Back to Front Page

ህውሃት የስልጣን ጥምና የጦርነት አባዜ የለውም:: ግን ለመብቱ ይከራከራል እንደ ሌሎች ለጥቅም ሲል በቀላሉ አይበረከኩም::

ህውሃት የስልጣን ጥምና የጦርነት አባዜ የለውም:: ግን ለመብቱ ይከራከራል እንደ ሌሎች ለጥቅም ሲል በቀላሉ አይበረከኩም::

ይደረስ ለተከበሩ አብደረህማን አህመድን የቀድሞ ፓርላማ አባል

ከስዮም ሓጎስ 1-10-2012 ዓም መቐለ

06-05-20 ኣይጋ ላይ የፃፋት አነበብኩኝ:: የመሰሎትን የመፃፍና ሃሳብን በነፃነት የመናገር አሁን የጀመሩት ሳይሆን ከዚህ በፊትም በኢህዴግም ዘመን የተለያዩ መጣጥፎች በዚህ አምድ ይፅፉ ሰለነበር እከታተላሎሁ: አደንቃሎሁም:: አብዛኛው ፅሕፎች ምክር አዛል ነበሩ:: አሁንም እንድዙያው ይመስለኛል:: ከዚህ በፊት ለነበሩትና የሚያወጥዋቸው ፅህፎችና ምክሮች አስተያየት ሰጥቼ አላውቅም::

በአሁን የፃፋት ፅሁፍ ግና የተወሰነ መልስ ለመስጠት ፈለግሁኝ: ትንሽ የተዛቡና ሃቅ እያወቁ የተሸፋፋኑ ጉዳዮች ስላነሱ:: ምክንያቱም በኔ ግምገማ እርስዎ:

1.   በኢህአዴግ ገዜ የፓርለማ አባል ሰለነበሩና አገዛዙን ሰለሚያውቁ

2.   ከዚህ በፊት የሚፅፋቸው ፅህፎት የተሻሉና ሚዛናዊ ሰለነበሩ

3.   ያሎት ልምድና የነበሩዎት ሚዛናዊ አቋም በተለይ በነበሩበት ፓርቲ

Videos From Around The World

እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ግምት ውስጥ በማስገባት የአሁኑ ሃስብዎ ወይ የፅህፍዎ መልክት ትንሽ የተዛባና ሓቁን የሳተና: በተለይም እርስዎ በምድርም በሰማይ ሚስክር መሆን የሚችሉ ሰዉና የተከበሩ የፓርላማ አባልና ሰለነበሩ: ግልፅ መሆን የሚገባቸውን በፍራቻ ምክንያት ይመስለኛል ተድበስብሰው የተለፉ መልስ ለመስጠት ፈለግሁኝ::

በዝርዝር እንምልከታቸው

1.   ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ መንግስት በትግራይ ጉዳይ ቸልተኛ ሆኗል የሚል ስሜት አድሮብኛል ይላሉ

ግን ያቀረቡት ማስረጃና መረጃ መንገድ ከመዝጋት ያለፈ ሌላ ማስረጃ አለቀረቡም: ለምን? የትግራይ ህዝብ በዚህ ሁለት አመታት ከፈዴራል መንግስት ብዙ ብዙ ጫና ተደርጎበታል:: መንገደ መዝጋት ብቻ አልነበረም: ዶክሜንተሪ ተሰርቶብት የዘር ጭፍጨፋ እንድደረግበት ተቀሰቀሰ: ግና የኢትዮጵያ ህዝብ ጨዋ ነውና በትእግስት አለፈው: ከመቶ ሺ በላይ የትግራይ ሰው እንድፈናቀል ተደረገ አንድም ርድታ እስካአሁን አላገኘም:: ወደ ትግራይ ኢንቨስተመት እንዳይሰፋፋ ባለሃበቶችን አሰረ ከለከለ:: በተጨማሪም የክልሉ ሰላም እንድናጋ በተለያዩ አቅጣጫዎችን በተለይ በአማረ ክልል ትንኮሳ ደረሰበት:: ከኤርትራ የተጀመርነው ሀዝብ ለህዝብ ግንኝነት ዘጋ:: አሁንም ይባስ ብሎ ለኮሮና ቫይረሰ ለመከለካል የተመደበውን በጀትና ንብረት ወደ ትግራይ እንዳይሄድ ከለከለ ወዘተ

