Back to Front Page

የኢትዮጵያ ነገር

የኢትዮጵያ ነገር

 

(ዳንሾ ሄሮን - 21/08/2012 ዓ/ም)

 

ግብያ

 

ዛሬ ከመቸውም ጊዜ የኢትዮጵያ የወደፊት ዕጣ ፈንታ የሚወስኑ ክስተቶችና የመንግስት ውሳኔዎች እያየን ነው። ምርጫ በኮቪድ-19 ሰበብ ተራዝመዋል። የተወካዮች ምክርቤት የስልጣን ዘመንም ለማክተም ጥቅት ወራት ቀርተውታል። ይህ መንግስት በምን ህገመንግስታዊ አሰራር ስልጣኑ ማራዘምና የተራዘመው ምርጫ እንደሚያካህድ በጣም አከራካሪ ሆነዋል። ለአበዛኞቻችን ከፊት የተጋረጠው አደጋ እየታየን ነው። ለኔ መፍትሄውም በኢትዮጵያዊያን ፌደራሊስት ኃይሎች እጅ ብቻ ያለ ሆኖ ተሰምቶኛል። የፌደራሊስት ኃይሎች መተባበር ኢትዮጵያንበማዳን ጉዳይ ላይ ትልቅ ሚና ይኖረዋል። አለመተባበራቸው ደግሞ በተገላብጦሽ ይሆናል። እኔ በበኩሌ መፍትሄ ያልኩት ሃሳብ እንደሚከተለው አቅርብያለሁኝ። የፌደራሊስት ኃይሎች ዋጋ እንደሚትሰጡትም ተስፋ አደርጋለሁኝ።

 

እስከ 1987ዓ/ም የማቃት ኢትዮጵያ የዳግማዊ ሚኒሊክ ኢትዮጵያ ብዬ ጠራታለሁኝ። ከዳግማዊ ሚኒሊክ በፊት የነበረች ኢትዮጵያ ምን መልክ እንደነበራት ለታሪክ ተማራማሪዎች ልተውላቸው። ነገር ግን የዳግማዊ ሚኒሊክ ኢትዮጵያ ለኔ ምን እንደምትመሰል እንደመግብያ ትንሽ ልበል።

 

የዳግማዊ ሚኒሊክ ኢትዮጵያ ጁቡቲ አታጠቃልልም። ኤርትራንም አትጨምርም።የሚገርመው ነገር ግን ትግራይንም ለአፍታም ጨምረ አታቅም። ትግራይ የሚለውን ጂኦግራፊያዊ አከባቢ ሚኒሊካዊያን ኢትዮጵያ የሚለው ካርታቸው ላይ ያካቱትታል። ነገር ግን ትግራይ የምትባለው መሬት አቅፋ የያዘችው የትግራይ ህዝብ የሚገባውን የኢትዮጵያዊነት ቦታ አልሰጡትም ነበር። የትግራይ ህዝብ የኢትዮጵያን መሠረ እንደመሆኑ መጠን የኢትዮጵያዊነት ክብር ልጐናፀፍ ዘንድ የዳግማዊ ሚኒሊካውያን ሂሊና አልፈቀደም። እነዚህ የዳግማ ሚኒሊክ አስተሳሰብ የተጠናወታቸው የትምክህት አስተሳሰብ አቀንቃኞች ካለፉት መቶ ሰላሳ አመታት ጀምሮ እስከ አሁን የትግራይ ህዝብ ኢትዮጵያዊ ክብር ልጐናፀፍ ሂሊናቸው ካልፈቀደ ምን ይደረግ? ይህ ለኔ አንድ መሰረታዊ ጥያቄ ነው። ምክንያቱም የሰውን ሂልና ማስገደድ የሚችል ኃይል የለምና።

Videos From Around The World

 

በሁለተኛ ደረጃ እቺ የዳግማዊ ሚኒሊክ ኢትዮጵያ ፤ የትግራይ ህዝብ ከነ ሙሉ ክብሩ ፣ ባህሉ ፣ ታኩ ፍላጐቱና ጥቅሙ ማቀፍ ካልቻለች እውነተኝ ኢትዮጵያ የሚያስብላት መስፈርት ታሟላለች ወይስ የሚለውን ጥያቄ ልትሰነዝርያስገድደሃል።የትግራይ ህዝየኢትዮጵያ ኣካል አደለም እንዳትለው የኢትዮጵያ መሠረት ስለመሆኑ በጠንካራ የታሪክ መረጃዎች የተረጋገጠ ሓቅና ያልተበረዘ እውነታ ነው። በሌላ መልኩ ይህን እውነታ በመጣስ በማስመሰል ፖለቲካ የተካኑት የትምክህትኃይሎች የትግራይ ህዝብ እውነተኛ ህልውና አልፈለጉም። ስለዚህ ትግራዎትና ሌሎች ኢትዮጵያ ይህንን Paradox መፍታት ይጠበቅብናል ብቻ ሳይሆን የግድ መፍትሄው አሁን መጠት አለን።

 

