Back to Front Page

የአብዪ አሕመድና ኢሳያስ አፈውርቂ የሰሙኑ ግንኙነት እንድምታውና ቀጣዩ የትግል አቅጣጫ።

የአብዪ አሕመድና ኢሳያስ አፈውርቂ የሰሙኑ ግንኙነት  እንድምታውና ቀጣዩ የትግል አቅጣጫ።

ብርሃን ንርአ

27/05/2012ዓ/ም

brhannrae@gmail.com

የአራት ኪሎ ጠቅላይ ሚኒስተር አብዪ አሕመድና የኤርትራው ፕረዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የተላያዩ ምክንያቶች በመጠቀም ሲገናኙ መክረማቸው የተላያዩ ብዙሃን መገናኛና ማህበራዊ ሚድያዎች ዘግበውታል።ይህ ግንኙነትም የተለያየ ትርጉም ተሰጥቶበታል።በትግራይ የሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች ወደሌላ የኢትዮጵያ ክልል በማዛወርና ስደተኞቹ ለኤርትራ መንግስት ተላልፈው እንዲሰጡ ለማድረግ ተስማምተዋል የሚል ግምት አለ።ከዚህ በተጨማሪም አብዩ ምርጫ ለማካሄድ ዝጉጁ አይደለም የኦሮሞ ፈደራሊስት ሃይሎችና ህወሓት እንደፓርቲ በማገድ የሓይል እርምጃ ለመውሰድ ያስባል ስለዚህ የኤርትራ መንግስት ድጋፍ ጠይቀዋል የሚሉ መላምቶቹም አሉ።ከዚህ መላምት የሚገናኝ አብዪ ለኤርትራ እንዲሰጡ ተወስነዋል የሚባሉት የኢትዮጵያ መሬቶች ኤርትራ ገብታ እንድትይዛቸው ተስማምተዋል፤ከዚህ ተግባር ጎን ለጎን የአማራ ክልል መንግስትም ወልቃይት እና ራያ የኔ ነው በማለት አካባቢዎቹ ለመቆጣጠር ዝግጅት አድርገዋልም እየተባለ ነው።በእነዚህ የተቀናጁ እንቅስቃሴዎች የትግራይ ህዝብና መሪ ድርጅቱ ህወሓትን ጨፍልቆ ለማምበርከክ አቅደዋል የሚልግምትም አለ።ይህ በእንዲህ እንዳለ ኤርትራ ለኔ ተወስነዋል የምትላቸውን የኢትዮጵያ መሬቶች ወደራስዋ የማስገባት ጉዳይ ትግራይ ውስጥ ያለው ሰራዊትና ጦር መሳርያ በኤርትራ በኩል ለማስወጣት ይጠቀሙበት ይሆናል የሚል አስተያየትም እየተሰጠ ነው።ከዓፋር ክልል ወደ ትግራይ የሚገቡ መንገዶች ለመዝጋትም ሸርበዋል የሚልም እየተነገረ ነው።

ከላይ የተጠቀሱትን መላምቶች አጣቃላይ ይዘታቸው ስንመለከት  የትግራይ ህዝብና መሪ ድርጅቱህወሓት ለማምበርከክ በጥብቅ መምከራቸው የሚያመላክቱ ናቸው።

Videos From Around The World

መደምድምያው አብዪና ኢሳያስ የትግራይ ህዝብና መሪ ድርጅቱ ህወሓት ለመጨፍለቅ ማሴራቸው እርግጥ ከሆነ የትግል ኣቅጣጫው ምን መምሰል ኣለበት የሚል ጥያቄ መቅረቡ የግድ ነው።ቀጥለን የትግል ኣቅጣጫ ምን መምሰል እንዳለበት ወደ ማየቱ እንሸጋገር።

1.የትግራይ ህዝብና መሪ ድርጅቱ ህወሓት

የትግራይ ህዝብና መሪ ድርጅቱ ህወሓት ሁለገብ ዝግጅት ማድረግ አለባቸው።የትግራይ ህዝብና መሪ ድርጅቱ ህወሓት ከመቸውም ጊዜ በበለጠ ዲሞክራስያዊ አንድነታቸው መጠናከር ይኖርበታል።የመጀመርያና የመጨረሻ እቅዳቸው ዘላቂ ሰላምና ደህንነት ማረጋገጥ መሆን አለበት።ማንኛውም እቅድ ወይም እንቅስቃሴ ለዘላቂ ሰላምና ደህንነት ተገዥ መሆን አለበት።ህዝቡ ከድህነት ለመውጣት፣ጠንከራ ዲሞክራስያዊ ስርዓት ግንባታ፣መልካም አስተዳደር ለማስፈን የሚካሄደው ትግል ለዘላቂ ሰላምና ደህንነት ባለው ፋይዳ መቃኘት አለባቸው።