2.   ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ ስልጣን ከጨበጡ በኋላ የትግራይ ጎምቱ ፖለቲከኞች ጓዛቸውን ጠቅልለው ወደ መቀሌ መሄዳቸው በገሃድ የተስተዋለ ጉዳይ ነው፡፡ ይህ ግን መሆን ያልነበረበት የህወሓት ትልቁ ስህተት ሆኖ ይታየኛል ይላሉ፡

ወደ መቐለ መምጣታቸው እርግጥ ነው ግን ስህተት አልነበረም ምክንያቱም

         በተለያዩ የአገራችን ክፍሎት የተነሱት ተቃውሞ ትግራይም በግልፅም ባይሆን ነበር :: በተለይ የመልካም አስዳደር እጦት ሙስናና ፀረ ዲሞክራሲ:: ስለዚህ ህውሃት በትግራይ አትኩሮ መስራት አለበት ተብሎ በተወሰነው መሰረት ነው አብዛኛው አመራር ወደ ትግራይ የመጣው:: ይህንን ውሳኔ ያኔም በግልፅ ተደርጎ ነበር:: ስለዚህ አሁን በስልጣን ያሉ አመራሮች ከዶር ዓብይ በፊት ትግራይ ላይ ነበሩ::

         ጎምቱ ፖለቲከኞች ጓዛቸውን ጠቅልለው ወደ መቀሌ መሄዳቸው ይላሉ ታዲያ እነዚህ ፓለቲኮኛች በጥሮታ ሲሰናበቱ መቀሌ መኖሪያ መድረጋቸው ምን ስህተት አለበት በፈለጉት ቦታ የመኖር መብት አላቸው ::

         ሌላው ደግሞ ሁሉም የህወሃት ባለስልጠናት ከፌዴራልና አዲስ አባባ መስተዳደር አልለቀቁም ነበር እስከ ቅርብ ግዚያት ድረስ የህወሃት ምክትል ጨምሮ በፌደራል ነበሩ ግና አልተፈለጉም ቀስ በቀስ እንድለቁ ተደረጉ

         አዲስ አባባ ቢሆም ግን ወይ ይታሰሩ ነበር ወይ ይገደሉ ነበር ለምን የሻዕብያም ቂም ስላለበት ወይም ሻዕበያ ለማስደሰት ተብሎ ነገሮችን ሰለሚታቀዱ ይህንንም ከጀነራሎችና የአማራ ክልል በላስልጣናት ግድያ ማያያዝ ይጠቅማል

 

3.   እኛ ከሌለን ሀገር መምራት አይቻልም፤ ተለምነን እንመለሳለን በሚል ስሌት ወደ ትግራይ በመሄድ መቀሌ የመሸጉ ይመስለኛል ይላሉ

ይህንን በጣም ውሸትና በማሰረጃ ያልተደገ ነው ምክንያቱም

         ህወሃት ከላይ በተቀመጠው ግምገማ መሰረት ቀድሞም ትግራይ ትኩረት ማድረግ ይፈልጋል እንጂ ወደ አዲሰ አበባ ቤተመንግስት ለመመለስ ፍላጎት የለውም::

         የትግራይ ህዝብ ዲሞክራዊያ ወይም ደግሞ በትክክል የተዳሰ ኢህአዴግ እንድኖር እንጂ የትግራይ ሰዎች በስልጣን እንዱቆዩ አይፈልጉም ነበር ይንን ዶር ዓብይ መቐለ ሲመጡ የነበረውን አቀባበልና የትግራይ ህዝብ ድጋፍ ማስረጃ ይሆናል:: ዶር ዓብይ እኮ እኔ ራሴ ጭምር የማያዳላ ቂመኛ ያልሆነ እውነተኛ መሪ እንድሆን እመኝ ነበር ግን አልሆነም:: በመምጣቱ እንድም የተግራይ ሰው አልተከፋም በኢህዴግ ውስጥ ሰላም ልማትና ዴሞክራሲ እስካመጣ ድረስ