የመጀመርያው መፍትሄ በመሠረታዊ እውነታው ላይ መስማማት ነው። ይህ መሠረታዊ እውነታ ምንድ ነው ያልን እንደሆነ የትግራይ ህዝብ ከነሙሉ ክብሩ ፣ ባህሉ ፣ታኩ ፣ ፍላጐቱና ጥቅሙ ያላቀፈች ኢትዮጵያ እውነተኛ ኢትዮጵያ አደለችም ነው። ስለዚህ በዚሁ ምንያት የዳግማዊ ሚኒሊክ ኢትዮጵያ የውሸት ኢትዮጵያ ነበርች ማለት ነው። የትግራይ ህዝብ ለይስሙላ ሳይሆን ከሂሊና በፈለቀ መልኩ ያላቀፈች ኢትዮጵያ ፤ ኢትዮጵያናት ብሎ የሚከራከረኝ ኃይል ወይም ግለሰብ ካለ ጉዳዩ አውቆ የተኛ ብቀሰቅሱት አይሰማም ይሆናል። የዳግማዊ ሚኒሊክ ኢትዮጵያ ትግራይን እንደማትጨምር መሠረታዊ እውነታ ስለሆነ እውነታዊ መቀበል ግድ ይለናል።

 

በዚህ መሠረታዊ እውነታ ከተስማማን ታድያ እውነተኛ ኢትዮጵያ እንዴት እንገንባ የሚል ጥያቄ ማንሳታችን አይቀሬ ይሆናል። ይህ ጥያቄ አነሳን ማለት ወደ መፍትሄው መራመድ ጀመርን ማለት ነው። ከዚሁ ጥያቄ በማያያዝ ለሚናሰላስለው መፍትሄ ሁለት አማራጮች ይኖሩታል።

 

1. እውነተኛህብ-ብሔራዊት ፌዴራላዊት ኢትዮጵያ መገንባት

2. በዓይነቱ ልዩ የሆነና የሰለጠነ መበታተን ይሆናሉ።

 

እነዚህ ሁለት አማራጭ መፍትሄዎች በዝርዝር ከማየታችን በፊት አንድ በትክክል ማየት ያለብን ነጥብ አለ። እቺ ለአፍታም ቢሆን የትግራይ ህዝልባዊ በሆነ መልኩ ያላቀፈችው የውሸት ኢትዮጵያ የሆነችው የዳግማዊ ሚኒሊክ ኢትዮጵያ ሌሎች ኢትዮጵያ ተብለው የሚገለፁ ህዝቦችስ በትክክል አቅፋለች ወይ ነው ነጥቡ። የዳግማዊ ሚኒሊክ ኢትዮጵያ የውሸት ኢትዮጵያ ናት ብለን ከደመደምን ፤ ከትግራይ ህዝብ በተጨማሪ ኢትዮጵያዊያ ተብለው የሚገለፁ ሌሎች ህዝቦች በትክክል የሚታቀበት ተኣምር እንደማይኖር መገንዘብ እንችላለን። ይህ ማለት የሶማሌ ህዝብም ይሁን የኦሮሞ ህዝብ ፤ የአፋርም ይሁን የጋንቤላ ህዝብ ፤ የቤንሻንጉል ጉምዝም ይሁን የአገው ህዝብ ፤ የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦችም ይሁኑ የቅማነት ህዝብ ወዘተ ከነ ሙሉ ክብራቸው ፣ ባህላቸው ፣ እሴታቸው ፣ ታሪካቸው ፣ ፍላጐትና ፣ ጥቅማቸው አልታቀፉም።

 

ይህች የውሸት የሆነችው የዳግማዊ ሚኒሊክ ኢትዮጵያ ህዝቦች በዕኩል በጋራ ተጠቃሚነት ላይ መሠረት በማድረግ አላቀፈችም።የኤርትራና የጁቡትም የሚያክል ታላቅ ህዝቧም በጠራራ ፀሓይ ክዳለች። በዚሁ መቶ ሰላሳአመታትንም ሰፊ የሆነ የውሸት ታሪክ ገምብታለች። ለትምክህት ኃይሎችብልፅግና ሲባልም ህዝብዋ በአሰቃቂየድህነት አረንቋ ውስጥ አምቃ ኑራለች። በዚሁ ጉዳይ ልብትሉሉኝ የሚገባ ነገር ድህነት ማስወገድ ፈልጋለሁኝ ብሎ ለታገለ ህዝብም አይ!በድህነትሰቆቋ ውስጥ ነው መኖር ያለብህ ብላ አስገድዳለች። አሁንም ለማስገደ እየተሞከረ ነው።

 

የዳማዊ ሚኒሊክ ኢትዮጵያ ወደ ትክክለኛው ኢትዮጵያ ለማሸጋገር ለዘመናት ሰፊ የህዝብ ትግል ቢደረግም አንኳሩ ግን ከ1966 ዓ.ም ወዲህ የተደረገው የህዝብ ትግል ነው። ከላይ የተገለፀው Paradox የሚፈታበት መሠረት ማኖር የተጀመረው ከ1966 ዓ.ም ወዲህ በተደረገው እልህ አስጨራሽ ትግልና የተከፈለው ሰፊ የሆነ መስዋዕትነት ነው። ወደድንም ጠላንምአንድ ታላቅ የህዝብ ተጋድሎ እውቅና መስጠት ይኖርብናል። ይህም የትግራይ ህዝብ የአስራ ሰባት ዓመት የትጥቅ ትግል ይሆናል። በተጨማሪም የኦሮሞ ህዝቦች ፣ የአፋር ፣ የሶማሌ፣ የቤንሻንጉል እንሁም የአማራ ህዝብ ሰፊ ትግል አካሄዱ። የኤርትራ ህዝብም ለነፃነቱ እልህ አስጨራሽ ትግል አካሄደ። በነዚህ ህዝቦቸ ተጋድሎ ለዘመናት ያንሰራራና ሥር የሰደደ የገ መደቦችና ትምክህተኞች አከርካሪ ለመጨረሻ በሚመስል መልኩ ተመታ።