ከዚህ በተጨማሪ የትግራይ ህዝብና መንግስት ትግራይ ውስጥ ካለው የኢትዮጵያ መከለከያ ሰራዊት በጥብቅ ግንኙነት በጋራ መስራት ይጠበቅባቸዋል።ትግራይ ውስጥ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሰራዊት ህዝባዊ ውግናውን ያረጋገጠ ሰራዊት ነው የሚል ይነገርለታል።ትግራይ ውስጥ የሚገኝ ሰራዊት ትጥቁን ጭኖ ለመውጣት በተንቀሳቀሰበት ወቅት እኛን ትታቹሁ የት ነው የምትሄዱት ብሎ በተቃወመበት ወቅት አንድም ወታደር በህዝብ ላይ ኣንድም ጥይት አልተኮሰም።የህዝቡ ጥያቄ ትክክለኛነቱን አምኖ ወደ መጣበት ቦታ በሰላማዊ መንገድ ነው የተመለሰው።አብዪ አሕመድ የሰራዊት መሪዎቸ በማቀያየር ከትግራይ ህዝብ ለማጋጨት ቢሞክርም አልተሳከለትም።ትግራይ ውስጥ ያለው የኢትዮጵያ መከለካያ ሰራዊት ህዝብ ላይ ጥይት የመተኮስ ፍላጎትም ዓላማም የለውም።ከእነደዚሁ ዓይነት ሰራዊት ለዘላቂ ሰላምና ደህንነት መረጋገጥ ተባብረህ መስራት ተገቢ ነው።

ትግራይ ውስጥ ያለውን የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጦርነት ወደአለባቸው ሌሎች የኢትዮጵያ ክልሎች በመንቀሳቀስም ህዝብን ለመውጋት ዓላማም ፍለጎትም የለውም።በነዚህ ሁለት ምክንያቶች አብዪ ከትግራይ ውጭ እንዲንቀሰቀስ ከወሰነና የግድ መንቀሳቀስ እንዳለበት ከተገነዘበ እንዲሁም የአገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ሰራዊቱን ለቆ የሚወጣ ወታደር ሊኖር ይችላል ተብሎ ይገመታል።ሰራዊቱን ለቆ የሚወጣ ወታደር ሁለት አመራጨች ሊኖሩት ይችላሉ።አንደኛ ከትግራይ ህዝብ ጋር በፈጠረው ማህበራዊ ግንኙነት ምክንያት ውትድርናውን ትቶ ትግራይ ውስጥ ለሞኖር ይፈልግ ይሆናል።ሁለተኛው ወደ ትውልድ ክልሉ ለመሄድ ይፈልግ ይሆናል።በዚህ ምክንያት በራሳቸው ፍላጎት መከለካያ ሰራዊቱን ለቀው ለሚወጡ ወታደሮች የትግራይ ህዝብና መንግስት ትግራይ ውስጥ ለመኖር ለወሰኑት እንደ የትግራይ ክልል ነዋሪዎች በማየት የትግራይን ህዝብ የሚያገኘውን መብትና ጥቅም እንዲከበርላቸው ማድራግ ይጠበቅባቸዋል።ትግራይን ለቀው ወደ ክልላቸው ለመሄድ ለወሰኑትም ተገቢ እንክብካቤ በማድረግ ወደ ፈለጉት ክልል መሸኘት ይገባል።

2.ትግራይ ውስጥ የሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ለህገ መንግስታዊ ስርዓቱ ተገዢ መሆን የግድ ይለሃል።የብሄር፣ብሄረሰቦችና ህዝቦች መብት መከበር መታገልን ይጠበቅበሃል።ይሁንና በኢትዮጵያ በህዝብን ያልተመረጠ ፓርቲ ስልጣኑን ሲቆጣጠረው ዝምታን መምረጥህ በኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ትእዝብ ላይ እንድትወድቅ አድርጎሃል።አሁንም ቢሆን ጊዜው አልረፈደም ለህገ መንግስት፣ ለብሄር፣ብሄረሰቦችና ህዝቦች መብት መከበር ዘብ በሞቈም ለህዝብ ተማኝነትህን ማረጋገጥ ይጠበቅበሃል።በተለይ ትግራይ ውስጥ የምትንቀሳቀሰው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ህገ መንግስት እንዲጠበቅ የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች መብት እንዲከበር ከትግራይ ህዝብና መንግስት አብረህ ለመስራት ሰፊ እድል አለህ ይህንን እድልህ በፍጥነት ተጠቀምበት።

3.የኢትዮጵያ የሕብረ ብሄር ፌደራሊስት ሐይሎች

የአራት ኪሎ ጠቅላይ ሚኒስተር ቀደም ብሎ እንደተገለፀው የሕብረ ብሄር ፈደራሊስት ሐይሎች በህግ ለማገድ እንዲሁም ሽብርተኞች ናችሁ በማለት ከምድረገፅ የምትጠፉበት እርምጃ ለመውሰድ በዝግጅት ላይ ነው።የቅደም ተከተል ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር በኢትዮጵያ አሃዳዊ ስርዓት የሚፃረር ማንኛውም ሐይል ለማጥፋት የአራት ኪሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ቆርጦ ተነስተዋል።አንድ በአንድ እስከምትጠፉ ድረስ መጠበቅ የለባቹሁም።አሁንም በመሰረታቹሁት የጋራ ፎረም አስተባቢሪነት ሁሉንም አቅማቹህ በመጠቀም ህጋዊና ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል አጣናክራቹሁ በመቀጠል ኢትዮጵያን ከመበታተን ታደግዋት።

ድል ለኢትዮጵያ ህብረ ብሄራዊ ፌደራሊስት ሐይሎች!

Back to Front Page