ህወሃት ስልጣን ጥም የለውም:: እኔ ብቻ አውቃሎሁ የሚል ትምክህትም የለውም:: ህወሃት የስልጣን ጥማት ቢኖር እኮ አንዳንዶቹ እንደሚሉት መከለከያ: ፌደራል ፓሊስ: ደህንነት ይዞ ለዚች አገር ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እንድኖር ያደረገና ፓርቲ ነው እንጂ እንደ ለሎች የአፍርካ አገሮች ለስልጣን ብሎ በተከላከለ ነበር:: ስለዚ ለዚች አገር ሰላመዊ የስልጣን ሽግግር እንድኖር እንጂ አሁን ትምክህተኛች እንደሚሉት የስልጣን ጥማት የለውም::

4.   አሁን በስልጣን ላይ ያሉት ብዙዎቹ የብልጽግና ፓርቲ አመራር አባላት እንደ ኢህአዴግ በማእከላዊ መንግስት ደረጃ ለ27 ዓመታት ከህወሓት ጋር በጋራ ሲወስኑ እንዳልነበር ሁሉ፤ ቀደም ባሉት ዓመታት የተሰራውን ስህተት ሁሉ ጠቅልለው ለህወሃት የማሸከም አዝማሚያ አንጸባርቀዋል ህወሃቶችም ቢሆኑ ስህተቱ ሁሉ ተጠቅልሎ ለእኛ ተሰጠ በሚል ሆደባሻነት ማለቃቀሳቸው ተስተውሏል ይላሉ

 

ህወሃት የሚያለቅስ ድርጅት ባይሆንም ቅሬታው ግን ትክክል ነው ግን እርስዎ የተከበሩ አቶ አብዱርህማን እውነቱን እንዴት መናገር ፈሩ ወይስ እርስዎ እንደሚሉት አዝማሚያ ብቻ ነው እያሳዩ ያሉት::ወይስ ጥላቻ እንዴት ይህንን ሀቁን አይናገሩም

         በግልፅ 27 አመታት ጨለማ ነበር

         አባይ ግድብ ለፖለቲካ ፍጆታ ነው ጥቅም የለውም

         የሰብአዊ መብት ጥሰት በትግራይ ሰዎች ብቻ ነው የተፈፀመው

         ልማት የውሸት ነበር ወዘተ

የትግራይ ሰዎች አባርሮ የሌሎች ብሄር ሰዎች 27 አመታት ስልጣን ላይ የነበሩትና ከተራ አባል እስከ ጠቅላይ ሚንስቴር ያደረሰ ድርጅት ከተራ ተማሪ እስከ ዶክቴሬት ያስተማረ ድርጅት እኮ ነው ሲሰደበና ሲዛትበት የሚውል ይህንን አይን ያወጣ ጥላቻ በትግራይ ሰዎች የተደረገና አሁም የቀጠልም ይገኛል:: ሰለዚህ አዝማምያ ሳይሆን ጭፍን ጥላቻ የህወሃት አህዴግ 27 አመታት አሻራ ለማጥፋት የተደረገ ያለ ዘመቻ ነው::

5.   በትግራይ መገንጠልን የሚያቀነቅኑ ፓርቲዎች ተፈጥረዋል ይላሉ

ትክክል ነዎት ግን ፓርቲዎች ብቻ አይደሉም ሰዎችም በከፊል ህዝቡም እያሰበው ያለ ጉዳይ ነው :: ለምን አሁን ያለው መንግስት ለትግራይና መሪ ድርጅቱ ቀን ተለሊት ለማዳካምና ለማጥፋት የሚሰራ ሰለሆነ ነው ለምሳሌ