 

እንግድህ የደርግ ውድቀት ለአዲስትዋን እውነተኛ ኢትዮጵያ ግንባት በር የከፈተ ሲሆን ለዘላቂ ዕድገትዋንም ማረጋገዋነኛ ዕድል ነው የሚል የአብዛኞቻችን እምነት ነበር። ህዝቦቸ በእውነተኛ ኢትዮጵያዊነት ላይ ተመርኩዘው እውነተኛዋ ህብረ-ብሔራዊት ፌደራላዊት ኢትዮጵያዊ ለመገንባት አንድ የቃል ኪዳን ሰነድ ያስፈልጋቸው ነበር። የቃል ሰነዳቸው ዋነኛ ማጠንጠኛም በ ሃሳብ ጠቃለል ይችላል

 

ፈቅደንና ተከባብረን አንድ እንሁን ይላል

 

በዚች በአንድ ዐረፍት ነገር የሚገለፅ ሃሳብ ውስጥ ብዙ መሠረታዊ የሆኑ ፅንሰ ሃሳቦች ተካተው ታገኛለህ። የመጀመርያውና ዋነኛው የብሔር ፣ ብሔረሰብና ህዝቦች ሙሉ ነፃነት በሰፊው ተካቶ ታገኘዋለህ። በሁለተኛ ደረጃም የህዝቦች ዕኩልነት ፍንትው ብሎና ጐልቶ በዚህ ዐረፍት ነገር ውስጥ ታየዋለህ። በሶስተኛ ደረጃም የብሔር ብሔረሰብና ህዝቦቸ የራስ ዕድል በራስ የመወሰን መብት እስ መገንጠል ሳይዛነፍ ቦታ ይዞ ታየዋለህ። በተጨማሪም ይህ ዐረፍተ ነገር ውስጥ የሰፈረው ሃሳብ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦቸ በራሳቸው ፈቅደው ተከባብረውና ተባብረው የጋራ ተጠቃሚነታቸው በሚያረጋግጥ መልኩ አንድ ታላቅ የጋራ የሆነች ሃገር መገንባት የሚያስችል ችሎታና አቅም እንዳላቸው ግልፅ አድርጐ ያሳያቸዋል።

 

ከላይ ከተገለፁት ነጥቦች ባሻገር ይህ ዐረፍት ነገር ሌላም ጥልቅ መልእክት ይዞ እናገኘዋለን። የዳግማዊ ሚኒሊካዊያን አስተሳሰብ አቀኝቃኞች የቀድሞ ገናናነታችን እንመልሳለን በሚል ስሌት ለሚያካሂዱት ማንኛውም ጥረት ከእንግዲህ በኢትዮጵያ ምድርና ህዝብ ዋጋ እንደሌለው አንጥሮ ያሳያቸዋል። እነሱም የትምክህተኞች የገናናነትና የበላይነት ፍላጐት ለማሳካት የሚያስችል መግብያ ቀዳዳ የሌለው ሃሳብ ሆኖ ያገኙታል። በዚሁም ምክንያት የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ሰንደው በጠንካራ መሠረት ያኖሩት የቃል ኪዳን ሰነድ አምርረው ይጠሉታል። ቀደው ለመጣልም ሲወራጩ ታያለህ። የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በተለይ አዲሱ ትውልድ ልብ ማለት ያለበት እዚሁ ላይ ነው።

 

ብዙ የመገናኛ ብዙሃን ድስኩር የጋዜጣ ጋጋታ የማህበራዊ ሚድያ ወከባ ሳያስፈልግ አንድ ጥያቄ በመጠየቅ ብቻ እውነታውን መርምሮ ማግኘት ይቻላል።ለምን ህዝቦች በመፈቃቀድ በመተባበርና በጋራ ተጠቃሚነመርህ ላይ ሆነው የመሠረትዋት ኢትዮጵያ በትምክህት ኃይሎች ዘንድ አልተፈለገም?

 

ከላይ የተጠቀሰውና የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቃል ኪዳን ሰነድ መሠረት የሆነው ዐረፍት ነገር ትርጉም ሰፊ ሆንም ለኢትዮጵያ ህዝቦቸ አንድ ያጐናፀፈው ዕድል ደግሞ ልግለፅ። ይህ ዓረፍት ነገር በማያሻማ ሁኔታ በማንም ገዢ ጉልበት ሳይሆን ፤እንደ ህዝብ በራስህ ፈቅደህ የኢትዮጵያ አካል ሁነህ ኢትዮጵያን ትገነባለህ አልያም ደግሞ በራስህ ፈቅደህ የራስህን ሀገር ትመሠርታለህ ይላል። ስለዚህ ይህ ፅንሰ ሃሳ በሰለጠነ መንገድና ምንም ዓይነት የጥቅም ሁን የመብት መዛነፍ ሳይኖር ፈቅደህ አንድ ለመሆን ያስችላል እንዲሁም ምንም ዓይነት የጥቅምም ይሁን የመብት መዛነፍ ሳይኖር በሰለጠነ መንገድ መበታተንንም ያስችላል። ለሁለቱም አማራጮች በቂ ቦታ አስቀምጧል። ከዚህ ውጭ ያለው አማራጭ የአውሬና ወሮ በሎች አማራጭ ሆኖ እናገኘዋለን።

