Back to Front Page

ሪፐብሪካን ጋርድ !!!

ሪፐብሪካን ጋርድ !!!

የማን  ጋርድ ?
ያምንና  ለነማን ... ማንን  ብቻ  ለመጋረድ
ሪፐብሊካን  ጋርድ !!!

እየመረጡ  ከለላ ... እየመረጡ  መጋረድ
ሪፐብልካን  ጋርድ !!!

ማንን  ጋረዳችሁ ... ማንንስ  አዳናችሁ
ጠ/ሚሩ  ምናሉ ... ጥያቄ  ስታቀረቡ
ኢንጅነር  ስመኘውን ... እንጋርደው  ስትሉ
ሪፐብሊካን  ጋርድ !!!
አኮረፉ ... አስመሰሉ... አያገባችሁም  አሉ
ሪፐብሊካን  ጋርድ ... እስቲ  ተናገሩ

በ ጠ/ ሚሩ ...የተመረቃችሁ ...
የተጋበዛችሁ ... የተሞገሳችሁ
ሪፐብሊካን  ጋርድ !!!

ጄነራል  ስዓረን... እንጋርደው  ስትሉ
ምናሉ ... ኮረኔሉ
ይሄ  ስራ ... የናተ  አይደለም  አሉ
ሪፐብሊካን  ጋርድ !!!
የምንና  የማን  ጋርድ?

በ ጠ/ሚሩ ... የተመሰገናችሁ
ሪፐብሊካን  ጋርድ !!!

ጄነራል  ገዛኢን ... ያልጋረዳችሁ
የ ጠ/ ሚሩን ... ትእዛዝ  አክብራችሁ ?
ሪፐብሊካን  ጋርድ !!!
የማን  ጋርድ ?

... ከናተ  ሚበልጥብኝ ... የለም  ተባላችሁ
ተመሰገናችሁ ... ተወደሳችሁ
ሪፐብሊካን  ጋርድ !!!

መረጥ  መረጥ ... ጋረድ  ጋረድ
አዲሱ  ጠብቃ ...
ሪፐብሊካን  ጋርድ !!!
... የማን  ጋርድ ???

ኢዮብ ከጮማ እምኒ

01-04-20

Back to Front Page