Back to Front Page

ኢኮኖሚስት ዶክተሮች

ኢኮኖሚስት ዶክተሮች

የብልጽግና ምቀኞች
የሚነዳ መኪና ... አልባዎች
ሀብት ፈጣሪ ሳይሆኑ ... ሀብታሞችን አጥኚዎች
ኪሰ ቀዳዳዎች
እንኳን አገር ...
ቀበሌ የማይመሩ
ሚልየኖሮችን ... የሚመራመሩ
የሚያጠኑ ... የሚጠራጠሩ
ዶ/ሮች ... ድሀዎች ...
ፕ/ሮች ... ጀዝባዎች
እኛ... ያልተማርነው ... ሀብታሞቹ
የብልጽግና ...
መሪዎች ሾፌሮቹ
... ሞተሮቹ
አንድ መጸሀፍ ... ሳናነብ

ሳንደክም ሳንጥር

ዲግሪውን… አስገብተን ያለታክስ
ከመሬት ተነስተን
በቅጽበት ... ተወንጭፈን
5 ሚሊየን... ለእራት ከፍለን
በልተን ... ጠጥተን
አግስተን ... ወዝተን አብጠን
መዐት ሚሊየን ... የተትረፈረፈን
... ምርጥ ሀብታሞች
ዲግሪ ... አልባዋችነን


እኛ ...
የፎቅ ባለቤት ... ባለብዙ መኪናዎች
የቀበሌ ... አስተዳዳሪ
... የአገር መሪ
ዘናጮች ... ቀብራሮች
ታክስ ... ሸዋጂዎች

እዘኑ ..
ለኢኮኖሚስት ... ድሀ ምሁሮች
ያልተማሩት ከኛ ...
ሀብትን እንዴት ... እንደምናከማች
ተደፍታችሁ ስታጠኑን ...
እንዴትእንደሰራን ... ገንዘቡን
ስትደኹዩ ... ስንከብር
ስንጠግብ ... ስትራቡ
እኛስንመራ ... በኛስትመሩ
ስናተርፍ ... ስትከስሩ
ይሄነውትርፉ ...

የኢኮኖሚስት የዶክተሩ

ኢዮብ ከጮማ እምኒ

3-17-20

Videos From Around The World

Back to Front Page