 

ትክክለኛው ሃሰብ ይህ ከሆነ ዘንድ ሁለቱም አማራጭ ያልኳቸው መፍትሄዎች ለመግለፅ ልሞክር

 

1.       እውነተኛ ህብ - ብሔራዊት ፌደራላዊት ኢትዮጵያ መገንባት

 

ኢትዮጵያ ከእውነተኛ ፌደሬሽን ውጭ መቀጠል የሚትችል ሀገር አደለችም። ይህን ሐቅ መቀበል ያቃተው ወገን ካለ ማሰብና ማስተዋል የተሳነው በስሜት የሚነዳ ምስኪን ብቻ ነው የሚሆነው። እውነተኛ ፌደሬሽን የበለጠ ለመገንባት የመጀመርያው እርምጃ በ1987 ዓ.ምየፀደቀው የኢፌዴሪ ህገ-መንግስት ሳይሸራረፍ መቀበል ይሆናል። ይህ ግን በቂ አይደለም። የሚከተሉት መናጋት የሌለባቸው መሠረተ-ሃሳቦች በስሜ ሳይሆን በምክንያት መረዳት ያስፈልጋል።

 

የመጀመርያው ጉዳይ የሚኒሊክ ኢትዮጵያ የግድ መቀጠል ያለባት አደለችም።ልትቀልም ላትቀልም መወሰን ያለባቸው ገዎች ሳይሆኑ ህዝቦች መሆናቸው ማመንና መቀበል ግድ ይላል። ስለዚህ መስፋትም መጥበብም ትችላለች። ይህ ማለት ህዝቦች ፈቀደውና የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብታቸው ተጠቅመው ተሳስረው የጋራ ሀገረ-መንግስት መገንባት ይችላሉ ፤ እንዲሁም የየራሳቸው ሀገረ መንግስስት መገንባት ይችላ።የዳግማዊ ሚኒሊክ ኢትዮጵያ ሀገር ሳትሆን ግዛት ነበረች ወይም ደግሞ Empire ነበረች ብለን ማመን ሽንፈት ሳይሆን ከእውነት ጋር መታረቅ ነው። ከእውነት ጋር የታረቀ አስተሳሰብ ዋና ምሰሶ አይለቅም። በሌላ መልኩ ይህን እውነታ ከልብ ከተቀበልን የዳግማዊ ሚኒሊክ ኢትዮጵያ ከግዛት አንድነት ወደ ሀገረ-መንግስትነት የመሸጋገር ዕድልዋ በጣም ሰፊ ያደርገዋ

ኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ተገድደው የሚቋጠሩባት ከረጢት መሆኗ ቀርቶ ፈቅደውና ተከባብረው የሚገነቧት ሀገረ-መንግስት መሆኗ ከተረጋገጠላቸው አብሮ የመኖርና አንድ የኢኖኖሚ ማህበረሰብ የመንገንባት ፍላጐታቸው ይበልጥ ይጠናከራል። የራሴን ሀገረ-መንግስትና የኢኮኖሚ ማህበረሰብ መገንባት እፈልገለሁኝ የሚል ህዝብ ወይ ብሔር ካለም የራሱን ዕድል በራሱን የመወሰን መብት ሙሉ ለሙሉ ካረጋገጥንለት ከጊዜ በኋላ መልሶ የጋራ ኢኮኖሚያዊ ትስስር መፍጠሩ አይቀሬ ይሆናል። ለዚህ ደግሞ ጠንካራ መሠረት የሚያጐናፅፈን የ1987 ዓ.ም የፀደቀው ህገ መንግስት ይሆናል።

 

የህዝቦች የራስን ዕድል በራስ የመወሰን ሙሉ መብት ለማጎናፀፍ የስችል ያለውን ህገ መንገስት ማሻሻልና የበለጠ ማጠናከር ደግሞ ዋናና አስፈላጊው ነገር ነው። ጠንካራና እውነተኛ ፌዴራላዊት ኢትዮጵያ ለመገንባት ህገ-መንግስቱ ላይ መሻሻል የሚገባቸው አንቀፆች ይኖራሉ። ህገ-መንግስቱ የክልሎች ስልጣነ የበለጠ ከፍ የሚልበትና አንዳንድ ክልሎች እንደፍላጐታቸው ማለትም በReferendum (በህዝብ ቀጥተኛ ድምፅ) ተወስኖ በኮንፌደሬሽን ደረጃ የሚደራጅበት ሰፊ ዕድል መፍጠር በሚያስችል መንገድ መሻሻል አለበት። ይህ ማድረግ የሚያስፈልገው የህዝቦች ነፃነት የበለጠ በሰፋ ቁጥር ከቂም በቀል ርቀው በሰለጠነ መንገድ ወደ አንድ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ የሚመጡበት የወደፊት ዕድልም ስለሚያሰፋ ነው።

 

ስለዚህ ከላይ በተገለፀው ሃሳብ መሠረት እውነተኛ ህብ-ብሔራዊት ፌደራላዊት ኢትዮጵያ ለመገንባት ዋነኛ መነሻችን አሁን ያለው ህገ-መንግስት ሆኖ እናገኘዋለን። ይህ ህገ-መንግስት መሠረት ይሁን እንጂ ለብሔር ብሔረሰብና ህዝቦች በበለጠ ሰፊ ዕድል ይሰጥ ዘንድ ሰፊ ማሻሻያ ያስፈልገዋል። በፌደራል መንግስትና በክልል መንግስታት መሃከል ያለው ግንኙነት በጣም የላላ እንዲሆንና ለክልል መንግስታት በቂ ስልጣን እንሰጥ ፣ የክልል መንግስታት ሃብታቸውን በራሳቸው መየሚያስተዳሩበት ስልጣን እንሰጥ የጋራ የሆነውን ሃብት ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ለሁሉም እንዲዳረስ የሚያስችል ሆኖ እንዲያሰራን ህገ-መንግስቱ የበለጠ መሻሻል አለበት።

