ጠላት ኣይሆንም ጃል!።

አብይ አሁን የሚችለውን ሁሉ ካደረገ በኋላና ማጠፍያ ሲያጥርበት በስብሰባ ትግራይን ለማወደስ ቢሞክር መልሳችን ለማያውቅሽ ታጠኚ ነው።

አንድ እርገጠኛ ሁኜ የምትነብየው ቢኖር ኣብይ እንደ ነድ ራሱ ነዶ ያልቃል።

 

ለትግራይ ህዝብ ያለኝ ምክር ይህ ነው

በክርስትና ሃይማኖት የሚጠቀስ ታሪክ ኣለ። እሱም ስለ ሳጥናኤል ነው።

ሳጥናኤል የፈጣሪንአምላክነት በመካድ ራሱ ፈጣሪ መሆኑንና ለሱ ብቻ እንዲያመልኩ ለመላእክት ነገራቸው ። ቅዱስ ገብርኤል የሚከተለው ብሎ መለሰ ይባላል።

 

ንቁም በበህላዌኔ እስከ ነኣምር ፈጣሪነ ፈጣርያችንን እስከ ምንለይ ድረስ ባለንበት እንጽና የሚል ነው። የትግራይ ህዝብም ይህንኑ የቅዱስ ገብርኤል መመርያ ነው መከተል ያለበት ይመስለኛል። በኢትዮጵያ ምድር የተሻለ ነገር እስኪመጣ ከድርጅትህ ጋር ሁነህና መታረም የሚገባቸውንም ሳትዘነጋ ወደ ፊት መጓዝ ነው አሁን ያለህ ምርጫ!

 

በትግራይ ላሉ ተቃዋሚ ድርጅቶችም ምክር አለኝ

 

ማንም የትግራይ ሰው የሚመስለው አቋም ማራመድ መብቱ ነው። ይህ እንደተጠበቀ ሁኖ ግን ብልጽግናን ትቶ ወያኔ ብቻ የሚቃወሙ ድርጅቶች ግን የጤና አይመስልም። የመርህ ጉዳይ ከሆነ የአብይ ይሁን የህወሓት ላይ የሚታይ ጉድለት ማውገዝና መናገር ተገቢ ነው። በግል ቁርሾ ብቻ ፖለቲካን ማራመድ ግን የፖለቲከኛን ቀሚስ ያሳጣል። የሞራልና የ መርህም ጥያቄም በታዛቢው ወገን ያስነሳል እላለሁ።

 

የብልጽግና አላማ ትግራይን ለማዳከምና ለማንበርከክ ከኢሳያስ ጋር እየሰራ ለመሆኑ ጥርጥር የለውም። እና ይህንኑ የማይገባው የትግራይ ፖለቲከኛ ካለ ራሱን ይመርምር።

 

ትግራይ ነጻ መውጣት አለባት የሚሉ ሰዎች እውነት ለትግራይ አዝነው ወይ መልካም አስበው ሳይሆን ውስጠ ወይራው ህዝቡን እንዴት እንከፋፍለው ነው። ይህንኑ ለማረጋገጥ እኮ ሩቅ መሄድ አያስፈልግም። የግንቦት ሰባት መሪዎች ትናትና ምን ይሉን ነበር አሁን በተግባር እየሰሩት ያሉት ምንድነው ብሎ ማየት ያስፈልጋል። ኣብይ በኦሮምያና በሌሎች ክልሎች የሚያደረገው ጭፍጨፋ/አረመንያዊ ተግባር አንድ ቃል ትንፍሽ ብለው አያውቁም። ምነው ቢባል የሰው መብት ተደፈጠጠ ወይም ተጣሰ አይደለም ጉዳያቸው። አላማቸው እንዴት ያለውን ህገመንግስትና ፈደራላዊ ስርአት አፍርሰን ተደላድለን እንኑር ነው።ለዚህ ነው አብይና ግንቦት ሰባትእጅ ለጅ ተያይዘው እመረሹ ያሉት።

 

አንድነት ክታብ አይደለም

ያገር ኣንድነት ለዘላለም የሚታሰር ጌጥ ወይም ክታብ አይደለም። ለሁላችን ከጠቀመን እንይዘዋለን ላንድ ወገን ብቻ የሚያገለግል ከሆነ ደግሞ አውልቀን እንወረውረዋለን። በስመ አንድነት ከእንግዲህ የሚታለል ወገን የለም።ድሮ ያንድነት ሃይሎች የሚመስሉን የነበሩ ኣሁን ጥቅም ሲያገኙ ዳግማይ ይሁዳ ሆነው ቁጭ ብለዋል። የነሱ አንድነት የምር ሳይሆን ወደ ስልጣንና ግላዊ ጥቅም የሚወጡበት እርካብ ሁኖ ነው ያገኘነው። አንድነት እንዲኖር በእኩልነትና በመከባበር የሚያኖረን ተቅዋማዊ የሆነ ስርአትና ህግ መፍጠር መቻል አለብን። በኢትዮጵያ ምድር ከእንግዲህ የእኩልነትና መከባበር አገር እንጂ አንዱ የሚያፍርባት ሌላው አንገቱን ቀና አድርጎ የፈለገውን የሚፈጽምባት ምድር አትሆንም። ከእንግዲህ ለጭቆናና መድልዎ አገራችን ጀርባ እንደሌላት መታወቅ አለበት።

ባገሪቱ ያለው ዘርፈ ብዙ ቀውስ ተመልክተን አብይ እጀ ቆረጣ ኢትዮጵያ ሊመርቃት መጣ ያስብላል!

ቸር ያሰማን!

 


Back to Front Page