         እርስዎ እንዳሉት ሁለት አመታት መንገደ ተዘጋ ህዝቡ ግን አልተበረከከም

         የውሸት ዶክሜንቲ ፊልም ሲሰራ አሁን አልተበረከከም

         ሌቦች ፀጉረ ልውጦች ወዘተ ተብሎ ሲሰደብ መገንጠል ቢያስብ ምን ችግር አለው

         ሌቦች በሄር የላቸውም ሁሉም እህአዴግ ውስጥ የነበሩና አሁን ስልጣን ላይ ያለሁት እስቲ ባንክ ሒሳባቸው ይታይ ወይስ ኢሳት እንጀመረው የሌሎች ብሄር ባለስልጣነት ሃብት ይመርመር ወይስ ውጤቱ የሌላ ብሄር ሲሆን አይ የትግራይ ብቻ ነው የሚንፈልገው ለማለት ካልሆነ

6. ፈንቅል?

         ይህንን የትግራይ ህዝብና ህወሃትን አለማወቅ ነው:: ችግሮች የሉም ማለት አይደልም:: ብዙ ችግሮች አሉ:: ግን የሚፈታው በትግራይ ውስጥ እንጂ በሌላ አካል ድጋፍና ርዳታ የሚሹ አይደሉም::

         ለአንዳንዶቹ ምኛት ነው እንኳስ ህወሃት ፈንቅሎ ወደ ብልፅግና ለመደመር ይቅርና የተደመሩት ቄሮና ፋኖም ፀፀቱ አልቻልቱም የፈዴራል መንግስትና ብልፅግና ሃዲዱ ስለሳቱ

7.   በማእከላዊ መንግስት የሚከናወኑ ተግባራትን ስናይ የጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዓብይ መንግስት ትግራይን በተመለከተ የሚያራምደው ያልተጻፈ ፖሊሲ ይኖረው ይሆን?

አዎ ነው መልሱ እርስዎም እያወቁ ነው የሚጠይቁት ምክንያቱም

         ብልፅግና ህወሃት እንድትኖር አይፈልግም::የብሄር ፌደረራለዝን አይፈልግም ህግ መንግስቱ አይፈልግም :: አሃዳዊነት ይሰብካል ይህንን ለማሳካት ይተጋል ለዚህም ህወሃት እንደ እንቅፋት ይቆጥራል

         ህወሃት ለማጥፋት በሕጋዊ መንገድም ይሁን በፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ በወታዳራዊ ጭምር ተሞክራል

         ብዙ ክፋቶት እየተሰሩ ነው ምክንያቱም ሻዕቢያና ኢዜማ ኢሳት ምክርንና ተንኮል ተጨምሮበት ህወሃተና የትግራይ ህዝብ ለማንበርካክ እየተሰራ ነው ብዙም ተሰርተዋል

 

7.   በዚህ ላይ የህወሓት ተከበሃል፣ ካለ እኔ ማንም ሊደርስልህ አይችልም የሚል ፕሮፓጋንዳና ማስፈራሪያ ሲታከልበት ህዝቡ ውስጥ የመጠቃት ስሜት ሊፈጠር እንደሚችል መገመት ይቻላል ይላሉ

 

ምን ነካዎት የተከበሩ አቶ አብደረሁማን: የትግራይ ህዝብ እኮ ማንም የሰጠውን የሚውጥ አይደልም ወይ በስሜት የሚነዳ ህዝብ አይደልም ማመዛን የሚችልና የሚያዋጣውን የሚያውቅ ነው:: ህወሃት ስላላችው አይደለም ግን መሬት ላይ ያለ ሃቁ ነው:: ከላይ የተጠቀሱት ብዙ በደሎች በህዝቡ ደርሰዋል የታገለለትን አለማ እኮ ራስ በራስ ለማስተዳደር: በራሱ ቋንቋ እንድማርና ፍትሕ እንድያገኝ እንጂ ከአዲስ አበበ በሚላክለት የንጉስ ስጦታ ለመተዳደር አይደለም:: ይህንን ህዝብ በደንብ ያውቃል:: የተለያዩ ማስ ሚዲያዎች የብልፅግናም ጭምር ይከታተላን:: ግን ሃቁ የት እንደ ሆነ ያውቃል:: ያመዛዝናን:: ሰለዚህ ህውሃት ስላለች ሳይሆን ሀቁ በተግባር እያየ ሰለሆነ ነው::