 

ሌላኛው መረዳት ያለብን መሠረታዊ ጉዳይ በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ የአንድ ብሔር የበላይነት ማምጣት የማይቻል ስለመኖኑ ነው። በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ የህዝብ ቁጥርላይ ተመስርቶም ይሁን በሌላ መንገድ የአንድ ብሔር የበላይነት አመጣለሁኝ ብሎ ማሰብ ከዕብደት ሊያስቆጥር ይችላል።ብዙ ቁጥር ትንሹን ቁጥር ደፍጥጦ ይግዛ የሚለውን አስተሳሰብ አንድም በጣም ኃላቀር አስተሳሰብ ነው። ሁለትም የገዢዎች እንጂ የህዝበ ፍላጎት ሊሆን አይችልም።በኢትዮጵያ ውስጥ የህዝብ ነፃነት ፣ ዕኩልነትና መሠረታዊ የዴሞክሲያዊ መብትና የጋራ ተጠቃሚነት ላይ በትንሹም ቢሆን ማዛነፍ ሰላም በሰፊው ከማደፍረሱ በላይ ሀገሪቱ ሀገረ-መንግስት ሁና የመቀጠል ዕድልዋ በእጅጉ ያቀጭጫል።

 

አንድ በበሰለ መንገድ ማየት ያለብን ጉዳይ ኢትዮጵያ ውስጥ የአንድን ብሔር የበላይነት ማረጋገጥ የሚትችለው በጉልበትና በጉልበት ብቻ ነው። በ21ኛው ክፍለ ዘመን በጉልበትና በጉልበት ብቻ የሚታረጋግጠው የበላይነት የት ድረስ ይወስደኛል ብሎ ማሰብ ደግሞ የብልህ ነው።በኔ እምነትና አረዳድ ስንዝር መራመድ አያስችልም። ስለዚህብዙ ቁጥር ስላለኝ ወይም ደግሞ ጉልበት ስላለኝ የበላመቀዳጀት አለብኝ ብሎ ለሚያስብ ወገን ኢትዮጵያ ከእንግዲህ ይህንን አስተሳሰብ ፈፃማ እንደማታስተናግድ በአንክሮት መረዳቱ የብልህ ይሆናል። የቁጥር የፖለቲካ ጫወታ ፍትሃዊ የሚሆነው በበጀት ቀመር ፣ በሃብት አጠቃቀም ላይ እና በምክር ቤተ ውክልና ብቻ ነው።ከዚህ ውጭ ልናውለው የሞከርን እንደሆነ ፍፁም ኢ-ፍትሃዊ አስተሳሰብ ስለሆነ የኢትዮጵያን አጠቃላይ ሁኔታ ያናጋል። ወደ ሌላ ጦስም ይወስደናል።

 

በሶስተኛ ደረጃ እውነተኛ ህብ-ብሔራዊት ፌዴራላዊት ኢትዮጵያ ለመገንባት አስቀድመን መረዳትና ማመን ያለብን ጉዳይ አንድ አለመሆናችን ነው። በሂደት እንደማህበረሰብ ወደ አንድ ህዝብነት መምጣት የምንችልበት ዕድል ዝግ ባይሆንም ፤ እስከ አሁን ግን አንድ ሆነን አናቅም። በባህል ፣ በቋንቋ ፣ በታሪክ ፣ በማሕበረሰባዊ እሴት ወዘተ መሠረታዊ ልዩነቶች አሉን።አንድ ነንአንድ ህዝብ ነን ወዘተ እያልን ብንፎክርና ብንደሰኩር አየር ላይ የሚዋልል ድምፅ ከመሆን አልፎ መሬት ላይ ያለውን የልዩነታችንን ስፋት ማጥበብ አይችልም። እንድያውም አንዳንድ ወገኖች አንድ ነን ብለው ሲጮሁ ለብዙ ህዝ የሚያስበረግግ ይመስለኛል። እውነታው ለመቀበል ሂሊናችን ከፈቀደ የኢትዮጵያ ህዝብ በመቶ ሰላሳ ዓመታት ታሪክ ውስጥ የአንድነት ጭላንጭል ያየው በኢህአ የአመራር ዘመን ብቻ ነበር። ምክንያቱም በኢህአየአመራር ዘመን ሙሉውን ባይሆን ህገ-መንግስቱ በከፊል መሬት ላይ የሚተረጐምበት ዕደል ነበረውና።

 

