እነሱ ሲወርዱ
ሲወርዱ ... ሲዘቅጡ
ሲበላሹ ... ሲጎተቱ
ሲታወሩ .. ሲጨፈኑ
እኛ ... ወደላይ
... ወደላይ
አሸነፍነው ችግሩን
... በሽታ ህማሙን
ታከምን አገገምን
... ተፈወስን
ተንሳን ጠንክረን
... አምሮብን
በሩጫ ... ፈጠን
... ፈጠን
ራመድ ... ሮጥ ሮጥ
ልክ እንደበፊቱ
...
ወጣነው ተራራውን
... ሜዳ አቀበቱን
ወደላይ ... ወደላይ
ተሳብን ተመዘዝን
ማንም እንዳይደርስብን
ይሰሙን ዘንድ
...
ሞንጆሪኖ አለች
... አወጀች ...
ጆሮ ያለው ይስማ
... የሌለው ይበደር
ይሄንን ጀግና
ህዝብ ... በማንም የማይበገር
እነሱ ሲወርዱ
... እኛ ስንከበር
ሞንጆሪኖ ጮክ
ብላ ...
በሜሌንየም አዳራሽ
... ይሄን ስትናገር ...
ጆሮ ያለው ሰማ
... የሌለው ሲደናበር
ኢዮብ ከ ጮማ እምኒ
3-1-20
Videos From Around The World
|
Back to Front Page