 

7.   ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ካነሳሷ ህዝባዊ አልነበረቺም፡፡ ነገር ግን ደርግን በመደምሰስ ሂደት ህወሓት ትልቅ ሚና እንደነበራት፡፡ ደርግን ታግለው ያሸነፉት የህወሓት ጎምቱዎች ዛሬ (ከዘመኑ ጋር በመዘመን) ራሳቸውን ታግለው ማሸነፍ ግን አልቻሉም፡ አኩራፊዎች ሆነዋል ይላሉ

ከዚህ ሃረግ ሁለት ነገሮች እንመልክት

    I.      ህዝባዊ አልነበረቺም፡ደርግን በመደምሰስ ሂደት ህወሓት ትልቅ ሚና እንደነበራት ሊካድ የማይገባው ሀቅ ነው፡፡ የህዝብ ተሳትፈና ድጋፍ ከሌለህ ጦርነትም ልማትም ሰላምም ማምጠት አይቻልም:: በፍፁም::ስለዚህ ይህንን አባባል ትክክል አይመሰለኝም እንደ ማንኛውም ድርጅት ደካማ ጎኖች ነበሩት ግን ህዝቡን ተጠቃሚ የደረጉና ኢትዮጵያ በታርኳ አይታው የማታውቀውን ልማትና ሰላም አምጥታለች:: ይህንን ህዝብ በሳተፋ መስክ የተፈፀመ ነበር፡፡ በተለይ አቶ መለስ በህወት በነበሩት አመታት ህዝባዊነት የሚታማ አልነበረም

   II.      ለወቅቱ የሚመጥን ፖለቲካ ከማራመድ አልቻሉም

የተከበሩ አቶ አብዱረሁማን የህወሃት መሪዎች አኮ 75% ወጣቶች 100% የተማሩና አለም አቀፋዊ ኩነቶት የሚተነትኑ ናቸው፡፡ በአሁኑ ግዜ ይህንን አገር አቀፋዊና አለም አቀፋዊ ትንተና በሳይንሳዊ መንገድ ያልያዘ አመራር መሪ አይደልም:: ስለዚ ይህንን የህወሃት አመራርን አይመለከተም ወይስ ባዶ ማሰሮ ብዙ ይጮሃል (Empty pots makes noises) እንደሚባለው በዙ ስላልተናገሩ ይሆናል፡፡ ብዙ መናገር የችሎታ መሳያ ሳይሆን ርካሽ ተወዳጅነት (populist) ባህረይ ነው:: ወይም ለመወደድ መፍጨርጨር ነው፡፡ ዋና ነገር የያዙት አቋም ነው መለክያው፡፡ አቋሞቹ ደግሞ ግልፅ ናቸው::በጋራ እንወሰን እንመከከር ችግሮችም ውጤቶም የጋራ ናቸው:: ህገ መንግስቱ ይከበር::የውጭ ጣልቃ ገብነት ይቁም:: ከውጭ የሚደረገውን ውል ስምምነት ግልፅ ይሆን ወዘተ ናቸው::

7.   ተወልደው ያደጉት የፖለቲካ ችግሮች በጥይት እንጂ በውይይት በማይፈታበት የፊውዳሉ ስርዓተ ማህበር መሆኑ፣ 

ምን ነው የተከበሩ አቶ አብዱረሁማን ይህንን ከእርሶወ አይጠበቅም:: ህዝብ እኮ ጦርነት አይፈልግም: በተለይ የትግራይ::የትግራይ ህዝብ እኮ ለዚህ አገር ብሎ ቁጥሩ እኪጠፋ ድረስ ከአፄ ዮሀንስ እስከ 2010 መስዋእትነት የከፈለ ህዝብ ነው:: ግን ጦርነት ናፋቂ ስለሆነ አይደለም:: ግን በዚህ ሂደት የተማረው ነገር ለነፃነት ለፍትህ: ለእኩልነት ይታገላል:: አሁም ከመሪ ድርጅቱ ይቀጥልበታል::