አንዳንድ የትምክህት ወገኖች ወደ አፄ ሚኒሊክና አፄ ሃይለስላሴ ጊዜ የነበረው አንድነታችን እንመለስ ይላሉ። ሓቁ ግን በዚያን ዘመን አንድነት ሳይሆን የነበረው በአንድ ብሔር ተወላጅ የሆኑ ገዢ መደቦችየሚትራቆት አሳዛኝ የውሸትዋ የዳግማዊ ሚኒሊክ ኢትዮጵያ ነበረች። በዚያን ዘመን ብሔርና ብሔረሰብ መሠረት ያደረገ ሰፋፊ ውግያና ግጭት ፣ መከፋፈል ነበረ። ከዚያም አልፎ በጐሳዎችና በመሳፍንት መሃከል የሚያባር ጦርነትና ግጭት ነበር። ነገር ግን እንደዛሬው ቴክኖሎጂ ባደገበት ዘመን ኮሽ ያለ ሁሉ መዘገብ የሚያስችል የመረጃ ትስስርና ቴክኖሎጂ አልነበረም። ስለዚህ ትናንት አንድ ነበርን የሚለውን የትምክህት ኃይሎች ትርክት ውሃ አይቋጥርም ብቻ ሳይሆን የልበ-ወለድ ፖለቲካ ዋነኛ ነፀብራቅ ነው።

 

አንድ አለመሆናችን ማመን ፖለቲካዊም ይሁን ማህበረ-ኢኮኖሚ ላይ ያለው ጠቀሜታ ምንድ ነው ብሎ መጠየቅ ይቻል ይሆናል። ዋነኛው ጠቀሜታው በልዩነት ላይ እንዴት አብረን መኖር እንችላለን የሚለውን መሠረታዊ መፍትሄ ለማምጣት ይረዳናል። ዋነኛ መፍትሄውም ልዩነትን ማስተናገድ የሚችል ህገ-መንግስታዊ ሥርዓት መዘርጋት ይሆናል።ስለእውነት እንነጋገር ከተባለ ይህ ህገ-መንግስታዊ ሥርዓት በተግባር ላይ ለማዋልከ1987 ዓ.ም ጀምሮ ሰፊ ትግል ተካሂዶበታል።አሁንም ትግል ላይ ነን። ነገር ግን የዚህ ህገ-መንግስታዊ ሥርዓት ግንባታ ሂደትና ከዳግማዊ ሚኒልካዊት ኢትዮጵያ ወደ እውነተኛዋ ህብ-ብሔራዊት ፌደራላዊት ኢትዮጵያ ለመሸጋገር የተደረገውና እየተደረገ ያለው ትግል የመሳካትና ያለመሳካት ጉዳይ ጥያቄ ላይ ወድቀዋል። ይህ ማለት የትምክህት ኃይል ቅስም ካልተሰበረና የፌደራል ኃይሎች ካልተባበሩ እውነተኛው ህብ-ብሔራዊት ፌደራዊት ኢትዮጵያ የመገንባት ሂደት በእጅጉ ማለት ነው። ይህ ደግሞ ውጤ ወደደንም ጠላንም የተኮላሸና የከሰመ የሀገረ-መንግስት ግንባታ ይሆናል። በዚሁ ምክንያት የተበታተነች ኢትዮጵያ ለማየት እንገደዳለን።

 

ስለዚህ ይህ እንዳይሆን አንድም አንድ አለመሆናችን መገንዘብ ያስፈልጋል። ሁለትም ልዩነታችንን በትክክልና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ሊያስተናግድ ዘንድ የዘረጋነውን ህገ-መንግስታዊሥርዓት ለማጠናከር የፌደራል ኃይሎች ትብብርና መቀራረብ ያስፈልጋል። አሁን ላይ በልዩነት ላይ አብሮ የሚያኖረን የዘረጋነው ህገ-መንግስታዊ ሥርዓት ተሻሽሎና በልፅጎ ፤ ሳይዛነፍ መሬት ላይ ውርደን ማስኬድ ከቻልን እውነተኛ ፌደሬሽን ላይ የተመሠረተ ሀገረ-መንግስት ግንባታ ማሳካት ከመቻላችን በላይ በጊዜ ሂደት ወደ የሰለጠነ ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ትስስር የተሻገርን ጊዜ አንድ የመሆን ዕድላችን ይሰፋል።

 

በኔ እምነትና አረዳድ እውነተኘህብ-ብሔራዊት ፌደራላዊት ኢትዮጵያ ለመገንባት ዋነኛ ቁልፍ ጉዳይ ህገ-መንግስቱ ነው። የፖለቲካ ፓርትዎችና ህዝቡ ህገ-መንግስታዊ ሥርዓቱ ለማስቀጠል ህገ-መንግስቱ ራሱ በሚፈቅደው መንገድ ማበልፀግና ማሻሻል ከቻሉና በመሠረታዊ የህገ-መንግስት መርሆዎች ከተስማሙ ፤ የርኦተ-ዓለም ልዩነት ሀገር ለማፍረስ ምክንያት ይሆናል ብዬ አላምንም። የሀገሪቱን ተጨባጭ ሁኔታና መሠረታዊ ችግሮችና ግጭቶች ታሳቢ ያደረገ ህገ-መንግስት ተቀርፆ ተግባር ላይ ተፈትነዋል። ሓቁን በአደባባይ ሙልጭ አድርጎ የሚኪድ ብዙ የትምክህት ወገን ኖርም ቂሉ ውጤቱ አመርቂ ነበር። ህገ-መንግስቱ ሙሉ በሙሉ መሬት ላይ ቢወርድ ኖሮ ደግሞ ውጤቱ የበለጠ አመርቂ ይሆን ነበር። ስለዚህ በዚህ ህገ-መንግስት መሠረት የተሻለች ኢትዮጵያ መገንባት እንደሚቻል ምንም ጥርጥር የለውም። ፓርቲዎቹም በፖለቲካ-ኢኮኖሚዊ ላይ ርተዓለማቸው መተግበር ይችላሉ-ህዝብ መርጦ ስልጣን እስከ አስረከባቸው ድረስ።

