Back to Front Page

ተናገሪ ፒኮክዬ

ተናገሪ ፒኮክዬ

ተናገሪ ... ሳትፈሪ
ተናገሪ ... የሚሉሽን  የሚያደርጉሽን
ቀላቢሽን ... ደጓሚሽን
ተናገሪ ... በደሉን  የአንበሳውን
ተገዶ ... ጡረታ ... የወጣውን
... የናቁትን  የረሱትን
እንዳያገሳ ... የለጎሙትን
ምንስ  ይላል ... ምንስ  ሆኗል
ጤነኛ  ነው ... ወይስ  ታሟል

እስቲ  ሹክ  በይ ... ፒኮክዬ
የባዕድ  ነሽ ... አገር  በቀል
አገር  ወዳጅ ... አገር  አፍራሽ
የግብጽ  ነሽ ... ወይስ  የአባይ
ተናገሪ ... ማነው  ስሙ ... የስመኝ  ገዳይ
በቀለመሽ  በክንፎችሽ ... ዝርገፍ  አርጊው  ሳታስመስይ
አይን  አለሽ ... ከሩቅ  የሚያይ
የገዛኢን  የሰዓረን ... ተላላኪ  ነፍሰገዳይ
ሹክ  በይው ... ለአንበሳው
ለተረሳ ... ለታሰረው

የህዝብ  ነሽ ... የጭቁኖች
የጥቂቶች ... የገዳዮች
የአገር  ሻጮች ... የባንዳዎች
ንገሪን ... ፒኮክዬ
ታጋይ  ነበርሽ ... ወይስ  ሰላይ
እየበረርሽ ... በ ሰማይ  ላይ
ለጠላቶች ... ወሬ  አቀባይ

ሹክ  በይን ... ፒኮክዬ
የትግራይ  መሪ  ምን  በደለ ...
ምንስ  አሉ ... እነ  ክፉ ... እነ  አቧራ
ምን  ዶለቱ ... ምን  አቦኩ ... ፈተፈቱ
ሀሞት  የለሽ ... ፈሪዎቹ

በረሽ  ነበር  በሰማዩ ... በኢትዮጵያ... ክልል  ሙሉ
ታዝበሻል ... አይንሽ  አይቷል
ግድያውን  ቃጠሎውን ... ሰቆቃውን
መፈናቀል ... መባረሩን
በየት  ክልል ... በማን  መሪ
ማን  ተገፋ ...ፒኮክዬ ... ብታወሪ
ማን  በደለ ... ማንስ  ዋሸ
ማን  ነበር  መንጋ ... መንገድ  የዘጋ
ማን  ልጨብጥ  አለ ... የፎከረ  የሸለለ
እንቡጭ  ያለ ... የተረገመ  ያልታደለ
የተላላከ ... የተከተለ
ፒኮከዬ ...
ዝርግፍ  አርጊው ... እንደ  ክንፍሽ
ምንስ  ሰማሽ ... ምንስ  አሉሽ
እንዲታየን ... ውብ  ቀለምሽ

ኢዮብ ከጮማ እምኒ

05-22-20

Back to Front Page