..... ኣውራ ዶሮ!
ያሬድ ሕሉፍ 11-12-20
ቀኑን ያለቀበት ኣውራ ዶሮ ቁንጩን ሺቅብ ገትሮ ኣቦራ ሲረጭ ጭሮ ጭሮ: እንደ ቢራቢሮ: ቀይ ብጫ ኣረንጓዴ ክንፍን ገትሮ: ፈክሮ ፈክሮ: በስማይ ይሁን በጏሮ ማን ኣለ ከኔ ሌላ ዘንድሮ ሄደ ሊዋጋ ከቀበሮ ለምን ቅምጢትዋን በላህብኝ ብሎ::
መስሎት እንደኣመሉ እንደወትሮ:
ቀዝሮ ቀንዝሮ ሲደፈጥጥ ሴትየዋ ደሮ ጫጭቶችዋን ኣባሮ::
እየተዝመገመገ ጥልቅ የጭን ገረዲቱን ሊነቅ::
ታድያ ቢጠብቁ: ቢጠብቁ እግረኛ ሠራዊት እርሱን የሚያደንቁ የኖሩት እድሜ ልክ ሲያላግጡ: ነገር ዓለሙ ሲያውቁ እዝያው ከጉድጏድ ድብን ብሎ ማለቁ እግሬ ኣውጪን ብለው ፈርጠጡ ሳያስቡት ለካስ ሞትም ኣለ ብለው ደነገጡ::
Back to Front Page |