Back to Front Page

Pre-trial Publicity of Political Crimes

Pre-trial Publicity of Political Crimes / ፖሊቲካ-ነክ የወንጀል ክሶችን ከችሎት በፊት በመገናኛ ብዙሃን ማቅረብ

†ESAYAS HAILEMARIAM 07-19-20

ማንኛውንም በሂደት ላይ ያለ የወንጀል ክስን (pending criminal case) በ አወንታዊም ሆነ አሉታዊ መልኩ የመገናኛ ብዙሃን ሽፋን (positive or negative pre-trial publicity) መስጠት፣ የተከሳሾችን ከፍርድ በፊት እንደ ንፁህ የመቆጠር መብት (presumption of innocence) አደጋ ላይ በመጣል ተጠርጣሪዎች ፍትሃዊ እና ተመጣጣኝ ውሳኔ እንዳያገኙ በማድረግ ፍርድ ያዛባል።

አሉታዊ የመገናኛ ብዙሃን ሽፋን (negative pretrial publicity)፣ ተከሳሹ ከሚገባው በላይ እንዲቀጣ፣ ወይም ጭራሽ መቀጣት የሌለበት ንፁህ ግለሰብ እንዲፈረድበት ሲያደርግ፤ አወንታዊ የመገናኛ ብዙሃን ሽፋት (positive pre-trial publicity) ደግሞ ከፍተኛ ቅጣት የሚገባው በቀላል ቅጣት እንዲያመልጥ፣ ብሎም በነፃ እንዲሰናበት በማድረግ የወንጀል ፍትህ-ስርዐት አስተዳደርን (administration of criminal justice system) የሚጎዳ ድርጊት ነው። 

 

የዴሞክራሲ ባህላቸው ባልበለፀገ ሃገራት የፍትህ-ስርዐቶች፣ ከፖለቲካ ጋር በተገናኘ የተከሰሱ ተጠርጣሪዎች ላይ በዘጋቢ ፊልም (documentary)፣ የመንግስትና የግል የመገናኛ ብዙሃንን በመጠቀም፣ ገና ፍርድ ቤት ብይን ሳይሰጥ፣ አንዳንዴም ገና ፖሊስ ምርመራ ሳይጀምር፣ ተጠርጣሪው ወንጀሉን ፈፅሞታል ለማስባል ወይም ትክክለኛ የወንጀሉ ፈፃሚወችን ለመሸፈን ሌላ የመባ ፍየል (scapegoat) በመፈለግ፣ በተጠርጣሪ ወይም ተከሳሾች ላይ ሰፊ የፕሮፓጋንዳ ስራ መስራት የተለመደ ነው።

ዳኞች እና ዐቃብያን- ህጎች፣ እንደማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል የመገናኛ ብዙሃን ወይም ሚዲያ መከታተላቸው ስለማይቀር፣ (በተለይ ትኩረት የሚስቡ የፖለቲካ ይዘት ያላቸው ክሶችን) ፣ የክሱን መዝገብ ገልጠው ግራና ቀኙን በቀረበው ማስረጃ ከመመዘን ይልቅ ስለ ተከሳሹ ከመገናኛ ብዙሃን ወይም ሚዲያ  የሚሰሙት መጥፎም ሆነ ጥሩ ዘገባ በነፃነት፣ ያለ ውጫዊ ተፅእኖ ሚዛናዊ ውሳኔ የመስጠት ጥረታቸው (veil of ignorance in constitutional jurisprudence) ላይ ተፅእኖ በማሳደር ውሳኔያቸውን ያዛንፈዋል።

ከፖለቲካ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ ወይም የተከሰሱ ግለሰቦች ላይ መጠነ ሰፊ አሉታዊ ዘጋቢ ፊልሞች (negative documentaries) በማህበራ ድረገፆች ዘመቻ በመክፈት የፍርድ ውጤቱን አንድ ወገን በሚፈልገው መንግድ እንዲሄድ የማድረግ ዝንባሌ ኢትዮጵያን ጨምሮ በበርካታ ሃገራት የተለመደ ተግባር ነው።

የዚህ አይነቱ ድርጊት (pre-trial publicity)፣ በተለይ በፖለቲካ ስልጣን ላይ ባለ አስፈፃሚ አካል ተፅእኖና ትእዛዝ የሚተገበር፣ ፍትህን የሚያዛባ ድርጊት ሲሆን፣ በተከሳሾች ላይ ዘጋቢ ፊልሞች (documentaries) የሚለቀቁባቸው ምክንያቶቹ ከዚህ የሚከተሉት ናቸው፥

ምክንያቶች፤

1.   በስልጣን ላይ ያለ አካል፣  ዳኞች ምን አይነት ፍርድ ሊፈርዱ እንደሚገባቸው መልእክት ለማስተላለፍ  (ጣልቃ በመግባት)፤

2.   ተፎካካሪ የፖለቲካ ባላንጣዎችን (political rivals) ለማዳከም እና ለመጉዳት፤

3.   ተከሳሹ የሚፈረድበት ወይም የተፈረደበት ቅጣት ተገቢ መሆኑን ህዝብን ለማሳመን (legitimizing criminal punishment)፤ እንዲሁም፣

4.   ሌሎች የፖለቲካ ባላንጣዎች ተመሳሳይ እጣ ፈንታ እንዲሚያጋጥማቸው ለማስፈራራት ናቸው።

 

ፖሊቲካ- ቀመስ የወንጀል ክሶችን በመገናኛ ብዙሃን የማቅረብ (pre-trial publicity) ጉዳቶች:

1.   የተከሳሾችን የፍሬ ነገር እና ስነ-ስርዐት መብቶችን (substantive and procedural due process rights) ይጥሳል፤

2.   የፍርድ ቤቶችን ተቋማዊና የውሳኔ ነፃነት (institutional and decisional independence of the judiciary) ይጋፋል፤

3.   ዜጎች በፍር ቤቶች ላይ ያላቸውን እምነት ይሸረሽራል (erodes the publicís confidence in courts)፤

4.   ለዴሞክራሲ መጎልበት ወሳኝ የሆነው ነፃና ፍትሃዊ የፖለቲካ ተሳትፎ እንዳይኖር እንቅፋት ይሆናል።

Videos From Around The WorldESAYAS HAILEMARIAM
UNIVERSITY OF CALIFORNIA, BERKELEY SCHOOL OF  LAW
HTTPS://WWW.FACEBOOK.COM/O.CALIFORNICATION.O
Back to Front Page