አሁን ያለው የህወሃት አመራር ለሰላምና ልማት የሚያስቀድም እንጂ ለጦርነት ብሎ ግዜ የሚያባክን አይደለም:: ግን ማንም ደግሞ እንደ በግ ጎትቶ እንድወስደው አይፈልግም:: ይህንን ከትግራይ አይታሰብም:: ስለዚህ ጦርነት የሚፈልግ አይደለም ያውም የርስ በርስ ጦርነት (civil war) ከትግራይ ህዝብና ህወሃት በላይ ማን ምስክር አለ:: የጦርነት አስከፊነት ህዝቡም በሪ ድርጅቱም ይረዳዋል:: ሰለዚህ የተከበሩ አቶ አብዱረሁማን የጦርነት የትጥቅ ትግል ዘፈኖች ፊልሞች ለኛ ለተጋሩ ልክ እንደ ህንድ ፊልም ትዝታችን ናቸው እንጂ ሌላ ተሳቢ የተደረጉ አይደሉም:: አልሸነፍም ባይነት ወይም ጦርነት ተፈልጎ አይደልም::

7.   እስከዛሬ ለሰሩት በጎ ነገር ሲባል የወንድ በር (Safe Exit) መስጠቱ አስፈላጊ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡በህግ መጠየቅ እንደተጠበቀ ሆኖ የወንድ በር (Safe Exit) የመስጠቱ አስፈላጊነት ሊሰመርበት ይገባል ይላሉ፡፡

ግን ለምን ይህንን ፈለጉ ከርስዎ የሚጠበቅ አይደለም:: ምክንያቱ እስከ አሁን ለሰሩት ማለት አንዱ ሰጪ አንዱ ተቀባይ የምን የሞግዚት አስተዳደር ነው:: ህወሃትና የትግራይ ህዝብ እያለ ያለው ሁሉም ነገር ግልፅነት ይኑረው:: አንዱ የበላይ አንዱ የበታች አስረሳሰብን ተግበርም መኖር የለበትም ነው ::

ሌላው የወንድ በር (Safe Exit) ላኮረፈ ልጅ ነው የሚያገለግለው እንጂ ህወሃት የመሰለ ጠንከራ ድርጅትና የህዝብ ድጋፍ ያለው ድርጅት በማንንም እጅ ተባርኮለት የሚሰጠው ሳይሆን በፖለቲካ ድርድርና ሁሉም ነገር በግልፅነት ተወያይቶ የሚፈታ እንጂ እንደ ህፃን ልጅ እሺ እንድልህ መደለያ በመስጠት ወይ በመሸወድ አይደለም

በህግ መጠየቅ እንደተጠበቀ ሆኖ ምን ማለት ነው? የትግራይ ሰዎች ብቻ ናቸው እስከ አሁን የተጠየቁ ያሉት ለምን ሃቁን አይነገሩም? ከሌላ ብሄር ማን ታሰረ ሁሉም አሁም ስልጣን ላይ ናቸው:: ሌባ ሁሉም ብሄር ጋ ይኖራል በወንጀልም ከተራ መንግስት ሰራተኛ ጀምሮ እስከ ጠቅላይ ሚንስቴር: አፈ ጉባኤ: ፖሊስ ኮሚሽነር: ኢንሳ ዳሬክተር: ክልል አስዳዳሪዎች: ለምን የህወሃት ብቻ? ማን ተጠየቀ ሌላ ስለዚህ ክብርነትዎ በምድርም በሰማይም ከእርስዎ በላይ ሚስክር የሚሆን የለምና ሃቁ ይናገሩ ወይም አታዳፍኑት ወይም የእርስዎ መልእክትም ወደ ህወሃት ጣት መቀር እንዳይሆብዎ::