 

ከላይ እውነተኛ ህብ-ብሔራዊት ፌደራላዊት ኢትዮጵያ ለመገንባት የሚያስችሉን መሠረታዊ ነገሮች አይተናል። ነገር ግን ይህ ህደት ይሳካ ዘንድ አሁን ስልጣን ላይ ከወጣው ብዱን ምን ይጠበቃል? ይህ ብዱን ህገ-መንግስታዊ ሥርዓቱ ለማስኬድ የሚያስችል ፍላጐትና አቅምስ አለው ወይ? የሚሉትን ጥያቄዎች መመለስ ደግሞ ግድ ይለናል።

 

ርግጥ በጥቅት ግለሰቦች የተገነባው አሁን የመንግስት በትረ ስልጣን የተቀዳጀው ቡድን ይህን ህገ መንግስታዊ ሥርዓት ሊያስኪደውስ ይቅር ፤ ሲያፈረርሰው እያየን ነው። ስለዚህ ይህ ቡድን እውነተኛ ህብ-ብሔራዊት ፌደራላዊት ኢትዮጵያ በመገንባት ሂደት ያለው ፋይዳ ኣሉመሆኑ ለችንም የሚያግባባ ጉዳይ ነው። ይህ ቡድን ወደ ስልጣነ የወጣበት መንገድ የቡድኑ ባህርያት እንዲሁም ከብዱኑ ጀርባ ያሉ ኃይሎች ኢኮኖሚያ ይሁን ፖለቲካዊ ፍላጐት መረዳት ደግም አስፈላጊ ይሆናል። በተጨማሪም በዋናነት የመንግስትን የስልጣን ማሽን ተቆጣጥሮ ፤ ከህግና ህገ-መንግስት በላይ በመሆን ሀገሪቱን እያተራመሰ ያለውይህ ቡድን ራሱ መሆኑ፤ ጉዳይ ውስብስብ ያደርገዋል።ስዚህ ኢትዮጵያን በማዳን ሂደት ከዚህ ቡድን ምንም ስለማይጠበቅ የፌደራል ኃይሎች ጠንክረውና ትክክለኛ ስትራተጂ ቀርፀው ወደ ትግል መግባት አለባቸው።

 

 

2.       በሰላምና በሰለጠነ መንገድ የመበታተን ጉዳይ

 

የኢፌዴሪ ህገ-መንግስት በመፈቃቀድና በመከባበር አንድ መሆን በሚያስችል ሁኔታ እንደደነገገው ሁላ ፤ በመከባበርና በመፈቃቀድ ላይ ተመስርተህ መለያየት እንደሚቻልም በግልፅ አስቀምጧል። ብሔር ፣ ብሔረሰቦችን ህዝቦች ፈቅደውና ተከባብረው አብሮው መኖር የሚያስችላቸው አማራጭ ሁሉ ተሟጦ፤ፈቅድውና ተከባብረው በአንድነት ሊያስቀላቸው የሚችል እሴት ሁሉ ከተናደ ቀጥሎ ያለው አማራጭ ፈቅደውና ተከባብረው መለያየት ነው። ይህ የፍቺ ሂደት ሰለማዊስልንና የሰከነ ለማድረግ ደግሞ ዋናኛ መሣሪያ አሁንም ህገ-መንግስቱ ይሆናል።

 

መለያየታችን ነጌ ታሳቢ ማድረግ እንዳለበት በአፅንኦት ማስገንዘብ እፈልጋለሁኝ። ዛሬ ተለያይተው ነጌ ተለቃቅሰው መገናኘት ልኖር ስለሚቸል ተለቃቅሶ ለመገናኘት ተጣልቶ ከመለያየት ይልቅ ተለቃቅሶ ለመገናኘት በፍቅር መለያየት ይሻላል። ለዚሁም ነው ሰላማዊና የሰለጠነ የመበታተን ስትራተጂ የሚያስፈልገው። በሌላ መልኩ የኢትዮጵያ መለያየት ህጋዊ ማድረግ የሚቻልበት ሰፊ አማራጭ ስላለ ከሌሎች የመበታተን አማራጮች ሁሉ ህጋዊነት የተላበሰ የመበታተን ሂደት መከተል ለማንኛውም ወገን ብዙም ላያስከፋ ይችላል የሚል ግምት አለኝ። በሰላምና በሰለጠነ መንገድ ህገ-መንግስቱ መሠረት አድርጐ ለመለያት የሚከተሉትን ነጥቦች ግምት ውስጥ ማስገባቱ የተሻለ ስለመሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው።

1.   መለያየቱ ግዛት ሳይሆን ህዝብና የህዝብ ደህንነት ማከል ማድረግ አለበት። ይህ ማለት የህዝብ ምርጫ ማክበር ዋነኛ ምሰሶ ማድረግ አለብን ማለት ነው። በተለይ በክልሎች ወሰን ኑሮው መሠረት ያደረገ ህዝብ ወዴት መጠቃለል እንዳለበት የራሱና የራሱ ብቻ ምርጫመሆን አለበት። ሌላው ወገን በየትኛውም አቅጣጫ ይሁን ልወስንለትና ልመርጥለት አይገባም። ይህን ለማሳካት አከራካሪ በሚባሉ አከባቢዎች የህዝብ-ውሳኔ (Referendum) ማካሄድ የግድ ይሆናል ማለት ነው።

2.   የሃብት ክፍፍልን በተመለከተም ህገ-መንግስቱ ውስጥ የተመለከቱ ነገሮቸ ካሉ እነሱን ጥቅም ላይ ማዋል አንድ ጉዳይ ሆኖ ፣ በማንኛውም መልኩ የጋራ በመሆነው የሃብት ክፍፍል ሂደት ፍትሃዊ ማድረግ ለማንኛውም ወገን ጠቃሚ ኖኖ እናገኘዋለን።

3.   የመበታተን ሂደቱ ቀጥሎ ሊፈጠር የሚችለውን ማህበራዊ ይሁን ኢኮኖሚያዊ ትስስር ኩፍኛ እንዳጐዳው ከስሜ በፀዳ መልኩ ተቀራርቦ መፈፀም የተሻለ አማራጭ ይሆናል።

 

ማጠቃ

 

ኢትዮጵያ እውነተኛ ፌደራላዊና ህብረ-ብሔራዊ ሀገረ-መንግስት መገንባት ላይ እንታተኩር ቀዳሚ ምክሬ አድርጌ አስቀምጫለሁኝ። ይህን ያለማሳካትዋና ይህን ግንባታ ለማካሄድ መሪዎችዋ ፈቃደኛ ያለመሆን ጉዳይ ወደ መበታተን እንደሚያመራም በግልፅ ተቀምጧል።

 

እነዚህ አማራጮች ተግባር ላይ ለማዋል በዋናነት የመንግስት በትረ ስልጣን ህጋዊ ባልሆነ መንገድ በተቆጣጠረው ቡድን እጅ ያለ ልመስለን ይችላል። ነገር ግን ህዝቡ ፣ የህዝብ አስተዳደርዎችና የፖለቲካ ድርጅቶች እንዲሁም ህቁ ቆም ብሎ ካሰበበት የመንግስት በትረ ስልጣን የተቆጣጠረው ቡድን በአንድ ቀንም ልናድ የሚችል የአቅመ ቢሶች ስብስብ ነው። በርግጥ ይህን ቡድን የሀገሪቱን ሁኔታ ኣሳስቦ ወደ ትክክለኛ መንገድ መመለስ ከቻለ ለኢትዮጵያ መልካመ ዕድል በማስፋት የመጀመርያው አማራጭ ተፈፃሚ በማድረጉ ሂደት ላይ የጐላ ሚና መጫወት ይላል። ይህ ማለት እውነተኛ ፌደራላዊት ህብረ-ብሔራዊ ሃገረ-መንግስት ለመገንባትና ይህን ሂደት በጠንካራ መሠረት ላይ ለማስቀመጥ በሚደረገው ትል ተባባሪ ከሆነ ፤ ኢትዮጵያ የጐላ ዕንቅፋት ሳይደቀንባት መቀጠል ትችላለች።

 

ነገር ግን ይህ በግላጭ የምዕራባዊያን ቅጥር መሆኑ የሚታወቅ ቡድን አጀንዳው ምዕራባዊያን ማስደሰት መሆኑ አስቀርቶ ኢትዮጵያን ወደ ማዳን ልያደርገ ይችላል ወይ የሚለውን ጥያቄ ስመረምር ይህ ቡድን ከምዕራባዊያን እጅ መውጣት የሚችልበት አቅምና ፍላጐት የሌለው ልፍስፍስ ቡድን ሆኖ ታገኘዋለህ።ሆኖበሌሎችየሀገራቸው ጥቅም አሳልፈው መስጠት በማይፈልጉ ኢትዮጵያዊያን ኃይሎች ምክር ተሰጥቶትና ተደግፎ አጀንዳ መቀየር የሚችልበት ትንሽ ዕድል እንዳለ ደግሞ ማየት ይቻላል። በርግጥ ይህ ዕድል ግምት ውስጥ ልታስገባው የሚያስቸግርና በጣም ጠባብ መሆኑ ደግሞ ሌሎቹ አማራጮች ልናይ ያስገድደናል። ስለዚህ የዚህ ልፍስፍስ ቡዱን ተስፋችን አሟጥጠን የመጀመርያው አማራጭ ማንኛውም ቅን ሂሊና እንዲሆን የሚፈልገው አማራጭ ስለሆነ ኢትዮጵያ በመላ ተባብረን የትምክት ኃይል አምበርክከን ተግባራዊ ልናደርገው የሚገባ አማራጭ ነው ብዬ አምናለሁኝ።

 

ለኢትዮጵያ መልካም ነገር ለማምጣትና ሁሉንም ህዝብ በዕኩልነት የሚታቅፍ እውነተኛ ፌደራላዊት ህብረ-ብሔራዊት ኢትዮጵያ ለመገንባት ከማንም ኃይል በላይ የፌደራል ኃይሎች መተባበርና አብሮ መስራት እንዳለባችሁ ትልቅ አፅንኦት ለመስጠት ፈልጋለሁኝ። የፌደራል ኃይሎች ባለፉት ጊዝያት በተለያየ አጋጣሚ ተነካታችሁና ተቋስለችሁ ሊሆን ይችላል ፤ ነገር ግን ይህን ርሾ ወደ ጐን መተውና መተባበአመራጭ የሌለው የኢትዮጵያ መድሓኒት መሆኑ ልንገነዘብ ይገባል።

 

 

 

Back to Front Page