 

12.ህወሓት ዴሞክራሲን በማምጣቱ ሂደት ባይዋጣላትም ደርግን በመጣሉ ሂደት የነበራት ሚናና የተግባር እንቅስቃሴ አክብሮት ሊቸረው የሚገባ መሆኑም መታወቅ አለበት ይላሉ፡፡

እርስዎን የመሰለ በኢህዴግ ዘመን የነበረ ሰለ ህወሃትና የኢትዮጵያ እድገትና ልማት ካልመሰከረ ማን ይመሰክራል ወይስ ፍራቻ ወይስ ጥላቻ ይገርማል:: ህወሃት ኢህዴግ በዴሞክራዊ ማምጣት አልተሳከላም እስማማሎህ:: ይህንንም ድርጅቱ ይቀበላል:: ለሌሎች ጥፋቶት ተፈፅመዋል:: ትክክል:: ይህንን ድርጅቱ ይቀበላል::

ግን የህወሃት ስኬት ደርግ በመጣል ብቻ እንድመሰገን ከፈለጉ በጣም ተሳስተዋል አለምና የኢትዮጵያ ህዝብ ያለፉትን 27 ዓመታት ልማትና ሰላም ምስክሮች ናቸውና:: ከተሰሩት ጥቂት ልጥቀስ

         40 ዩንቨርስቲዎች ተሰርተዋል በማይተሰብ ክልልም ጥምር

         20000 ኪሎ ሜትር አስፋትና 30000 ኪሚ የጠጠርመንገደ ተሰርተዋል

         10 ትልልቅ የሃል ማመንጫ ግድቦች ተሰርተዋል

         100 በላይ ትላልቅና መከከለኛ ሆስፒታል ተሰርተዋል

         በእያንዳዱ ወረዳና ከፍተኛ ትቤት እና መለስተኛ ሆፒታል ተሰርተዋል

         የኢትዮጵያ ህዝብ የድህነት መጠን ከ60% ወደ 23% ወርደዋል

         የኢትዮጵያዊያን የመኖር እድሜ ክልል ከ45 ወደ 65 ከፍ ብለዋል

         አዲስ አበባ ከተራ ከተማ ወደ ከፍተኛ አለደገችም? ሌሎች የክልል ከተሞችስ?

ማጠቃለያ

ፓርቲና ህዝብ በመርህ ደረጃ አንድ አይደሉም ትክክል ነዎት:: ግና የትግራይ ህዝብና ህወሃት ግንኝነት ከፓርቲ በላይ ነው:: በአጥንትና ደም የተጣበቀ ነው:: ለዚህ ነው ህወሃት ከነ ችግሮቹ የሚንደግፈው:: ደግሞም አባላትና መሪዎች አይሳሰቱም ማለት አይደልም:: ግን በህደትና በግምግማ መስመሩ ሳይለቅ ይቀጥላል እንጂ ማንም የሚፈነቅለው ወይም የሚያለየው የለም::

በፌዳራል መንግስትና ህወሃት ያለው ፍጥጫ በውይይት እና በድርድር ለመፍታት አስበው ከሆነ ጥሩ ነው::ግን ሃቁና በግልፅ በመነጋገር እና ጥፋቶቹ ደግሞ በተገመገመው ስፋት መሰት እርምጃ መውስድና ማስተካካል እንጂ ህወሃት ልክ የኢትዮጵያ ድርጅት እንዳልሆ በማሰብ ከምደረ ገፅ ለማጥፋት መሞከር ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝና

:: ስለዚህ የሁለም ሶስተኛ ወገን ሚና መሆን ያለበት ሀቁ በማቅረብ ወደ ድርድር እንድመጡ መጋበዝ እንጂ አንዱ ቡራኬ ሰጪ እንዱ ተቀባይ መሆን የወንድ በር (Safe Exit) ማበጀት ለግዜው ይሆናል እንጂ ዘለቂነት የለውም::

 

 


Back to Front Page